#Kicking_Away_the_Ladder!
አሁን ላይ በኢኮኖሚ ብልጽግና ላይ ደርሰዋል ተብለው የሚገለጹ ሀገራት በማደግ ላይ ባሉበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት የሚጠብቁ አልነበሩም! ምክንያቱም በፍጥነት ለማደግ ተቋማትን ከገበያ ጣልቃ ገብነት ለመጠበቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ለማደግ በሚሞኩሩበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት ማረጋገጥ አለባችሁ በሚል ጫና ከፈጣን እድገታቸው ለመገደብ ዘወትር ይጥራሉ፡፡
የዛሬ 20 ዓመት በHa-Joon Chang የተጻፈው እና ያደጉ ሀገራት እነሱ ባደጉበት መንገድ ታዳጊ ሀገራት እንዲሄዱ አይፈቅዱም! ያደጉበትን መንገድ ለመከተል የሚፈልጉትን በተለያየ ዘዴ ያከላክላሉ Kicking Away the Ladder "መንሰላሉን ገፍቶ መጣል" ወይም ያደጉበትን ትክክለኛ ሚስጥር ይደብቃሉ ይላል፡፡
አሜሪካ ለማደግ በሄደችባቸው ወቅቶች በገበያ ጣልቃ በመግባት የግሉን ሴክተር ትደግፍ ነበር፤ ጠበቅ ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ትጠቀም ነበር፤ ክልከላዎችን ታደርግ ነበር፤ ወዘተ ነገር ግን አሁን ላይ በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ከዓለም ባንክ፤ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት እና ከሌሎች ተቋማት ብድር እና እርዳታ ለማግኘት ማሟላት አለባቸው በሚል ያዘጋጀቸውን (Washington Consensus) ማለትም ነጻ ገበያ መፍጠር፤ የገበያ ጣልቃ ገብነትን መቀነስ፤ ሰብአዊ መብት ማክበር፤ ክልከላዎችን ማንሳት፤ ወዘተ ይከበር የሚለው ህጓን ድሮም አሁንም በተገቢ መልኩ በራሷ ሀገር የማይተገበሩትን ታዳጊ ሀገራት ላይ አሳሪ በማድረግ አውጥታለች ይላል፡፡
የሰዎችን ጉልበት ብዝበዛ፤ የተፈጥሮ ሃብቶችን በገፍ መጠቀም፤ የአየር ብክለት፤ የውሃ ብክለት፤ መርዛማ ኬሚካል መጠቀም፤ ደን መጨፍጨፍ፤ ወዘተ ለማደግ ሲሞክሩ አንደልባቸው የተጠቀሙት መንገድ ነበር! ነገር ግን አሁን ላይ ለማደግ የሚሞክሩ ሀገራት እነዚህን ተግባራት እንዲያደርጉ በተለያየ ዘዴ አይፈቅዱም፡፡
በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት እንግሊዝም፤ ጀርመንም፤ አሜሪካም በባሪያ ንግድ የተወሰዱ ሰዎችን እና ህጻናትን ሳይቀር ለምርት ሲጠቀሙ ነበር! ነገር ግን እነሱ ለማደግ ሲሉ ያለፉበትን ይህን አካሄድ አሁን ላይ ለየትኛው ሀገር የሰብሃዊ መብት ጠባቂ ነን በሚል ምክንያት ይህ እንዲሆን አይፈቅዱም!
