The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ኢትዮጵያ የDual Exchange Rate ልትጀምር ትችላለች?|ባንኮች በጥቁር ገበያ ተመን ዶላርን መመንዘር ሊጀምሩ ይችላሉ?


የገንዘብን የመግዛት አቅም በተለያየ ምክንያት ማዳከም አስፈላጊ ነው ተብሎ በታመነ ጊዜ ወይም ምንዛሬን ከቁርጥ ተመን ወደ ገበያ መር ለማዞር በሚደረግ ሽግግር ወቅት ጠቅላላ ገበያውን በአንዴ እንዳያናጋው ዘርፍ ወይም የንግድ ሁኔታው በመለየት የተለያየ የምንዛሬ መጠንን ተግባራዊ ማድረግ (አንዱን ዘርፍ በቁርጥ ተመን (Fixed Exchange Rate) መምራት ሌላው ዘርፍ በገበያ ተመን (Floating Exchange Rate) መምራት) ማለትም መንግስት በአንድ ሀገር ውስጥ የተለያየ የውጪ ምንዛሬ ተመን ሲጠቀም Dual Exchange Rate ወይም Multiple Foreign Exchange Rate ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ ወደዚህ የምንዛሬ ስልት ልትገባ ትችላለች? ብትገባ ጉዳቱ ምንድን ነው? ወይስ ሌላ ምርጫ አላት? ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/UujOi3y6prA ምርጥ ትንታኔ እስከመጨረሻው ተከታተሉት! ለሌሎች ያጋሩ።
ካፒታሊዝም በተለይ የነፃ ገበያ አቀንቃኞች የማይነግሩን 23 ቁልፍ ጉዳዮች!


ይህ መፅሐፍ በዓለም ላይ በአንደኝነት ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ የኢኮኖሚክስ መፅሐፍ ነው። የካፒታሊዝም ስርዓት በዋናነት የነፃ ገበያ እንከን የለሽ እና አሁን ላይ የዓለም ሀገራት በሙሉ እንዲከተሉት ጫና የሚፈጠርበት እየሆነ ቢሆንም ደቡብ ኮሪያዊው የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ሃ ጁን ቻንግ 23 ካፒታሊስቶች የማይነግሩን ጉዳዮች (ከአዳም ስሚዝ ነፃ ገበያ አመክንዮ ጀምሮ) ብሎ ያቀረባቸውን 23ቱን በሙሉ አቅርቤላችኋለሁ https://youtu.be/d5YIsV1P4aA እስከ መጨረሻው ተከታተሉት ለሌሎች አጋሩት።
ካፒታሊዝም በተለይ የነፃ ገበያ አቀንቃኞች የማይነግሩን 23 ቁልፍ ጉዳዮች!


ይህ መፅሐፍ በዓለም ላይ በአንደኝነት ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ የኢኮኖሚክስ መፅሐፍ ነው። የካፒታሊዝም ስርዓት በዋናነት የነፃ ገበያ እንከን የለሽ እና አሁን ላይ የዓለም ሀገራት በሙሉ እንዲከተሉት ጫና የሚፈጠርበት እየሆነ ቢሆንም ደቡብ ኮሪያዊው የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ሃ ጁን ቻንግ 23 ካፒታሊስቶች የማይነግሩን ጉዳዮች (ከአዳም ስሚዝ ነፃ ገበያ አመክንዮ ጀምሮ) ብሎ ያቀረባቸውን 23ቱን በሙሉ አቅርቤላችኋለሁ https://youtu.be/d5YIsV1P4aA እስከ መጨረሻው ተከታተሉት ለሌሎች አጋሩት።
ቢዝነስ ብዙዎች ስለሰሩትም ሆነ ፋይናንስ ስለተገኘበት ብቻ አያዋጣም!


