St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Announcement -Fellwship program
t.me/spmmc

The department of internal medicine, SPHMMC, kindly invites all qualified and competent applicants to apply for the fellowship program in adult cardiology

Admission requirements
1. The candidate must have doctor of medicine from a recognized medical school
2. Completed residency program in internal medicine from a recognized medical school.
3. Served at least for two years
4. Must complete the screening process for admission to be undertaken by the department of internal medicine including entrance examination.
5. Registered and licensed to practice internal medicine in Ethiopia by the relevant authorities.
6. Should have adequate physical and mental health to deliver both his/her academic and clinical service responsibilities.

Applicants should write a brief intent letter describing their interest in the fellowship, expectations and impact on their career after joining the program.
Applicants should submit the following documents.
 Application letter
 Recent CV with an intent letter
 Copy of credentials including degrees, student copy
 Two letters of recommendation in a sealed envelope
 Letter of sponsorship from sponsoring institution (not applicable for private/self-sponsoring applicants)

Interested applicants can apply in person to the department of internal medicine or use this email: esubalew49@gmail.com/esubalew.woldeyes@sphmmc.edu.et until October 15/2021.
Interview of candidates will be on November 1/2021 and admission will be December 01/2021
ዛሬ የዓለም አቀፍ የፋርማሲስቶች ቀን ነው፡፡ ውድ የሀገራችን ፋርማሲስቶች እንኳን አደረሳችሁ!
#WPD2021 #WorldPharmacistDay21
#AskYourPharmacist
#WPD2021
#WorldPharmacistsDay2021
#pharmacistsalwaystrusted
#communitypharmacist
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ !
ለአንቺ
በእርግዝናሽ ወቅት ማወቅ ያለብሽ ሰባት ነገሮች።(የሐኪምሽ ምክር)

1. በ እርግዝናሽ ወቅት በቂ የሆነ የፅንስ ክትትል አድርጊ።

ማርገዝሽን ካወቅሽበት ቀን ጀምሮ ተገቢውን የእርግዝና ክትትል ማድረግ ይኖርብሻል ።
በክትትል ወቅትም አስፈላጊ የሆኑ የደም የሽንት የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብሻል::

2. አይረን እና ፎሊክ አሲድ መውሰድ አለብሽ ። ምክንያቱም ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ የቀይ ደም ህዋስ እንዲመረት እና የደም ማነስ እንዳይከሰትብሽ ያደረጋል።

ፎሊክ አሲድ በበቂ ከወሰድሽ ሕፃኑ ላይ የ ነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) እንዳይከሰት ይከላከላል ።

ፎሊክ አሲድን የሚይዙ ምግቦች ፡- ብርቱካን ፣ ወይን ፣ ፓፓያ ጎመን ፣ሩዝ ፣ ባቄላ ፣ ስኳር ድንች ፣ እንቁላል ፣ ዳቦ ፎሊክ አሲድን ከነዚህ ውስጥ ማግኝት እንችላለን ፡፡

3. የደም አይነትሽን ማወቅ ይጠቅምሻል ።የ የሚጠቅምሽም ባንቺ እና በ ልጅሽ የደም አለመመሳስል ምክንያት ፅንሱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዳይደርስ እንድትከላከይ ይረዳሻል ::

በተለይ ያንቺ የደም አይነት ኔጌቲቭ የሚባለው ከሆነ

ለምሳሌ A negative, B negative, AB negative ወይም O negative ከሆነ የሾተላይ መከላከያ ወይም አንታይ ዲ (Anti - D) የሚባለውን መድሃኒት እርግዝናው ከታወቀ በ 7 ተኛ ወር ላይ እና ከወሊድ በኋላ በ 72 ሰአት ወሰጥ መውሰድ ይኖርብሻል።

4. ለህመም ማስታገሻ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶችን ያለ ሀኪም ትእዛዝ አትውሰጂ።

በተለይ በመጀመሪያዎቹ 16 ሳምንታት የእርግዝና ወቅት የህፃኑ ዋና ዋና የሚባሉ የሰውነት ክፍሎች የሚፈጠርበት ግዜ ስለሆነ ፅንሱ ላይ ጉዳት ያደርሳያደርሳል

5. በእርግዝና ግዜ የአተኛኘትሽን አስተካክይ።

በእርግዝና ወቅት መተኛት ያለብሽ በግራ ጎንሽ መሆን አለበት።
በግራ ጎንሽ ስትተኚ ወደ ፅንሱ የሚሄደውን ምግብ እና የደም ዝውውርን እንዲጨምር ያደርጋል:: በጀርባሽ የምትተኚ ከሆነ ግን በተቃራኒው ወደ ልጅሽ የሚሄደው ምግብ እና የደም ዝውውር ሊቀንስ ይችላል።

6. ምግብሽን ሳታበስይ አትመገቢ!

