The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
አዲስ አክሲዮን በመግዛት እና ነባር አክሲዮን በመግዛት መካከል ያለው ልዩነት፤ እድል እና ስጋት! አክሲዮኖችን መግዛት ኢንቨስትመንት መሆን የሚችለው የተጠና እና ምክንያታዊ ሲሆን ነው። የአክሲዮን ትርፋማነት እንዴት ይለካል?


ስለዚህ አዲስ የሚመሰረት አክሲዮን ለመግዛት እና ስራ ከጀመሩ ተቋማት ነባር አክሲዮን ለመግዛት ከመወሰን በፊት ከግምት መከተት ያለባቸው ጠቃሚ ሃሳቦችን https://youtu.be/x0niSsaddBc  ይመልከቱ።
ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ (GDP) ያለው ድርሻ ስሌት| በኢትዮጵያ ግብር ከGDP ያለው ድርሻ 6.4%| የግብር መጠን ማነስ ስትራቴጂ ወይስ ድክመት? የዓለም ተሞክሮ እና የኢትዮጵያ ንፅፅር! ኬንያ ከኢትዮጵያ በእጥፍ የሚበልጥ ግብር ከጠቅላላ የኢኮኖሚ አቅም (GDP) ንፅፅር መያዟ እንደሃገር ምንን ያመለክታል?


ይህን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/mWUzC13I6lc ትንታኔ  ይመልከቱ!
የውጪ ባንኮች መግባት ብቻውን በኢትዮጲያ Liberalization ተከናወነ ላያስብል ይችላል! ምክንያቱም መንግስት ከውሃ እና መብራት ክፍያ ጀምሮ እስከ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ እና ጠቅላላ የመንግስት የፕሮጀክቶች ሞዳሊቲ ተቀማጭ እና ፋይናንስ ስርዓትን በመንግስት ባንክ እና በቴሌ በኩል ሞኖፖሊ ማድረጉን ማቃለል ከጀመረ ምን አልባት ሊሆን ይችላል፡፡
የዓለም ባንክ ሃገራት ቢያንስ የ15 ከመቶ የግብር ገቢ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ምጣኔ ቢኖራቸው ጥሩ ነው ይላል!


ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ ያለው ድርሻ በዓመት ውስጥ የሚሰበሰብ የግብር መጠን በዓመት ውስጥ ለሚመዘገበው ጠቅላላ ኢኮኖሚ ምርት መጠን (GDP) በማካፈል የሚገኝ ስሌት ነው፡፡


#ለምሳሌ:- በኢትዮጲያ በ2016 ዓ/ም 440 ቢሊየን ብር ከግብር ቢሰበሰብ እና ለጠቅላላ ሃገራዊ ምርት 7 ትሪሊየን ብር ቢካፈል (ማለትም 130 ቢሊየን ዶላር* በ54ብር ምንዛሬ ተባዝቶ 7 ትሪሊየን ብር ቢመጣ) ግብር ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) 6.2 ከመቶ ሊመጣ ይችላል (በ2016 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ 520 ቢሊየን ብር ተገማች ገቢ ውስጥ 440 ቢሊየን ብሩ ማለትም 84.6 ከመቶውን ከግብር ነው!)፡፡


#ለምሳሌ፡- የአውሮፓ ሃገራት ከፍተኛ የግብር ከጠቅላላ ኢኮኖሚ ምጣኔ አላቸው (ሲዊድን (42 ከመቶ)፤ ዴንማርክ (35 ከመቶ)፤ ፈረንሳይ 45 ከመቶ፤ ወዘተ የደረሰ ሽፋን ሲይዙ)፤ አሜሪካ (26 ከመቶ)፤ ቻይና (4.6 ከመቶ (የትልልቅ ተቋማት ባለቤት መንግስት ከመሆኑ ጋር ሊገናኝ ይችላል)፤ ህንድ (11 ከመቶ)፤ ግብጽ እና ኬኒያ (13 ከመቶ)፤ ናይጄሪያ (10.8 ከመቶ)፤ ወዘተ፡፡


