The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
#Concept_Note _አሰራር

አንድ ጥናት ወይም ፈንድ ለማፈላለግ ከሚሰራ ፕሮጀክት (ከፕሮፖዛል በፊት) በፊት የሚዘጋጅ ሃሳባዊ መግለጫ ሲሆን ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ እንዲሆን ይመከራል (ነገር ግን እንደ ተቀባይ ድርጅት ወይም የትምህርት ተቋም የገጽ መጠኑ በጥቂቱ ከፍ ሊል ይችላል)፡፡

ርዕስ

1.የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ (የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ የሚሰራ) አልያም ለመስራት የምታስቡትን ማንኛውም የጥናት ርዕስ በተገቢው መጥቀስ::

መግቢያ (Introduction)

1.ለመስራት ያሰባችሁት ጥናት አልያም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ጭብጥ በአጭሩ ማስረዳት፤

2.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ አስፈላጊነት በአግባቡ ማስረዳት፤

3.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ስለሚፈታቸው ችግሮች ወይም ስለሚያረጋግጠው ጉዳይ ማስረዳት፤

4.እንደ አስፈላጊነቱ ከማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ፋይዳዎች አንጻር ምን እንደሚመስል ማስረዳት፤

ዓላማ (Objectives)

1.ዋና የጥናቱ ውጤት መግለጫ ዓላማ (General Objective) እና ትክክለኛ ገላጭ የሆኑ ዝርዝር ዓላማዎች (Specific Objectives) መግለጽ፤

የጥናት ስልት (Research Methodology)

1.የታሰበውን ጥናት ከክፍተት መነሳቱን ማረጋገጥ (Research Gaps)፤

2. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛ ስልት (Research Design) ማቅረብ፤

3. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ/ስብጥር ስልት ማቅረብ፤

4.የታሰበውን ጥናት የውጤት ትንተና ስልቶቹ (Data Analysis Methods) ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

5.የታሰበውን ጥናት የጥናቱን ጥራት (Validity እና Reliability) ስለሚረጋግጥበት መንገድ ማስረዳት፤


የሚጠበቅ ውጤት (Impact)

1.ከታሰበው ጥናት ይመጣሉ የሚባሉ ውጤቶች እንዴት እንደሚለኩ ማስረዳት፤

2. የሚመጣውን ጥናት ግኝት እንዴት ወደ ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚቻል ማስረዳት፤


የጊዜ እና የወጪ ሰሌዳ (Work Plan and Budget Schedule)

1.ትክክለኛ የጥናቱን እና የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ መግለጽ፤

2.ለጥናቱ ወይም ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ የበጀት ዝርዝር ማቅረብ፤

ዋቢ ጽሁፍ (Reference)

1. በአጭር ሰነድ ውስጥ የተጠቀማችሁት ዋቢ ካለ ትክክለኛ መንገዱን ተከትሎ መጥቀስ፤
አሁን ላይ በኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊው ግን የጎደለው ዘርፍ "የፖለቲካ ኢኮኖሚ!"


ፖለቲካ ኢኮኖሚስቶች የሶሾሎጂ፤ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚክስ ዘርፎችን ከግምት በመክተት የመንግስት ፖሊሲዎች፤ የፖለቲካ ሁኔታዎች እና የፖለቲካ ተቋማት ጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ እንዴት ተጽኖ እየፈጠሩበት እንደሆነ እና ወደፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው ተጽዕኖ ካልነገሩን በድህነት ውስጥ ያለንን ቆይታ ያረዝሙታል፡፡


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ትንታኔ https://youtu.be/2mLF_Sxvl24 ይመልከቱት ።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊው ግን የጎደለው ዘርፍ "የፖለቲካ ኢኮኖሚ!"


ፖለቲካ ኢኮኖሚስቶች የሶሾሎጂ፤ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚክስ ዘርፎችን ከግምት በመክተት የመንግስት ፖሊሲዎች፤ የፖለቲካ ሁኔታዎች እና የፖለቲካ ተቋማት ጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ እንዴት ተጽኖ እየፈጠሩበት እንደሆነ እና ወደፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው ተጽዕኖ ካልነገሩን በድህነት ውስጥ ያለንን ቆይታ ያረዝሙታል፡፡


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ትንታኔ https://youtu.be/2mLF_Sxvl24 ይመልከቱት ።
#ፖለቲካል_ኢኮኖሚ

ፖለቲካል ኢኮኖሚ፡ በህዝብ እና በመንግስት መካከል ስላለ ግንኙነት የሚያጠና የማህበራዊ ዘርፍ ሲሆን የፖለቲካ ኢኮኖሚስቶች በዓለም ላይ ያሉ ኢኮኖሚያዊ አመክንዮዎች መካከል ዋናው መነሻ በምድር ላይ ያለውን አነስተኛ ሃብት እንዴት ለብዙሃኑ መጠቀሚያነት ማዋል እንደሚቻል በማብሰልሰል የፖለቲካ ርዕዩተ ዓለሞች (ለምሳሌ ካፒታሊዝም፤ ሶሻሊዝም፤ ኮሚዩኒዝም፤ ወዘተ) አስተሳሰቦች በነባራዊው ዓለም እንዴት እንደሚተገበሩ ማጥናት ነው፡፡