የልማት ባንክ ስልጠና የወሰዱ ብዙ ሰዎች ሲያወሩኝ ሊዝ ፋይናንስ አግኝተው መስራት እንጂ ሊሰሩ የወሰኑት ቢዝነስ ከፍላጎታቸው፤ ከቦታ፤ ከገበያ፤ ከተስፋ እና ስጋቱ አንፃር አተያያቸው የሚጠበቅ ቢሆንም ከመሰረታዊነት አንፃር የተለያየ ነው።


ከአነቃቂ ንግግር በኋላ ባሉ ቅስፈቶች የለውጥ ስሜት ግልብጥብጡ ስለሚወጣ ሰው በአብዛኛው በስሜት ይሞላል። ለአንዳንድ የልማት ባንክ ስልጠና ሰዎች ማሽን ማግኘት የቢዝነሶች ውጥታማነት በሙሉ የመጨረሻው እንደሆነ እንዲሰማቸው አድርጓል።



የራስን ቢዝነስ ለመስራት ፈጣን ፍላጎት ጥሩ የመሆኑን ያህል ትዕግስት እና ደጋግሞ ማሰብ ይበልጥ ጥሩ ነው።


ስለዚህ ለመስራት የምታስቡትን ከወረቀት ባላነሰ ገበያ ውስጥ ወርዳችሁ ቦታውን፤ ፉክክሩን፤ የግብዓት ሰንሰለቱን፤ የስራ ማስኬጃ ወጪ ተለዋዋጭነቱን፤ የመጪው ጊዜ አዝማሚያን፤ ለምን ለብቻ ወይም በጋራ መስራት እንዳለባችሁ፤ ልዩነት የሚፈልገው የሽያጭ ስልታችሁ፤ ወዘተ አጣርታችሁ ያዙ።


ከብዙ ብድር ፈላጊዎች መካከል በአዋጪነት ተመራጭ ሆኖ ለመገኘት እግረመንገድ (ቢዝነስ ፕላን ያስፈልጋል ስለተባለ ብቻ) ሳይሆን ከልብ የቢዝነስ ፕላናችሁን ለመስራት ሞክሩ! ልማት ባንክ ሊሰጥ ያዘጋቸው ሊዝ ፋይናንስ ባይደርሳችሁ እንኳን በግላችሁ፤ ከቤተሰቦቻችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ፤ በተቋም ተደራጅታችሁ ለመስራት በቂ መነሻ ሊሆን ይችላል (ሌላው ቢቀር ለሌሎች ጥሩ ቢዝነስ ፕላን በማዘጋጀት ገንዘብ መስራት ትጀምሩ ይሆናል።


ይህንን እያልኳችሁ ያለሁት ብዙዎችን ስላዋራሁ ነው። ከስልጠና በኋላ በኤክስፖርት ደረጃ እያሰቡ ስለ ስራማስኬጃ ወጪ አለመገመት፤ ከማሽን ባልተናነስ ማህበራዊ ኔትዎርክ ቢዝነስን ውጤታማ ለማድረግ ሚና እንዳለው ከግምት አለመክተት፤ በወረቀት እና በምልከታ ያለ የቢዝነስ ሃሳብ በተግባር ተገለባብጦ ሊገኝ እንደሚችል ያለመጠርጠር፤ ወዘተ ካለ ሁለቴ ማሰብ መጥፎ አይደለም ለማለት ነው።


ምን አልባት ከረዳችሁ ናሙና ጥናቶች እና ማብራሪያ ያለባቸው ስለሆኑ የሚከተሉትን መጠቀም ትችላላችሁ!


1. የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት/Feasibility Study አዘገጃጀት!(https://youtu.be/GZoZ9jcmIJs)


2. በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?
(https://youtu.be/7R9GyixR59s)


3. የቢዝነስ አዋጪነት መለኪያዎች/NPV, IRR, CBR, Payback Period እንዴት ይሰራል?(https://youtu.be/VpmcOTD90h8)
ስለ ካፒታሊዝም የማይነግሩን 23 ጉዳዮች (ሃ ጁን ቻንግ)!


1 there is really no such thing as a free market (በእውነት ነፃ ገበያ የሚባል ነገር የለም)።


2 Companies should not be run in the interest of their owners (ኩባንያዎች በባለቤቶቻቸው ፍላጎት ብቻ መመራት የለባቸውም)።


3 Most people in rich countries get paid more than they should (በበለጸጉ አገሮች ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች ከሚገባው በላይ ክፍያ ያገኛሉ)።


4 The washing machine has changed the world more than the internet (የልብስ ማጠቢያ ማሽን ከኢንተርኔት በበለጠ ዓለምን ለውጧል)።


5 Assume the worst about people, and you get the worst (በሰዎች ላይ መጥፎውን ያሰበ መጥፎውን ያገኛል)።


6 Greater macroeconomic stability has not made the world economy more stable (ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት የዓለምን ኢኮኖሚ የበለጠ የተረጋጋ አላደረገም)።


