Ethiopian University መረጃ
14.7K subscribers
292 photos
2 videos
127 files
664 links
Download Telegram
#MizanTepiUniversity

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦

​➢ ነባር የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችም ሆነ አዲስ ከቴፒ ግቢ ወደ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ የምዝገባ ቀን መስከረም 6 እና 7/2019 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 8/2019፤

​➢ ነባር የማዛን እና የቴፒ ግቢ የሁለተኛ እና ከዛ በላይ ዓመት የሆናችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀን መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 13/2019 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እና በተባለው ቀን እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል።

​➢ ከምዝገባ ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማይቀበል መሆኑን ያሳውቃል።

​ማሳሰቢያ

​በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መለቀቂያ ሰርቲፊኬት ፈተና (የ12ኛ ክፍል) ተፈትናችሁ ውጤት መጥቶላችሁ ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና የአቅም ማሻሻያ (Remedial) የማለፊያ ውጤት የመጣችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።
❤5
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች (2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ) ሪፖርት ማድረጊያ ቀን መስከረም 11/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡
 
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት እና የግል ሰነዶች መያዝ እነዳትዘነጉ የተባለ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 13/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
👍2
#BulehoraUniversity  #ጥሪማስታወቂያ

​የ2019 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ እና ድህረ ምረቃ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 11-12 ቀን 2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

​ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ነው ::

የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የዲፓርትመንት ምርጫ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ የምርጫው ውጤት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም የሚገለጽ ይሆናል።

​☞ ነባር ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በተገለጸው ቀን በአካል ቀርበው ካልተመዘገቡ፤ ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ የሚቆጠር መሆኑን እናሳስባለን።

​☞ በ2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ የምናስታውቃችሁ ይሆናል።

​☞ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
❤3👍1
#WaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ እና ድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 08 እና 09/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በቅጣት ምዝገባና መማር ማስተማር የሚጀመረው መስከረም 11/2019 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።

በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲው ያጠናቀቃችሁና የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
❤6
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ጥሪ፦

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በሪሚዲያል ወይም በፍሬሽማን ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ትምህርት መስከረም 14/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

በሪሚዲያል ወይም በፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ እንዲሁም ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
❤3👍1
ለተማሪዎች በሙሉ የቀረበ ታላቅ የእድል ጥሪ ከኣቢሲንያ ባንክ (Apollo)! 🎓📱የዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ ተማሪ ነህ/ነሽ? ከትምህርትህ ጎን ለጎን ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና የባንክ ስራ እድል ማመቻቸት ትፈልጋለህ? የBank of Abyssinia Apollo Campus Champion በመሆን እነዚህን ልዩ ጥቅሞች ያግኙ፡💰 በእያንዳንዱ ሰው 100 ብር ገቢ: በየሰው በቀላሉ 100 ብር ያግኙ!📜 የአቢሲንያ ባንክ የብቃት ሰርተፍኬት (Digital Certificate)💳 ነፃ የቨርቹዋል ካርድ (Free Virtual Card)💵 እስከ $1,000 USD FCY Allocation: ለውጭ ሀገር ትምህርትና ሰርተፊኬቶች💼 የቀጥታ የስራ እድል (Job Opportunity): ምርጥ 5 ውስጥ ለሚወጡ ተማሪዎች በአቢሲንያ ባንክ የቅጥር እድል!🎓 እስከ 100,000 ብር የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ: ለግራጁዌሽን መፅሔት እና ለዲፓርትመንት  TRIP!  ——————————⚙️ እንዴት መመዝገብ ይቻላል? (How to Register)1. የ Apollo App ያውርዱ ወይም ይመዝገቡ።  2. ሲመዘገቡ የሚጠይቃችሁን Referral Code / ID ቦታ ላይ ይህንን ያስገቡ፡👉C988711748  3. አካውንቱን ለመቀስቀስ (Activate ለማድረግ) ከ100 ብር በላይ ዝውውር (Transaction) ያድርጉ!  📍 የእርሶ Referral ID:C988711748
  አሁኑኑ ተመዝግበው መስራት ይጀምሩ
❤3
#WachamoUniversity

ለዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤

​የ2019 ትምህርት ዘመን የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ/ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ትምህርት መስከረም 13/2019 ዓ/ም የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን።

​ማሳሰቢያ፡-

👉 ​Pre-engineering, Other Natural Science and Other Social Science የነበራችሁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምደባ በፖርታላችሁ (portal.wcu.edu.et) በመመልከት አዲስ በተመደባችሁበት ካምፓስ እንድትመዘገቡ እያሳስባለን።

👉 ​በ2018 ዓ/ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት አጠናቃችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ/ም ወደ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ የሚገለጽ ስለሆነ በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳስባለን።
❤8
የ 2019 ዓ.ም የከፋተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር!

👉Exit Exam --ሰኔ 3--13/2019

👉Grade 12 Exam -- ሰኔ 28--ሐምሌ 9/2019

የትምህርት  ሚንስትር  አጠቃላይ  የአመት ካላንደር ከላይ ተያይዟል
❤10
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም ለመልሶ ቅበላ ብቁ የሆናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን 👇
ሰኞ መስከረም 11/2019 ዓ.ም

የትምህርት ክፍል ምርጫ 👇
መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም (የ1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች)

የምዝገባ ቀናት 👇
መስከረም 12 እና 13/2019 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀምርበት ቀን 👇
ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም.

በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሳችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል በመገኘት የምዝገባ ሂደታችሁን እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።
❤7
#ASTU

በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመማር አመልክታችሁ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ መስከረም 02/2019 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ለመማር የመግቢያ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ውጤታችሁ እንደሚለቀቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ለመማር አመልክታችሁ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን https://stu.astu.edu.et/astu-results ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ።
❤3
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የመመዝገቢያ ጊዜ 👇
መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም

በቅጣት ለመመዝገብ 👇
መስከረም 13/2019 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀመረው 👇
መስከረም 13/2019 ዓ.ም

በ2018 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደ ፊት በሌላ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል።
❤5👍1
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
❤1
የፈተና ክፍያ ተመን ጭማሪ ተደረገ

​የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመራበት ደንብ ቁጥር 260/2004 መሠረት የሚሰጣቸውን የፈተና አገልግሎቶች በመንግሥት በጸደቀ ተመን መሠረት ያስተዳድራል።

በአዲሱ የመንግሥት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም መሠረት የተሻሻለው ክፍያ ተመን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 593/2016 መሠረት ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተገቢ ሆኗል።

​በመሆኑም በተሻሻለው ተመን መሠረት በእያንዳንዱ ተፈታኝ ላይ ለምዝገባና ለፈተና አሰጣጥ:-

👉 ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና 2,000 ብር

👉 ለድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና 3,500 ብር

👉 ለሙያ ብቃት ፈተና ምዘና 3,500 ብር  እና

👉 ለሊቃውንት ማረጋገጫ ፕሮግራም ፈተና 950 ብር በምዝገባ ሲስተሙ ላይ በተቀመጠው የክፍያ ሥርዓት የሚፈጸም ይሆናል።

እንዲሁም የተሻሻለው ተመን ከመውጣቱ በፊት ለተከፈሉ ፈተናዎች የሚከፈል ቀሪ ክፍያዎች 750 ብር በእያንዳንዱ ተፈታኝ ተሰልፎ እንዲፈጸም፤ ያልተከፈሉ ክፍያዎችም የተሻሻለው ተመን በሲስተሙ ላይ ከመጫኑ በፊት በመክፈል ተገቢውን አገልግሎት እንድታገኙ እናሳስባለን።
❤18
#AssosaUniversity

በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እስከ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ዋና ሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-
● ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ፣
● ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ሁለት መጠኑ 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ።
❤5
#AksumUniversity

ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

​የዩኒቨርሲቲያችን አዲስ የተመደባችሁ እና ነባር መደበኛ ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፤ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ከጥቅምት 24-25/2019 ዓ.ም ባለው የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን አውቃችሁ፤ በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እያሳወቅን፤ ከዚህ ውጭ በውክልና ምንም ዓይነት ምዝገባ የማይፈቀድ መሆኑን ቅድመዉ ለማሳወቅ እንወዳለን። 

​ማሳሰቢያ፦

➻​በ2018 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፤ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የምትገቡበት የመግቢያ ቀናት፤ ከላይ የተጠቀሱት የመግቢያ ቀናት ተመሳሳይ መሆኑን አውቃችሁ፤ በአካል ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁ እንድታከናውኑ ጭምር ለማሳወቅ እንወዳለን። 

➻​ሁሉም ነባር ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ኢ-መደበኛ (Extension) ተማሪዎች፤ ምዝገባችሁ የሚከናወነው ከጥቅምት 28-29/2019 ዓ/ም ባሉት ቀናት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
❤1
#AmboUniversity

በ2019 አዲስ የተመደባችሁ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ማለፊያ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 16-17/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳዉቋል ::

የምዝገባ ቦታ :-
👉  የማህበራዊ ሳይንስ መስክ በዋና ካምፓስ፤

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት ተመዝገቡ ተብሏል ::

በተጨማሪ እንዲሁም ኦንላይን በestudent.ambou.edu.et ማመልከቻና ሙሉ መረጃ ሞልታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት መጠኑ 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
❤2
#debraTaborUniversity #Tigrai

​ትግራይ ክልል ውስጥ ካሉት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የቆያችሁና በዝውውር በ2019 ዓ/ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ከ04 - 06/02/2019 ዓ/ም ድረስ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን።
❤1
#AksumUniversity

ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

​የዩኒቨርሲቲያችን አዲስ የተመደባችሁ እና ነባር መደበኛ ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፤ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ከጥቅምት 24-25/2019 ዓ.ም ባለው የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን አውቃችሁ፤ በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እያሳወቅን፤ ከዚህ ውጭ በውክልና ምንም ዓይነት ምዝገባ የማይፈቀድ መሆኑን ቅድመዉ ለማሳወቅ እንወዳለን። 

​ማሳሰቢያ፦

➻​በ2018 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፤ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የምትገቡበት የመግቢያ ቀናት፤ ከላይ የተጠቀሱት የመግቢያ ቀናት ተመሳሳይ መሆኑን አውቃችሁ፤ በአካል ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁ እንድታከናውኑ ጭምር ለማሳወቅ እንወዳለን። 

➻​ሁሉም ነባር ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ኢ-መደበኛ (Extension) ተማሪዎች፤ ምዝገባችሁ የሚከናወነው ከጥቅምት 28-29/2019 ዓ/ም ባሉት ቀናት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
❤7