በ18ኛው ክፍለ ዘመን አዳም ስሚዝን እና ጆን ስትዋርት ሚል (Principles of Political Economy ጸሃፊ (ከ1806-1973) የመሳሰሉ ኢኮኖሚስቶች የሃገር ሃብትን ለዜጎች እንዴት ማሰራጭት እና ማስተዳደር እንደሚቻል ማሰላሰል በጀመሩበት ወቅት ፖለቲካል ኢኮኖሚ የሚባለው አስተምሮት ተጀመረ፡፡

ፖለቲካ ኢኮኖሚስቶች የሶሾሎጂ፤ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚክስ ዘርፎችን ከግምት በመክተት የመንግስት ፖሊሲዎች፤ የፖለቲካ ሁኔታዎች እና የፖለቲካ ተቋማት ጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ እንዴት ተጽኖ እየፈጠሩበት እንደሆነ እና ወደፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው ተጽዕኖ ያጠናሉ፡፡

በጣም ታዋቂ የሆኑትን የፖለቲካ ኢኮኖሚ አስተምሮቶች ለማየት ያህል….

ሶሻሊዝም፡- በአንድ ሃገር ውስጥ ያለ ምርት እና ሃብት ስርዓት እና ስርጭት ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ ሳይሆን ለጠቅላላ ማህበረሰቡ የሚሰጥ መሆን አለበት ምክንያቱም በዜጎች መካከል ያለው የሃብት ልዩነት የጠበበ እና ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚዘውሩት ስልጣን እና ሃብት መኖር የለበትም የሚል ነው፡፡

ካፒታሊዝም፡- በገበያ የምርት መጠን፤ ዋጋ፤ የስርጭት ሁኔታ በፍላጎት እና በአቅርቦት ሰበብ በራሳቸው እንዲመሩ መፍቀድ የሚል ነው፡፡

ኮሚዩኒዝም፡- ጥብቅ የሆነ የመንግስት የቁጥጥር ስርዓት ያለበት የገበያ ስዓትት መፍጠር የሚል ነው፡፡

የፖለቲካ ኢኮኖሚ አስተምሮት ጠቀሜታን ብንመለከት፡ በዋናነት ፖለቲካው ኢኮኖሚው ላይ እና ኢኮኖሚው ፖለቲካው ላይ የሚፈጥሩትን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ያጠናል፡፡ ምክንቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አስተሳሰቦች ይመጣሉ ይሄዳሉ እንዲሁም የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቻቸው አብረው ይመጣሉ አብረው ይሄዳሉ ስለዚህ ጠቅላላ ህዝቡ በሂደቶቹ ምን እንደሚያስተናግድ ለመለየት ሲባል ነው፡፡

የፖለቲካ ሁኔታዎች መለዋወጥ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን ይለዋውጣል ለምሳሌ፡ የገንዘብ ፖሊሲ፤ የአስተዳደር ፖሊሲ፤ የምግብ ዋስትና ሁኔታ፤ የዓለም ንግድ ስርዓት፤ የሰራተኛ ገበያን፤ ጠቅላላ የምርት መጠንን፤ ችግሮችን የመፍታት ሁኔታ፤ የአካባቢ ሁኔታን የመቆጣጠር አቅም እና የሃብት ክፍፍልን የመጠበቅ ሁኔታ፤ ወዘተ፡፡

የዓለም ኢኮኖሚ ስርዓት እርስ በእርሱ የተሳሰረ ነው! ማለትን የአንዱ ሀገር የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሌላው ሃገር ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለዚህ ነው የአንድ ሃገር የፖለቲካ ሁኔታ እና የኢኮኖሚ ውሳኔ የሌላው ሃገር ህልውና የሚፈትነው፡፡ ለዚህ ነው በዚህ ወቅት የዩክሬንም የራሽያም የልብ ወዳጅ መሆንን ከባድ የሚያደርገው፡፡

ፖለቲካ ኢኮኖሚውን በአግባቡ የተረዳ ሃገር የጸና ኢኮኖሚ መፍጠር አይቸገርም፡፡ ማለትም የፖለቲካ መሪዎች ወደ ፊት የሚያሻግር ፖሊሲ እና አሰራር ፈጠሩ ማለት ጠቅላላ ኢኮኖሚው የተረጋጋ እና ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በማንኛውም ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት የመንግስት መሪዎች ወደፊት የሚያስቡ ከሆነ የፖለቲካ ሃይል ለውጥ ሳይመጣ እንኳን ለኢኮኖሚ መረጋጋት እና እድገት ትልቅ እድል የሚፈጥሩ ህጎችን እና ፖሊሲዎችን በስራ ላይ ለማዋል መሞከር ይችላሉ።
4ቱ የስራ አጥነት አይነቶች! ስራ፤ ሰራተኛ፤ ስራ አጥነት (Unemployment) እና ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) በኢኮኖሚክስ ውስጥ እንዴት ይገለፃሉ? ስራ አጥነት ለምን ዜሮ አይመጣም?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/bYNpiinwRTA የኢኮኖሚ ትንታኔ ይመልከቱ።
4ቱ የስራ አጥነት አይነቶች! ስራ፤ ሰራተኛ፤ ስራ አጥነት (Unemployment) እና ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) በኢኮኖሚክስ ውስጥ እንዴት ይገለፃሉ? ስራ አጥነት ለምን ዜሮ አይመጣም?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/bYNpiinwRTA የኢኮኖሚ ትንታኔ ይመልከቱ።
ስራን ስራ የሚያሰኘው ምንድን?፤ ሰራተኛ የሚባሉት እነማን ናቸው?፤ ስራ አጥነት (Unemployment) እንዴት ይከፋፈላል?፤ ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) እነማንን ያጠቃልላል?


