የደም ግፊት በሽታ ምንድን ነው?
የደም ግፊት ልኬት ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ሆኖ ሲቆይ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ይባላል፡፡ልባችን ደም ለማዘዋወር ከፍተኛ በሆነ ሀይል ደም በሚረጭበት ወቅት ከፍተኛ የደም ግፊት ይፈጥራል፡፡ ይህም በኋላ ላይ የአዕምሮ ስራ መታወክ /ለስትሮክ/ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
የደም ግፊትን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ በአብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት ወይም የበሽታ ስሜት የለውም፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት አንዴ ከተከሰተ በኃላ ትክክለኛው መጠን እስከሚደርስ ድረስ በየጊዜው መለካት ያስፈልጋል፡፡ የደም ግፊታችንን መጠን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ በጤና ባለሙያ በመለካት ብቻ ነው፡፡
በተለያየ ወቅት ሦስት ጊዜ ተለክተው የደም ግፊትዎ ከፍተኛ ከሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ነው ማለት ይቻላል፡፡
እነዚህ የደም ግፊት ምልክቶች የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ናቸው፡፡ ሃይለኛ ራስ ምታት፣ ድካም ወይም መደናገር፣ ብዥታ፣ የደረት ህመም፣ የመተንፈስ ችግር፣ የተዛባ ልብ ምት፣ ደም የተቀላቀለበት ሽንት፣ ፈጣን የልብ ምት /ከፍተኛ ድምፅ ያለው ምት በደረት፣ አንገት እና ጆሮ አካባቢ/ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን አብዛኛው ሰው የከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ቢኖርበትም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ፡፡ በምልክት ብቻ በመታገዝ የከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ አለ ወይም የለም ማለት አይቻልም፡፡
ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ተጋላጭ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
• ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ( በተለይም ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ፣)
• የሰውነት ክብደታቸው ከፍተኛ የሆነ፣
• ጭንቀትየሚያበዙ
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያዘወትሩ፣
• የደም ግፊት በሽታ በቤተሰባቸው ታሪክ ያለባቸው፣
• ሲጋራ የሚያጨሱ ወይም አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ፣
• ብዙ ጊዜ ጨው የበዛበት ምግብ የሚመገቡ፣
• የአልኮል መጠጥ የሚያዘወትሩ፣
• በቂ ፍራፍሬ እና አትክልት የማይመገቡ፣
• የኩላሊት በሽታ ያለባቸው፣ እና
• የስኳር በሽታ ያለባቸው፣
ለከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም አዋቂ የሆነ ሰው ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ወደ ጤና ባለሙያ በመሄድ የደም ግፊታቸውን እንዲለኩ ይመከራል፡፡
እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ከታየ ሐኪም መድሃኒት ሊያዝ ይችላል፡፡ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ለምሳሌ፣
• ፍራፍሬ እና አትክልት በብዛት መመገብ፣
• በየቀኑ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
• አዘውትሮ በምግብ ወቅት ምንም አይነት ጨው አለመጨመር ፣
• ሲጋራ ማጤስ እና የአልኮል መጠጥን ማቆም
• ጭንቀትን መቀነስን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ
ምንግዜም የሐኪም ምክርን ተግባራዊ ያድርጉ፡፡ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መድሓኒትን መውሰድ ፈፅሞ ተገቢ አይደለም፡፡ የደም ግፊትዎን በየጊዜው መለካትና መጠኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር ተሻሽሎ በወጣ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ
____________
በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመግታት እና በስራ ላይ በነበረው መመርያ ቁጥር 30/2013 ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ በተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም ከነሀሴ13 ቀን/2013 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) አውጥተዋል፡፡
ይህንን አስመልክቶ መግለጫው የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን አካላትም በመመሪያው ዙሪያ ባለሞያዎችን በመጋበዝ ህብረተሰቡ መመሪያውን እንዲያውቀው በስፋት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሰሩ እና እንደወትሮው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የወጣው መመሪያ ቁጥር 803/2013 አስራአንድ ክፍሎችና ሰላሳ ሰባት አንቀፆች ያሉት ሲሆን በዚህ መመሪያ በዋናነት የተዳሰሱት ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል ፡፡
◾️የተከለከሉ ተግባራት እና የተጣሉ ግዴታዎች በተመለከተ
• ማንኛውም ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ቫይረሱ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው፣
• ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ለማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ወይም የእርስ በእርስ አካላዊ ንክኪ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
• እድሜያቸው ከ6 አመት በታች ከሆኑ ህፃናት እና በማሰረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው ሰዎች በስተቀር በማንኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ መገኘት ወይም መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣
• በማንኛውም መንግስታዊ እና ግል ተቋም ሰራተኞችና ተገልጋዮች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዲሰጡ ወይም እንዲያገኙ ማድረግ ወይም በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግ የተከለከለ ነው፣
• በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ወይም ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፣
• ማንኛውም የመንግስታዊ እና የግል ተቋማት ለሰራተኞች ስለ በሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡
◾️በቤት ውስጥ ማቆያ እናክብካቤ ወቅት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ በተመለከተ
• ማንኛውም ከባድ ባልሆነ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ 19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል፣
• ከሌላው የቤተሰብ አባላት በ 2 የአዋቂ ርምጃ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ራስን ቢያንስለ 10 ተከታታይ ቀናት በመለየት መቆየት፣ በነዚህ ወቅቶች ከቤት አለመውጣት ይጠበቅበታል፡፡
◾️የኳራንቲን እና የድንበር ላይ ጤና ቁጥጥርን በተመለከተ
ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ 120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋገጠ የRT PCR ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣት አለበት፣ አገር ውስጥ ከገባ በኋላም ለ7 ቀናት በቤቱ ራሱን ለይቶ የማቆየት ግዴታ አለበት፣
እራስን ለ7 ቀናት በቤት ውስጥ ለይቶ የማቆየት ግዴታ የሚከተሉትን አካላት አይመለከትም፡
• በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ 19 ታመው ያገገሙ መሆናቸውን የሚግልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
• ዲፕሎማቶች
• የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ
• ለኮንፈረንስ ለመሳተፍ የመጣ መንገደኛ ወይም ቱሪስት ወይም ለድንገተኛ አገራዊ ጉዳይ የመጣ መንገደኛ አገር ውስጥ ከገባ በሃላ ተጨማሪ የኮቪድ-19 ምርመራ ተሰርቶለት ዉጤቱ ኔጌቲቭ ከሆነ ለ 7 ቀናት ራስን ለይቶ ማቆየት አይጠበቅበትም፡፡
የኮሮና ቫይረስ ፖዘቲቭ የሆነ ማንኛውም ሰው ወደ ሀገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
◾️በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፍ የትራንዚት መንገደኛን በተመለከተ
በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚገባ ማንኛውም የትራንዚት መንገደኛ አየር መንገዱን ለቆ ወይም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት የለበትም ፡፡
◾️በአስክሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች በተመለከተ
ከቀብር በኋላ ለቅሶ መቀመጥ በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ሲደረግ ሀዘንተኛው እና የቤተሰቡ አባላት እና ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 ሰው ሳይበልጥ እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በመጠበቅና ባለመነካካት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ሌሎችበአገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው ማንዋል ላይ የተቀመጡትን ጥንቃቄ ተፈጻሚ በማድረግ መሆን አለበት፡፡
◾️በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች በተመለከተ
• የኮቪድ 19 ጥንቃቄዎችን ባማከለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል፣
• ከ50 ሰው በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት አዳራሽን ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን፣ በማይበልጥ ሰው ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እና በተዋረድ ባሉ የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች አስቀድሞ በማኘት ሊከናወን ይችላል፣
• ስብሰባውን የጠራው እና መስተንግዶ ሰጪ አካል መሰረታዊ የመካላከያ ዘዴዎች መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
◾️የሃይማኖት ስነስርዓቶችን አተገባበርን በተመለከተ
• ሀይማኖታዊ ስርዓት የሚፈጽሙ ሰዎች ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በሚፈጽሙበት ወቅት ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎች በታች ተጠጋግቶ ስርዓቱን መፈጸም የተከለከለ ነው፣
