St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Today is World Sexual Health Day.💜

Look after your #SexualHealth by using protection.

More than 86 million curable STIs are contracted every year among persons aged 15 to 45 years in the African Region.

Key facts
Among the 1.9 billion Women of Reproductive Age group (15-49 years) worldwide in 2019, 1.1 billion have a need for family planning; of these, 842 million are using contraceptive methods, and 270 million have an unmet need for contraception [1,2]
The proportion of the need for family planning satisfied by modern methods, Sustainable Development Goals (SDG) indicator 3.7.1, was 75.7% globally in 2019, yet less than half of the need for family planning was met in Middle and Western Africa [1]
Only one contraceptive method, condoms, can prevent both a pregnancy and the transmission of sexually transmitted infections, including HIV.
Use of contraception advances the human right of people to determine the number and spacing of their children.
(WHO)
t.me/spmmc
St. Paul’s Hospital Millennium Medical College from Ethiopia joins the global community in celebration of #WorldFieldEpidemiologyDay. EFELTP builds the capacity of the health care system by training the public health workforces in field epidemiology who specialize in Surveillance and emergency responses and other competencies.
#WorldFieldEpidemiologyDay
#TEPHINET
#tephinet
የደም ግፊትዎን በየጊዜው በባለሙያ ይለኩ።
The number of adults aged 30-79 living with hypertension has doubled from 650 million to 1.28 billion since 1990. Although it can be easily detected through measuring blood pressure, at home or in a health centre, about 580 million people with hypertension are unaware of their condition because they were never diagnosed.
👉 t.me/spmmc
#በእጅጉ_ጥንቃቄ_ያስፈልጋል
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 22 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል።
በዚሁ ቀንም 727 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ይገኛሉ።
በየዕለቱ የማስጠንቀቂያ መልእክቶች ቢተላለፍም ወረርሽኙ ግን እየጨመረ ነው። አሁንም የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር የኮቪድ-19 ቫይረስን በጋራ እንከላከል።የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
t.me/spmmc
In connection with world Epidemiology day, Let you know about Our College Activities
• SPHMMC has started the EFELTP in 2015
• Since 2015 five cohorts graduated in field epidemiology program consecutively
• A total number of graduated is 106
• 5 cohorts graduated since the program has started in SPHMMC

Major Achievement of SPHMMC
• Some of our residents have presented their abstracts in international conferences, TEPHINET (Training Programs in Epidemiology and Public Health Interventions Network), AFENET and national conferences
• And the others got mini-grants by PMI program
• Our residents and graduates have investigated and responded to many outbreaks
• They have promptly involved in fighting Covid 19
• They have evaluated the country’s public health surveillance system at each level
• Analyzed data for notifiable and non-notifiable disease
• They have managed disaster situations throughout the country including the IDPs, and natural disasters
t.me/spmmc
#WorldFieldEpidemiologyDay
#TEPHINET
የልጆችን የአይምሮ ብቃት የሚቀንሱ ሰባቱ የወላጅ ስህተቶች

1. የልጅዎን ስሜቶች አለመረዳት ወይም መቀነስ
ልጆች ስለ ስሜቶቻቸው መግለፅ እና ማውራት ጤናማ መሆኑን ማወቅ አለባቸው ፡፡
ለምሳሌ አንድ ህፃን ጎዳና ላይ ያሉ ልጆችን አይቶ "ወይኔ ሲያሳዝኑ ቢል ወላጅ ደሞ “ አይ እነዚህማ መጥፎ ልጆች ናቸው፡፡ ምንም አያሳዝኑም” የሚል ከሆነ ህፃናት ስሜቶቻቸው ምንም ፋይዳ እንደሌላቸው እና እነሱን ማፈኑ የተሻለ እንደሆነ ይረዳሉ ያደርጉታልም ፡፡ በዚህም በራስ የመተማመን ብቃታቸው ይወርዳል፡፡