7 Free-market policies rarely make poor countries richer (የነፃ ገበያ ፖሊሲ ድሃ አገሮችን ሀብታም የማድረግ እድሉ ዝቅተኛ ነው)።


8 Capital has a nationality (ካፒታል ዜግነት አለው)።


9 We do not live in a post-industrial age (የምንኖረው ከኢንዱስትሪ በኋላ ባለው ዘመን ላይ አይደለም)።


10 The US does not have the highest living standard in the world (ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ላይ ከፍተኛው የኑሮ ደረጃ የላትም)።


11 Africa is not destined for under-development (አፍሪካ ላለመልማት የተፈጠረች አይደለችም)።


12 Government can pick winners (መንግስት አሸናፊዎችን መምረጥ ያስቀድማል)።


13 Making rich people richer doesn’t make the rest of us richer (ሀብታሞችን ማበልፀግ ሌሎቻችንን ሀብታም አያደርገንም)።


14 US managers are over-priced (የአሜሪካ አስተዳዳሪዎች ከዋጋ በላይ ናቸው)።


15 People in poor countries are more entrepreneurial than people in rich countries (በድሃ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች ከበለፀጉ ሀገራት ሰዎች የበለጠ ስራ ፈጣሪ ናቸው)።


16 We are not smart enough to leave things to the market (አብዛኛው የገበያ ምርቶችን ለመተው ብልህ አይደለንም)።


17 More education in itself is not going to make a country richer (ትምህርት ብቻውን ሀገርን ሀብታም አያደርገውም)።


18 What is good for the General Motors is not necessarily good for the US (ለጄኔራል ሞተርስ ጥሩ የሆነው ለአሜሪካ ጥሩ አይደለም)።


19 Despite the fall of Communism, we are still living in planned economies (የኮምኒዝም ውድቀት ቢከሰትም አሁንም የምንኖረው በታቀደ ኢኮኖሚ ውስጥ ነው)።


20 Equality of opportunities is unequal (እኩል እድል መስጠት እኩልነት አይደለም)።


21 Big government makes people more, not less, open to changes (ትልቅ መንግስት ሰዎችን ለለውጥ ይደርጋቸዋል እንጂ አያሳንሳቸውም)።


22 Financial markets need to become less, not more, efficient (የፋይናንሺያል ገበያዎች የበለጠ ግዙፍ መሆን የለባቸውም)።


23 Good economic policies do not require good economists (ጥሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጥሩ ኢኮኖሚስቶችን አይፈልግም)።


👉23ቱን በሙሉ በትንታኔ https://youtu.be/d5YIsV1P4aA መከታተል ትችላላችሁ።


👉 መፅሃፉን ለምትፈልጉ https://t.me/wasealpha ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
ሀገራት ድሃ የሚሆኑበትን ዋናው ምክንያት በሰዎች በሚፈጠር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቋማት ሁኔታ ነው!


ከ 15 ዓመት በላይ በወሰደ ጥልቅ ጥናት Acemoglu እና Robinson እንዳረጋገጡት (Why Nation Fail) በዓለም ላይ ባላደጉ ሀገራት ላይ ያለው ደካማ ፖለቲካዊ ተቋማት ሁኔታ፤ ደካማ ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ሁኔታ ማለትም…..


1. የመንግስት በገቢያ ላይ ትልቅ ጣልቃ ገብነት መኖር፤


2. የግል ሴክተርን ያለማሳተፍ፤ አለምአቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን ያለመከተል ፤

3.  ለፖለቲካ ሹመኞች ብቻ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመፍጠር ልምድ፤ ወዘተ ችግሮችን በመፍጠር እንጂ ሌላ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ያልሆነ ጠንካራ እና አሳማኝ ምክንያት ላለማደጋቸው ተጠቃሽ እንደማይሆን አረጋግጠዋል፤


በመጽሃፉ የኢትዮጲያም ሁኔታ በሰፊው የተገለጸ ስለሆነ የመፅሃፉን ዳሰሳ https://youtu.be/jy7810klwrw አቅርቤላችኋለሁ።


በዚህ አጋጣሚ ለማንበብ ከፈለጋችሁ ሙሉ መጽሃፉን በ Telegram ገጼ ላይ ስላስቀመጥኩት https://t.me/wasealpha በመግባት ይህንን መጽሃፍ ብታነቡት ጥሩ ትምህርት ታገኙበታላችሁ፤
ቢሮክራሲ እና ሙስና ዋጋ ንረት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ!


አምራቾችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች በማምረትም ሆነ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ውስጥ የሚገጥማቸውን ማንኛውም ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ወጪ በሙሉ የመጨረሻ ሸማች እና ተጠቃሚ ላይ እንዴት እንደሚደምሩት የሚከተለውን ትንታኔ https://youtu.be/Ot20N07m1UY ተመልከቱ።
ቢሮክራሲ እና ሙስና ዋጋ ንረት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ!


አምራቾችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች በማምረትም ሆነ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ውስጥ የሚገጥማቸውን ማንኛውም ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ወጪ በሙሉ የመጨረሻ ሸማች እና ተጠቃሚ ላይ እንዴት እንደሚደምሩት የሚከተለውን ትንታኔ https://youtu.be/Ot20N07m1UY ተመልከቱ።
ሀገራት ብራቸውን ለምን በብዛት አያትሙም? ሀገራት የራሳቸውን ገንዘብ የማተም መብት አላቸው? ሀገራት ለምን ገንዘባቸውን በሌሎች ሀገራት እዲታተም ያዛሉ? ኢትዮጲያ ገንዘቧን የት ነው የምታሳትመው? ይህንን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትንታኔ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡ https://youtu.be/AjAMg_NgH70
የዘመናዊው ኢኮኖሚክስ አባት አዳም ስሚዝ ከሚስማማበት ነጥብ አንዱ የኢኮኖሚ ተዋንያን ራስ ወዳድ ናቸው።


የኢኮኖሚ ተዋንያን የሚባሉት አምራች፤ ሸማች እና መንግስት (ብሄራዊ ባንክን እንደ አራተኛ ይታሰባል) ማለት ናቸው።


አምራቾች ከመንግስት መሰረተ ልማት እና ግብዓቶች ከሸማቾች ደግሞ ቀጥተኛ ትርፋቸውን ሲያገኙ ለመንግስት ግብር በመክፈል ለሸማች ደሞዝ ሊከፍሉ ይችላሉ። አምራቾች እስካተረፋቸው ድረስ ማህበራዊ እሴትንም ቢሆን ከግምት ሳይከቱ ቢሆን ከፍተኛ #ትርፍ ለማግኘት ይጥራሉ።


ሸማች ከመንግስት የተለያዩ ድጎማዎችን ቢቀበልም ግብር ለመንግስት በልዋጩ ይከፍላል። ሸማች ለአምራቾች እና ሻጮች ክፍያ ቢፈፅምም ሲቀጠር ደሞዝ ያገኛል። ሸማች የተሻለ #እርካታ የሚያገኝበትን ምርት እና አገልግሎት በዝቅተኛ ወጪ ማግኘት ይፈልጋል።


መንግስት ከሸማቾች እና ከአምራቾች ጋር የሚኖረውን የመስጠት እና የመቀበል ግንኙነት ጤነኛ እንዲሆን ግብር መሰብሰብ፤ በጀት መደልደል እና ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር ሚና ይጠበቅበታል።


ከላይ የተጠቀሱት የሶስቱ ተዋንያን የግንኙነት መርህዎች ከፍተኛ የባህል ተፅዕኖ ባለባቸው ሀገራት ለመተግበር ውስን የማዝገም አዝማሚያ ቢኖረውም በተለይ የኑሮ ውድነት ሲኖር እየጎላ ይመጣል።


ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛው የኢኮኖሚ ተዋናይ ለፈተና ይበልጥ እየተጋለጠ ነው?
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ገደብ መጣል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች!


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያለው የሞኖፖሊ አቅም እንዲቀንስ የሚፈለገው ለማህበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች የሚሰጠው ግምት አነስተኛ ሆኖ ለፖለቲካል አዎንታዊ አስተዋጽኦ ብቻ ሲባል የሚኖርን የኢንተርኔት ገደብ ለመቀነስ ነበር። ነገር ግን ጅምሩ አሁንም ደካማ ነው!