በ19ኛው ክፍለዘመን የአውሮፓ ሀገራት በተለይ እንግሊዛዊ የሌሎች ሀገራት ዜጎች የፈጠራ መብት እንደራሱ አድርጎ የመጠቀም በህግ መብት ነበራቸው፤ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ምርጫ ለሴቶች በአውሮፓ ሀገራት አይፈቀድም ነበር እንዲሁም ህፃናትን ከጉልበት ስራ የሚጠብቅ ህግ አልነበራቸውም (በወቅቱ በአሜሪካ 50% የሚሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ሰራተኛ እድሜው ከ16ዓመት በታች ነበር!፤ ወዘተ።
ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ የቻይና ምርቶች የህጻናትን እና እስረኞችን ጉልበት ተጠቅማ ነው የምታመርተው (ሰብዓዊ መብት ረገጠች) ስለዚህ በተመረጡ ቁሶች ላይ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል የሚል ዛቻ በተደጋጋሚ ታነሳለች (የኢኮኖሚ ተፎካካሪነትን ለመቀነስ ነው!)፡፡
ያደጉ ሀገራት ለሃይል ግብዓት ዩራኒየምን አበልጽገው ከኒዩክሌር ሃይል ይጠቀማሉ (መሳሪያም አድርገው ይታጠቃሉ)! ነገር ግን ታዳጊ ሀገራት የሃይል ምርጫቸውን ኒዩክሌር ለማድረግ ቢያስቡ ጫናው ከባድ ነው (ኢራን እና ሰሜን ኮርያ ተመሳሳይ ጫና ውስጥ ናቸው)፡፡ በምድር ላይ የመጀመሪያውንም ሆነ የመጨረሻውን አቶሚክ ቦምብ ጃፓን ላይ የሞከረችው ሀገር አሜሪካ ብቻ ነች፡፡
በዚህ ወቅት ለማደግ እየሞከሩ ያሉ ድሃ ሀገራት አሁን ላይ ያደጉ ሀገራት ለማደግ ይሞክሩ በነበረበት ወቅት ከነበራቸው የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀት አላቸው! ነገር ግን የበለፀጉ ሀገራት ለማደግ ሲሉ ማንኛውንም ጤናማ ያልሆነ አካሄድ ሞክረዋል (በወቅቱ ቁጥጥር ያደርግባቸው የነበረ አካል አልነበረም) ድሃ ሀገራት በዚህ ፍትሃዊነት በጎደለው ቁጥጥር በበዛበት ጊዜ እንደምንም ብሎ ማደግን እንዴት ያሳኩታል?

ስለሚከተሉት ጉዳዮች ማለትም ስለ ማንኛውም ጉዳይ የእጥረት ሁኔታ (Scarcity)፤ ስለምንም አይነት አቅርቦት እና ፍላጎት (Supply & Demand)፤ ስለ ተግባራቶቻችሁ ወጪ እና ትርፍ (Costs & Benefits) እና በእንቅስቃሴዎቻች በሙሉ ስለሚኖሩ እድሎች (Incentives) ማሰብ እና መጨነቅ ከያዛችሁ ኢኮኖሚክስን እየኖራችሁት ነው!
የጃፓን ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ቀደምት ጠንካራ ኢኮኖሚ ነበር ነገር ግን ከ1990 እስከ 2012 ለ 22 ዓመታት ኢኮኖሚው እድገቱ ቆሞ! በጃፓን የህዝብ እድገት ቆመ፤ የዋጋ ጭማሪ ቆመ፤ የኢኮኖሚ እድገት ቆመ! ዓለም እድገት ጫፍ ደርሶ እንደሚቆም ያየው በጃፓን ነው!
ጃፓን በ20 ዓመት ውስጥ የኢኮኖሚ ደረጃዋን በቻይና በእጥፍ ተበለጠች። ሽንዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ እድገቱ የቆመ ሀገር ነበር የተረከቡት! ነገር ግን ለማምጣት በሞከሩት 3 የለውጥ እርምጃዎች (Monetary, fiscal and structural reform) በስማቸው "አቤኖሚክስ" የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።
የአቤ ለውጦች ውጤት በግማሽ እንደተሞላ ብርጭቆ ነው ቢባልም ጥሩ መማሪያ ይሆናል።
https://youtu.be/BQoeipxoTSc

YouTube
አቤኖሚክስ (Abenomics = Shinzo Abe + Economics)| የጃፓን ኢኮኖሜ እንዴት እድገቱን ጨረሰ?