ልጅዎ በከባድ አውሎ ነፋስ ወቅት የፍርሃት መግለጫዎችን እያሳየ ከሆነ ለምሳሌ “አሁን እንደፈራህ አውቃለሁ፡፡ አይዞህ እኔ አለሁልህ/አለሁልሽ ” ይበሉ፡፡
በተጨማሪም ስሜቶችን በራሳቸው እንዴት ማስተዳደር እና መቋቋም እንደሚችሉ ያስተምሯቸው ።
2. ሁልጊዜ ከውድቀት ማዳን
ልጆች በውድቀት የሚመጡትን ትምህርቶች መማር አለባቸው፡፡ከስህተታ ቸው እንዲማሩ ዕድል ካልተሰጣቸው ፣ ወድቀው ተመልሰው ለመነሳት የሚያስፈልገውን ጽናት እና ብርታት በጭራሽ አያዳብሩም ::
3. ልጆች አቅም በላይ ብዙ ነገር መስጠት
ልጆች አዳዲስ ነገሮችን ማግኘት ይወዳሉ ::ወላጆች ደሞ ልጆቻቸው የወደዱትን ሁሉ መስጠት ያስደስታቸዋል። ትልቁ የ ወላጅነት መለኪያ አድርገውም ያዩታል።ለምሳሌ : አዲስ አሻንጉሊት መግዛት አዲስ ልብስ መግዛት አዲስ ትምርት ቤት ማስገባት እና የመሳሰሉት
ነገር ግን ብዙ ጥናት እና ምርምሮች እንደሚያሳዩት ለልጆች የሚፈልጉትን ወይም የጠየኩትን ወድያው ወድያው የሚሰጣቸው ከሆነ ራስን መግዛትን ትዕግስትን ኃላፊነትን እና የመሳሰሉትን ክህሎቶች ያጣሉ፡፡
ልጆችዎ የሚፈልጉትን ነገር ለማሳካት ወይም ለማግኘት የሆነ ነገር መሞከር እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡
ለምሳሌ ወላጆች ከ ጨዋታ ወይም ቴሌቪዝን ሰዓት በፊት የቤት ሥራን መጨረስ ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንዳለባ ቸው ግልጽ ሕጎችን በማውጣት ራስን መግዛትን ሊያስተምሯቸው ይችላሉ ፡፡

4. ፍፁም እንዲሆኑ መጠበቅ
ልጅዎ ትልልቅ ግቦችን እንዲያነጣጠር እና በሁሉም ነገር ምርጥ እንዲሆን መፈለግ ተፈጥሯዊ ነው ፡፡የሚጠበቁ ነገሮች ተጨባጭ መሆናቸውን በማረጋገጥ በልጆችዎ ውስጥ የአእምሮ ጥንካሬን ይገንቡ ፡፡
ልጆችዎ ባሳ ኳቸውም እንኳ የሚገጥሟቸው መሰናክሎች አሁንም ጠቃሚ የሕይወት ትምህርቶችን እና በሚቀጥለው ጊዜ እንዴት እንደሚሳኩ ያስተምራቸዋል ፡፡
5. ሁል ጊዜ ምቾት እንደሚሰማቸው ማረጋገጥ
ልጅዎ በአፍላ እድሜያቸው ምቾት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
በተለይም አዲስ ነገር ሲያደርግ-አዳዲስ ምግቦችን መሞከር ፣ አዳዲስ ጓደኞችን ማፍራት ፣ አዲስ ስፖርት መጫወት ወይም ቤቶችን መንቀሳቀስ እና ወደ አዲስ ትምህርት ቤት መሄድ ፡፡
ግን ደሞ የማይመቹ ጊዜዎችን መቀበል የአእምሮ ጥንካሬን ከፍ ሊያደርግ ይችላል ፡፡
ልጆችዎ አዳዲስ ነገሮችን እንዲሞክሩ ያበረታቷቸው።እንዲጀምሩ እርዷቸው ፣ ምክንያቱም ያ በጣም ከባድ ክፍል ነው።ግን ያንን የመጀመሪያ እርምጃ ከወሰዱ በኋላ ፣ እነሱ እንዳሰቡት ከባድ እንዳልሆነ ይገነዘቡ ይሆናልና እነሱም በዚህ ረገድ ጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ!
6. የወላጅ-ልጅ ድንበሮችን አለማዘጋጀት
እርስዎ ልጆችዎ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲያደርጉ ይፈልጋሉ ፣ ግን እርስዎም አለቃ መሆንዎን ማወቅ አለባቸው።
ለምሳሌ ፣ ለ 12 ዓመት ልጅዎ የሚሆን የክትትል መመሪያ ካዘጋጁ በየቀኑ መመሪያዎቹ ተጠብቀው መቆየታቸውን ያረጋግጡ፡፡
ደንቦችን ወደ ውስጥ መግባትና ብዙ ጊዜ እንዲደራደሩ መፍቀድ በእርስዎ እና በልጅዎ መካከል ወደ ስልጣን ሽኩቻ ሊያመራ ይችላል ፡፡
7. ለራስዎ እንክብካቤ አለማድረግ
ዕድሜያችን እየጨመረ በሄደ መጠን ጤናማ ልምዶችን ለመጠበቅ የበለጠ ከባድ ይሆናል (ለምሳሌ ፣ ጤናማ ምግብ መመገብ ፣ በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ) ፡፡
ለዚያም ነው ለልጆችዎ የራስ-እንክብካቤ ልምዶችን መቅረጽ አስፈላጊ የሆነው ፡፡
በተጨማሪም በልጆችዎ ፊት ጤናማ የመቋቋም ችሎታዎችን መለማመድ በጣም አስፈላጊ ነው።ለምሳሌ ፣ ስለ ሥራ በጣም ከተጨነቁ ለልጅዎ “በሥራ ላይ በጣም አድካሚ ቀን ነበረኝ ፣ ከሻይ እና ከመጽሐፍ ጋር እዝናናለሁ” ለማለት ይናገሩ ፡፡