በእርግዝና የሚከለከሉ ምግቦች ብዙም የሉም ። እንደውም ጤናማ ከሆኑ(ማለትም የበሰሉ እና በንፅህና የተዘጋጁ) ከሁሉም የምግብ አይነት እናት እንድትመገብ ይመከራል ።
ጣፋጭ እና የ ታሽጉ ምግቦችን አታዘውትሪ።

7. በ እርግዝና ወቅት በቂ እና ጤናማ የሆነ ኪሎ መጨመር ይኖርብሻል።

ከእርግዝና በፊት ከምትመገቢው ምግብ ተጨማሪ ምግብ ያስፈልግሻል።
------
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
በዛሬው ዕለት ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫው ዋና ዋና ሀሳቦች ባጭሩ እነሆ፡-

“አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ (ዴልታ) ቫይረስ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ነው፡፡
ከመስከረም 10 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመረመሩ 57 ሺሕ 940 ሰዎች መካከል 8 ሺሕ 753 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ የመያዝ ምጣኔውም 15 በመቶ ደርሷል፡፡

በክልሎችም የመያዝ ምጣኔው ከአገር አቀፍ የመያዝ ምጣኔ ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡ በሣምንቱ በአገር አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 271 ነበር፡፡
በዚሁ ሣምንት ከ798 በላይ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ሕክምና ማዕከል ገብተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች የታካሚዎች ቁጥር በመጨመሩ የጽኑ ሕክምና ክፍሎች ሞልተው ታካሚዎች ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡
በወረርሽኙ የመያዝ፣ የሞት እና የጽኑ ሕሙማን ቁጥር መጨመር የአዲሱ ኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡
“የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ አለመደረጋቸው እና የክትባት ሽፋን ዝቅተኛ መሆንም ለስርጭቱ መስፋፋት በምክንያት ይጠቀሳል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 14 ከተሞች በተደረገ ጥናት የመከላከያ መንገዶች አተገባበርን ዝቅተኛ መሆኑንና በኅብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት መኖሩን ታውቋል፡፡

ለወረርሽኙ ፖለቲካዊ አንድምታ መስጠት፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ዓርአያ ሆነው አለመገኘት፣ በየደረጃው የተዋቀሩ ግብረ ሀይሎች መመሪያ የማስፈጸም ተሳተፎ እያነሰ መምጣት ኅብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን እንዳይተገብር ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

t.me/spmmc
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የላብራቶሪ አቅሙን ለማጎልበት እና ጥራት ያለውን አገልግሎት እንዲሠጥ የሚያስችለውን በቴክኖሎጂ የሚታገዝ ኮባስ 6 ሺህ 800 የላብራቶሪ የምርመራ ማሽን አስመረቀ፡፡

ክብርት የጤና ሚኒስትርዋ በተገኙበት የተመረቀው ዘመናዊ የላብራቶሪ ሞሎኪዩላር የምርመራ ማሽን ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገዛ ነው። የሮች ከምፓኒ ስሪት የሆነው ማሽኑ በአንድ ቀን ብቻ 1 ሺህ 200 የናሙና ምርመራ ውጤቶችን የማከናወን አቅም አለው፡፡ ማሽኑ ከኮቪድ በተጨማሪ ኤች አይ ቪ፡ ቲቢ፤ሄፕታይተስ ቢ፡ ሄፕታይተስ ሲ፡ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርንና ልዩ ልዩ የአባላዘር በሽታዎችን እንዲሁም ሌሎች ምርመራዎችን የማከናወን አቅም ያላው ነው፡፡

የሮሽ ከምፓኒ የኮሌጁን የላቦራቶሪ እድሳት እና ለስራ አመቺና ውበት ያለው እንዲሆን አድርገው ሰርተው አስረክበዋል፡፡

SPHMMC gets the first automated COVID-19 testing machine ‘COBAS 6800’ that can test 1200 samples in 24-hours.
The machine can perform real-time PCR testing, the most reliable test to detect the presence of Novel Coronavirus.
Mr Berhane Meskel, Head of the central Laboratory at SPHMMC, said with the help of the Roche 6800, dozens of swabs are able to be tested at once – with the potential of testing 1,200 samples in a 24-hour period.
He mentioned that COBAS 6800 is a sophisticated machine enabled with robotics that minimizes the chance of contamination and the risk of infection to the health care workers. Reportedly the COBAS 6800 can also detect other ailments like Hepatitis B&C, HIV, MTb, Papilloma, CMV, Chlamydia, Neisseria, etc.
The machine, installed at a cost of more than 10 million ETB, Will significantly enhance the testing capacity.
ዛሬ የዓለም የልብ ቀን ነው፡፡(መስከረም 19/2014)
ምንግዜም የደም ግፊትዎን ይለኩ፡፡
#WorldHeartDay
#Cancer is the 2nd leading cause of death globally.
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ የዓለም ዓቀፍ ትንባሆ ቁጥጥር ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት የዊከንፊልድ ሽልማት ተሸለሙ።
____________

