St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የሕጻናት ሆድ ቁርጠት
t.me/spmmc

ህፃናት የሆድ ቁርጠት ብዙ ጊዜ ብዙ ህፃናት ላይ የሚከሰት ጊዜያዊ ችግር ሲሆን በተለይም 4 ወር ዕድሜ ድረስ ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ህመም አይነት ነው ዋና መለያውም የማያቋርጥ ረጅም ለቅሶ እና መነጫነጭ ነው።
በአብዛኛው ህፃናቱ የሆድ ቁርጠት የሚጀምራቸዉ በተወለዱ ከ3-6 ሳምንት ዕድሜያቸው ሲሆን ከፍተኛ የሚሆነው ስድስተኛ ሳምንት ላይ ነው ::

የሆድ ቁርጠት ያለባቸው ህፃናት በቀን ከ3 ሰአት በላይ፣ በሳምንት ደሞ ዉስጥ ከ3 ቀናት በላይ ያለቅሳሉ። ሁኔታዉም ከ3 ሳምንት በላይ ይቆያል።

ለቅሷቸዉ ከወትሮው በተለየ በጣም ጮክ ብለዉ ያለማቋረጥ ነዉ ሚያለቅሱት።

ሕጻናቱ ከዚህ አልፎ አልፎ ከሚከሰተው ቁርጠት ዉጪ በሌላዉ ሰአት ጡት በደንብ ይጠባሉ፤ ምንም አይነት ሌላ የህመም ምልክትም አይኖርባቸውም።

ህፃናት የሆድ ቁርጠትን የሚያመጣዉ ምክንያት በዉል ባይታወቅም ሆድ ዉስጥ አየር በብዛት ሲጠራቀም የሚከተለው የአንጀት ጡንቻዎች መኮማተር የህመሙ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

የህፃናት የሆድ ቁርጠት በአብዛኛው ጊዜ እስከ 6 ወር ዕድሜ ዉሰጥ በራሱ ጊዜ ይጠፋል።

የህፃናት የሆድ ቁርጠት ለወላጆች በጣም አስጨናቂ ነዉ። በተለይም ልጆቹ በየትኛውም አይነት መንገድ ለቅሶዉን ስለማያቋርጡ ሁኔታዉ ወላጆችን ለማረጋጋት ለሀኪሞችም ፈታኝ ነዉ።

ሕክምናው ምንድነው?

ወላጆች መረዳት ያለባቸዉ የሆድ ቁርጠት ይህ ነዉ የሚባል ፍቱን መፍትሔ እንደሌለው ሆኖምግን ከጊዜያዊ ምቾት መንሳት በቀር ህፃናቱን ለክፉ የማይሰጥ መሆኑን እና እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ የሚቀንስ እና በኋላም የሚጠፋ መሆኑን ነዉ።
ህፃኑን ከፍ አድርጎ ይዞ ጀርባዉን መታ መታ እያደረጉ እንዲያስገሳ ማድረግ ሆዱ ዉሰጥ የተጠራቀመውን አየር እንዲያስወጣዉ ስለሚረዳ ይህን መንገድ መሞከር መፍትሔ ሊሰጥ ይችላል

የሚከተሉት ደግሞ ህፃናቱ ለቅሶዉን እንዲያቋርጡ የሚረዱ መንገዶች ናቸዉ

1.ህፃኑን ወደ ላይ ከፎ አድርጎ ትከሻ ላይ መያዝ እና ጀርባውን መታ መታ ማድረግ
2.ወደ ሌላ አዲስ ክፍል ወይም ከቤት ወደ ዉጪ መዉሰድ (change environment )
3. ሆዱን ቀስ እያሉ መዳበስ (massage)
4. ሞቅ ባለ ዉሀ ገላውን ማጠብ
5. ዥዋዥዌ ማድረግ
6. ዝቅ ያለ ማያቋርጥ ድምፅ መክፈት (white noise )

እናት ምን ማድረግ አለባት?
ወላጅ ከሆኑ የልጅዎ የሆድ ቁርጠት እርስዎንም ከባድ ጭንቀት እና መወጣጠር ዉሰጥ ሊከት ይችላል። በዚህ ሰአት እርስዎ ራቅ ብለዉ እርፈት መዉሰድ ይኖርቦታል። ልጆን ሊንከባከብ ወይም ሊይዝ የሚቺል ሰው ቤት ዉስጥ ብያግዞ መልካም ነው:: እርሶም ልጅዎ ለከፋ ነገር እንደማይዳረግ ለራስዎ በመንገር ለመረጋጋት ይሞክሩ።