ስራ ማለት ማለት ገቢ የሚያስገኝ እንቅስቃሴ ሆኖ በኢኮኖሚው ውስጥ ውጤት የሚያመጣ ተግባር ማለት ነው፡፡ ሰራተኛ ማለት ደግሞ ማንኛውም ገቢ የሚያስገኝ ስራ ወይም በኢኮኖሚው ውስጥ ባለ የማምረት ስርዓት ውስጥ ገብቶ የሚሰራ ሰው ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ስራ እየፈለገ ነገር ግን ማንኛውንም ስራ አግኝቶ መስራት የማይችል ሲሆን ስራ አጥ ይባላል፡፡ ብዙ ስራ አጥ አለ ማለት ጠቅላላው ኢኮኖሚ ደካማ የማምረት አቅም ውስጥ ነው ማለት ነው፡፡

የስራ አጥነት መጠን የአንድ ሃገር የኢኮኖሚ ደረጃ ዋና መገለጫ ነው፡፡ አንዳንድ ሀገራት ስራ እስኪያገኙ ስራ አጦችን የሚደጉሙ አሉ፡፡ የስራ ፈላጊ (Labor Force) ቁጥር የሚሰላው ስራ የመስራት አቅም እና ፍላጎት ኖሯቸው ስራ በመፈለግ ውስጥ ያሉ ሰዎች (እድሚያቸው በአብዛኛው ሃገር ከ15 ዓመት እስ 64 ዓመት እድሜ ክልል ያሉ ሰዎች) ብዛት ማለት ነው፡፡

የስራ አጥነት ደረጃ የሚሰላው (በብዙ ዘዴ መረጃው ሊሰበሰብ ይችላል) ስራ ያጡ ሰዎችን ለጠቅላላ ስራ ለሚፈልጉ ሰዎች ብዛት በማካፈል ነው፡፡ ወይም ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎችን ለጠቅላላ ስራ ፈላጊዎች በማካፈል የሚቀነሰውን ከመቶኛ በመውሰድ ነው፡፡

ስራ የሚሰሩም ሆነ ስራ አጥ የሆኑ ሰዎች መረጃ በቀጥታ እያንዳንዱን ቆጥሮ በመውሰድ አልያም ከሚመረጡ ከብዙ ናሙና መካከል በእድሜ እና በሌሎች መስፈርቶች ስራ መስራት የነበረባቸው እየሰሩ ያሉ እና ስራ ፈልገው ያጡትን መረጃ ይሰበሰባል፡፡

ስራ አጥ ሲደመር ሰራተኛ እኩል ይሆናል ስራ ፈላጊ ቁጥር (Unemployed + Employed = Labor Force)::

ለምሳሌ፡- 100 ለስራ ዝግጁ የሆነ ዜጋ (Labor Force) ባለበት ሀገር 70 ሰዎች ማንኛውም አይነት ስራ ቢኖራቸው 70 ከመቶ ስራ ያለው (Employed) እና 30 ከመቶ ስራ አጥ (Unemployed) ሊባል ይችላል ወይም (የስራ አጥነት ደረጃ (Unemployment Rate) መጠኑ 30 ከመቶ ሊባል ይችላል)፡፡ ስራ አጥነት በፍጹም ዜሮ ሊመጣ አይችልም ምክንያቱም በሰዎች እና በኢኮኖሚው ቁጥጥር ውስጥ የማይውሉ ምክንያቶች ስለማይጠፉ ነው! ነገር ግን እነዚህ ምክንያቶች ከጠቅላላ ስራ ፈላጊው መካከል ከ4 ከመቶ እንዳይዘሉ ይመከራል፡፡

ስራ አጥነት ውስጥ በጡረታ የተገለሉ ሰዎች፤ በአካል ጤንነት ምክንያት ስራ የመስራት እክል ያለባቸው ሰዎች፤ ተማሪዎች አይጠቃለሉም፡፡

ይህ ቁጥር ተለዋዋጭ በመሆኑ እንደየሃገራቱ ሁኔታ በየተወሰነ ጊዜ መረጃው ይሰበሰባል (ከ100 ቀንሰውም ወይም ጨምረውም ሊሆን ይችላል ወይም 70 ከመቶውም ሆነ 30 ከመቶው ሊለዋወጥ ይችላል)፡፡

ከአቅም በታች ሰራተኞች (Underemployment): በሰራተኛ ገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሆነው ነገር ግን ዝቅተኛ ስራዎችን ወይም ዝቅተኛ ክፍያ የሚገኝባቸውን ስራዎች ላለመስራት በመወሰን ምን አልባት ለተወሰነ ሰዓት ብቻ የሚሰሩ ነገር ግን የሚፈልጉትን እና አቅማቸውን እና እውቀታቸውን ተጠቅመው በሙሉ ጊዚያቸው መስራት የማይችሉ ሰዎች ናቸው፡፡

በኢኮኖሚክስ ስራ አጥ ማለት የሚመገብ ግን የምርት ስርዓት ውስጥ የማይሳተፍ ሰው ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ ስራ አጥነት በፍላጎት (ሆን ብሎ የማይሰራ ወይም ሌላ ስራ ለመፈለግ ሲል ስራው የለቀቀ ሰው) እና ያለፍላጎት (መስራት እየፈለገ ወይም ከሚሰራበት ስራ ተባሮ ስራ እየፈለገ ያለ ሰው) በሚል ይከፈላሉ፡፡ ነገር ግን ስራ አጥነት አይነት አላቸው እነሱም……..