ሄራን ገርባ ትንባሆ በህብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደም በመሆን ጠንካራ አመራር ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም
ትንባሆን ለመቆጣጣር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን ጠንካራ ህግ እንዲፈጸም በስፋት ሰርተዋል፡፡

ወይዘሪት ሄራን ባሳዩት የአመራር ብቃት እና ለሌሎች አራዓያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው ሽልማቱን ማግኘታቸው ተገቢ መሆኑን የጁዲ ዊከንፊልድ ሽልማት ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡
የልጆች አስተዳደግ ዘይቤዎች (Parenting styles)
እርስዎስ ልጅዎን እንዴት እያሳደጉ ነው?

ህፃናት የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች ናቸው ዛሬ አበባው ላይ የምናደርገው እንክብካቤ ፍሬው ላይ ውጤቱን እናየዋለን።

እንደ የስነ-ልቦና ባለሞያዎች ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉባቸው መንገዶች በአራት ይከፈላሉ፡፡

1.አምባገነን (ኮስታራ) ፦

ይህ አይነት የልጅ አስተዳደግ በአለማችን በይበልጥ ደግሞ በሀገራችን ለረጅም ጊዜ የነበረ የማሳደጊያ መንገድ ነው፡፡ ከእናቶች ይልቅ ደግሞ አባቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው 'ኮስተር' ብለው ይነግሩና ልጆች 'ወለም ዘለም' ሳይሉ እንዲከተሉ ይጠብቃሉ፡፡

እንደዚህ ሆነው የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው ስኬታማ ለመሆንና 'ትክክል' የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሲሆኑ አዲስ ነገር ለመሞከር ወይም ያልተለመደ ስራ ለመስራት ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ ሲርቁ የማያምኑባቸውን ነገሮች ለማድረግ ይገፋፋሉ፡፡

አምባገነናዊ ስልትን የሚጠቀሙ ወላጆች በትንንሽ ጉዳዮች ላይ እራሱ ጥብቅ የሆነ የዲሲፕሊን/ የመመርያ ዘይቤን ይጠቀማሉ ፡፡

በዚህ ስልት ውስጥ ቅጣት በጣም የተለመደ ነው በወላጅና በልጅ መካከል በሚደረግ ንግግር ውስጥም ደግሞ ወላጆች ብቻ ተናጋሪ ሲሆኑ ልጆቻቸውን አያዳምጡም ወይም የልጆችን ሃሳብ በፍጹም አያንሸራሽሩም

የተለያዩ ጥናቶች የዚህ አይነቱ የወላጅነት ስልት ብቻውን ውጤታማ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።

በእርግጥ ለነገሮች ገደብና ወሰን መስጠት ልጆችን ለማሳደግ ጤናማና የሚመከር ነው ነገር ግን ከፍቅር ከክብርና ከእንክብካቤ ጋር አብሮ መሆን አለበት።

ልጆች መጥፎ ምግባር በሚያሳዪበት ግዜ በማስፈራራት እና ከባድ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ቅጣቶችን በመጠቀም ጥሩ ባህሪን ለማስፈፀም ለግዜው ቀላሉ መንገድ መስሎ ሊታይ ይችላል ነገር ግን የዚህ አይነቱ ቅጣት ዘላቂ የሆነ የባህሪ ለውጥ አያመጣም!

እንደዚህ አይነት ወላጆች ልጆቻቸው ዝቅተኛ ውጤት ሲያመጡ በመቅጣት በማሸማቀቅ እና በማሳፈር ልጆቻቸው ችግሮችን የመፍታት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የረዷቸው ይመስላቸዋል ግን ይሄ ልጆች ለራሳቸው ዝቅተኛ ክብር እንዲኖራችው ከማድረጉም በላይ የአዕምሮ ዕድገታቸውን ያጨናግፋል በረጅም ግዜ ሂደት ውስጥም ወላጆች ለልጆቻቸው ይህንን ስልት እንደ አርዓያ ያወርሷቸዋል ።በዚህ ምክንያት ልጆቹ ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ይህን ስልት እንደ ብቸኛ ችግር መፍቻ ዘዴ እኩዮቻቸው ላይ እና ወደፊት ወላጅ ሲሆኑ

2.የሚያሞላቅቁ (ሁሉንም የሚፈቀዱ)፦

ይሄ የልጅ አስተዳደግ በቅርብ የተጀመረ ሲሆን በከተማዎች በጣም እየተስፋፋ የመጣ አይነት ነው፡፡

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ያለ ገደብ እንደፈለጉ አንዲሆኑ ይፈቀዳሉ፡፡ ልጆቻቸው ያለ ከልካይና ያለ ገደብ እንደልባቸው እንዲሆኑ ከመፍቀድ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አይነግሯቸውም፡፡ ልጆቻቸው እስከፈለጉ ድረስ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ለማሟላት ይጣጣራሉ፡፡