በሌላ ጊዜ ቁርጠቱ እንዳይደጋገም የሚከተሉትን ያድርጉ ።

1.ጡት ወይም ጡጦ ከጠባ በኋላ ማስገሳት
2. ልጁ ጡት ወይም ጡጦ ሲያጠቡት ባዶ አየር ወደ ሆዱ በብዛት እንዳይወስድ መከታተል
3. ልጅዎ ከበቂ በላይ ወይም በታች ፈሳሽ እየሰጡት እንዳልሆነ ያረጋግጡ ( በቂ የሆነ ፈሳሽ ሚባለዉ እስከ 6 ወር ላሉ 150 ሚሊሊትር × ክብደታቸው በኪሎግራም ፤ ከ7-12 ወር ላሉ 120 ሚሊሊትር × ክብደታቸው በኪሎግራም ነዉ ፥ ለምሳሌ የ 7ወር ክብደቱ 8ኪሎ የሆነ ልጅ በቀን ማግኘት ያለበት 120×8=960ሚሊልትር ፈሳሽ ነዉ። )

ልጆች የሆድ ቁርጠት ሲይዛቸዉ ጡት ማጥባት ማቆም ወይም የታሸገ ወተት ይወስዱ ከነበረ ደግሞ አይነቱን(brand) መቀየር አይመከርም ፤ ጥቅምም የለዉም።

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም)
የአዕምሮ ጤና ምንድነዉ?
ስለ አዕምሮ ጤና ከማዉራታችን በፊት ጤና ምንድነዉ የሚለዉን ማየቱ መልካም ነዉ። ጤና (Health) ለሚለዉ ቃል ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል መልስ እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን እንደ አለም ጤና ድርጅት አተረጓጎም ፡- ጤናን “የበሽታ አለመኖር ሳይሆን የተሟላ አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ደህንነት ነዉ” በማለት የሶስቱ ፈርጆች ጤናማነት ሲሟላ የሚመጣ ሁኔታ አድርጎ ይወስደዋል።
ወደ አዕምሯዊ ጤና ስንመጣ የአንድን ሰዉ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት ይገልጻል። አዕምሯዊ ጤና ስሜታዊና አዕምሯዊ ደህንነት ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ የማገናዘብ አቅሙንና ስሜታዊ ችሎታዉን ተጠቅሞ በማህበረተሰቡ ዉስጥ ግዴታዉን በመወጣት የዕለት ተለት የኑሮ ፍላጎቱን መሟላት መቻል ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ሰዎች አቅማቸዉ እና መክሊታቸዉን የመጠቀም እና ከችሎታቸዉ ከፍታ የመድረስ ብቃት ነዉ። በስራ ዉጤታማ መሆንና ለማህበረተሰቡ አስፈላጊዉን አስተዋጽኦ ማበርከት መቻል አዕምሯዊ ጤናቸዉ የተስተካከለ ሰዎች መገለጫ ጠባይ ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ባጠቃላይ ከአሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ስሜቶቻችን ጋር የጠበቀ ቁርኝነት አለዉ። የአዕምሯዊ ጤና ባለቤት ልንሆን የምንችለዉ ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ስንታረቅና ፍሬያማ ግኑኝነት መፍጠር ስንችል ነዉ። ከራስ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ራስን በማወቅ ከአሉታዊ ስሜቶች (መናደድ፣ ማዘን፣ መፍራት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት፣ ቅናት፣ ቂም እና ተጠራጣሪነት) በመራቅ ወደ ሳቢ ስሜቶች (ፍቅር፣ ደስታ፣ አድናቆት፣ ሩህሩህነት፣ ጉጉነት፣ ፈጠራና የማወቅ ፍላጎት) መሳብ መቻል ከሌሎች ጋር ለምንመሰርተዉ የሰመረ ግኑኝነት ጠንካራ መሰረት ይጥላል።
አዕምሯዊ ጤና የሰመረ መሆኑ መገለጫዎች መካከል፡-
👉በራስ መተማመን
👉በመጥፎ ልማዶች ያለመዉደቅ እናም ራስን በማየት መታረም
👉ያለመሰላቸት
👉በየጊዜዉ አዲስን ነገር ለመማር ዝግጁ መሆን
👉ስለ ህይወት ትርጉም ያለዉ እንደሆነና፣ የተስተካከለ እና ቀና አመለካከት መኖር
👉አሉታዊ ስሜቶችን እና ዉጥረትን መቆጣጠር መቻል
👉መረጃዎችን አቀናብሮ መጠቀም መቻል
👉ለራስ እንደሚያስቡ ለሌሎችም ግድ ማለት መቻል
👉ችግርን መፍታት መሞከር ካልሆነም ለሌሎች ማካፈል እና አስፈላጊ ሲሆን ትብብር መጠየቅ መቻል
👉ራስን በበጎ አኳኋን መመዘን፣ ማሻሻል እና ማሳደግ መቻል
👉ራስን መምራት መቻል
👉በራስ መወሰን መቻል
እነዚህን ባህርያት መላበስ ከህይወታችን አሰራር ጋር የጠበቀ ዝምድና አላቸዉ። በመሆኑም በህመም ላለመጠቃት ብርታትም ጭምር ናቸዉ።
ባጠቃላይ፤ ዉጤታማነትና ስኬት የአዕምሮ ጤንነት ዋና ማሳያዎች ናቸዉ። ዘና ማለት፣ እችላለሁ ባይነት፣ የተወዳዳሪነት ስሜት፣ ጭንቀትን መቆጣጠር መቻልና ከመጥፎ ሁኔታ በቶሎ ማገገም መቻል አዕምሮ ጤንነት ትሩፋቶች ናቸዉ።
ዶ.ር አስራት ሀ/ጊዮርጊስ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
ራዳት ፕሮፌሰርና የአዕምሮ ሕህክምና ስፔሺያሊስት
•
ነፍሰ ጡር እናቶች ለትምባ ጭስ ከተጋለጡ በራሳቸውና በጽንሱ ጉዳት ያስከትላል፡፡
#ትምባሆማጨስያቁሙ!#NoTobaccoDay2021
#WorldNoTobaccoDay #CommitToQuit #የዓለምሲጋራየማይጤስበትቀን
የጨቅላ ህፃናት አደገኛ የሕመም ምልክቶች ምንድናቸው ?