ጃፓን በ20 ዓመት ውስጥ የኢኮኖሚ ደረጃዋን በቻይና በእጥፍ ተበለጠች። ሽንዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ እድገቱ የቆመ ሀገር ነበር…

የኑሮ ውድነት = የዋጋ መጨመር + የገቢ አለማደግ ነው! ስለዚህ የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ በአንዴ በ70% ጨምሮ የወላጆች ገቢ በነበረበት ከቆመ የኑሮ ውድነት ትክክለኛ ትርጉሙን ያገኛል!።
የትምህርት ቤቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ወላጆችን ብቻ ሳይሆን ወላጅ በሆኑ አከራዬች፤ የአገልግሎት እና ሸቀጥ አቅራቢዎች በኩል ወላጅ ያልሆነውም የዋጋ ጭማሪው ንዝረት ይደርሰዋል።
ስለዚህ ስለ ፍትሃዊነት ማሰብ እና እንዲታሰብ ማድረግ ግድ ነው!

የዋጋ ንረት እና ልጆች የመውለድ መጠን ምን ግንኙንት አላቸው? Does inflation determine fertility rate?
2022 ላይ በቱርክ በተደረገ አንድ ጥናት የዋጋ ንረት በአንድ ከመቶ ሲጨምር የወሊድ መጠን በ0.035% ይቀንሳል (ተቃራኒ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው)። ወላጆች የመኖሪያ ወጪ ሲጨምርባቸው ተጨማሪ ልጆች ለመውለድ ያላቸው ፍላጎት ይቀንሳል እንደማለት ነው።
የቤተሰብ ቁጥር ከገቢ መጠን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ብዙ ጥናቶች አሉ (ቤተሰቦች ገቢያቸው እያደገ ሲሄድ የቤተሰብ ቁጥራቸውን ለመጨመር ይወስናሉ ለማለት ሲሆን ውስን ተቃራኒያዊ ውጤት የሚታይበትም ጥናትም አለ)።
በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ለረጅም ዓመታት የመጨመር ባህሪ አለው! ለምሳሌ ያህል ብናይ የህዝብ ቁጥር እድገት ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በአማካይ ከ2.5 እስከ 2.7 የደረሰ በማደግ መለዋወጥ እንዳለው Projection ቢሆንም የህዝብ ትሬንድ ላይ ያሳያል! ከዚህ በመነሳት በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት የህዝብ ቁጥር እድገት ሁኔታ ላይ ተፅዕኖው ደካማ ነው የሚል Hypothesis ለማስቀመጥ ያስደፍራል? (ለውይይት ያህል ነው!)።
ሌላው Hypothesis እንደ ግለሰብ እና ቤተሰብ በመጪው ጊዜ የኢኮኖሚ ሁኔታ ለውጥ ላይ መተማመን ሲቀንስ የአሁንን ሃይል በማሰብ የቤተሰብ ቁጥር መጨመርን ከዋጋ ንረት ጋር ያለማጣበቅ ባህሪ ሊኖር ይችላል።
ጥሩ የጥናት ሃሳብ የሚሆን ይመስለኛል! የዋጋ ንረት እና የህዝብ ቁጥር እድገት ግንኙነቱን በTime series መረጋገጥ ቢቻልም የመጨመርም ሆነ የመቀነስ ምክንያቱን በDescriptive ማወቅ የሚቻል ይመስለኛል።
በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት (ለረጅም ጊዜ ቀጣይነት ይዞ የሚያድግ ነው) እና የውልደት መጠን/የህዝብ ቁጥር እድገት ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላችኋል? ከትዝብቶቻችሁ ተነስታችሁ ያለው Rationality ምን ይመስላችኋል?