• የሀይማኖቱ ስርዓት የሚከናወንበት ህንፃ ውስጥ ህንፃው የሚሸፍነውን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ ይኖርባቸዋል፣
• በእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የእምነቱ ተከታዮች የእምነት ስርዓቱን በሚፈስጽሙበት ወቅት ሲቆሙም ሆነ ሲቀመጡ የሁለት ሜትር ርቀት የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፣
• ማንኛውም ሰው የአፍእና አፍንጫ መሸፈኛ ሳይደረግ ወደእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
◾️የቤ

ት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተ
• ለልደት፣ ምረቃ፣ማህበር፣ሀዘንን መሰረት የሚያደርጉ ዝግጅቶች (ከቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነስርዓቶች ውጭ) እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለ ነው፣
• ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም ሰው ከ50 በላይ የማይበልጡ ሰዎች በመሆን እና ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር) ተራርቆ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ 19 መከላከያ የንጽህና እርምጃዎች በመተግበር የሰርግ ስነስርዓት ማካሄድ ይችላል፡፡
◾️የአደባባይ በዓላት አከባበርን በተመለከተ
• ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኑ ስርጭት መረጋጋት እስኪጀምር ድረስ በታቸለ አቅም ባይደረጉ ይመከራል፣
• ማንኛውም በአደባባዮች ላይ የሚከበሩ በዓላትን የሚታደምም ሆነ አከባበሩን የሚያስተባበር ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ እና በአከባበርም ወቅት ሁለት ሜትር ርቀትን ጠብቆ የመቆምና መቀመጥ ግዴታ አለበት፣
• ማንኛዉም በአደባባይ የሚከበሩ በዓላትን የሚያስተባብር አካል በዓላት የሚከበሩባቸው አደባባዮች የሚሸፍኑትን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ ስርዓቱን ማካሄድ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
◾️አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች፣መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች በተመለከተ
• በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ ይገባል፣
• አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣
• የሚስተናገዱ ሰዎች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጭ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
◾️ሲኒማ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና የስዕል ጋላሪ ቤቶች በተመለከተ
አገልግሎቱ የሚሰጥበት አዳራሽ ወይም ስፍራ ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ፣ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (ሁለት ሜትር) በማራራቅ እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በማስደረግ አገልግሎቱን መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
◾️ስፖርታዊ ውድድሮች በተመለከተ
• ማንኛዉም የስፖርት ዉድድር የስፖርት ዉድድሩ ስፍራ የሚይዘው የታዳሚ ብዛት ታሳቢ በማድረግ ከአንድ አራተኛዉን ታዳሚ የማይበልጥ እንዲታደም በማድረግ ማከናወን ይቻላል፣
• እነዚህ ውድድሮች ወረርሽኙን ባገናዘበ መልኩ መከናወን መቻላቸውን በማረጋገጥ ፈቃድ የመስጠት እና በውድድር ወቅቶችም የጥንቃቄ እርምጃዎች የማይተገበሩ ከሆነ አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት የሚፈጸም ይሆናል።
በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚገኙባቸው ተቋማት ላይ የተጣሉ ክልከላዎች እና መደረግ ያለባቸው
◾️የጥንቃቄ እርምጃዎች በተመለከተ
• የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ በሚከተሉት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ ነው:: ነገር ግን እርዳታ ሰጭዎች ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ማንኛውንም ድጋፍና መሰል ተግባራትን ማድረግ ይችላሉ
i. የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና
ii. የማገገሚያ ማዕከላት
• በማረሚያ ቤቶች ላይ የሚደረግ የታራሚን በአካል የመጎብኘት ሂደት በታራሚው እና በጠያቂው መሀል ሁለት የአዋቂ እርምጃ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣ ታራሚውም ሆነ ጠያቂው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በማስደረግ፣ ጠያቂው ወደማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ከመግባቱም በፊት እና ሲወጣ እጁን በውሃ እና ሳሙና እንዲታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር እንዲያጸዳ በማድረግ፣ እንዲሁም ሌሎች በዝርዝር በማንዋል የሚወጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተከትሎ መሆን አለበት፡፡

የህፃናት ጭንቅላት መናጋት(shaken baby syndrome) ምንድነው?