ተፈጥራዊ ስራ አጥነት (Frictional Unemployment)

ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የስራ አጥነት አይነት ሲሆን ከአንድ ስራ ወደ ሌላ ስራ በመዘዋወር ወቅትየሚፈጠር ስራ ያለመስራት ሁኔታ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ አዲስ ተመራቂ ሰዎች በተመረቁ ቅስፈት ስራ ላይጀምሩ ይችላሉ ወይም አንድ ሰው ከአንድ መስሪያ ቤት ለቆ ወደ ሌላ መስሪያ ቤት በሚዘዋወርበት ወቅት ስራ ላይ የማያሳልፍበት ቀን እንደ ስራ አጥነት ይቆጠራል ወይም አንድ ሴት ለመውለድ ፍቃድ ወጥታ እስክትመለስ ስራ አጥ ነች፡፡

የዚህ አይነት ስራ አጥነት ተፈጥሯዊ ሲሆን ሂደቶች እና መረጃዎች አስፈላጊ በመሆናቸው የሚፈጠር ክፍተት የሚያመጣቸው ናቸው፡፡ ሰራተኛ ቀጣሪ ተቋማት ሳይቀሩ ሰራተኛ ለመቅጠር የሚከተሉት ሂደት ጥቂት ቀን መውሰዱ አይቀርም፡፡

በኢኮኖሚው ድክመት የሚመጣ ስራ አጥነት (Cyclical Unemployment)

የኢኮኖሚ ሁኔታ ሲቀዛቀዝ እና በቀላሉ የሚያስፈልጉትን ሰራተኞች ይዞ መቀጠል ሲቸገር የሚቀነሱ ሰራተኞች ወይም ስራቸውን የሚያጡ ስራ ፈላጊዎች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ሲሚንቶ አጣው በሚል የኮንስትራክሽን ተቋራጭ ሰራተኛ ቢበትን ማለት ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ስራ አጥነት የኢኮኖሚክሰ ትምህርት የራስ ምታት ነው፡፡ በተለያዩ ዘዴዎች ኢኮኖሚው ሰራተኛ ለመበተን የተገደደበትን ምክንያት በመቀነስ ስራዎቹ እንዳይጠፉ ማድረግ አለበት፡፡

በአሰራር ለውጥ ምክንያት የሚመጣ ስራ አጥነት (Structural Unemployment)

አዳዲስ የአሰራር ሀዴዎች ወይም ቴክኖሎጂ በመምጣቱ ሰራተኞችን ከስራቸው አፈናቅሎ በማሽን ወይም በቴክኖሎጂ ሲተካ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በየቤቱ ልብስ በእጅ የሚያጥቡ ሰዎች በልብስ ማጠቢያ ማሽን ሲተኩ፤ ጋሪ ነጂዎች በባጃጅ አሽከርካሪዎች ሲተኩ፤ ፍተሻዎች በማሽን መፈተሸ ሲጀመሩ፤ በሰው ጉልበት ይሰራ የነበረ የምርት ስርዓት በማሽን መመረት ሲጀምር፤ ወዘተ፡፡

በፖሊሲ ለውጥ ሰበብ የሚፈጠር ስራ አጥነት (Institutional Unemployment)

መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎችን በሚቀርጽበት ወቅት የቀጣሪዎችን እና የሰራተኞችን ሁኔታ በመንካቱ የሚፈጠር የሰራተኛ ቁጥር የመቀነስ አጋጣሚ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ንግድ ፍቃድ ለማደስ ያለን ስርዓት ቢያንዛዛ ሰራተኛ ለጊዜውም ቢሆን ሊቀነስ ይችላል፡፡
የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ "አዲስ ብድር አልሰጥም!" ብሏል። ይህን ያለው ለምን የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ህግን አውጥተሽ ተግባራዊ አደረግሽ በሚል ነው።


ቶማስ ሳንካራ እንዳለው "የሚያበሉህ ይቆጣጠሩሃል" ድሃ ሀገር የራሱ #ባህላዊ_እሴት ቢኖረውም የኢኮኖሚ ጥገኝነት እስካለበት ድረስ የሊበራል ሃገራት ህብረት በትር የማይቀር መሆኑን ነው እያሳዩ ያሉት።


ስለዚህ የአንድ ሃገርን ባህል እና እሴትን ለማስጠበቅ የኢኮኖሚ አቅምን ማሳደግ መሰረታዊ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ…….

1. ለመንግስት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር ባለፈው አመት ከተሰጠው ከ1/3ኛ እንዳይበልጥ ይደረጋል።

ምን ማለት ነው?