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጥልቀት ኢንተርኔትን የተደገፈ አይደለም! ነገር ግን ለበርካታ ቀናት የኢንተርኔት ገደብ የጣለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች ምንድን ናቸው?


https://youtu.be/WYZbF1lVCKw
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ገደብ መጣል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች!


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያለው የሞኖፖሊ አቅም እንዲቀንስ የሚፈለገው ለማህበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች የሚሰጠው ግምት አነስተኛ ሆኖ ለፖለቲካል አዎንታዊ አስተዋጽኦ ብቻ ሲባል የሚኖርን የኢንተርኔት ገደብ ለመቀነስ ነበር። ነገር ግን ጅምሩ አሁንም ደካማ ነው!


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጥልቀት ኢንተርኔትን የተደገፈ አይደለም! ነገር ግን ለበርካታ ቀናት የኢንተርኔት ገደብ የጣለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች ምንድን ናቸው?


https://youtu.be/WYZbF1lVCKw
#Research_Gap ማውጣት የምትችሉባቸው 9 አማራጮች፦ አዲስ ጥናት ለመስራትም ሆነ ከዚህ በፊት ከተጠኑ ጥናቶች በመነሳት አዲስ ነገር ለመጨመር እና ጥሩ ጥናት ለማከናወን Research Gap የሚለይባቸው በርካታ አማራጮችን አስቀምጫለሁ እስከመጨረሻው ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙ አጋሩ።


https://youtu.be/yxh5T8vbI5o
#እሸቱ_መለሰ ላይ የሚታየው ቅንነት፤ ልዩ የሆነ ትጋት፤ የማድረግ መተማመን፤ የማስተባበር አቅም እጅግ በጣም የሚገርም ነው! ከሱ ጋር ተባብራችሁ ፈንድ ያሰባሰባችሁ እና ለመቀዶንያ ድጋፍ ያደረጋችሁ ለጋሶች በሙሉ የሚያስቀና አርዓያነት አድርጋችኋል። እናመሰግናለን።
በኢትዮጲያ የሞንተሪ እና የፊስካል አማራጮች ከፖለቲካ ጫናዎች አንጻር ተጽዕኗቸው አዝጋሚ መሆን በግለሰቦች እና በድርጅቶች ውስጥ የቀጣይ ጊዜ ወጪ እና የቀጣይ ጊዜ ዋጋ (Replacement Cost) የመተመን ሁኔታን ከአመክንዮ እንዲወጣ እያደረገው ነው፡፡

ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ለሚሸጡትም ሆነ ለሚገዙት ቁስ በቀጣይ ተመሳሳዩንም ሆነ ግብዓቱን ለመተካት ከግምት የሚከቷቸው ሁኔታዎች በቀጣይ የገንዘብ የመግዛት አቅም፤ በቀጣይ የግብዓቶች ዋጋ፤ በቀጣይ የቋሚ ቁሶች ዋጋ ሁኔታ፤ እንዲሁም በቀጣይ የፍላጎት እና አቅርቦት ሀነታ ከግምት ሊከቱ ይችላሉ፡፡ 

በአዋጪነት ጥናት መለኪያ የቀጣይ ጊዚያትን ዋጋን አሁን ላይ መለካት (Net Present Value (NPV)  ወይም በሂደት የዋጋን መቀነስ (Depreciation Costs) በተለምዶም ሆነ በሳይንሳዊ መንገድ በማስላት ለመሸመትም ሆነ ለመሸጥ ይወስናሉ፡፡

#ለምሳሌ፡- በሂደት የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም በተገማች መጠን (Straight-Line) እየተለወጠ ሊሄድ ይችላል፡፡ (ምን አልባት ላለፉት ዓመታት በየዓመቱ የኢትዮጲያ ብር ከዶላር አንጻር በሁለት ብር ሲዳከም ከነበረ ኢኮኖሚው በቀጣይ በሁለት ብር እንደተለመደው በየዓመቱ እየተለወጠ ሊቀጥል ይችላል ብለው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ነገር ግን እርግጠኝነት በሌለው ሁኔታ ፈጣን የገንዘብ የመግዛት አቅም የማዳከም ለውጦችን ሲያደርግ ከነበረ በቀጣይ ሰዎች ምንዛሬ የመቀነስ እና ባለበት የመቆም ሳይሆን በከፍተኛ ሁኔታ ስለመለወጡ ዋስትና ባለማግኘት ብር ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ይለጠጣል (Accelerated Basis) ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡

#ለምሳሌ፡- አሁን ላይ ሰዎች ቤት የመግዛትም ሆነ ሰርቶ መሸጥ ላይ ያላቸው ፍላጎት ከኤክስፖርት፤ ከአገልግሎት ሴክተር፤ ከግብርና፤ ከአምራች ሴክተር በላይ የሚያጓጓው በቀጣይ የቤት ዋጋ ሁኔታ ያሳየው መለዋወጥ በግነት ተገማች በመሆኑ እና በሌላ ሴክተር የሰሩት ብር ሊኖረው የሚችለው የመግዛት አቅም በግነት እየቀነሰ መሆኑን ማየታቸው ነው፡፡

አምራቾችም ሆኑ ሻጮች ዛሬ ላይ ለገበያ የሚያቀርቡትን ዋጋ የሚወስኑት ነገ ላይ ለማምረትም ሆነ ለማቅረብ ሊያስወጣቸው የሚችለውን ተለዋዋጭ ወጪ ከግምት በመክተት በመሆኑ ለማምረት የሚያስፈልግ የግብዓት ዋጋ በምን ያህል ሊለወጥ እንደሚችል እርግጠኛ ስለማይሆኑ ዛሬ ላይ ቶሎ ቶሎ ዋጋዎችን ያንራሉ (ከ3 ቀን በፊት የገዛችሁትን እቃ በተለወጠ ዋጋ ይዘው ይጠብቋችኋል እንደማለት ነው! ይህ ማለት በየ3 ቀኑ ዋጋ በመጨመር እያተረፉ ነው ማለት ብቻ ሳይሆን የተያያዥ ወጪዎችን መገመት አለመቻላቸውንም (Replacement Cost) በመፍራትም መሆኑን ያሳያል፡፡

#ለምሳሌ፡- የዛሬ ዓመት የገዛውን የልጁን ሳይክል በአዲስ ለመለወጥ የሚያስብ ወላጅ! አሮጌ ሳይክሉን ሸጦ አዲሱ ዋጋ ላይ ለመድረስ ሊጨምር የሚችለውን ዋጋ (እጥፍ ሊሆን ይችላል!) ስለዚህ በሸመታዎች እርግጠኛ ለመሆን ተደጋጋሚ ስሌት ማድረግ ግድ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- በወቅታዊ ዋጋ አዲስ አበባ ውስጥ ጤፍን በኪሎ ከ80ብር በላይ እየሸመቱ ያሉ ሰዎች በቀጣይ ወር ጤፍ ተመርቶ የሚደርስ ምርት ባይሆንም ኢኮኖሚያዊ ባልሆነ ማስተካከለያ በቀጣይ ወር ጤፍን 60 ብር ቢያገኙት! ወይም ያላቸውን ስጋት ይዘው በቀጣይ ወር ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ተጨምረውበት ጤፍን በ100 ብር ቢያገኙት ገበያውን እንዴት መገመት እንዳለባቸው ግራ እንዲጋቡ ያደርጋል፡፡

የዚህ አይነት እርግጠኝነት የጎደለው የዋጋ ሁኔታ መኖር ሰዎችም ሆኑ ድርጅቶች ያለፉ ጊዚያትን የዋጋ መለዋወጥ ተመርኩዘው በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የሚገምቱ በመሆኑ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያት ውጪ ያሉትን ዋጋ የመወሰኛ ምክንያቶች (ምዝበራ እና የጸጥታ ችግር) በፍጥነት በማስተካከል ዋጋ እየተለወጠ ያለው ከሚጠበቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደሆነ ለማሳየት መሞከር አስፈላጊ ነው፡፡
የኢኮኖሚ ሸፍጠኞች ንዛዜ| Confessions of an Economic Hit Man


በጥልቀት ለመነበብ ወቅት የሚፈልጉ መጽሃፎች አሉ! ከእነዚህ መካከል አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ላይ ያላትን ኢኮኖሚያዊ ሸፍጥ የሚያጋልጠው የጆን ፓርኪንስ ድንቅ መጽሃፍ የኢኮኖሚ ሸፍጠኞቹ ንዛዜ (Confessions of an Economic Hit Man) አንዱ ነው፡፡