t.me/spmmc
የህፃናት ጭንቅላት መናጋት በህፃናት ላይ የሚደርስ የጥቃት አይነት ሲሆን የሚከሰተውም የጨቅላ ህፃን ልጅ ጭንቅላት በሀይል ሲወዘወዝ ወይም ሲነቀነቅ ነው ::
ይሄ አደጋ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው አሳዳጊዎች የህፃኑ ለቅሶ ለማስቆም በሚል ካለማወቅ ወይም በጣም ከመጨነቅ የተነሳ ልጁን በሀይል ሲወዘውዙት ነው ::
በዚህ ወቅት የልጁ አንጎል በራስ ቅሉ ውስጥ ከኃላ ወደ ፊት ከፊት ወደ ኋላ እየሄደ ከራስ ቅሉ (አጥንቱ) ይጋጫ ል ።በዚህም ጊዜ በተለያዩ አይምሮ ወይም አንጎል ክፍል ዉስጥ ደም መድማት ያስከትላል።
የህፃናት ጭንቅላት መናጋት (shaken baby syndrome) የደም ስሮችን እና የአንጎል ህዋሶችን በማውደም አይምሮ ዉስጥ በቂ የደም ዝውውር እንዳይኖር እና የነርቭ ህዋሶች ኦክሲጅን እንዳያገኙ ይከለክላል❗️
ከዚህ አልፎ ተርፎም የሕፃናቱን አንጎል በመጉዳት ሞትን ሊያስከትል ይችላል‼️
✔️ ህፃናት በተለያየ ምክኒያት ያለቅሳሉ፤ ወላጆች አልያም ተንከባካቢ ሞግዚቶች የሚያለቅሰዉን ህፃን ተረጋግተው ማባበል ይጠበቅባቸዋል።
✔️ በማልቀስ ላይ ያለው ልጅዎ ዝም አልል ሲል ተረጋግተው የሚችሉትን ሁሉ ያድርጉ።
በፍፁም ጨቅላ ህፃን ልጅዎን በሀይል አይወዝዉዙት። በህፃናት የአንጎል ላይ የማይስተካከል ጉዳት ለማድረስ የጥቂት ሰኮንዶች መናጋት ብቻ ይበቃል❗️
ልጁዎትን በመንከባከብ ረገድ ሌላ ተቀጣሪ የሆነ ሰው ፣ የቤት ሠራተኛ ፣ እህትና ወንድም ወይም አያት ካገዟችሁ ስለ ህፃናት የአንጎል መናጋት አደጋን እንደሚያውቁ እርግጠኛ ይሁኑ ‼️
🔷 ጨቅላ ልጁዎት በጣም አልቃሻ እና አስቸጋሪ ከሆነ፣ ለሌሎች ከመስጠትዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ።
ታዲያ የህፃናት አንጎል መናጋት(shaken baby syndrome) ምልክቶች ምንድናቸው?