ግብር ብቸኛ የኢኮኖሚ የገቢ ዋስትና ላይሆን ይችላል! በዓለም ላይ 14 ሀገራት ምንም የገቢ ግብር ከኢኮኖሚው የማይሰበስቡ ሲሆን ከነሱ ውስጥም የተባበሩት አረብ ኢሚሬት፤ ባህማስ፤ ሶማሊያ፤ ባህሬን፤ ኪዌት፤ ኳታር፤ ወዘተ፡፡ ምክንያታቸው የተለያየ ቢሆንም ገቢን ከሌሎች ሴክተሮች ለመሰብሰብ፤ በግብር ቅነሳ አምራች እና ሸማች ክፍሉ ከጫና ተላቆ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ፤ ሀገራቸውን ለዜጎቻቸው መኖሪያነት ምቹ ለማድረግ፤ የውጪ ኢንቨስትመንት ወደ ሃገራቸው ለመሳብ፤ ወዘተ ሲሉ ነው፡፡


የስትራቴጂ ትግሉ፡- ከአምራች ክፍሉ ግብርን በመቀነስ የካፒታል እጥረት ሳይገጥመው በመንቀሳቀስ ከፍተኛ የስራ እድል እንዲፈጥር እና ከፍተኛ ምርት እንዲያመርት መፍቀድ በሚለው እና ከሚጣል ከፍተኛ ግብር የሚገኘውን ገቢ ለኢኮኖሚው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን እና ድጎማዎችን ለማቅረብ ማሰብ መካከል ነው፡፡


ነገር ግን እንደ ኢትዮጲያ ከግብር ማዕቀፍ ውጪ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተሳታፊዎችን በማስቀመጥ እና የግብር አሰባሰብ ህግ እና አሰራር ደካማ በመሆኑ የሚነሳ ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ ያለው ድርሻ ማነስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቋማት ድክመት እንጂ እና ስትራቴጂ መሆን አይችልም፡፡


https://youtu.be/mWUzC13I6lc
ከ27 በላይ የኢኮኖሚክስ ዘርፎችን ተዋወቁ! በዓለም ላይ ምንም አይነት ሳይንስ ከኢኮኖሚክስ ጋር የሚገናኝበት ምክንያት አያጣም! ከBlue Economics እስከ Defence Economics ድረስ የተለያየ ባህሪ ትመለከታላችሁ።

ይህንን https://youtu.be/SxENGD5vPUE ቪዲዮ ተመልከቱ ለሌሎችም ግንዛቤ እንዲያገኙበት አጋራቱ።
ከ27 በላይ የኢኮኖሚክስ ዘርፎችን ተዋወቁ! በዓለም ላይ ምንም አይነት ሳይንስ ከኢኮኖሚክስ ጋር የሚገናኝበት ምክንያት አያጣም! ከ Blue Economics እስከ Defence Economics ድረስ የተለያየ ባህሪ ትመለከታላችሁ።

ይህንን https://youtu.be/SxENGD5vPUE ቪዲዮ ተመልከቱ ለሌሎችም ግንዛቤ እንዲያገኙበት አጋራቱ።
በዓመቱ ውስጥ ኢኮኖሚ በ59% ያድጋል?

ማካሁ (Macau) የምትባል በቻይና ነፃ ግዛት የሆነች ሀገር አለች (እንደ ሆንግ ኮንግ በቻይና ውስጥ ነፃ አስተዳደር ማለት ነው) ጠቅላላ የህዝብ ብዛቷ 700ሺህ አልደረሰም። ነገር ግን ዋነኛዋ የዓለም የቁማር መጫወቻ "Gambling capital of the world" ወይም  የ"Monte Carlo of the East") ከተማ ነች (በዚህ ዘርፍ ከአሜሪካዋ ላስ ቬጋስ እና ከፈረንሳያዋ ሞንቴ ካርሎ የቁማር እና የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች በላይ ሆናለች)።


በቱሪስቶች እና ቁማር ለመጫወት በሚፈልጉ በተለይ ከኮቪድ በፊት ከ40ሚሊየን በላይ ህዝብ በዓመት የምትጎበኘው ማካሁ የቁማር ዘርፉ የከፍተኛ ግብር የሚጣልበት በመሆኑ የተከማቸ እዳ የሌለበት ኢኮኖሚ አላት።


