St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
for face bookk.png (3508×4961)
የዓለም የጉበት ሕመም ቀን አስመልክቶ The impact and updates on Viral Hepatitis
በሚል ለተማሪዎች የትምህርት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ ነበር።
ትምህርቱን የሰጡት ዶር ኃይለ ሚካኤል ደሣለኝ ናቸው።

July 28 World Hepatitis Day with a theme "Invest in Eliminating Hepatitis"
ስመ ጥሩው ሐኪም ዶር ያዩ ቅዱስ ጳውሎስን ተቀላቅሏል።
ድጋፋችንን ለሚጠብቁ ህፃናት እንደግፍ! 12ደብተር፣2እስክሪብቶ፣2እርሳስ፣2ላጲስ፣2መቅረጫ ለአንድ ልጅ እናበርክት!
120 ተማሪዎችን እንደግፍ!
The Ethiopian National Accreditation Office has accredited the microbiology and clinical chemistry laboratory of St. Paul's Hospital Millennium Medical College.
ጽ/ቤቱ ለአራት የሕክምናና ለአንድ የፍተሻ ላቦራቶሪ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰጠ

Published on: Thursday August 08, 2019

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሸን ጽ/ቤት የአክሬዲቴሸን ተጠቃሚ ለመሆን ለጽ/ቤቱ ማመልከቻ ላቀረቡና የተቀመጠውን ዓለም አቀፍና ብሔራዊ መስፈርቶች ላሟሉ ለአራት የሕክምናና ለአንድ የፍተሻ ላቦራቶሪ የአክሬዲቴሸን አገልግሎት ሰጠ፡፡
በዛሬው እለት በሕክምና ዘርፍ ISO 15189  በሕክምና ላቦራቶሪ ለአራት ተቋማት የአክሬዲቴሸን አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን እነዚህ የተቋማት ለጽ/ቤቱ የአክሬዲቴሸን አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ሰነዶቻቸውና በመስክ ግምገማ ተገምግመው  በአቀረቡት የአክሬዲቴሸን ወሰን ዓለም አቀፍ እውቅና ይገባቸዋል ተብሎ በጽ/ቤቱ የአክሬዲቴሽን አጽዳቂ ኮሚቴ አክሬዲቴሽኑ የጸደቀላቸው ናቸው፡፡
አክሬዲቴን አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የህክምና ላቦራቶሪዎች ተቋማት የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሕብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ  በአንድ የፍተሻ ወሰን ማለትም በጅን ኤክስፐርት፣የነቀምት ሕብረተሰብ ጤና ምርምር እና ሪፈራል ላቦራቶሪ በኤች.አይ.ቪ/ዲ.ኤን.ኤ/ ፒ.ሲ.አር HIV/DNA/PCR የፍተሻ ወሰን፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በማይክሮ ባዮሎጂና በክኒሊካል ኬሚስትሪ  የፍተሻ ወሰን የአክሬዲቴሽን ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በፍተሻ ላቦራቶሪ ISO/IEC 17025  ብለስ አግሪ ፉድ ላቦራቶሪ ሰርቪስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በማይክሮ ባዮሎጂና በኬሚካል የፍተኛ ወሰን የአክሬዲቴሸን አገልግሎት ተጠቀሚ ሆኗል፡፡
እነዚህ ተቋማት የአክሬዲቴሸን ተጠቃሚ በመሆናቸው ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ይበልጥ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ ዜጎች ለተደጋጋሚ ወጪ እንዳይዳረጉ በማድረግ ረገድም ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሸን ጽ/ቤት በሃገሪቱ የአክሬዲቴሸን አገልግሎት ለተስማሚነት ምዘና ተቋማት እንዲሰጥ በሚኒስትሮች ምክርቤት በድጋሚ እንደገና በደንብ ቁጥር 421/2010 የተቋቀመ ብቸኛ የመንግስት ተቋም ነው፡፡
ጽ/ቤቱ ከተቋቋመበት ከየካቲት 3 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ራሱን በማደራጀትና ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች በመቅሰም ላለፉት ስምንት ዓመታት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
በሃገር ውስጥ ለተስማሚነት ምዘና ተቋማት ከሚሰጠው አገልግሎት ጎን ለጎን ራሱን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስገምገም የዓለም አቀፉ የላቦራቶሪ አክሬዲቴሸን ትብብር ILAC ሙሉ ሲግናቶሪ አባል ወይንም MRA ለመሆን የበቃ ሲሆን የአለም አቀፍ የላቦራቶሪ አክሬዲቴሸን ፎረም IAF  አባል ለመሆን በቅቷል፡፡
ተቋሙ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸው በሕክምና ላቦራቶሪዎች ISO15189  ለፍተሻ ላቦራቶሪዎች ISO/IEC 17025፣በኢንስፔክሽን ISO/IEC1720 በፐርሰኔል ሰርቲፍኬሽን በ17024፣በምርት ሰርቲፍኬሽን 17065፣የአመራር ስርዓት ሰርቲፍኬሽን 17021 እንዲሁም በካሊብሬሸን ዘርፍ ISO/IEC 17205 ነው፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት በዛሬዎቹን አምስት ተቋማት ሳይጨምር ለ60 ተቋማት በ89 የፍተሻ ወሰኖች የአክሬዲቴሽን አገልገሎት ሰጥቷል፡፡
 