ነጻ ገበያ ስለሆነ ከፈለክ ግዛ ካልፈለህ ትተህ ሂድ፤ ከፈለኩ እሸጣለሁ ከፈለኩ አልሸጥም፤ በገዛ ንብረቴ ዋጋ መወሰን እችላለሁ፤ ነጻ ገበያ ስለሆነ ጣልቃ መግባት አንችልም፤ ወዘተ ማለት ነጻ ገበያ ማለት አይደለም፡፡ የገበያ ህግን ማስከበር አለመቻልም ሆነ በገበያ ህግ አለመገዛት ሁሉ የነጻ ገበያነት አመክንዮ አይደለም! https://youtu.be/43OTRHCSavc
YouTube
የነፃ ገበያ ትክክለኛ እሳቤ ምንድን ነው?| እንደፈለጉ ዋጋን መወሰን የነፃ ገበያ አመክንዮ ነው? በኢትዮጵያ ነፃ ገበያ ይተገበራል?
ነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ዋና ተዋናይ የሆኑት ሸማቾች እና አምራቾች/ሻጮች ሌላው ተዋናይ መንግስት ተቀንሶ ገበያው ላይ የመወሰን መብት እዲወስዱ የተሰጠ የውክልና አካሄድ ነው፡፡ በዜጎች መካከል ያለው የሃብት ክፍፍል ሲዛነፍም፤ ፍታዊነትን ለመጠበቅ እና ለብዙሃን የገበያ ምቹነት ሲባል ገበያ በመንግስት መጎብኘቱ አይቀርም!
ምክንያቱም ነጻ ገበያን ይዞ ብቅ ካለው አዳም ስሚዝ (1723-1790) ጀምሮ ላለፉት…

1287_2015_የኤክሳይዝ_ታክስ_አዋጅ_ማሻሻያ._
7.6 MB
የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል! አዲስ ወደ ኤክሳይዝ ታክስ የተጨመረ እንዲሁም ከታክስ የተቀነሰ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ የተደረገባቸው የቁሳቁስ ዝርዝሮች።
በተሻሻለው ኤክሳይዝ ታክስ . . አዲስ የተጨመሩ ፦
✔️- የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክት)፣ የገመድ አልባ ስልክ አገልግሎት፣ የገመድም ሆነ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቶች 👉 የማስከፈያ ምጣኔ 5 %
የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ዋጋቸው የቀነሰ ፦
📃 ስኳር ለህክምና ከሚውለው በስተቀር
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10 %
📃 ማስቲካ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10 %
📃 በቀጥታ ለምግብነት እንዲውል የተዘጋጀ ቸኮሌት እና ጣፋጭ ከረሜላዎች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10 %
📃 ባህሪው ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 60 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10 %
📃 ጨው
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 25 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10 %
📃 ኬሮሲን፣ ቤንዚን እና ናፍጣ ነዳጆች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 15 %
📃 ጨርቅና ልብስ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 8 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 5 %
📃 ምንጣፎች፣ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ የወለል መሸፈኛዎች
- በፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 30 %
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 15 %
በአዲሱ አዋጅ ነፃ የሆኑ የማይመለከታቸው ፦
📹 📷 ቪድዮ መቅረጫ ወይም ማባዣ መሳሪያዎች፣ የቴሌቪዥን ስርጭት መቀበያዎች፣ ፎቶ ወይም ቪድዮ ካሜራ 👉 ነፃ (ነባሩ ማስከፈያ ምጣኔ 10 % ነበር)
ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የሆኑ ዕቃዎች ፦
የሚከተሉት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡
1. አውሮፕላን በዓለምዐቀፍ ትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለበት ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በጉዞ ወቅት የሚጠቀሙባቸው በነፃ የሚሰጡ ዕቃዎች፤
2. የዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱለር ሚሲዮኖች ወይም ዲፕሎማቶች አና ቆንስላዎች ወይም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ የዲፕሎማቱ እና የቆንስላው ቤተሰቦች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዟቸው በዲፕሎማቶች መብትና ጥቅም ደንብ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፣
3. በመንግሥት ጥሪ መሰረት በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመርጃ እንዲውሉ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች፣
4. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወይም የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዙዋቸው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤
5. ከተሽከርካሪ በስተቀር ወደአገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤

#ኤክሳይዝ_ታክስ ማን ይከፍላል? ኤክሳይዝ ታክስ በተወሰኑ የምርት እና የአገልግሎት ባህሪ ባላቸው ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች ላይ በዋናነት በአምራቾች እና አስመጪዎች ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ቢሆንም እንደአለመታደል ሆኖ ከዋጋ ጋር ለሸማች አውርደው ይሰጡታል!