ቻይና ትከተል በነበረው የኮቪድ ቁጥጥር ምክንያት ጠቅላላ የጎብኚ ቁጥሯ ቀንሶ ኢኮኖሚዋ ተዳክሞ የነበረ ቢሆንም (የማካሁ GDP በ2022 በ26.8 ቀንሶ ነበር ) የክልከላ መሻሻሉን ተከትሎ ከፍተኛ ቱሪስት በመገኘቱ ተቀዛቅዞ የነበረው ገቢ ከክልከላው ወቅት አንፃር በዚህ ዓመት በ59 ከመቶ GDP ለማደግ ችሏል (የማካሁ GDP 30 ቢሊዮን ዶላር አልፏል)።


በቀጣይ የIMF ትንበያ ማኩሀ በ2024 በ20.6 ከመቶ፤ በ2025 በ8.5ከመቶ ልታድግ ትችላለች የሚል ትንበያ አለ! ይህ የቁጥር መቀነስ የሚያሳየው ጎብኚ ሊቀንስ ይችላል ማለት ሳይሆን 2023 ካደገው ከፍተኛ መጠን ስለሆነ ልዩነቱ የሚሰላው በቀጣይ በንፅፅር መቀነሱ አይቀርም።


#ለምሳሌ፦ በጦርነት ምክንያት የዩክሬን ኢኮኖሚ መቀነሱ አይቀርም ነገር ግን ጦርነቱ ተጠናቆ ወደ ምርት ስርዓት ብትገባ የጠቅላላ ምርቷ GDP በትልቅ ቁጥር ሊያድግ ይችላል ምከንያቱም ንፅፅሩ ከጦርነቱ ወቅት ጋር መሆኑ ነው።
አንድ ዶላር በአንድ ብር እንዲመነዘር ቢወሰን የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በወራት ውስጥ ምን ያስተናግዳል?


በስልጣን ደረጃ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ (መንግስት) ከዛሬ ጀምሮ አንድ ብር ከአንድ ዶላር ጋር እኩል ነው ብሎ መወሰን ይችላል!


ምን አልባት (በኢኮኖሚክሰኛ Let Assume ተብሎ እንደሚጀመረው) በውሳኔ (Artificial Exchange Rate) ተጠቅሞ መንግስት አንድ ዶላርን ከአንድ ብር ጋር እኩል ቢያደርግ ሊገጥሙት የሚችሉት ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ችግሮች ምንድን ናቸው ?


https://youtu.be/Xg8JMetAv5E
አንድ ዶላር በአንድ ብር እንዲመነዘር ቢወሰን የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በወራት ውስጥ ምን ያስተናግዳል?


በስልጣን ደረጃ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ (መንግስት) ከዛሬ ጀምሮ አንድ ብር ከአንድ ዶላር ጋር እኩል ነው ብሎ መወሰን ይችላል!


ምን አልባት (በኢኮኖሚክሰኛ Let Assume ተብሎ እንደሚጀመረው) በውሳኔ (Artificial Exchange Rate) ተጠቅሞ መንግስት አንድ ዶላርን ከአንድ ብር ጋር እኩል ቢያደርግ ሊገጥሙት የሚችሉት ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ችግሮች ምንድን ናቸው ?


https://youtu.be/Xg8JMetAv5E
አንድ ወዳጄ አንድ ሚሊየን ብር ቤት መግዛት በሚችልበት ወቅት በቁጭት መቆጠብ ጨምሮ ዛሬ ላይ ሚሊየን ብሩ ላይ ሲደርስ "ይገርምሃል ሚሊየን ብሩ ጥሩ የቤት እቃ ለማሟላት እንጂ ለቤት ግዢ የሚታሰብ አልሆነም" አለኝ!


"ታዲያ በዚህ ብር ምን ብሰራ ያዋጣል?" ቢለኝ የተቀመጠ ገንዘብ የመግዛት አቅም በሂደት መዳከሙ ላይቀር አዋጪነት ጥናት እራሱ ሚሊየን ብር የሚያስወጣ እየሆነ ስለሆነ ቶሎ አነስተኛ የቢዝነስ አማራጭ መፈለግ ሳይሻልህ አይቀርም አልኩት።
የመውጫ_ፈተና_ውጤት


በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 62.37 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል።


በግል ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት 17.2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል።


በድምሩ ከአጠቃላይ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 40.65 ከመቶ ነው።


ትምህርት ሚኒስቴር
Article Review እንዴት ይሰራል?| How to write article review?