# ጡት አለመጥባት ወይም መጥባት መቀነስ
# ቶሎ ቶሎ መተንፈስ( በደቂቃ ከ 60 በላይ የሚተነፍስ ከሆነ)
# ረጅም ሰዓት የሚቆይ ማቃሰት
# የሰውነት ትኩሳት ከ 38 ሴንቲግሬድ በላይ ከሆነ
# የሰውነት በጣም መቀዝቀዝ ከ 35.5ሴንቲግሬድ በታች ከሆነ
# የሰውነት መንቀጥቀጥ
# በጣም ተከታታይ እና ኃይለኛ ትውከት
# የአይን እና የሰውነት ቢጫ መሆን
# በጣም መፍዘዝ እና አለመንቃት ወይም ራስን መሳት
# የከንፈር እና የምላስ መጥቆር
# የሆድ ከመጠን በላይ መነፋት
# በተወለደ በ48 ሰዓት ዉስጥ ዓይነምድር ከሌለው
# በተወለደ በ24 ሰዓት ውስጥ ሽንት ካለሸና

ውድ ወላጆች ከላይ ላይ የተገለፁት ምልክቶች በልጅዎ ላይ ከተከሰቱ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ ይገባችኋል ።

ዶክተር ፋሲል መንበረ
በ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
ስመ ጥሩዋ ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በኮሌጃችን በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነው። ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና ነርሶቻችን የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ይገኛሉ።

በጤናቸው ካለፉት ቀናት ሲነጻጸር መሻሻል አሳይተዋል ማለት ይቻላል ።

ከዚህ ውጭ ካለ በቂ መረጃ በፌስ ቡክና በሌሎች ማህበራዊ ገጾች የሚጻፉትን በሙሉ ተዓማኒነት የላቸውም።
የተከበራችሁ የክብርት ዶር አበበች ቤተሰቦች እና መላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ የእኚህን የአገር ባለውለታ የጤና ሁኔታ በቅርብ የሚከታተልዋቸውን ሐኪሞች ዋቢ አድርገን በየጊዜው የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
t.me/spmmc
በማሽን ከመተንፈስ፤በማስክ መተንፈስ ይበጃል፡፡
ይጠንቀቁ !
ብዙ እናቶች ˝̋̋ የጡቴ ወተት ትንሽ ነው፣ ልጄንም አያጠግበውም ˝ እያሉ ይጠይቃሉ፡፡የዛሬው ጤና መረጃ ትኩረቱ እዚህ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡
የ እናት ጡት ወተት በምን ምክንያት ይቀንሳል?
• ልጅሽ እንደተወለደ ወዲያው ጡት ካልጠባ
• ልጅሽ በትክክለኛ ባልሆነ አያያዝ እና አጠባብ ጡት የምትሰጭው ከሆነ
• ልጅሽን ቶሎ ቶሎ በሰዓቱ ካላጠባሺው
• የአዕምሮ ዉጥረጥ መጨናነቅ እና አለመረጋጋት ካለ
• በቂ እረፍት ካልወሰድሽ
• በቂ ምግብ እና ፈሳሽ ካልወሰድሽ
• ልጅሽ ከእናት ጡት ወተት ዉጭ ሌላ ወተት የሚወስድ ከሆነ
• ማንኛዉም ሱስ ካለብሽ
• መድሃኒቶች የምትጠቀሚ ከሆነ በተለይ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች
• ደም ግፊት እና ከመጠን ያለፈ ዉፍረት
• ከፍተኛ የካፌን ንጥረ ነገሮች ያላቸዉን ምግቦች እና መጠጦችን(ቡና ሻይ ለስላሳ መጠቶች) የምታዘወትሪ ከሆነ