Economic Hit Man ማለት የተደራጁ ቡድኖች በተለያየ መንገድ የአለም መሪዎች ለአሜሪካ የግል ፍላጎት ተገዢ እንዲሆኑ የማግባባት ወይም የማስገደድ ስራ እንዲሰሩ የሚያደርጉ ማለት ነው፡፡


👉ሸፍጠኞቹ በኢትዮጵያም ኦፕሬሽን ነበራቸው!


https://youtu.be/ENynHCQrWYg


መጽሃፉን ማንበብ ለምትፈልጉ 👉Telegram:- https://t.me/wasealpha አስቀምጬላችኋለሁ።
የኢኮኖሚ ሸፍጠኞች ንዛዜ| Confessions of an Economic Hit Man


በጥልቀት ለመነበብ ወቅት የሚፈልጉ መጽሃፎች አሉ! ከእነዚህ መካከል አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ላይ ያላትን ኢኮኖሚያዊ ሸፍጥ የሚያጋልጠው የጆን ፓርኪንስ ድንቅ መጽሃፍ የኢኮኖሚ ሸፍጠኞቹ ንዛዜ (Confessions of an Economic Hit Man) አንዱ ነው፡፡


Economic Hit Man ማለት የተደራጁ ቡድኖች በተለያየ መንገድ የአለም መሪዎች ለአሜሪካ የግል ፍላጎት ተገዢ እንዲሆኑ የማግባባት ወይም የማስገደድ ስራ እንዲሰሩ የሚያደርጉ ማለት ነው፡፡


👉ሸፍጠኞቹ በኢትዮጵያም ኦፕሬሽን ነበራቸው!


https://youtu.be/ENynHCQrWYg


መጽሃፉን ማንበብ ለምትፈልጉ አስቀምጬላችኋለሁ።
እንደሃገር ሃብታችን ማህበራዊነታችን ነው የሚለውን መተማመኛ ወደ #ነበር እየለወጥነው ነው?


በኢኮኖሚክስ ትምህርት ውስጥ Zero Price ወይም በነጻ የሚቀርብ አገልግሎትም ሆነ ቁሳቁስ የሚባል ነገር ብዙም የለም! ስለዚህ በኢኮኖሚክስ ምንም የማያመርት እና ሰርቶ ገቢ የማያስገባ ሰው ዋስትና የለውም ማለት ነው! የፍላጎት እና የአቅርቦት ግራፍ ሲሰራ ከዜሮ የማይጀምረው ይህንን ለማሳየት ሲባል ነው፡፡


ነገር ግን ይሄ የኢኮኖሚክስ አመክንዮ ውድቅ እንዲሆን የሚደረገው ሰዎች በመረዳዳት ያላቸውን ተካፍለው ሲጠቀሙ እና ሲኖሩ ብቻ ነው! ሀረር ተወልጄ ሳድግ ቆንጆ ማሳያዎች ነበሩኝ ለሌሎቻችሁም በያላችሁበት ተመሳሳይ ይመስለኛል።


የኢኮኖሚክስ ትምህርት በጥላቻ የተሞላ እና ወደ አንድ ወገን ብቻ ያጋደለ ነው ወይም ስለትርፋማነት ብቻ ነው የሚጨነቀው የሚል የሚያከራክር ሃሳብ አለበት ይሉታል (Economics has Bias!) በደረስንበት ግሎባላይዝ ዓለም ትችቱ እውነትነት ያለው ቢመስልም ታሪካቸውን ባለቀቁ የዓለም ሀገራት ደግሞ እውነታው የተለየ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ::


#ለምሳሌ፡- ለረጅም ዘመናት ኢኮኖሚስቶች የሚያስቡት አንድ ፕሮጀክት፤ ፕሮግራም እና ፕላን ምን ያህል ወጪ አስወጥቶ ምን ያህል ትርፍ ያስገኛል? ሲከፋ አብዛኛውን ሰው ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጀምሮ በጣም ጥቂቶች ብቻ ቢጎዱ ምንም ችግር የለውም (Tolerated Point!)፤ በአንድ ሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት እስካመጣ ድረስ የተወሰኑ ግሩፖዎች ከኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ ተጠቃሚነት ውጪ ቢሆኑም ለግዜው አካሄዱ ኢኮኖሚያዊ እድገትን እስካመጣ ድረስ ምንም ችግር የለውም፤ ወዘተ የሚሉ አስተሳሰቦች ነበሩበት፡፡