መንግስት የበጀት ጉድለት በገጠመው ቁጥር ከብሄራዊ ባንክ ቀጥተኛ ብድር እንደሚወስድ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ባለፈው በጀት ዓመት የመንግስት የበጀት ጉድለት ከፍተኛ የነበረ በመሆኑ ከበጀት ጉድለት መሙያ ስልቶች መካከል የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፤ የብሄራዊ ባንክ ቀጥተኛ ብድር እና የብር ህትመት መሆኑ እንዳለ ሆኖ አምና መንግስት ከተበደረው (ምን ያህል እንደተበደረ ባላውቅም) አንጻር በዚህ በጀት ዓመት መበደር የሚችለው ከ30 ከመቶ መብለጥ የለበትም ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ፡- ዓምና የመንግስት በጀት ጉድለት የነበረው 300 ቢሊየን ብር ቢሆን እና ከሱ ውስጥ 100 ቢሊየኑን ከብሄራዊ ባንክ ተበድሮ የበጀት ጉድለቱን አቃሎ ነበረ ብለን ብናስብ ዘንድሮ መበደር ያለበት አምና ወስዶት ከነበረው 100 ቢሊየን ብር ውስጥ 33 ቢሊየን ብር (1/3ኛ) መብለጥ የለበትም ማለት ነው፡፡


2.መንግስት ቅድሚያ የግምጃ ቤት ሰነድ አማራጭን አሟጦ እንዲጠቀምና አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ብቻ የቀጥታ ብድር ይጠቀማል።

ምን ማለት ነው?

ከበጀት ጉድለት መሙያ ስልቶች መካከል የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፤ የብሄራዊ ባንክ ቀጥተኛ ብድር እና የብር ህትመት (የውጪ ብድር እና እርዳታን ጨምሮ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁሉም ስልቶች የየራሳቸው ተጽዕኖም እድልም ያላቸው ቢሆንም ከብሄራዊ ባንክ የሚወስደውን ብድር የመጨረሻ አድርገን እንጠቀማለን ማለት ነው (በኔ ሃሳብ ለመንግስት የመጨረሻ አማራጭ መሆን ያለበት ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስደው ብድር ይልቅ አዲስ የሚታተም ብርን ማስቀረት ነው!)፡፡

3. በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሰኔ መጨረሻ የሃገር ውስጥ ብድር ዕድገት በ14 በመቶ ጣሪያ ይገደባል። ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሰረት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል።

ምን ማለት ነው?

ብድር የሚቀርበው በባንኮች በኩል መሆኑ ይታወቃል (የትርፋቸው መሰረታዊ መነሻም ከብድር ከሚገኝ ወለድ ነው) ስለዚህ በየዓመቱ ለማበደር የሚይዙት ተጨማሪ ጣሪያ ይኖራቸዋል ስለዚህ በቀጣይ በጀት ዓመት ዘንድሮ ካበደሩት አንጻር ተጨማሪ ለማበደር ሲያስቡ እስከ 14 ከመቶ ብቻ አድርጉ ማለት ነው (በአጭሩ ከፍተኛ መጠን ብድር ወደ ገበያ እንዳይለቁ ማለት ነው!)፡፡

4. ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስዱት ብድር የብድር ፋሲሊቲ ላይ የሚከፍሉት ወለድ ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።

ምን ማለት ነው?

ባንኮች ያላቸው ገንዘብ በደንበኞች እጅ እና በብሄራዊ ባንክ እንደሚቀመጥ ይታወቃል ስለሆነም ተጨማሪ ገንዘብ ፈልገው ከብሄራዊ ባንክ ሲበደሩ ወትሮ ይከፍሉ ከነበረው የ16 ከመቶ ወለድ ወደ 18 ከመቶ ወለድ ያድግባቸዋል ማለት ነው (በአጭሩ ወለዱን ፈርተው ተጨማሪ እንዳይበደሩ እና ለደንበኞቻቸው እንዳያበድሩ (ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ኢኮኖሚው እንዳይለቁ) ማለት ነው!)፡፡


5.ቁልፍ የሆኑ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ላኪዎችን ለማበረታታት ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ምንዛሬ የማስተላለፍ ግዴታ ከ70/30 ወደ 50/50 እንዲሻሻል ይደረጋል። ላኪዎች 50 በመቶውን ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስገቡ፣ 10 በመቶውን አብረው ለሚሰሩት ባንክ እንዲሰጡ እና 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

ምን ማለት ነው?

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ 70 በመቶውን ገቢ እንዲያደርጉለት ወስኖ የነበረ ሲሆን ቁልፍ ሴክተር አምራቾችን ለማበረታታት በማሰብ 50 ከመቶውን ብቻ አስገቡ 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ወስኗል፤ 10 ከመቶው ደንበኛ የሆኑበት ባንክ ይወስዳል ማለት ነው (በአጭሩ የውጪ ንግድ ላይ ተሳትፎ ያላቸው ከሚሰሩት የውጪ ምንዛሬ ማዘዝ የሚችሉት ከ30 ከመቶ በታች ከነበረው አሁን ወደ 40 ከመቶ አደገ ማለት ነው)፡፡

6. በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የዋጋ ንረቱ ከ20 በመቶ በታች እንዲሆንና በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ይሰራል፡፡