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕጸናት ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር
t.me/spmmc
The St. Paul’s Hospital Millennium Medical College central Lab has been newly equipped with the COBAT 6800, a fully automated, high-end machine for performing real-time PCR testing COVID 19 in a bid to providing city residents and beyond with efficient and prompt services.
The COBAT 6800 can also detect other pathogens like viral hepatitis B and C, HIV, MB (both rifampicin and isoniazid resistance), papilloma, CMV, Chlamydia, Neisseria etc.
COBAT 6800 will provide patients with quality, high-volume testing with a high throughput of testing approx. 1200 samples per 24 hrs.
Moreover, COBAT 6800 is a sophisticated machine that is assisted with robotics thereby minimizing the chance of COBAS 6800 contamination and the risk of interaction to the health care workers. The machine, COBAT 6800, installed in St. Paul Hospital is the second one in our country.
አዲሱ ዓመት የሰላም : የጤና እና የብልጽግና ይሁንልዎ!
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼🌼
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ወቅታዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።
************
የመግለጫው እጥርጥር ይኸው።
#በጣም_አሳሳቢ

ባሳለፍነው ሳምንት ዴልታ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በሃገራችን መኖሩ ተረጋግጧል ። ይህ የቫይረስ ዝርያ በስርጭት ፍጥነት ቀደም ብሎ ከነበሩት አልፋ እና ቤታ ዝርያዎች በሁለት እጥፍ እንደሚበልጥ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡

#የዴልታ ቫይረስ ዝርያ በአለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በበሽታው የሚያዙ፣ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡

#በሃገራችንም የበሽታውን ሁኔታ ስንመለከት ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 9,164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ከመያዛቸውም በላይ በሳምንቱ ቀናት በአማካይ 737 የሚሆኑ ሰዎች ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል ገብተዋል ።

#በቁጥር 158 የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በዚሁ ሳምንት በአማካይ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ አስራ ሰባት ነጥብ ሰባት በመቶ(17.7%) የደረሰ ሲሆን ይህም ከላፈው ሳምንት ሲነጻጸር ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል።፡፡ አማካይ የሞት ምጣኔ አንድ ነጥብ ስድስት (1.6%) መድረሱን ደርሷል።

#ቫይረሱ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ችግር ለመግታትና ለመቆጣጠር የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን ማስወገድ እንዲሁም የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ተገቢ ነው።
t.me/spmmc
ምች የሚባል በሽታ ግን ምንድነው ?
( ምች በፀሐይ ይመጣል ወይስ አይመጣም?)

🔘 ምች የሚባለው በሽታ በእንግሊዘኛው herpes labialis የሚባለው ሲሆን ዋናው የበሽታው ምልክት ደሞ ሄድ መጣ የሚሉ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስሎች ናቸዉ።

የምች መንስኤው ምንድነው?

የበሽታው ዋናው መንስኤው herpes simplex የሚባለው ቫይረስ ሲሆን በመሳሳም ወይም በ ሌሎች አካላዊ ግንኙነቶች አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ::

ምልክቶቹ

- የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት
- ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች
- ትኩሳት
-የራስ ምታት
- የጡንቻ ላይ ህመም
-የአንገት ላይ ንፍፊትቶች እብጠት

-ለምች የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው?

1. ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ

ፀሐይ ብርሃን ለብቻው ምች አያመጣም።
ነገር ግን ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex 1) ቀድሞ ይዞን እራሱ ነርቭ ህዋሶች ዉስጥ ይደብቃል ።

የፀሐይ ብርሃን ዉስጥ ባለው ultraviolet የሚባለው ጨረር ደሞ ሊነሳሳው (re activate ሊያረገው) እና ከተደበቀበት የነርቭ ስር ዉስጥ በ መውጣት ድጋሚ ወደ ቆዳ አካባቢ በመሄድ ሄድ መለስ የሚል ቁስል ሊያመጣ ይችላልይችላል
2. ቅባት ያለዉ ምግብ መመገብ
3. ጭንቀት
4. ኤች አይ ቪ ኤድስ
5. የካንሰር ህክምና
6. የወር አበባ ዑደት ጊዜ የሆርሞን መለዋወጥ

የጤና ባለሙያ ማማከር ያለብን መቼ ነው ?