ጥያቄው ነባር ኤክሳይዝ ታክስ ሲቀነስ ከነባር ዋጋ መውረድ ያለመደው ገበያ (ገደብ የሌለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ፍላጎት) ባለበት የሸማች ጫና ይቀንሳል ወይ የሚለው ነው!
ታክስ ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል! ለምሳሌ ሀገራት ታክስ ለመጨመር ሲወስኑ የሚከተለው አመክንዮ ሊኖራቸው ይችላል ሊቀንሱ ሲያስቡም በተቃራኒው.....
መንግስታት በሁለት መንገድ ታክስን ሊጨምሩ ይችላሉ፤ አንደኛው የገቢ መጠናቸውን በመጨመር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማዋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የገንዘብ አቅርቦትን እና ፍላጎትን ለመቆጣጠር በሚያስቡበት ወቅት ነው፤ #ለምሳሌ የገንዘብ አቅርቦት በሰዎች እጅ ሲበዛ በታክስ ሰበብ መሰብሰብ የተለመደ አሰራር ነው፤ የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ታክስ መቀነስ ሌላው አሰራር ነው (ታክስ ተቀነሰ ማለት ሰዎች ለመንግስት ይከፍሉት የነበረው ገንዘብ እጃቸው ላይ ይቆያል ማለት ነው)።
በተጨማሪም ከውጪ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚጣል ታክስ የውጪ ምንዛሬን አቅርቦት መሰረት ያደረገ መሆን ስለሚኖርበት ሀገራት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሲገጥማቸው ከውጪ በሚገቡ እና መሰረታዊ በማይባሉ ቁሶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ይጥላሉ::

በከባዱ የኢኮኖሚክስ ዘርፍ የመጀመሪያውን የኖቤል ሽልማት ያገኘችዋ ብርቱ ሴት Elinor Ostrom! የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ ሊማርበት የሚችለው Economic Governance ፈጣሪ!
https://youtu.be/QG8I8GbgyfI
https://youtu.be/QG8I8GbgyfI
YouTube
በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴት (Elinor Ostrom)!
በEconomic Governance ማለትም የጋራ ኢኮኖሚያዊ ሃብቶችን ስለማስተዳደር በሰራችው ጥናት ዓለም የሚያከብራት ታላቅ ኢኮኖሚስት!