ነፃ የዳሌ የትከሻና የጉልበት ቀዶ ሕክምና እየተሰጠ ነው

11 August 2019

ታደሰ ገብረማርያም

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የቃጠሎ፣ የድንገተኛና የአደጋ ሕክምና ሆስፒታል (አቤት) ውስጥ የዳሌ፣ የትከሻና የጉልበት ሕመም ላለባቸው ሰዎች ነፃ ሕክምና መስጠት ተጀመረ፡፡
ከነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምናውን ያከናወኑት በኢትዮ አሜሪካ ዶክተርስ ግሩፕ አስተባባሪነት ከአሜሪካ የመጡት የዳሌ ንቅለ ተከላና የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምና ቡድኖች ናቸው፡፡
ከነዚህም መካከል የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና ቡድን ሕክምናውን ያከናወነው ባለፉት 15 ቀናት ሲሆን፣ የአርቶሮስኮፒክ ቡድን ደግሞ ተመሳሳይ የሆነውን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው ከነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ብቻ ነው፡፡
የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና ተባባሪ ፕሮፌሰርና የቡድኑ መሪ ክብረት ከበደ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የዳሌ ንቅለ ተከላ ሕክምና የማከናወኑ ሥራ በጣም ውድ የሆኑ መሣሪያዎችን ይጠይቃል፡፡ ሕክምናውንም ለማግኘት 700 ታካሚዎች ተመዝግበው ነበር፡፡ ከነዚህ መካከል ሕክምና የተደረገላቸው የጉዳት መጠኑ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰባቸው ሲሆኑ፣ የቀሩት ወደፊት ሕክምናውን ማግኘት የሚችሉበት እንደሚመቻች ነው ያመለከቱት፡፡
የቡድኖቹ ዋና ዓላማ የአቤት ሆስፒታል የአርትሮስኮፒ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ሲሆን፣ ለዚህም ለአገልግሎት ይዘዋቸው የመጡትንና አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺሕ ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎችን ለሆስፒታሉ ማበርከታቸውን፣ በቀዶ ሕክምናው ወቅት ለሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር መከናወኑን ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡
ከመሣሪያዎቹም መካከል 500,000 ብር የሚያወጣውና አርትሬስ አርትሮስኮፒክ ታወር የተባለው መሣሪያ እንደሚገኝበት፣ መሣሪያውም በትንንሽ ቀዳዳ ካሜራ አስገብቶ ጉዳት የደረሰበትን ጉልበትን ትከሻን በመለየት ለማከም የሚረዳ መሆኑን አክለዋል፡፡
ሁለቱም የሕክምና ቡድኖች በአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የሚገኘውን ክሊኒክ ጎብኝተዋል፡፡ ክሊኒኩን አግባብ ባላቸው ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎች ለማደራጀት የአርቶሮስኮፒ ቀዶ ሕክምና ቡድኑ ቃል ገብቷል፡፡
የዚሁ ቡድን መሪ ዊሚ ዲዮጌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ሕክምናውን ለማግኘት 40 ታካሚዎች ተመዝግበዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የጉዳት መጠናቸው ልዩ ሙያ የሚፈልግ 23 ታካሚዎች ቅድሚያ ይህም ሆኖ ግን ያለው ችግር በሙሉ ተቃሏል ማለት እንዳልሆነና ሌሎች ሐኪሞች እየተመላለሱ ክፍተቱን እንዲሸፍኑ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአቤት ሆስፒታል ምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር ኒውሮሎጂስት አብርሃም ታደለ (ረዳት ፕሮፌሰር) ጉልበት የሚገናኘው በላይኛውና በታችኛው አጥንት ባሉ በሁለት ትላልቅ ጅማቶች መሆኑን ገልጸው፣ በስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት መሀል ያሉት ጅማቶች የመቆረጥ አደጋ እንደሚደርስባቸው፣ እነዚህን ጅማቶች ለመስፋት ወይም ለመቀየር ደግሞ አስቸጋሪ እንደሆነ፣ ልዩ ችሎታና መሣሪያም እንደሚጠየቅ አመልከተዋል፡፡
የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የአጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት ይሄይስ ፈለቀ (ዶ/ር) ቡድኖቹ ከሚያበረክቱት የሕክምና አገልግሎት ሁለት ዕድሎችን ማግኘት እንደሚቻል አመልክተው፣ የመጀመርያው ዕድል በጣም ተፈላጊና ውድ የሆኑ መሣሪያዎችን በነፃ ማግኝት ሲሆን፣ ሁለተኛው ዕድል ደግሞ ወጣት ቀዶ ሐኪሞችን ክህሎታቸውን እንደሚያሳድግና የስፖርትና የዳሌ ሕክምናን ደረጃ ከፍ ማድረጉ ነው ብለዋል፡፡
በአቤት ሆስፒታል የአርቶፔዲክስና የትራዎማ ክፍል ኃላፊና የአርቶፔዲክ ቀዶ ሐኪም ዘገነ ታዬ (ዶ/ር) ወደ ሆስፒታሉ ለሕክምና ከሚመጡት ሕሙማን መካከል አብዛኞቹ ከአደጋ ጋር የተያያዙ እንደመሆናቸው መጠን ቡድኖቹ በሰጡት አገልግሎትና ባበረከቱትም የሕክምና መሣሪያ ዘርፉ የበለጠ እንዲጠናከር ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

FacebookTwitterLinkedInShare
The Ethiopian National Accreditation Office has accredited the microbiology and clinical chemistry laboratory of St. Paul's Hospital Millennium Medical College.

የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ
ዓለም አቀፍና ብሔራዊ መስፈርቶች በሟሟላቱ በማይክሮ ባዮሎጂና በክኒሊካል ኬሚስትሪ  የፍተሻ ወሰን የአክሬዲቴሽን አግኝቷል።
ለኮሌጁ አክሬዲቴሽኑን የሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሸን ጽ/ቤት ነው።

የተገኘው አክርድቴሽን በሕክምና ዘርፍ ISO 15189  በሕክምና ላቦራቶሪ አገልግሎት ነው።