St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
የጤና መረጃዎ!

አንዲት ሴት መንታ ስታረግዝ ምን ማወቅ አለባት?

በእርግዝና ወቅት የሚታዩት አብዛኞቹ ለውጦች በመንታ እርግዝና ላይ ይጋነናሉ። ለምሳሌ፦ ድካም፣ የወገብ ህመም፣ የእግር ማበጥ፣ ክብደት መጨመር ወዘተ።

መንታ ጽንስ ያረገዘች እናት ለአንድ ጽንስ ከምትመገበው የእለት የምግብ መጠን በላይ እንድትመገብ ይመከራል። ይህም ነፍሰ ጡር ከመሆንዋ በፊት ከምትወስደው መጠን በተጨማሪ 600 ኪሎ ካሎሪ መውሰድ ይጠበቅባታል።

ከዚህ በተጨማሪ መንታ ያረገዘች እናት ማወቅ ያለባት በእርግዝና ጊዜ ለጤና ችግሮች የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ ስለሆነ ተገቢውን ክትትልና የህክምና እርዳታ ማግኘት አለባት።

ሊያጋጥሙ የሚችሉት ችግሮች ዋና ዋናዎቹ፤
· የደም ማነስ
· የጽንስ አቀማመጥ መዛባት
· የደም ግፊት
· የስኳር ህመም
· በማህጸን ደም መድማት
· የምጥ ያለግዜው መምጣት
· ከወሊድ በኋላ ከፈተኛ ደም መፍሰስ የመሳሰሉት ናቸው።
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ቸር እንሰንብት
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5141 የላብራቶሪ ምርመራ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 1637 ደርሷል። በሌላ መልኩ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 250 ደርሷል።

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል፡፡
የ2012 ዓም የደም ልገሳ መርሀግብር ይፋ ሆኗል፡፡ ሰኔ 13 እና 14 ከኮሌጁ አጠገብ በሚገኘው የቀድሞ ሞቢል የነበረበት ቦታ ላይ ይካሄዳል፡፡
በሳይካትሪ ለመቀጠር አመልክታችሁ ፡ ለቃለመጠይቅ ፈተና ያለፋችሁ ሰኔ 11 ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ቢሮ ቁጥር 98 እንድትገኙ ትጠየቃላችሁ፡፡( ውጤታችሁ ከ50 በመቶ በላይ ያመጣችሁ ብቻ፡፡)
የስም ዝርዝራችሁን ከላይ ይመልከቱ።
ወድ ኢትዮጵያን በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች እንኳን
ለዛሬዋ የአለም ደም ለጋሾች ቀን እንኳን አደረሳችሁ!

ሰኔ 13 እና 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-10:00 ሰዓት የሚቆይ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ሰለዚህ እርሰዎም እንዲለግሱ ጥሪ እናቀርባለን።

ሁላችንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረግን ÷ በዚህ ወረርሽኝ ወቅትም ደም የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ተገቢውን የደም አቅርቦትና ህክምና እንዲያገኙ እንርዳ!
በዛሬው ቀን በሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ 87 ታካሚዎች አገግመው ወጥተዋል፡፡ማዕከሉ ከተከፈተ በኋላ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎቻችንን የዛሬው ቀን በእጅጉ የተደሰቱበት ነበር፡፡ እንኳን ደስ ያለችሁ!
በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ውስጥ 656 ታካሚዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
እስቲ የጤና ባለሙያዎቻችንን አመስግኑልን!
ዶር አብዱ በፋና ጤና የካንሰር ህመም አና የኮርና ወረርሽኝ በሚል ትምህርት ሰጥተዋል። ተመልከቱት!
የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን

(ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)
.
በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ።
.
በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ, solarretinopathy, photic retinopathy, foveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል።
.
ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን (ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
.
በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደ ቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር ፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለ ሐምራዊ-ለ Ultraviolet-B ) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።
.
❓አጋላጭ ሁኔታዎች፡-
.
- ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡
- ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡
.
- ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡
- የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡
.
- ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።
.
❓ምልክቶቹ፦
.
በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦
- የዕይታ መቀነስ
- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ
- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)
- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡
.
ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።
.
❓ህክምናው፦
.
ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው ።
.
❓መከላከያ መንገዶች፦
⛔ ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት ፣
በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም።
.
⚠️ ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል ፣ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ መርዳት
✅ የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደ እኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡
.
❓የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል ?
.
❌ በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም።

ጥላሸት የተቀባ መነጽር፣ የራጅ ፊልም፣ የተለመደ የፀሐይ መነጽር፣ ካሜራዎች ወዘተ የሚታዩ የብርሃን ጨረሮችን ቢቀንሱም አደገኛ የሆኑትን ልዕለሐምራዊና ንዑስቀይ ጨረሮችን መከላከል አቅም ስለሌላቸው በነሱ መተማመን አይገባም፡፡
.
መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።
.