እንደ ኢትዮጲያ ከሞላ ጎደል Progressive Capitalism (ማለትም በመንግስት፤ የግል ሴክተሩ እና የምርምር ተቋማት በመቀናጀት ስትራቴጂክ የሆነ አቅም በመፍጠር አቅርቦት እና ፍላጎትን ማቀራረብ ላይ ያነጣጠረ) ስርዓት ለመተግበር በምትሞክር ሃገር ውስጥ ነጻ ገበያ በመሆኑ ማሰገደድ አንችልም የሚሉ መግለጫዎች፤ ነጻ ገበያ በመሆኑ መብታችን ነው ተባልን የሚሉ ሸማቾች እና ነጻ ገበያ በመሆኑ ዋጋ ተማኝ ነን የሚሉ አምርቾች/ሻጮች፤ መስማት በጣም እንግዳ ነገር ነው፡፡
ነጻ ገበያ ማለት በጥቂት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ወይም ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት ገበያውን አቅርቦት እና ፍላጎትን ተከትሎ እንዲመራ መፍቀድ ማለት ነው (ነጻ ገበያ ስለዋጋ ያለ ጉዳይ ብቻ ማለትም አይደለም)፡፡
ነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ዋና ተዋናይ የሆኑት ሸማቾች እና አምራቾች/ሻጮች ሌላው ተዋናይ መንግስት ተቀንሶ ገበያው ላይ የመወሰን መብት እዲወስዱ የተሰጠ የውክልና አካሄድ ነው፡፡ በዜጎች መካከል ያለው የሃብት ክፍፍል ሲዛነፍም ሆነ ፍታዊነትን ለመጠበቅ ሲባል ገበያን ለብዙሃን ምቹነት ሲባል በመንግስት መጎብኘቱ አይቀርም! ምክንያቱም ነጻ ገበያን ይዞ ብቅ ካለው አዳም ስሚዝ (1723-1790) ጀምሮ ላለፉት 250 ዓመታት በወረቀት እንጂ በተግባር አሟልቶ መተግበር የቻለ አንድም ሃገር የለም፡፡
በዓለም የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ ነጻ ገበያ ስርዓት ምናባዊ ነው ተብሎ የሚተችበት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መተግበር አለመቻሉ ነው፡፡ ምክንያቱም መንግስታት በጥቂቱም ቢሆን ገበያውን ማየት አለመቻላቸው የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጣልቃ መግባታቸው ወደው ሳይሆን ተገደው ነው::
ሃገራት በተለይ ፖለቲከኞች ነጻ ገበያ ላይ ገደብ ለማስቀመጥ የሚደፍሩበት መሰረታዊ ምክንያት የሚመነጨው ለፖለቲካል ኢኮኖሚው ደህንነት፤ ፍታዊነትን ለመጠበቅ እና የህዝብ የጋራ መጠቀሚያ ሃብቶችን ለመፍጠር ሲባል ነው፡፡ ገበያ ቸል በተባለ ቁጥር የጥቁር ገበያ መጠንከር፤ የብቸኛ አምራች እና አቅራቢነት ባህሪ መፈጠር እንዲሁም ወደ ኢኮኖሚው ስርዓት መግባትን ከባድ የማድረግ ልምምድ ስለሚፈጠር ነው፡፡
ለነጻ ገበያ የቀረበ የኢኮኖሚ ስርዓት አመክንዬ ያላቸው ሃገራት ነጻ ገበያን የግለሰቦችን ሃብት የመፍጠር ነጻነት እና የግለሰቦችን መብት ማክበር ድረስ ነው የሚተገብሩት ምክንያቱም ነጻ ገበያ የመንግስት ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን የመንግስት ድጎማንም ማስቀረት አለበት ስለሚል ነው፡፡ በአይነትም ሆነ በፖሊሲ ባልተደጎመ አርሶ አደር በተመጣጣኝ ዋጋ እና በገፍ ሰብል ወደ ገበያ ለማቅረብ ላደጉም ሃገራት ቀላል አይደለም፡፡
ስለ ካፒታሊዝም በተለይ የነፃ ገበያ አቀንቃኞች የማይነግሩን 23 ቁልፍ ጉዳዮች! በሚለው ድንቅ መጽሃፉ ፕሮፌሰር ሃ ጁን ቻንግ እንደሚለው በእውነት ነፃ ገበያ የሚባል ነገር የለም There is Really No Such Thing as a Free Market ወይም ብዙ ኢኮኖሚስቶች እንደሚስማሙት No Pure Free Market Economies Actually Exist, and All Markets Are in Some Ways Constrained):: ይህ ከኢትዮጰያ እስከ አሜሪካ ገበያ ያለ ሃቅ ነው፡፡
አስታውሱ የነጻ ገበያ መስፈርቶች በሙሉ ተተገበሩ ማለት መንግስት የገበያ ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን ድጎማንም ማስቀረት አለበት ማለት ነው፡፡ በተለያየ መልኩ በድጎማ ስርዓት ውስጥ የማያልፍ አምራች እና ሻጭ ለማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በሚደጎም ነዳጅ፤ በሚደጎም ውሃ፤ በሚደጎም መብራት፤ በሚደጎም የህዝብ መገልገያ እየተጠቀሙ የሚያመርቱ አምራቾች ሸማቾችን መግፋት መብታቸው ሊሆን አይችልም፡፡
ነጻ ገበያ ነው ከፈለክ ግዛ ካልፈለህ ትተህ ሂድ፤ ከፈለኩ እሸጣለሁ ካልፈለኩ አልሸጥም፤ በገዛ ንብረቴ ዋጋ መወሰን እችላለሁ፤ ወዘተ ማለት ነጻ ገበያ ማለት አይደለም፡፡ ህግን ማስከበር ባለመቻል የሚመጡትም ሆነ በህግ ያለመገዛት አዝማሚያዎች ሁሉ የነጻ ገበያነት መገለጫ አይደሉም፡

House Tax .pdf
4.7 MB
የአዲስ አበባ ከተማ #የቤት_ግብር ተመን!