ይህን ስልት የሚጠቀሙ ወላጆች ‘’ ልጆች ሁልግዜም ልጅ ናቸው “ የሚል አመለካከት የያዙ ናቸው።አብዛኛውን ግዜ ከልጆቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነትም ከወላጅነት ሚና ይልቅ የጓደኝነቱ ሚና ጎልቶ ይወጣል።

እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች ከቤት ውጭ እንደፈለጉ መሆን ስለማይችሉ ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡

የተለያዩ ልምዶችን አይቆጣጠሩም እንዲሁም ልጆቻቸው የግል ደንብና ስርዓት እንዲኖራቸው አያስገድዱም ልጆቻቸውም ግብ እንዲኖራቸው እና ዓላማቸውን እንዲያውቁ ስለማይጠየቁ እራስን መግዛት ላይ ደካማ ናቸው። ይህ አይነቱ ስልት ደግሞ በመጨረሻ ወደ ዝቅተኛ የትምህርት እና የህይወት ውጤት ያመራል

የተወሰኑት ልጆች ደሞ ለምንም ነገር ሀላፊነት የማይሰማቸው ይሆናሉ፡፡

3.ግድ የለሽ( የማይሳተፍ )

እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው ግድ የሌላቸው ሲሆኑ ቁጣም ሆነ አድናቆት አያሳዩም፡፡ ልጆቻቸው እነሱን እስካላስቸገሩ ድረስ የትም ቢውሉ፤ የፈለጉትን ቢያደርጉ ግድ አይሰጣቸውም፡፡

እንደዚህ የሚያድጉ የተወሰኑት የቤተሰብ ሀላፊነት ስለሚሸከሙ ልጅነታቸውን ይነጠቃሉ፡፡ ሲያድጉ ብቸኝነት የሚሰማውና ሰውን ማመን የሚከብደው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በራስ መተማመናቸው ዝቅተኛ( ወይም ለማካካስ በጣም ከፍተኛ) ሊሆን ይችላል፡፡

4. ዲሞክራሳዊ (ነጻነት በወሰን የሚሰጡ) ፦

እነዚህ ወላጆች የልጆቻቸውን ሀሳብ፣ ስሜትና አስተያየት ያዳምጣሉ፡፡ በጣም ጠቃሚ ነገሮች ላይ የሚወስኑት ወላጆች ናቸው፡፡ በአቅማቸው የሚችሉትን ያደርጋሉ፡፡

ይህ አይነቱ አስተዳደግ ልጆች ሃሳባቸውን እንዲገልጹ መፍቀድ ፣ በአማራጮች ላይ እንዲወያዩ ማበረታታት ፣ ነፃነትን እና ምክንያታዊነትን ማሳደግ ፣ በልጆች ጠባይ ላይ ገደቦችን(ወሰኖችን) ማስቀመጥ ያለበት ፣ ሞቅ ያለ ፍቅርንና እንክብካቤን ማሳየት፤ ፍትሃዊ እና ወጥነት ያለው መመርያ መስጠት ህጎች ሲጣሱ ተገቢውን ቅጣት መስጠት ያካትታል::

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ወላጆች ያላቸው ልጆች የበለጠ ብቃትን ፣ ብስለትን ፣ በራስ መተማመንን እና ራስን መግዛትን የመሳሰሉ ባህሪዎችን ያሳዩ እና ከፍተኛ የሞራል ጤናማነትን እና ፣ ሕሊና ነጻነትም አላቸው ::

እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው ወሰን አስቀምጠው ነጻ እንዲሆኑ የሚፈቅዱ ሲሆኑ የልጆቻቸውን ምርጫ ያከብራሉ፡፡ በዚህ መንገድ የሚያድጉ ልጆቸ ከሌሎች ጋር ተባብረው መስራት የሚችሉና በራሳቸው የሚተማመኑ ስኬታማ ሰዎች ይሆናሉ፡፡

ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ
How can cervical cancer be cured?

👉🏽 regular screening
👉🏽 early diagnosis
👉🏽 prompt treatment
t.me/spmmc
October is #BreastCancerAwarenessMonth.

Awareness & regular screening is the best strategy to discover breast cancer early & improve the outcome. Know when & how often to do a:
✅self exam
✅clinical breast exam
✅mammogram

#PinkOctober
ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በድጋሚ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ዛሬ ተሾመዋል፡፡ የቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማህበረሰብ የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን፡፡ መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ!
Notice . To all who applied for MSc ln Medical Microbiology
Enterence exam date: October 18, 2021.
Time : 2:00 pm (afternoon)
Place: SPHMMC academic building.