በኔ እምነት የዋጋ ንረት በኢትዮጲያ ገበያ በዋናነት መነሻው ከገንዘብ ፖሊሲ የሚመነጭ ባለመሆኑ በአንድ ዓመት ውስጥ የዋጋ ንረትን ከ10 ከመቶ በላይ ለመቀነስ ሊቸገር ይችላል።

በአጠቃላይ የብሄራዊ ባንክ ካለው ስልጣን መካከል መጠቀም ያለበትን እና የሚችለውን ነው የወሰነው፡፡ የብሄራዊ ባንኩ ውሳኔ የገንዘብ ፈሰስን ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ግልጽ ነው! ነገር ግን ዋጋ ንረት ከፍተኛ ለሆነበት እና ከጦርነት ለማገገም ለሚጣጣር ኢኮኖሚ ገንዘብ አስፈላጊም ነው፡፡

የገንዘብ አስተዳደር ስራን ከባድ የሚያደርገው ያስፈልጋል የተባለ ገንዘብ ኢኮኖሚን ሊጎዳ ይችላል (በተለይ ምርታማነት ላይ ካልዋለ) በተቃራኒ ጉዳት አለው ተብሎ ከገበያ የተቀነሰ ገንዘብ አምራች ክፍሉን በካፒታል እጥረት አዳክሞ የምርት መጠንን በገበያ ሊቀንስም ይችላል፡፡ ነገር ግን የፊስካል ፖሊሲው ዋጋ ንረት ላይ ያለው ድርሻ ቀላል ባለመሆኑ ዋጋ ንረት በተገለጸው ቁጥር ልክ እንዲቀንስ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተቋማት ርብርብ ሳይደረግ ለመሳካት መቸገሩ አይቀርም፡፡
አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ የዋጋ ንረትን Significantly የመቀነስ አቅም ይኖረዋል? ገንዘብ ለዋጋ ንረት ስጋትም እድልም የሚሆንበት አመክንዮ ምንድን ነው?


ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ በሚከተለው https://youtu.be/fWN8twmF_Ss ትንታኔ ሰፋ ባለመልኩ ተመልከቱ ለሌሎችም አጋሩት።
አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ የዋጋ ንረትን Significantly የመቀነስ አቅም ይኖረዋል? ገንዘብ ለዋጋ ንረት ስጋትም እድልም የሚሆንበት አመክንዮ ምንድን ነው?


ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ በሚከተለው https://youtu.be/fWN8twmF_Ss ትንታኔ ሰፋ ባለመልኩ ተመልከቱ ለሌሎችም አጋሩት።
የአፍሪካ ሃገራት የራሽያን አጋርነት የሚፈልጉበት አመክንዮ ኢኮኖሚያዊ ነው?

ራሽያ እንደ አውሮፓውያን ጎረቤቶቿ በአፍሪካ ውስጥ የቅኝ ግዛት ቅርስ የላትም። ከቀድሞዎቹ የቅኝ ግዛት ኃይሎች አንጻር ከአፍሪካ ጋር ያላት አጋርነት አስተማማኝ ነው።

በብዙ አፍሪካውያን እዕታ ራሽያ ብሄራዊ ሉዓላዊነቷን በማጠናከር ረገድ የምትከተለው መንገድ ውጤታማ ሞዴል እንደሆነ ይታሰባል። እንደሚታወቀው ብዙ የአፍሪካ ሀገራት በድንበሮቻቸው አካባቢ ባለ ውዝግብ፣ በሀገር ውስጥ ሽብርተኝነት እና በተወሳሰበ የኢኮኖሚ ችግር ይፈተናሉ፡፡

በአፍሪካ ውስጥ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ድርሻ ብንመለከት ቀዳሚዎቹ እንግሊዝ (65 ቢሊየን ዶላር)፤ ፈረንሳይ (60 ቢሊየን ዶላር)፤ ቻይና (43 ቢሊየን ዶላር)፤ ጣልያን (32 ቢሊየን ዶላር)፤ ወዘተ ቀዳሚ ናቸው፡፡

የንግድ ልውውጡን ደርሻ ብንመለከት ቻይና (254 ቢሊየን ዶላር)፤ የአውሮፓ ህብረት (295 ቢሊየን ዶላር)፤ አሜሪካ (65 ቢሊየን ዶላር) ነገር ግን የራሽያ ድርሻ ከ15 ቢሊየን ዶላር የበለጠ አይደለም፡፡

ራሽያ ከአፍሪካ ከምታስገባው ሰባት እጥፍ በላይ ወደ አፍሪካ ትልካለች። በተጨማሪም የዚህ ንግድ 70 በመቶው ድርሻ የአራት ሃገራት ነው እነሱም ግብፅ (5 ቢሊየን ዶላር)፣ አልጄሪያ (3 ቢሊየን ዶላር)፣ ሞሮኮ (2 ቢሊየን ዶላር) እና ደቡብ አፍሪካ (1 ቢሊየን ዶላር) ላይ ያተኮረ ነው። ራሽያ በአፍሪካ ውስጥ በጣም ጥቂት ኢንቨስት አድርጋለች፡፡