ከመካከለኛው አፍሪካ 6 ሀገራት እና በምዕራብ አፍሪካ 8 ሀገራት ወጥ የሆነ XAF እና XOF የሚባሉ ተመሳሳይ ገንዘብ በጋራ እንደሚጠቀሙ ያውቃሉ? በሁለቱ ዞኖች 27 ሀገራት ያሉ ሲሆን 14ቱ ላላፉት 78 ዓመታት የአንድ ገንዘብ ተጠቃሚ ናቸው!
https://youtu.be/Oddh0gzK2l4
https://youtu.be/Oddh0gzK2l4
YouTube
በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ ከሚገኙ 27 ሀገራት መካከል 14ቱ ላለፉት 78 ዓመታት አንድ ወጥ ገንዘብ እንደሚጠቀሙ ያውቃሉ?

አሜሪካዊቷ Elinor Ostrom (ሊን) በ2009 በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ ሳይንቲስት ነች:: በርግጥ ከኢኮኖሚስቱ Oliver Williamson ጋር በጋራ ነው የተቀበሉት (ከሷ በመቀጠል በ2019 ድህነት ቅነሳ ላይ በሰራችው ስራ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል የወሰደችው ሁለተኛዋ ሴት የ46 ዓመት ሴት ፈረንሳዊቷ Esther Duflo ስትሆን በMIT መምህር ናት)::
ነገር ግን በ#Economic_Governance ማለትም የጋራ ኢኮኖሚያዊ ሃብቶችን ስለማስተዳደር በሰራችው ጥናት ዓለም የሚያከብራት ታላቅ ኢኮኖሚስት Elinor Ostrom ለዓለም ያስተዋወቀችው ዋናው ሃሳብ በማህበረሰብ ውስጥ የጋራ የምንላቸው መገልገያዎች እንዳሉ ይታወቃል::
ኦስትሮም እንደምትለው የጋራ መገልገያዎችን ሰዎች በፍታዊነት እንዲጠቀሙበት ከተፈቀደ (ከማንም ጣልቃ ገብነት ውጪ ማለቷ ነው) የማስተዳደሪያ ህጎችን አውጥተው በመጠቀም በገቢም ተጠቃሚ ሆነው አካባቢያቸውንም በዘላቂነት እንዲንከባከቡ ያግዛል ትላለች::
#ለምሳሌ:- ወንዞች፤ የግጦሽ መሬት እንዲሁም ደኖች የወል/የጋራ (Common Resources) መገልገያ እንደሚባሉ ይታወቃል:: ነገር ግን እነዚህን የጋራ መገልገያዎች እንዴት በጋራ በፍታዊነት መጠቀም እንደሚቻል የሚያስረዳ ታላቅ ሃሳብ ነው፡፡
ለዚህ አካሄድ ያዋጣል ያለችውን 8 መንገዶች አስተዋውቃለች፡፡ እነሱም….
