The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
#በድሃ እና #ከድህነት_ወለል_በታች በሚኖር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በኢትዮጵያ በቀን ስንት ብር የሚያገኝ ወይም ምን ያህል ካሎሪ ያለው ምግብ የሚመገብ ነው ከድህነት ወለል በታች የሚካተተው?



በዓለም ላይ ወጥ በሆነ መልኩ የድህነት ወለል የለም! ያደጉ ሃገራት የድህነት ወለል ላላደጉ ሀገራት ከጣሪያ በላይ ነው! ለምን?


ለድህነት ወለል መሰረታዊ ነጥቦች.......


1. ገቢ/ወጪ፤
2. የቤተሰብ ብዛት፤
3. እድሜ፤
4. የሚኖሩበት አካባቢ፤
5. የምግብ አይነት፤


እንዴት ተፅዕኖ እንደሚፈጥሩ https://youtu.be/iWiXhHwgJ7w በዝርዝር ቀርቧል።
#በድሃ እና #ከድህነት_ወለል_በታች በሚኖር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በኢትዮጵያ በቀን ስንት ብር የሚያገኝ ወይም ምን ያህል ካሎሪ ያለው ምግብ የሚመገብ ነው ከድህነት ወለል በታች የሚካተተው?



በዓለም ላይ ወጥ በሆነ መልኩ የድህነት ወለል የለም! ያደጉ ሃገራት የድህነት ወለል ላላደጉ ሀገራት ከጣሪያ በላይ ነው! ለምን?


ለድህነት ወለል መሰረታዊ ነጥቦች.......


1. ገቢ/ወጪ፤
2. የቤተሰብ ብዛት፤
3. እድሜ፤
4. የሚኖሩበት አካባቢ፤
5. የምግብ አይነት፤


እንዴት ተፅዕኖ እንደሚፈጥሩ https://youtu.be/iWiXhHwgJ7w በዝርዝር ቀርቧል።
በሀገራችን የባንክ ወለድን በመጨመር የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል?


በርካታ የዓለም ሀገራት እየተፈጠረ ያለውን ከፍተኛ #የዋጋ_ንረት ለመቋቋም በባንኮች ያለውን #የወለድ_መጠን በመጨመር ላይ ናቸው! ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተመሳሳይ ምክረ ሃሳብ ከኢኮኖሚስቶች እየተሰጠ ነው! እውነት በኢትዮጵያ የባንክ ወለድን በመጨመር በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት ይቻላል?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/hxMcsOOLkKA ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
የዓለም ባንክ በዛሬ መረጃ (https://www.facebook.com/worldbank) መረጃው ወቅታዊ ዋጋን (Nominal) መሰረት ያደረገ ነው ይላል)!

በዓለም ላይ የምግብ ዋጋ ንረት ከፍተኛ ሆኗል! ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ94.1% ሲንር፤ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ86% ንሯል እንዲሁም ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ምግብ በ93% ዋጋው ንሯል፡፡

የምግብ ዋጋ ንረት በ264% በዝምባብዌ እና በ139% በሊባኖስ ከፍተኛ ሲሆን ኢትዮጲያ ከ30% በላይ የምግብ የዋጋ ንረት ካለባቸው ውስን ሃገራት መካከል አንዷ ነች ይላል፡፡ ከምግብ እህል መካከል በ2ዓመት ውስጥ በቆሎ በ24% የጨመረ ሲሆን ስንዴ በ7% ዋጋቸው ጨምሯል፡፡

በስጋት የተሞላው የዓለም የግብርና ገበያ እና የራሽያ እና የዩክሬን ጦርነት አለመብረዱ ችግሩን ካባባሱት መካከል መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

በኢትዮጲያ ያለውን የስንዴ እና የጤፍ የዋጋ መጨመርን ነዋሪ በቀላሉ ሊተነትነው ይችላል፡፡
ዋጋ ንረት/Inflation ምንነት፤ ምክንያት፤ ደረጃ፤ ስጋት እና እድል!