አፍሪካ ከራሽያ እና ጎረቤቶቿ ጥምረት EAEU ማለትም ራሽያ፤ ቤላሩስ፤ ካዛኪስታን፤ ኪርጊዝታን እና አርመንያ በዓመት የ15 ቢሊየን ዶላር ቁሳቁስ ሸምታ የ4 ቢሊየን ዶላር ሸቀጦች ብቻ ትልካለች፡፡ ከዚህ መካከል የራሽያን ድርሻ ብንመለከት ከአፍሪካ የ14.7 ቢሊየን ዶላር ሽያጭ አስመዝግባ የ3 ቢሊየን ዶላር ሸመታ ብቻ አድርጋለች፡፡

አፍሪካዊያኖች በዋናነት ወደ ራሽያ የሚልኩት ፍራፍሬ እና ለውዝ (26 ከመቶ)፤ ካካዎ (11 ከመቶ)፤ ማዕድናት (9 ከመቶ) እና አትክልቶች (6 ከመቶ) ድርሻ አላቸው፡፡ በተቃራኒው አፍሪካዊያን ከራሽያ የሚያስገቡት እህል (24 ከመቶ)፤ ለውሃ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (20 ከመቶ ድርሻ)፤ ማሽኖች (5 ከመቶ ድርሻ)፤ የእንሰሳት ተዋጽዎ፤ ብረት፤ የአፈር ማዳበሪያ (4 ከመቶ ድርሻ)፤ ወዘተ ናቸው፡፡

ራሽያ በዋናነት ከአፍሪካ ጥሬ እቃ እና ማዕድናትን (በተለይ ዳይመንድ እና የከበሩ ድንጋዮች) ስትሸምት አፍሪካዊያን ምግቦቻቸውን እና የኢንዱስትሪ መሰረቶቻቸውን ለማሟላት ይሞክራሉ፡፡ ራሽያ ለአፍሪካ መንግስታት ወሳኝ አጋር ነች፡፡

ለምሳሌ፡ የዛሬ ዓመት ራሽያ ከግብጽ ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ በ30 ከመቶ ጨምሯል የጦር መሳሪያን ይጨምራል (ከራሽያ ወደ ግብጽ የመጡ ምርቶችን ብቻ የሚቆጣጠር ቢሮ እስከመክፈት ደርሰዋል)፤ አልጄሪያ ከራሽያ ጋር ያላት የአኩሪ አተር ንግድ በ25 ከመቶ ያደገ ሲሆን ከሞሮኮ ጋር ያላት የግብርና ውጤቶች ንግድ ልውውጥ በእጥፍ አድጓል፡፡

የምዕራቢያዊያንን ማዕቀብ ተከትሎ የኢራን የንግድ አጋር ራሽያ ሆናለች በዚህም ነዳጅ፤ ድሮን፤ ጥይቶች፤ የስፔስ ምርምር ድጋፎችን ይለዋወጣሉ፡፡ ቻይና የ85 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ውጤቶች ከራሽያ የምትሸምት ሲሆን በትንሹ ካየነው የ2.6 ቢሊየን ዶላር የእንጨት ውጤቶችን ትሸምታለች፡፡ በምትኩ ራሽያ ከቻይና ማሽኖች፤ መኪኖች፤ ኬሚካሎች፤ የምግብ ውጤቶች እና የግብርና ግብዓቶች ትሸምታለች፡፡


የራሽያ ዋና የንግድ አጋሮች በተለዋዋጭ ድርሻ አማካዩን ብናይ ቻይና (72 ቢሊየን ዶላር)፤ ጀርመን (27 ቢሊየን ዶላር)፤ አሜሪካ (17 ቢሊየን ዶላር)፤ ቤላሩስ (15 ቢሊየን ዶላር)፤ ወዘተ ናቸው፡፡

በንግድ አጋርነት ረገድ አሁን ላይ ራሽያ ለአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት እንደወሳኝ የኢኮኖሚ አጋር ሳይሆን እንደ ሊበራል ሃገራት ካለ በዝባዥ ስርዓት ተሟጋች እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አጋር ተገዳዳሪ እና ነባር ስርዓት ለዋጭ ሀገር አድርገው እንደሚቆጥሯት ነው የሚሰማኝ፡፡
#ብቸኛው_ጥቁር በኢኮኖሚ ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚው ሰር አርተር ሊዊስ (Sir Arthur Lewis) ማነው?

የሊውስን የመጀመሪያነት መገለጫ ተመልከቱ…….

1.  በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን ያገኘ የመጀመሪያው ጥቁር ሰው፤

2.  በለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ጥቁር ተማሪ፣

3.  በለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ጥቁር መምህር፣

4.  በማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው የጥቁር ፋኩልቲ አባል እንዲሁም

5.  በፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሮፌሰር በመሆን ለ20 ዓመታት አስተምሯል።

ሰር አርተር ሌዊስ በ1915 በካሪቢያን ደሴት ሴንት ሉቺያ ተወለደ። ከልጅነቱ ጀምሮ አስደናቂ አዕምሮ ስለነበረው በተርም በአንዴ ክፍሎችን በማለፍ መደበኛ ትምህርቱን በ14 ዓመቱ ጨርሷል። ከዚያም በእንግሊዝ በለንደን ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲማር የሚያስችለውን የነፃ ትምህርት ዕድል አገኘ።

