St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
#####(((#####################
የዛሬ ኮቪድ ሪፖርት

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8,705 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,893 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

# 24 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
#1,893 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።
# 995 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።

አደራ ! ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
t.me/spmmc
ለ2013 ዓም ለሕክምና ትምህርት ለመከታተል የቃለ መጠይቅ ፈተናውን ያለፋችሁ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ ።
እንኳን ደስ ያላችሁ።

Notice for selected students


Names of selected students will be submitted to MoSHE on Tuesday. Students who are selected will not be assigned to any other University.  Those who are selected but not interested to join the college, report to the registrar office till Monday 5

https://drive.google.com/file/d/19vEwWS7KVQp6DYO18v0VbW9bLh9f6mhN/view?usp=drivesdk

https://drive.google.com/file/d/19zCLVLP8umHQauPl3XT_adnETy2fvQ0F/view?usp=drivesdk
የዛሬ ኮቪድ ሪፖርት

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,480 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,973 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

# 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
# 1,973 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።
# 1013 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።

ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
የዛሬ የኮቪድ መግለጫ

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7,312 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,792 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

# 42 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

# 1,028 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።

ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
የዛሬ የኮቪድ ሪ ፖርት። ( ሚያዝያ 11 ቀን 2013)


ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5,833 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1,603 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

# 22 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
# 972 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ናቸው።

ርቀታችንን መጠበቅ፣ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አንርሳ!
የሐዘን መግለጫ


ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት በዳይሬክተርነት እና በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ - 19 ምላሽ ማስተባበሪያ ስር ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የማሕበረሰብ ክፍሎች በኮቪድ -19 ዙሪያ የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫና የድጋፍ ስራዎችን ለሀገራቸውና ለማሕበረሰባቸው በመስራት ላይ እያሉ በኮቪድ - 19 ቫይረስ ተይዘው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሕይወታቸው አልፏል።

ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ በ2012 ዓ.ም በጤና ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ስላበረከቱም ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እውቅና አግኝተው ነበር ።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብም የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለጽን ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
ምንጊዜም ከቤትዎ ሲወጡ ማስክ ማድረግ አይዘንጉ።
#SPHMMC_COVID
የኮቪድ ምልክቶች ከታየብዎ ጸሎትዎንና ስግደትዎን በቤትዎ ያድርጉ።
#SPHMMC_COVID_19
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎ ከአፍንጫዎ እስከ አገጭዎ መሸፈኑን ያረጋግጡ።
#COVID_19_SPHMMC
💔 💔ዛሬ ልጄ ከተወለደ ገና 4 ቀኑ ነው:: ለክትትል ሆስፒታል ሄደን ነበር እና ሐኪሙ ልጅሽ ቢጫ ሆኗል አለኝ እና በጣም ተጨንቂያለው ‼️ ለምንድነው ልጄ ቢጫ የሆነው መፍትሄውስ ምንድነው?? 🤔🤔
📌 አይጨነቁ‼️ በአለም ላይ ከሚወለዱ ህፃናት ቢያንስ 60% የሚሆኑት ቢጫ ሊሆኑ ይቺላሉ::
📌 የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሕክምናው Neonatal Jaundice ይባላል እንደ ምክንያቱ አይነት ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል:: ምክንያቶቹ ደሞ በጣም ብዙ ናቸው:: ለዛሬ የተወሰኑትን ብቻ መርጠን እናያለን::
📌 የመጀመሪያው ምክንያት ተፈጥሯዊ ቢጫነት (Physiologic Jaundice) የሚባለው ሲሆን ብዙ ጊዜ በብዙ ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚያጋጥመን በቀላሉ እና በራሱ ጊዜ የሚጠፋው ቢጫነት ነው:: ይህ አይነት ቢጫነት እስከ 10 ቀን ወይም እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ በራሱ ይጠፋል:: ጡት በደንብ ማጥባት እና ፀሐይ ማሞቅ በቂ ነው ::
📌 ሁለተኛው ምክንያት ደሞ የእናት እና የልጅ የደም አለመመሳሰል(Blood group incompatibility) ለምሳሌ:
➡️ 1. የእናትየደም አይነት Negative(O negative, A negative, B negative ወይም AB negative) ሆኖ የልጅ ደሞ Positive ሲሆን ከባድ ቢጫ መሆን ሊያመጣ ይቻላል አልፎ ተርፎም ህፃኑ ላይ ከባድ አዕምሮ ጉዳትም ሊያደርስ ይቺላል:: አልፎ አልፎም ገና ልጁ ሳይወለድ በማህፀን እንዳለ ሊሞት ይቻላል:: ይሄም በሀገራችን በተለምዶ ሾተላይ የሚባለው ነው‼️
➡️ 2. የእናት የደም አይነት O ሆኖ የልጁ ደሞ A ወይም B ከሆነም ቢጫ መሆን ይከሰታል
📌 ሶስተኛው ምክንያት ደሞ ልጁ በቂ የሆነ ወተት ካላገኘ ቢጫ ሊሆን ይቺላል::
📌 አራተኛው ምክንያት ደሞ የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን (neonatal sepsis) ሲሆን ይህም ብዙ ጊዜ በባክቴሪ የሚመጣ ነው::
👉 የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን ከላይ ያልተጠቀሱ በ ሕክምናው የሚታወቁ በጣም ብዙ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ከፈለጉ ሐኪሞን ያማክሩ:: አስፈላጊ ከሆነ ሐኪሞም የደም ምርመራ ለልጆዎ ልያዝ ይችላል::
📌ለማንኛውም ከልጆ ጤና የሚበልጥ ነገር የለምና የቅርብ ክትትል እንዲሁም ሕክምና ያድርጉ ‼️

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም)
Happy international #midwifeday !Thank-you everyone midwife working in SPHMMC and around the country .
ነገ የዓለም አቀፍ የሚድዋይፍ ቀን ነው። በመላው ሀገራችን ወገናችሁን በማገልገል ላይ የምትገኙ ክብር ይገባችኋል ።
እንኳን ለዓለም አቀፉ የሚድዋይፍ ቀን አደረሳችሁ!
#midwifeday
#internationalmidwifeday2021
#IDM2021
#UNFPA
Today is the international day of the midwife to all the amazing midwives.
Thank you for all you do for all women , families and your colleagues ! #IDM2021

ዛሬ የዓለም የሚድዋይፎች ቀን ነው ። እስቲ እንኳን አደረሳችሁ እንበላቸው።
Lia Tadesse, Minister of Health
UNFPA Ethiopia
የታካሚዎች መልዕክት