አርቲክል መገምገም ማለት Summary መስራት ወይም አጠር አርጎ መፃፍ ማለት አይደለም! ስለዚህ የተፃፈ አርቲክልን በማንበብ በራሳችሁ አገላለፅ በትክክለኛ መንገድ እንዴት መፃፍ እንደምትችሉ በምሳሌ አቅርቤላችኋለሁ። https://youtu.be/53BdeYtHSuw ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙበት አጋሩት።
Article Review እንዴት ይሰራል?| How to write article review?


አርቲክል መገምገም ማለት Summary መስራት ወይም አጠር አርጎ መፃፍ ማለት አይደለም! ስለዚህ የተፃፈ አርቲክልን በማንበብ በራሳችሁ አገላለፅ በትክክለኛ መንገድ እንዴት መፃፍ እንደምትችሉ በምሳሌ አቅርቤላችኋለሁ። https://youtu.be/53BdeYtHSuw ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙበት አጋሩት።
Article Review ለማድረግ
1.የአርቲክሉ
1. ርዕስ
2. ጸሃፊዎቹ
3. አሳታሚው
4. አርቲክሉ የታተመበት ቦታ
5. አርቲክሉ የታተመበት ቀን
6. የአርቲክሉ ህትመት ቁጥር
7. አርቲክሉ ስንተኛ ገጽ ላይ እንደሚገኝ

2. ርዕሱ እና አጻጻፉ ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ርዕሱ ከጽሁፉ ጋር ያለው ገላጭነት
2. ትክክለኛውን የጥናት አጻጻፍ ሂደት ስለመከተሉ

3. አጭር መግለጫው ወይም Abstract ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ገላጭ ስለመሆኑ
2. ዓላማውን ስለመግለጹ
3. የጥናት ስልቱን ስለመግለጹ
4. ዋና ዋና ግኝቶች ስለመገለጻቸው
5. ትክክለኛ መጠን መያዙ
6. የመፍትሄ ሃሳብ መጥቀሱ
7. ቁልፍ/key words ቃላትን ማካተቱ

4.የጥናቱ ሃተታ Problem Statement ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. የጥናቱ መነሻ ሃሳብ በአግባቡ ስለመጠቀሱ
2. በጥናቱ የሚሞላው Research Gap ስለመጠቀሱ
3. ጥናቱ የሚመልሳቸውን ጥያቄዎችን ስለመጥቀሱ

5.የጥናቱ ዓላማ Research Objectives ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎች ስለመኖራቸው

6.የጥናቱ መላምት Hypothesis ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ግልጽ፤ ከመርህ/ከቀደመ ጥናት ግኝት የተወሰደ እና የሚለካ ስለመሆኑ

7.ሀተታዊ ጽሁፍ Literature Review ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን
1. ከአመክንዮ ስለመነሳቱ
2. የቀደሙ ጥናቶችን ስለማጣቀሱ
3. ስዕላዊ መግለጫ Conceptual frame work ስለመስጠቱ
4. ጥራቱን የጠበቀ ስለመሆኑ

8.የጥናቱ ስልት Research Methodology ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ትክክለኛ የጥናት ስልት ስለመምረጡ
2. ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ ስልት ስለመጠቀሙ
3. የትንተና ስልቶቹ ትክክለኛነት
4. የጥናቱን ጥራት ስለሚሪጋግጥበት መንገድ
5. የስነ ምግባር ጉዳይ ስለመጠቀሱ

9.የውጤት ትንተና ክፍሉ Data Analysis ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. የጥናቱን ዓላማ የሚመልሱ ስለመሆናቸው
2. ትክክለኛ የውጤት መተንተኛ ቀመሮች ስለመጠቀሙ
3. ግኝቱን ከሌሎች ጋር ስለማመሳከሩ
4. ስለውጤቱ ትክክለኛነት የሚያቀርበው ማረጋገጫ