ለዚህም ነው ጥቂት ሃብታም ብዙ ድሃ የተፈጠረበት ኢኮኖሚያዊ ደረጃ በብዙ ሀገራት የሚስተዋለው ይህ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ ሲወጣ ለዝቅተኛው፤ ለመካከለኛው እና ለከፍተኛ ገቢ ባለቤቶች እየተባለ የሚቀረጸው አስተምሮቱ የፈጠረውን ክፍተት ለመድፈን ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- Pro-Poor Program በብዙ ባደጉም ባላደጉም ሀገራት የከፋ ድሃውን ዜጋ ከመካከለኛው ገቢ ባለቤት ጋር የማቀራረቢያ ዘዴ ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- ለመሰረተ ልማት ግንባታ ወይም ሰፊ ፕሮጀክት ለማቋቋም በቂ ያልሆነ ካሳ እየከፈሉ የማስነሳት አካሄድ ከነባር ግለሰቦቹ ኑሮ በላይ የፕሮጀክቱ መተግበር ለብዙሃኖች በገቢ፤ በስራ እድል፤ በገጽታ ግንባታ፤ ወዘተ የተሸላ ሚና አለው በሚል መነሻ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡


ከላይ የተጠቀሱት አይነት አስተሳሰቦች አሁን ላይ እድገት ሁሉንም አካል እኩል ተጠቃሚ ማድረግ አለበት በሚል አስተሳሰብ፤ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማህበራዊ ሁኔታዎችን ከግምት መክተት አለበት በሚል አስተሳሰብ፤ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ባህልን፤ ሃይማኖትን፤ አካባቢን፤ ወዘተ ሳይጎዳ መከናወን አለበት በሚል አስተሳሰብ አዲስ አይነት አካሄዶች በመምጣታቸው የኢኮኖሚክስ ትምህርት ይታይበታል የሚባለውን ወገንተኛ አስተሳሰብ መለወጥ ጀምሯል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑት Institutional Economics፤ Welfare Economics፤ Development Economics፤ ወዘተ የሚሉት የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፎች የሚያራምዱት ሃሳብ ነው፡፡


በኢኮኖሚክስ ትምህርት ውስጥ ሃብት በተለያየ መልኩ ይገለጻል፡- እነሱም መሬት፤ የተፈጥሮ ሃብት (ማዕድን)፤ የተማረ ሰው ሃይል፤ ቁሳቁስ፤ ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ ሲሆኑ ከቅርብ ግዜ ወዲህ #አብሮ_የመኖር እና #የመረዳዳት_ባህል እንደ አንድ ሃብት መቆጠር ጀምሯል፡፡


ኢትዮጲያ ለሺህ ዘመናት ከብዙ የዓለም ሃገራት በተሻለ መልኩ እንደልዩነት መፍጠሪያነት ስትጠቀምበት የኖረችበት ዋናው ሃብቷ Social Capital (መረዳዳት፤ አብሮ መኖር፤ መጠያየቅ፤ ወዘተ) ነው፡፡ ምክንያቱም ኢኮኖሚያዊ አቅምን የሚፈጥሩት መሬት፤ የተፈጥሮ ሃብት (ማዕድን)፤ የተማረ ሰው ሃይል፤ ቁሳቁስ፤ ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ እርስ በርስ ከመረዳዳት በበለጠ መሰረታዊ ተጽኖ ኢትዮጲያ ውስጥ አልነበራቸውም ብል ብዙ አይጋነንም!


ቀጣይ የኢኮኖሚያችን መሰረት መሆን ያለበትም አብሮነት፤ መተማመን እና መረዳዳት ነው፡፡ ማህበራዊ ካፒታል በሰፊው የሚያተኩረው ማህበረሰባዊ ተግባራትን የሚያከናውኑ ማህበራዊ ቡድኖችን ውጤታማ በሆነ መልኩ በማስተባበር ነው፡፡ እነዚህም ማህበራዊ ግንኙነቶች፤ የጋራ ስሜትን፤ የጋራ መረዳት፤ የተጋሩ ደንቦች፤ የተጋሩ እሴቶች፤ መተማመን፤ ትብብር እና የጋርዮሽነት ተግባራት ናቸው፡፡