ሉዊስ በወቅቱ በለንደን ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት ውስጥ ብቸኛው ጥቁር ተማሪ ነበር (በወቅቱ በዘረኝነት ይጠቃ እንደነበር ይገልጻል)፡፡ እስከ በ1940 ባለው ጊዜ ውስጥ ማለትም በ25 ዓመቱ የPh.D ትምህርቱን በማጠናቀቅ በለንደን ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ጥቁር ፋኩልቲ አባል ሆኖ በመቀጠር እስከ 1948 ድረስ ሰርቷል፡፡

በማንችስተር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሮፌሰር ሆኖ ባገለገለበት ወቅት የኖቤል ሽልማት ያስገኘለትን ታዋቂውን "Dual Sector Model" ወይም በስሙ የተሰየመውን "Lewis Model" በ1954 ባሳተመው ማለትም "Economic Development with Unlimited Supplies of Labor" ላይ አብራርቷል፡፡

ሃሳቡ ምንድን ነው?

ሊዊስ በሞዴሉ ያስተዋወቀው ነገር ቢኖር ድሃ ሀገራት ከፍተኛ የሰው ሃይል ያላቸው ቢሆንም በካፒታል ረገድ ደካማ በመሆናቸው የሰው ሃይልን ከካፒታል አቅርቦት ጋር አቀናጅተው ለማደግ ይቸገራሉ ነገር ግን ያላቸውን የሰው ሃይል በተለይ ደካማ የማምረት አቅም ላይ የሚገኙትን (በግብርና ሴክተር ላይ ተሰማርተው ለአቅም በታች እያመረቱ ያሉትን ጨምሮ) የሰው ሃይሎች ወደ አዋጪ ሴክተሮች በማዘዋወር መጠቀም የሚችሉ ከሆነ ከድህነት ለመውጣት ያላቸው እድል ፈጣን ነው የሚል ነው፡፡

ወይም በኢኮኖሚ እድገት ወቅት ድሃ ሀገራት ከፍተኛ የሰው ሃይል ጉልበት ኋላቀር በሆነው የግብርና ዘርፎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል ይህ ዘርፍ ደግሞ ደካማ የማምረት አቅም ላይ በመሆኑ በምርት አቅም ከድህነት ለመውጣት ጥሩ አቅም አይሆንም! ስለሆነው ይህንን ከአቅም በታች ያለ የሰው ጉልበት ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በማዘዋወር መጠቀም የሚቻል ከሆነ አንደኛ የባከነውን የሰው ሃይል ኢንዱስትሪው መቀበል ይችላል በተጨማሪ ኢኮኖሚ ኢንዱስትሪ መር የመሆን እድል ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ "Dual Sector Model" ማለት የፈለገው ግብርናውን እና ኢንዱስትሪው በተጻራሪ መቆማቸውን ለማሳየት ነው፡፡

ሊዊስ የእግሊዝን ጥምር ዜግነት በመውሰዱ ለታላቋ እንግሊዝ ዜጎች በክብርነት የሚሰጠውን ሰር የሚል ስያሜ በማግኘት በማዕረግ ስሙ "Sir" ሰር አርተር ሊዊስ ተብሎ በመኖር በ1991 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ከ1969-2022 ድረስ ለ55 ጊዜ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል ተሰጥቷል፤

82 ኢኮኖሚስቶች ኖቤል ተቀብለዋል፤

62ቱ አሜሪካዊያን (14 ጥምር ዜግነት ያላቸው ናቸው)፤

5 እንግሊዝ፤
4 ኖርዎይ፤
3 ፈረንሳይ፤
2 ሲዊድን
ጣልያን፤ ኔዘርላንድ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድ፤ ህንድ እና ጀርመን (አንድ አንድ አላቸው)፤


2 ብቻ ሴቶች (2009 እና 2019) እና 80 ወንዶች፤

1 ብቻ ጥቁር (1979)፤

ለ28 ጊዜ በጋራ እና ለ27 ጊዜ በግል የኖቤል ሽልማት ቀርቧል፤


እያንዳንዱን ኖቤል የተቀበሉ ኢኮኖሚስቶች ስም ዝርዝር እና ሽልማት ያሰጣቸውን ምክንያት https://youtu.be/0h27gLH7kgU በአጭሩ ተመልከቱ።
ከ1969-2022 ድረስ ለ55 ጊዜ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል ተሰጥቷል፤

82 ኢኮኖሚስቶች ኖቤል ተቀብለዋል፤

62ቱ አሜሪካዊያን (14 ጥምር ዜግነት ያላቸው ናቸው)፤

5 እንግሊዝ፤
4 ኖርዎይ፤
3 ፈረንሳይ፤
2 ሲዊድን
ጣልያን፤ ኔዘርላንድ፤ ካናዳ፤ ፊንላንድ፤ ህንድ እና ጀርመን (አንድ አንድ አላቸው)፤


2 ብቻ ሴቶች (2009 እና 2019) እና 80 ወንዶች፤

1 ብቻ ጥቁር (1979)፤

ለ28 ጊዜ በጋራ እና ለ27 ጊዜ በግል የኖቤል ሽልማት ቀርቧል፤


እያንዳንዱን ኖቤል የተቀበሉ ኢኮኖሚስቶች ስም ዝርዝር እና ሽልማት ያሰጣቸውን ምክንያት https://youtu.be/0h27gLH7kgU በአጭሩ ተመልከቱ።