- የበሽታ መከላከል ብቃት መቀነስ/የተዳከመ ከሆነ
- ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
- የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
- ህመሙ በተደጋጋሚ ከተከሰተ
-በአይን የመቆጥቆጥ ስሜት ሲሰማ

ሕክምናውስ ምንድን ነው?
-ጸረ- ቫይረስ መድሃኒት እና የህመም ማስታገሻ መድሐኒት መዉሰድ
- በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን
-በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ
- የአእምሮ ዉጥረትን/ ጭንቀትን መቅነስ
- ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ተክል ቅጠል በማሸት ቁስሉ ላይ ማድረግ/መቀባት

( በነገራችን ላይ ዳማከሴ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም ቫይረስን የመቆጣጠር እና የማጥፋት ባህሪ እንዳለው ብዙ ጥናቶች ጠቁመዋል ።)

-ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል፤
- ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ስለሆነ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ :- በተለይ አይንንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ፤
- የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
-የእጅን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካት በፊት እጅዎን በደንብ ይታጠቡ ።

መልዕክቱን ሌሎችም ያዳርሱ።
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
t.me/spmmc
ማስታወቂያ
የነርሲንግ ትምህርት ክፍል ዳይሬክቶሬት በ2014 ዓ.ም በስሩ አምስት ዲፓርመንቶች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በያመቱም አዲስ ተማሪ የምንቀበል ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ሶስቱ ከዚህ በታች በማተርስ ፕሮግራም (MSc) የዘረዘርናቸው ትምህርት ክፍል ውስጥ እስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የምትችሉ እና ብራሳቸሁ ከፍላቸሁ መማር የምትችሉ መስፈርቱን የምታሟሉ መመዝገቢያ ቦታው ከታች እንደገለፅነው ይሆናል
በመሆኑም አመልካቾች ከመስከረም 6/2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2014 ዓ.ም
ድረስ በኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ በመሄድ እንድትመዘገቡ እያሳወቅን የመመዝገቢያ መስፈርቱ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ነው ፡፡
ተ.ቁ የትምህርት ክፍል የትምህርት ዓይነትመ በማተርስ
1. በድንገተኛና ፅኑ ህሙማን
ነርሲንግ ት/ክፍል Respiratory Care Practitioner
Paramedic Science
Critical Care Nurse Practitioner
2. ቀዶ ህክምና ነርሲንግ ት/ክፍል Cardiothoracic surgery Nursing Admission requirement
3. ቀዶ ጥገና ነርሲንግ ት/ክፍል MSc Cardiovascular nursing


የቅበላ መስፈርት
• እውቅና ካለው ዩንቨርስቲ የትምህር ተቋም በነርሲንግ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው /ያላት
• በሙያው ሁለት አመት ያገለገለ /ያገለገለች
• ከሚሰሩበት ድርጅት የእስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማምጣት ሚችል /የምትችል
• በግሉ ከፍሎ መማር ሚችል /ምትችል
• ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሻል ትራንስክርቢት ማጣት የሚችል /የምትችል
• ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰራበት መስራቤት ማምጣት ሚችል /የምትችል
• የመግቢያው ፈተና ማለፍ የሚችል /የምትችል
• የመመዝገቢያ ቀናት ከመስከረም 06/2014 ዓ.ም ለሶስት ሳምንት ተከታታይ የስራ ቀናት
• የመመዝገቢያ Online https://197.156.83.153/sphnursing/
• የፈተና ቀን ጥቅምት 2/2014 ዓ.ም, ቦታ ቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ሜ/ኮሌጅ
Academic year 2021 entry Application
Master of Science in Medical Microbiology
 Candidates must be holders of first degree in medicine, medical laboratory technology, medical laboratory sciences, biology, veterinary medicine, microbiology, virology, biomedical sciences
 Candidates should have CGPA of 2.0 and above
 Should bring a letter of sponsorship from government hosting institute or self-sponsor applicants should enter a commitment to pay the cost of the training. Self-sponsors students will pay 1,400 birr per credit hour and should cover research associated expenses.
 Copy of Degree and transcript
 Two Recommendation letters
 Registration fee 50 birr (CBE account 1000006577192)
 The applicant shall not be older than 35 years at the time of admission
 Application date: September 15 to October 5, 2021
 Application online at: https://197.156.83.153/msmm
 Exam date: October 11, 2021
 Place: St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC)
Remarks: Those who have already submitted an application in person to the SPHMMC register office; no need for online application