🔘 በጣም የከፋ ከ ወትሮ ለየት ያለ ለቅሶ ወይም መነጫነጭ
🔘 የአተነፋፈስ ችግር ለምሳሌ ማቃሰት
🔘 ራስን መሳት እና ማንቀጥቀጥ
🔘 ኃይለኛ ትውኪያ
🔘 የገረጣ ወይም ደም ያዘለ ቆዳ
🔘 አልፎ አልፎ ህፃኑ የመናጋት አደጋ ደርሶበት እንኩዋን ጤነኛ መስሎ ሊታይ ይችላል❗️
ከላይ ያሉ ምልክቶች ግን ሁልጊዜ ከአይምሮ መናጋት ጋር ብቻ ይያያዛሉ ማለት አይደለም ‼️ ሌሎች ህመሞችም ከላይ ያሉትን ምልክቶች ሊያመጡ ይችላሉ ::
ሆኖም ጥርጣሬ ካለዎት ግን ሐኪምዎን ያማክሩ ::
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ክትባት ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የመግለጫቸው ዋና ዋና ዓብይ ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው
በባለፈው ሳምንት ብቻ 5547 ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ሁለት እና ሶስት በመቶ የነበረው የስርጭት ምጣኔ በአሁኑ ሰዓት በአማካይ አስራ ሁለት (12 %) በመቶ ደርሷል፡፡
በየቀኑ ወደ ጽኑ ህሙማን ማዕከላትም የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል። እስከ ትላንት ድረስ 510 ሰዎች በጽኑ ታመዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ብቻ 66 ሰዎች በወረርሽኙ አርፈዋል። በአሁኑ ሰዓትም በቀን በአማካይ 9 (ዘጠኝ) ሰዎች እየሞቱ ነው።
አሁን ላይ ያለው ቁጥራዊ መረጃዎችና ሁኔታዎች የሚያሳዩት የሶስተኛው ዙር ማዕበል (3rd wave) በሀገራችን እንደጀመረ ያመላክታል።
ሕብረተሰቡ የሚጠበቅበትን መሰረታዊ የመከላከያ መንገዶችን አጠናክሮ የማይተገብር ከሆነ ነገሮች እየከፉ ሊመጡ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ትንበያዎች ያሳያሉ።
በመሆኑም መሰረታዊ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ክትባቱን መከተብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ለማህበረሰቡ ተሰጥቷል ።
ርቀትን በ 2 ሜትር መጠበቅ፣ ማስክን ሁልጊዜና በአግባቡ ከማድረግ ባለፈ የእጅ ንፅህናን በተገቢው መንገድ መጠበቅ የሚኖርበት ሲሆን አላስፈላጊ መሰባሰቦችን መቀነስ (በተለይ በዝግ ቦታዎች ላይ የሚደረጉትን)፤ እንዲሁም ምልክቶች ሲታዩም በአፋጣኝ ራስን በማግለል የባለሙያ ምክር መጠየቅ ይገባል ።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 ማሻሻያ በማድረግ አዲስ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 803/2013) ወጥቷል።
መመሪያ 803/2013 ሊንኩን ተጭነው ማግኘት ይችላሉ፡-
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fbclid=IwAR1PfjwUw4CKLPJdf3EAN7gaAXK27zTeSBGIZhttWbvr0tpHYXvLuFgNrJ0

Google Docs
Covid-19 Directive 803 _210822_140019.pdf
የኮቪዴ-19 ወረርሽኝ የመከላከልና ለመቆጣጣር ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 803/2013 ያውቁታል?