ዋጋ ንረት/Inflation ሰፊ ትርጉም፤ የዋጋ ንረት የሚከሰትበት ምክንያት እና ተፅዕኖ፤ የዋጋ ንረት ሊኖረው የሚችለው እድል፤ የሚመከር የዋጋ ንረት ደረጃ፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት የተከሰተበት ወቅት፤ የዋጋ ንረት መከላከያ መንገድ፤ ወዘተ ላይ ጠለቅ ያለ ትንተና ተመልከቱ። https://youtu.be/DUByLZ0FAjE
የቤት ባለቤትነት የፋይናንስ ነፃነት ላያመጣ ይችላል! እንዴት?


የመሰረታዊ ፍጆታ ገንዘብ ያለው ተከራይ እና የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት ያለበት የቤት ባለቤት መካከል ያለው ልዩነት #ተስፋ ብቻ ነው?


50% የሚሆኑ ዜጎቻቸውን የቤት ባለቤት ማድረግ ያልቻሉ የበለፀጉ ሃገራት አመክንዮ ምንድን ነው?


👉 የዓለም መረጃ https://youtu.be/1QerIibWqZo
አንዳንድ ወጣቶች "ስራ የማይጠፋበትና የሚያበላ ዘርፍ ምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ። በርግጥ የሚያበላም ሆነ በፍጥነት ስራ የሚገኝበት ስለሚባል የትምህርት መስክ ዛሬ ላይ መወሰን ከባድ ነው።



ልጅ ሆናችሁ በምትመኟቸው ዘርፎች ተመርቀው ለለት ፍጆታ ትግል ውስጥ ያሉ ብዙ ናቸው። ከዚህ ዩኒቨርስቲ መመረቅ እድል ነው ትሉባቸው ከነበሩ ተቋማት ወጥተው የሰራተኛው ገበያው ያልወሰዳቸው ብዙ ናቸው።  ምርጫቸውን ሰፊ ለማድረግ ከአንድ በላይ ድግሪ ይዘው በአንዱም ያልተቀጠሩ ትንሽ አይደሉም።


ኮሌጅ አልሄድም ብለው ብዙዎችን ቀጣሪ የሆኑ ብዙ ናቸው! ኢኮኖሚ ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ ገቢ እየተገኘባቸው ያሉ መስኮች የኮሌጅ ድግሪ ግዴታ የሆነባቸው አይደሉም።


ስለዚህ ለመማር ዛሬ ላይ ስትወስኑ ወቅታዊው የሰራተኛ ገበያ፤ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እስከምርቃታችሁ እንደሚዘልቅ እርግጠኛ አትሁኑ።


የሰራተኛ ገበያው እና የቢዝነስ አዝማሚያው የሚወሰነው በጥረታችሁ እና ለሁኔታዎች ባላችሁ ተለዋዋጭ እይታ በመሆኑ ነባር መመዘኛዎችን በሂደት እየመረመሩ መሄድ ግድ ነው።
መንግስት ከወር በላይ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉ እየፈጠረበት ያለው #Opportunity_Cost ዝቀተኛ ከሆነ የማናውቀው ብዙ ነገር አለ ማለት ነው!
አፍሪካ የዓለምን 58% ከድህነት ወለል በታች ያለ ህዝብ ድርሻን ይዛለች! ነገር ግን ከድህነት ለመውጣት ከእቅዷ መካከል ከበለፀጉ ሀገራት የብድር እና የእርዳታ ጥያቄ እንደቀጠለ ነው።


"Existing debt relief mechanisms do not work well for Africa" ECA's Antonio Pedro.


የሚገርመው አፍሪካ ለመሰረታዊ ድህነቷ ምክንያት መካከል ሆን ተብሎ በሚከማች የውጪ እዳ ውስጥ መዝፈቅ መሆኑ በብዙ ጥናት እየተገለፀ የበለፀጉ ሀገራት ሆን ብለው ያከማቹትን እዳ ቀንሱ ስለተባሉ ይሳካል?
ቢሮክራሲ እና ሙስና ዋጋ ንረት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ!


አምራቾችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች በማምረትም ሆነ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ውስጥ የሚገጥማቸውን ማንኛውም ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ወጪ በሙሉ የመጨረሻ ሸማች እና ተጠቃሚ ላይ እንዴት እንደሚደምሩት የሚከተለውን ትንታኔ https://youtu.be/Ot20N07m1UY ተመልከቱ።
አንድ ጥናት ስመለከት፦ "ዩክሬይን ከራሽያ ጋር የገባችበት ጦርነት ቆሞ በየዓመቱ በአማካይ በ3% የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) እድገት ቢኖራት የዛሬ ዓመት ወደነበረችበት ለመመለስ 13 ዓመት ይወስድባታል" ይላል።


"If we assume that in periods of growth, the Ukrainian economy grew by 3% on average, recovery after the war would take 13 years".


ከዚህ ቀደም በሶርያ ጦርነቱ ከተከሰተ ከ5 ዓመት በኋላ ተረጋግታ ቢሆን እንኳ ከጦርነቱ በፊት ማለትም 2009 ወደነበረችበት ለመመለስ ከ30 ዓመት በላይ ሊፈጅባት እንደሚችል ጥናት ቀርቦ ነበር።


"Syria's Economy Will Take At Least 30 Years to Recover, Says the U.N 2014".


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ አውድ ቢጠና እንዴት ነው?
በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በዓለም ላይ የተለያዩ ገበያዎች አሉ! መንግስታት ሁሉንም የግብዓት ስርዓት የመቆጣጠር አቅም የላቸውም! በዋናነት በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ያለው ልዩነት ምንድን ነው? በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ምን አይነት ቁሶች እና አገልግሎት እንደሚገበያዩ፤ ለምን ገበያዎቹ እየሰፉ እንደሆነ የሚከተለውን የመረጃ ዳሰሳ ጥናት ላይ በምሳሌ የተደገፈ ትንታኔ አቅርቤላችኋለሁ። እስከመጨረሻው ተከታተሉት።

https://youtu.be/QM_w7F5axNU
ጥቂት ሰዎች "ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ መፅሃፍ ምን ትላለህ?" አሉኝ። በእርግጥ ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ የባለብዙ የቤትስራ ሃገር እየመሩ የመፃፊያ/የማፃፊያ ጊዜ እና ተመስጦ ማግኘታቸው እየገረመኝ ነው መሰለኝ እስካሁን የፃፏቸውን መፅሃፍት አንብቤ አላውቅም! ነገር ግን የመፅሃፉቱ ሽያጭ ዓላማ መጥፎ አይደለም!
አዳም ስሚዝ ለምን የኢኮኖሚክስ አባት ተባለ?፦ የዛሬ 300 ዓመት (1723-1790) የነበረው ኢኮኖሚስት እና ፊሎሰፈር አዳም ስሚዝ/Adam Smith ስለነፃ ገበያ (Free market)፤ የሠራተኛ ክፍፍል (Division of Labor) እና የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) መለኪያ ዙሪያ ባቀረባቸው ሃሳቦች ለ3 ክፍለ ዘመን የዘለቀ ተፅዕኖዎቹን እና ለምን የኢኮኖሚክስ/የዘመናዊ ኢኮኖሚክስ አባት እንደተባለ በዝርዝር ተመልከቱ።

#Subscribe ማድረግ አይርሱ! https://youtu.be/ac2msSux8-g
አዳም ስሚዝ ለምን የኢኮኖሚክስ አባት ተባለ?፦ የዛሬ 300 ዓመት (1723-1790) የነበረው ኢኮኖሚስት እና ፊሎሰፈር አዳም ስሚዝ/Adam Smith ስለነፃ ገበያ (Free market)፤ የሠራተኛ ክፍፍል (Division of Labor) እና የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) መለኪያ ዙሪያ ባቀረባቸው ሃሳቦች ለ3 ክፍለ ዘመን የዘለቀ ተፅዕኖዎቹን እና ለምን የኢኮኖሚክስ/የዘመናዊ ኢኮኖሚክስ አባት እንደተባለ በዝርዝር ተመልከቱ።

#Subscribe ማድረግ አይርሱ! https://youtu.be/ac2msSux8-g
ከገጠር ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት መሰረታዊ ምክንያቶች የሚመነጩት ከየት ነው? ከኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች መካከል ክብደት የሚወስደው የትኛው ነው? መንግስት ለምን ነጠላ ምክንያት ላይ ያተኩራል? https://youtu.be/5omIxKGsCqM