የጡትሽ ወተት በቂ ከሆነ ልጅሽ ላይ የሚከተሉትን ምልክቶች ይታያሉ፡፡
 ልጅሽ ጠብቶ በቀን ቢያንስ 5 ወይም 6 ጊዜ ሽንት ይሸናል፣
 2 ወይም 3 ጊዜ ይጸዳዳል፡፡
 ኪሎው እየጨመረ ይሄዳል(በቀን 30 ግራም)
 በደንብ ይተኛል (ቢያንስ 2 ሰዓት)
 በደንብ ሲጠባ እና ሲውጥ ላንቺም ይታወቅሻል

የጡት ወተትሽ በቂ እንዲሆን ማድረግ ያለብሽ ነገሮች፡፡
 ከላይ የተዘረዘሩትን የ ጡት ወተት የሚቀንሱ ነገሮችን አስወግጂ
 ጡትሽ ቶሎ ቶሎ ማለብ ወይም ማጥባት
 ልጅሽን ደረትሽ ላይ ዳይፐር ብቻ አርገሽ አስተኝው
 ለብ ባለ ዉሃ የተነከሩ 2 ፎጣዎች ከጡትሽ ከላይ እና ከታች ይዘሽ ቀስ ብለሽ ከላይ ወደ
ታች ማሳጅ ማድረግ
 በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
 በቂ ፈሳሽ መውሰድ በተለይ ከአትክልት እና ፍራፍሬ ፓፓያ, ብርቱካን, ሃባብ ማንጎ
መውሰድ
 በተቻልሽው መጠን በቂ እንቂልፍ እና እረፍት ማድረግ
 አለመጨነቅ

እነዝህን ሁሉ አርገሽ ምንም ለውጥ ከሌለ ወይም ልጅሽ ትኩሳት እና በጣም መነጫነጭ ካመጣ እንደራበው ጡትሽን ቀድመሽ ትሰጭ እና ቀጥሎ በንፁህና የተዘጋጀ የጣሳ ወተት መስጠት ትቺያለሽ፡፡ ይህ ግን የ መጨረሻ አማራጭ ብታደርጊው መልካም ነው::
ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)
New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) Registration Announcement
__________________

Dear Esteemed applicants,

Registration for 2021 New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) has already started and deadline is on June 18, 2021. So kindly read the requirement criteria for the registration and use link below to register.

Admission Policy: Applicants who fulfill the following parameters are eligible for entrance examination
1. Bachelor’s degree in Health sciences, Biology & Chemistry.
2. Cumulative GPA 2.75 for females & applicants from emerging regions and 3.0 for male applicants.
3. At least 2 years’ service after graduation.
4. Age not more than 35 years.
5. In Good health (must provide medical certificate)
6. Recommendation letter: one from work with a detail profile of the recruits using the template provided: social accountability, professionalism, participation in the community, free of addiction etc), and a second one from their undergraduate training program.
7. Additional copy of all necessary educational documents should be uploaded following appropriate format.
8. Deposit application fee of 50 birr (Commercial Bank of Ethiopia, St. Paul's Hospital Millennium Medical College፡ A/C Number - 1000006577192) and upload the deposit slip.
9. The application will be complete if all necessary information filled and uploaded
10. Application date ends on June 18th 2021 (አርብ ሰኔ 11 ቀን 2013 )
11. Upload all documents as Jpg | Png | Pdf | Gif format only.
12. Exam place is Addis Ababa
• Written Examination and Interview date will be announced soon.

• For additional information - you can contact via:

1. Dagnne Minda(ICT) email:dagne.minda@sphmmc.edu.et phone: +251911421162
2. Tamirat Dilnesie Teferra(Registrar) email: registrar@sphmmc.edu.et phone:+251916342554
3. Misganaw Tadesse(ICT) email: misganaw.tadesse@ sphmmc.edu.et phone: +251912103711
4. Elias Abreham(ICT) email: elias.Abreham@sphmmc.edu.et phone: +251962084685

register here >> http://197.156.83.153/registration/index.php/Welcome/register