መመሪያው ’የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ስላሚወሰድ ክልከላዎችን እና ስለሚጣሉ ግዴታዎች ስለመወሰን ተሻሽሎ የወጣ መመሪያ ነው፡፡ ሙሉ መረጃውን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fb
መመሪያው ’የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጣር ስላሚወሰድ ክልከላዎችን እና ስለሚጣሉ ግዴታዎች ስለመወሰን ተሻሽሎ የወጣ መመሪያ ነው፡፡ ሙሉ መረጃውን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
https://drive.google.com/file/d/1c63ANoG1UaFhssD6RZzitwroUNDNe1Ek/view?fb
Google Docs
Covid-19 Directive 803 _210822_140019.pdf
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

የኮቪድ-19 ምልክት ያላቸው እና ምርመራ ማድረግ የሚፈልጉ በ30 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚያደርስ ፈጣን የኮቪድ-19 መርመሪያ መሳሪያ (Antigen RDT) አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
t.me/spmmc
t.me/spmmc
ለ2013 ዓ.ም የህክምና ዶክትሬት ትምህርት ወይም (NIMEI) እጩ ተማሪዎች በሙሉ
__________
በ2013 ዓ.ም የህክምና ዶክትሬት ትምህርት ወይም New Innovative Medical Education Initiative (NIMEI) ለመከታተል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒም ሜዲካል ኮሌጅ የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በኮሌጁ የተመረጣችሁ ሰልጣኞች ትምህርታችሁን የምትከታተሉባቸውን ኮሌጆች ምድብ አባሪ በተደረገው ሊንክ( https://www.moh.gov.et/ejcc/am/NIMEI_Final_Deployment) መሰረት ኮሌጆቹ በሚያወጡት የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃል፡፡

ወላጆች ሊያውቋቸው ስለልጆች ሊያውቁት የሚገባ 10 አበይት ጉዳዮች
---------------------------------------------------
ወላጆች ማድረግ ያለባቸው
1. ለልጆች ስለሚችሉት ነገር እንጂ ስለማይችሉት ነገር አይንገሩዋቸው። ዘወትር አሉታዊ ንግግርን የሚሰሙ ልጆች ይህንን አሉታዊውን ንግግር ይላመዱታል፡፡
በጣም አንገብጋቢ ሁኔታ ላይ ከባድ አሉታዊ ቃላትን ከመናገር ከተቆጠቡ ልጆች የሚጠቀሙበትን ቃላት ይሰማሉም፤ያከብራሉም፡፡
2. ልጆችዎ እንዲይዙ የሚፈልጉትን ባህሪ ለማየት ለልጅዎችዎ አስተማሪ ቃላትን ይናገሩ፡፡
ልጆች መሆን የሚፈልጉት ጎልማሶች እንዲሆኑላቸው የሚመኙትን ነው፡፡
ልጆቻችን ተወዳጅና ብቁ እንዲሆኑ ከጠበቅን ልጆችም
እንደዚያ ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ፡፡
3. ልጆች የመወደድና ብቁ እንደሆኑ ስሜት ካደረባቸው በራስ መተማመናቸው ይጨመራል።
በቤተሰብ ደረጃ ማራኪ ምግብ ማዘጋጀት ልጆቹ የባለቤትነት ስሜት እንዲያዳብሩ እና ለቤተሰብ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ስሜት ያዳብራሉ።
4. በቤተሰብ ደረጃ አብሮ በአንድ መዓድ ( ጠረጴዛ )መመገብ በቤተሰብ ደረጃ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል ፡፡
ይህም ጊዜ ስለ ቤተሰቡ ሁኔታና ስለልጆች የቀለም ትምህርት ብቃትና የትምህርት ቤት ሁኔታ ለመወያየት ጊዜ ይሰጣል፡፡
