በዛሬው ቀን በሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ 87 ታካሚዎች አገግመው ወጥተዋል፡፡ማዕከሉ ከተከፈተ በኋላ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎቻችንን የዛሬው ቀን በእጅጉ የተደሰቱበት ነበር፡፡ እንኳን ደስ ያለችሁ!
በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ውስጥ 656 ታካሚዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
እስቲ የጤና ባለሙያዎቻችንን አመስግኑልን!

ዶር አብዱ በፋና ጤና የካንሰር ህመም አና የኮርና ወረርሽኝ በሚል ትምህርት ሰጥተዋል። ተመልከቱት!
የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን
(ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)
.
በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ።
.
በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ, solarretinopathy, photic retinopathy, foveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል።
.
ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን (ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
.
በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደ ቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር ፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለ ሐምራዊ-ለ Ultraviolet-B ) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።
.
❓አጋላጭ ሁኔታዎች፡-
.
- ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡
- ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡
.
- ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡
- የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡
.
- ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።
.
❓ምልክቶቹ፦
.
በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦
- የዕይታ መቀነስ
- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ
- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)
- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡
.
ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።
.
❓ህክምናው፦
.
ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው ።
.
❓መከላከያ መንገዶች፦
⛔ ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት ፣
በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም።
.
⚠️ ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል ፣ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ መርዳት
✅ የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደ እኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡
.
❓የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል ?
.
❌ በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም።
ጥላሸት የተቀባ መነጽር፣ የራጅ ፊልም፣ የተለመደ የፀሐይ መነጽር፣ ካሜራዎች ወዘተ የሚታዩ የብርሃን ጨረሮችን ቢቀንሱም አደገኛ የሆኑትን ልዕለሐምራዊና ንዑስቀይ ጨረሮችን መከላከል አቅም ስለሌላቸው በነሱ መተማመን አይገባም፡፡
.
መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።

😷#WearAMask to protect yourself & others around you from #COVID19.
#WearAMask #WearAMaskSPHMMC #WearAMaskEthiopia
#SPHMMC
#WHO #WearAMaskChallenge

በእርግዝና ወቅት ለስኳር ህመም የሚጋለጡት እነ ማን ናቸው?
በእርግዝና ወቅት በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የጤና እክሎች አንዱ የስኳር ህመም ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ 6-7% የሚሆኑት ነፍሰጡሮች የስኳር ህመም አላቸው፡ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 90% በእርግዝና ወቅት ብቻ የሚከሰተው የስኳር ህመም ይኖራቸዋል። ለመሆኑ በእርግዝና ወቅት ይበልጥ ለስኳር ህመም ተጋላጭ የሚሆኑ እነ ማን ናቸው?
1) እድሜዋ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነ
2) ከዚህ በፊት - ከ4ኪ.ግ. በላይ የሚመዝን ልጅ ወልዳ ከነበረ
- እርግዝናዋ ወቅት የስኳር በሽታ አጋጥሟ ትከነበረ
- የአፈጣጠር ችግር ያለበት ጽንስ ከነበራት
3) ባልታወቀ ምክንያት ጽንሷ ሞቶባት ከነበረ
4) የቅርብ ቤተሰቧ ውስጥ የስኳር ታማሚ ካለ
5) ከመጠን በላይ ወፍራም ከሆነች (BMI>30)
6) በምርመራ ላይ በሽንቷ ውስጥ የስኳር መጠን ከጨመረ
ለስኳር ህመም የመጋለጥ እድሏ ከፍኛ ነው፡፡ ይህች ሴት ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ወቅት በሚደረግላት ክትትል እና ህክምና ለስኳር ህመም እንዳትጋለጥ መከላከል ይቻላል፡፡
ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት::
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

በእርገዝና ወቅት የሚታዩ 7 ጤናማ ለውጦች
1. በደቂቃ ውስጥ ያለው የልብ ምት እና የትንፋሽ መጠን ይጨምራል
2. በመጀመሪያውና በመጨረሻው የእርግዝና ወራት የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
3. የእግር ማበጥ
4. የእንቅልፍ መዛባት
5. የምግብ ፍላጎት
ሀ. የመጀመሪያዎቹ ወራት - መቀነስ
ለ. የመጨረሻዎቹ ወራት - መጨመር
6. የምግብ ቶሎ አለመፈጨት
7. የሆድ ድርቀት ብዙ ነፍሰ-ጡሮች ላይ የሚታዩ ለውጦች ናቸው፡፡
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት

የማህፀን አፍ ካንሰር (cervical cancer)
· ካንሰር ማለት ከተለመደው የህዋሶች አሠራር ሥርዓት ውጪ የሚሠሩና የሚራቡ ህዋሳት ስብስብ ነው። ይህ መዛባት ጤናማውን ህዋስ በአግባቡ እዳይሠራ ያደርገዋል። የጉዳቱ መጠን በካንሰሩ አይነትና በተጠቁት የሰውነት ክፍሎች ይወሰናል።
· እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO ) ጥናት በየዓመቱ 529‚000 ሴቶች በዚሁ በሽታ የሚጠቁ ሲሆን የሚበዙትም በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ውስጥ ይገኛሉ። በሃገራችን ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ7ሺህ በላይ ሴቶች ሲጠቁ 6ሺህ ያህሉ በሞት ይለዩናል።
የማህፀን አፍ ካንሰር መንስኤ (Causes of cervical cancer)
· ኤችፒ.ቪ (HPV) የተባለው ቫይረስ ለዚህ ካንሰር ዋንኛው መንስኤ ሲሆን ሌሎች በውል ያልታወቁ ምክንያቶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ይታመናል።
የተጋላጭነት መንስኤዎች (Risk factors)
· ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ ወይም ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ ያለው ወዳጅ (partners) መኖር
· የመጀመርያው የግብረ ስጋ ግንኙነት በአሥራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ሲጀመር
· የአባላዘር በሽታ ወይም ኤች አይ ቪ (HIV) መኖር · ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ
· ሲጋራ ማጨስ
· የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም የሚቀንሱ መድኃኒቶች
ምልክቶቹ
· ህመም አልባ ከማህፀን ደም መድማት ሲሆን የሚደማበትም ሁኔታ፤
· ከመደበኛው የወር አበባ ውጪ
· ከየግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ
· ከማረጥ (menopause) በኋላ
· ብልትን ከታጠቡ በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡
· መጥፎ ጠረን ያለው ውሃማ የማህጸን ፈሳሽ
· የጎን፣ የወገብ ወይም የእግር ህመም
· በሽንት ቧንቧ ወይም በፊንጢጣ መድማት
· የእግር ማበጥ
· የሽንት ወይም የሰገራ ማምለጥ (Fistula) ዋንኞቹ ናቸው፡፡
ሕክምናው ምንድነው ?
· በመጀመሪያ የህመም ደረጃ ላይ ላሉ ታማሚዎቸች ቀዶ ጥገና የሚመከር ሲሆን የጨረር ሕክምና ለብቻው ወይም ከፀረ-ካንሰር መድኃኒት ጋር ህመሙ ለተባባሰባቸው ይመከራል
መከላከል ይቻላል ?
· ኤች.ፒ.ቪ (HPV) የሚያመጣውን ኢንፌክሸን የሚከላከል ክትባት መውሰድ
· የሚሰጠው እድሜአቸው ከ 9-25 ዓመት ላሉ እና የግብረሥጋ ግንኙነት ላልጀመሩ
· የቅድመ ካንሰር ምርመራ (Pap smear)
· በዚህ ምርመራ የማህፀን አፍ ካንሰር ከመከሰቱ ከ10 ዓመት በፊት ማወቅ ይቻላል
· በየ 3 ዓመት የሚደረግ ምርመራ
· ምርመራው ለነማን ይሰጣል?
· እድሜ ከ21 ዓመት በላይ
· የግብረ ስጋ ግንኙነት ለጀመሩ
· ከኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ ጋር የሚኖሩ · ምርመራው መቼ ይቁም ?
· እድሜ ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እና
· 3 ተከታታይ ኖርማል ውጤት ያላቸው ምርመራውን ሊያቆሙ ችላሉ፡፡
ቸር እንሰንብት።

ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ከማገገም በኋላ የጎንዮሽ ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጥናቶች አሳዩ
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) በአለማችን ከተከስተ ዕለት አንስቶ እስካሁኑ ደቂቃ ድረስ በሚሊዩን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም አጋልጧል፣ የበርካታ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፣ ማህበራዊ ስነ- ልቦናዊ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሏል፡፡ በሃገራችንም በመጋቢት ወር አንድ ታማሚ ከተመዘገበበት ዕለት ጀምሮ 48‚140 በቫይረሱ የተያዙ፣357 ፅኑ ህሙማን እና 17,415 ያገገሙ ሰዎች ደርሷል፡፡
የኮሮና ቫይረስ አዲስ ወረርሽኝ እንደመሆኑ በሰዎች ላይ የሚያስከትላቸውን የጎንዮሽ ችግሮች፣ የበሽታውን ሂደት፣ለመከላከል የሚያስችሉ ክትባቶች ብዙ ጥናቶች እና መላምቶች በመተንበይ ላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ከኮሮና ቫይረስ ካገገመ በኃላ ምን አይነት የረጅም ጊዜ የጤና እክል ይኖረዋል ለሚለው ጥያቄ በተደረጉ ጥናቶች እንደ ሳንባ ቁስለት፣ የኩላሊት፣ የልብ እና የጭንቅላት የጤና እክል እንደሚያስከትል የወጡ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ከኮቪድ-19 ባገገሙ ሰዎች ላይ የሚታየው የሳንባ ቁስለት፣ በሽታው በታመሙበት ጊዜ በአይን የማይታዩ ለኦክስጅን ዝውውር የሚረዱ የሳንባ ክፍሎች ላይ በሚፈጥረው ችግር ምክንያት ይከሰታል፡፡ ከኮቪድ-19 በኋላ የሳንባ ቁስለት ያለባቸው ሰዎች በተከታታይ እንደትንፋሽ ማጠር፣ ደረቅ ሳል የመተንፈስ ችግር ያሳያሉ፡፡ ምንም እንኳን በእድሜያቸው ትንሽ የሆኑ ወጣት እና ጎልማሳዎች ከበሽታው ሊያገግሙ ቢችሉም በቻይና፣ ቪየና እንዲሁም በቅርብ በ20 ዓመት የቺካጎ ነዋሪ ላይ የተደረገው የሳንባ ንቅለ ተከላ በሽታው የሚያመጣው የሳንባ ቁስለት የጎላ ተጵፅኖ እንዳለው አሳይተዋል፡፡
ሌላው በረጅም የጤና እክል የሚጎዳው አካላችን የአንጎል እና የነርቭ ስርአት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ካገገሙ በኃላ እንደራስ ምታት፣ መፍዘዝ፣ ነገሮችን በትኩረት አለማሰብ ወይም የማስታወስ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ተናግረዋል፡፡ ተመራማሪዎቸ ይህ የጤና ችግር ሊከሰት የሚችለው በበሽታው ምክንያት አንጎል ላይ በኦክስጅን እጥረት በሚመጣው ጉዳት እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቫይረሱ በልብ ጡንቻ ላይ ከሚኖረው ተጽእኖ ጋር ተያይዞ የልብ ህመም እና ድካም በብዙዎቹ ታማሚዎች ላይ እንደሚያደርስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
እነዚህ የልብ፣ የሳንባ እና የደም ቧንቧ ችግሮች በኮሮና ቫይረስ ቤተሰብ በሆነው በሳርስ ታማሚዎች ላይ በተደረገ ጥናት 44 በመቶው የሚሆኑት ላይ ቫይረሱ ከተያዙ ከ12 አመት በኃላ ቢከሰትም በኮቪድ-19 ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ መከሰቱ በሽታው ምን ያክል አስጊ እንደሆነ ያመለክታል::
ምንም እንኳ እነዚህ ችግሮች ከፅኑ ህመም ባገገሙ ታማሚዎች ላይ ጎልቶ ሊታይ እንደሚችል ጥናቶች ቢያሳዩም፤ ምን ያህሉ እንዲሁም የትኞቹ የማህበረሰብ ክፍሎች እነኚህን የረጅም ጊዜ የጤና እክሎች እንደሚያጋጠሟቸው ለማወቅ ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም ማህበረሰቡ ማገገም ማለት ወደሙሉ ጤነኝነት መመለስ ላይሆን እንደሚችል በመረዳት ቫይረሱን ለመከላከል አካላዊ ርቀታችን እና የእጃችንን ንፅህና በመጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በትክክል በመጠቀም እራስዎን እና ቤተሰቦን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ ማሳሰብ እንወዳለን ፡፡ “በቫይረሱ ለመያዝም ሆነ ወደ ሌሎች መተላላለፍ ምክንያት አልሆንም”
Source: EPHI

ወረ ግቡ ሴት ምን ማወቅ አለባት?
አንዲት እናት የመውለጃ ጊዜዋ ሲቃረብ የሚመጡትን ለውጦችና በወሊድ ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ቀድማ ማወቋ የበለጠ የስነ-ልቦና ጥንካሬ እንዲኖራት ያደርጋታል
ከምጥ በፊት የሚታዩ ለውጦች
1. የወገብ ወይም የእግር ህመም
2. የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
3. አልፎ አልፎ የሚከሰት የምጥ አይነት ስሜት (ወደታች የሚጫን ህመም)
4. የጡት መወጠር(መያዝ)፣ አልፎ አልፎ ወተት መፍሰስ።
5. የእንቅልፍ መዛባ
ከምጥ በፊት አንዲት ሴት ምን ማወቅ አለባት
1. የልጇን የማህጸን ውስጥ አቀማመጥ፣
2. የተገመተው የጽንስ ክብደት
3. የዳሌ አጥንቶቿ ስፋት ከጽንሱ ክብደት ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን
4. የጡቶቿ ጫፎች ጠፍጣፋ ከሆኑ የማስተካከያ ዘዴዎ
በወሊድ ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮች
1. የጽንሱ መታፈን (በተለያዩ ምክንያቶች)
2. ከፍተኛ የሆነ ደም መፍሰስ
3. የምጥ በጤናማ መንገድ አለመሄድ (መዘግየት፣ መፍጠን)
የእነዚህ ችግሮች መፈጠር የወሊድ ሁኔታሽንም ሆነ የህክምናሽን ይዘት ስለሚቀይርው ከጤና ባለሙያሽ ጋር በመመካከር አስፈላጊውን ትብብር እና ውሳኔ እንድታደረጊ ሊጠበቅብሽ ይችላል።
በዶ/ር ቤቴል ደረጀ - የማህፀን እና ጽንስ ስፔሺያሊስት)

MOH COVID19 Report for Parliament.pdf
1.7 MB
MOH COVID19 Report for Parliament.pdf
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ሪፖርትና የምክረ ሃሳብ ሰነድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡
የቀረበውን ሰነድ ከላይ የሚገኘው ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።