10.ማጠቃለያ እና የመፍትሄ ሃሳቦቹ Conclusion and Recommendation ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. የሚተገበር እና ተዓማኒነት ያለው የመፍትሄ ሃሳብ ስለመቅረቡ
2. የመፍትሄ ሃሳቡ ከጥናቱ ግኝት ብቻ ስለመነሳቱ

11.ዋቢ አጠቃቀስ Reference ላይ ያለ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

1. ወጥ እና ትክክለኛ ዋቢ ስለመጠቀሱ
2. የቅርብ ጊዜዎች ላይ ስለማተኮሩ
3. ተመሳሳይ ብቻ ያልሆነ የዋቢ ምንጮች ስለመጠቀሙ
በኢትዮጵያ የሚያዋጡ" እና "የማያዋጡ" የቢዝነስ አይነቶች ምንድን ናቸው! ማዋጣት ወይም ማትረፍ ማለት ምን ማለት ነው? ግለሰባዊ እና ቀመራዊ የአዋጪነት መለኪያዎች ምንድን ናቸው?


ሰዎች በብዛት የሚሰሩት የቢዝነስ አይነት መሆኑ በቢዝነሱ ለማትረፍ ዋና ማስረጃ ላይሆን ይችላል!


በገበያ ከፍተኛ ፍላጎት መኖር ብቻውን ለትርፋማነት ዋስትና ላይሆን ይችላል!


በገበያ ዝቅተኛ አቅራቢ መኖሩም ብቸኛ ወደገበያው ለመግባት ማስተማመኛ ላይሆን ይችላል!


የምትወዱት አይነት ስራ መሆኑም ብቸኛ የውጤታማነት ዋስታና ላይሆን ይችላል!


ብዙዎች እየሰሩበት ባለው የቢዝነስ ዘርፍ ብዙዎች ከስረው ወጥተዋል!


ከብዙዎች በላይ መነሻ ካፒታል የያዙ የቢዝነስ ጀማሪ ሰዎች ከስረው ያውቃሉ!


ተባብረው/በማህበር ሰርተውም ሆነ በግላቸው ተሯሩጠው የከሰሩ ሰዎች ጥቂት አይደሉም!


ስለዚህ ምን አስቦ? ምን ላይ መስራት ነው አዋጪው? ይህንን በተመለከተ የሚከተለው ቪዲዮ https://youtu.be/tYagUORYeXY ከረዳችሁ ተመልከቱት ሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት።
በኢትዮጵያ የሚያዋጡ" እና "የማያዋጡ" የቢዝነስ አይነቶች ምንድን ናቸው! ማዋጣት ወይም ማትረፍ ማለት ምን ማለት ነው? ግለሰባዊ እና ቀመራዊ የአዋጪነት መለኪያዎች ምንድን ናቸው?


ስለዚህ ምን አስቦ? ምን ላይ መስራት ነው አዋጪው? ይህንን በተመለከተ የሚከተለው ቪዲዮ https://youtu.be/tYagUORYeXY ከረዳችሁ ተመልከቱት ሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት።
ዋስይሁን "ሀብት በገንዘብ አይለካም!" ይባላል ስለዚህ ምን ትላለህ? አለኝ። በሌሎች ዘርፎች ሃብት ከገንዘብ ውጪ ይለካ ይሆናል! ግን በኢኮኖሚክስ የግለሰብም ሆነ የሃገር ሃብት ከገንዘብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ነው የምናሰላው (በኢኮኖሚክስ ውስጥ ገንዘብ ወጥ ሳይሆን በደረጃ የሚከፋፈል ነው M1, M2, M3, M4,.....)።
Concept Note አፃፃፍ! ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ የፕሮጀክትም ሆነ የጥናት መግለጫ Concept Note በቅድሚያ እንዴት እንደሚፃፍ ተመልከቱ

https://youtu.be/L21SgM0HK6A
Concept Note አፃፃፍ! ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ የፕሮጀክትም ሆነ የጥናት መግለጫ Concept Note በቅድሚያ እንዴት እንደሚፃፍ ተመልከቱ

https://youtu.be/L21SgM0HK6A