1.የጋራ ሃብቶችን በአግባቡ መከለል እና ተጠቃሚዎችን መለየት፤
2.አካባቢያዊ የአጠቃቀም ደንቦች እና ህጎች ማውጣት፤
3.ሁሉንም አካላት ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊ ማድረግ፤
4.የአጠቃቀምን ፍታዊነት የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራ መስራት፤
5.ህጎችን የሚጥሱ አካላትን ማስጠንቀቅ እና መቅጣት፤
6.በባህላዊ መንገድ ግጭቶች ሲከሰቱ በአፋጣኝ መፍታት፤
7.የበላይ አለቆች ባህላዊውን አስተዳደር እውቅና መስጠት አለባቸው እና
8.አጎራባች ክልሎችን የሚነኩ ሃብቶችን በጋራ ከክልሎች ጋር በመወያየት መጠቀም የሚሉ ናቸው።
በሀገራችን የጋራ የሆኑ ሀብቶችን በመጠቀም ዙሪያ መልካም ማህበራዊ አስተዳደር ቢኖርም የተፈጥሮ ሀብቶች እየገጠማቸው በመጣው እጥረት ምክንያት ሀብቶችን በጋራ በመጠቀም ዙሪያ በርካታ ግጭቶች ይፈጠራሉ (የሚነሱት የጥቅም ይገባኛል ግጭቶች፦ ነዋሪዎች የሚሞቱባቸው፤ ሀብቶች የሚወድምባቸው እንዲሁም ሰዎች የሚፈናቀሉባቸው ናቸው)።
የክልል አወቃቀር ባለበት የሀገራችን የመንግስት አስተዳደር በክልሎች መካከል፤ በዞኖች መካከል፤ በወረዳዎች መካከል፤ በቀበሌዎች መካከል፤ በጎጦች እና በመንደሮች መካከል በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የጋራ ሀብቶች እንዳሉ ይታወቃል!(ጎረቤት ሀገራት ደግሞ እንደ ሀገር ከሀገራችን ጋር የሚጋሩት የአባይ ወንዝ ምሳሌ መሆን ይችላል!)።
የጋራ ሀብቶችን በእኩል ተጠቃሚነት እና ባለቤትነት ስርዓት ለማስተዳደር መቸገር፣ ሀብቱ መስጠት የሚገባውን ጥቅም ለማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዳይሰጥ ምክንያት ይሆናል!
ይህ የሊን አስተሳሰብ ከሚነሱበት ትችቶች መካከል ስብጥር ማህበረሰብ ባለበት አካባቢ በአንድ መጠቀሚያ ሃብተ ላይ ስለፍታዊነት ለመስማማት እና ህብረት ለመፍጠር መቻላቸው አስቸጋሪ ስለመሆኑ እና የጥቅም ግጭት ሲፈጠር ሁኔታውን ለማስተካከል ምን ማድረግ እንዳለባቸው አስገዳጅ መፍትሄ አልጠቆመችም ይሏታል።
በ2013 በካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቷ አልፏል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፦ "ለመጪው የ2016 ዓ/ም ወደ ሃገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል!"
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ጠቅላላ የኤክስፖርት ገቢ መጠን 4.41 ቢሊየን ዶላር ነው! ስለዚህ ገቢው ካልተሻሻለ ነዳጅ ብቻ ነው መግዛት የሚችለው!
ለግንዛቤ ስለ የውጪ ምንዛሬ ምንጮች፦ #ከኤክስፖርት (ምርቶች ወደ ውጪ ተልከው)፤ ከአገልግሎት ሽያጭ (ለምሳሌ የአየር መንገድ እና የቴሌኮም ገቢ)፤ ከቱሪዝም (ለምሳሌ ከስብሰባ ተሳታፊዎች እና ቱሪስቶች)፤ ከሬሚታንስ (ውጪ ሃገር ያሉ ዜጎች የሚልኩት)፤ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (የውጪ ባለሃብቶች ሲገቡ) እና ከእርዳታ እና ከብድር ነው።