ጥናቶች አንደሚጠቁሙት ዘወትር ከቤተሰብ ጋር ማዕድ የሚቀርቡ ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውም ሆነ የትምህርት ብቃታቸው ከሌሎች አዘውትረው ማዕድ ከማይቀርቡት ልጆች የተሻለ ነው፡፡
5. ለልጆች ምርጫዎችን ማቅረብ ያለብዎት የልጆችን የምርጫ ውሳኔ ለመቀበል ፈቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው።
6. ልጅች ለመስራት የሚሞክሩትን ያጢኑና ከዚያም ለመስራት የሞከረውን ወይም የሞከረችውን ነገር ሁሉ ያድንቁ ።
አስፈላጊ ከሆነ ያግዙዋቸው ወይም ከሱ /ከርሷ ጋር አብረው ይሆኑ፡፡
7.ልጆች በአካል ንቁ እንዲሆኑ ቤተሰቦች የልጆችን የ ማህበራዊ ገፅ ዕይታ ጊዜያቸውን መቀነስን አለባቸው ።
በዚህ ፋንታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም በማውጣት አብሮ መስራት ::
8. የልጆችን ቴሌቪዥን፣ ኮምፒተርና ቪዲዮ የሚመለከቱበትን ጊዜን መወሰን ይገባል።
9. ለልጆችዎ ሊገባቸው ወይም ሊረዱት የሚችሉትን የተወሰኑ ጥብቅ ህጎችን ሊኖር ይይኑራቸው
በሕጉ ትግበራ ወቅት እናትም እና አባት አንድ አይነት አቁአም ይኑራቸው።
ልጆች ሲባልጉ ከመቅጣት ይቅር ምክርን ማስቀደም
ልጆች በምክር ካልተመለሱ በተቀመጠው ሕግ መሰረት መቅጣት ተገቢ ነው ።
10. ወላጆች ልጆች እንዲይዙት የምትፈልጉትን ባህሪ ልጆች ማወቃቸውን በደንብ መገንዘባቸውን እና መስማማታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ ።
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፈሰር

የጨቅላ ህፃናት ላብ መብዛት ምክንያቱ ምንድነው?
ላብ በተለያዩ ምክንያቶች ጨቅላ ህፃናት ላይ በተደጋጋሚ ሊታይ የሚችል ነው። ብዙ ጊዜ ደሞ ተፈጥሯዊ ሲሆን ምንም አይነት ችግር የሚያመጣ አይደለም።ነገር ግን
አንዳንዴ በሌሎች ምክንያቶችም ሊከሰት ይችላል ።
የህፃናት ላብ መብዛት ሌሎች ምክንያቶች ምንድናቸው ?
✔️ ረጅም ሰአት ማልቀስ
✔️ ጥልቅ የሆነ እንቅልፍ
✔️ የልብስ መብዛት እና በከፍተኛ ሙቀት መጨነቅ
✔️ በኢንፌክሽኖች የሚመጣ ትኩሳት
✔️ ኃይለኛ ማንኮራፋት እና የጉሮሮ መጥበብ
✔️ የተለያዩ የ አጥንት ህመሞች ለምሳሌ ፀሐይ እጥረት ምክንያት የሚመጣው ሪኬትስ እና ሌሎች ህመሞች
✔️ በተፈጥሮ ከፍተኛ የሆነ የላብ አመንጪ ህዋሳት(sweat gland) መብዛት
✔️ የልብ ህመም
የተለያዩ በተፈጥሮ የሚከሰቱ የልብ አፈጣጠር ችግሮች (Congenital Heart Diseases) ልጆች ላይ ላብ እንዲበዛ ሊያረጉ ይችላሉ ።
በተለይ የሚከተሉት ምልክቶች ከላብ መብዛት ተጨማሪ ልጆዎ ላይ የሚታዩ ከሆነ ሐኪምዎን ያማክሩ ።
# ጡት እየጠቡ ደክሟቸው ጡት የሚያቋርጡ ከሆነ
# ከንፈራቸው የሚጠቁር ከሆነ
#ተደጋጋሚ የሳምባ ምች የሚያጠቃቸው ከሆነ
# ቶሎ ቶሎ መተንፈስ እና ማቃሰት ካለ
# ስለዚህ ወላጆች መረዳት ያለባቸው ላብ ተፈጥሯዊ እና በእድሜ የሚጠፋ እንደሆነ እና ሆኖም ሌሎች አጠራጣሪ የሆኑ ማንኛዉም ምልክቶች ሲያዩ ግን ሐኪም ማማከር አለባቸው።
ዶክተር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

SPHMMC, department of psychiatry, child and adolescent unit provides a caregivers skill training (applying WHO's guidelines) for caregivers of children with neurodevelopmental disorders.
This is the 7th group to graduate after 10 weeks of training.