The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ያለ ውጪ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) እቃ ከውጪ እንዴት ማስገባት ይቻላል? የሚጠየቀው መስፈርት ምንድን ነው?

ዳያስፖራዎች ባላቸው የውጪ ምንዛሬ ከሀገር ውሰጥ የንግድ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ ሳይጠይቁ ካሉበት ቦታ ሆነው እንዴት በፍራንኮ ቫሉታ ዘዴ ወደ ኢትዮጲያ እቃ በማስገባት ለራሳቸው መጠቀም ወይም መነገድ ይችላሉ?

በተለያየ አጋጣሚ የውጪ ምንዛሬ ያከማቹ ሰዎች ከንግድ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ ሳይጠይቁ እንዴት በፍራንኮ ቫሉታ ዘዴ ወደ ኢትዮጲያ እቃ በማስገባት ለራሳቸው መጠቀም ወይም መነገድ ይችላሉ?

በፍራንኮ ቫሉታ እቃ ከውጪ ለማስገባት የሚጠየቀው መስፈርት ምንድን ነው ?የውጪ ንግድ (Import) ላይ ለመሳተፍ ምን አይነት መስፈርት ማሟላት ይገባል?

በዚህ ቪዲዮ መልስ ለመስጠት እንሞክራለን…https://youtu.be/8rcNPqAGb-Q
ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት #ቀረጥ_ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

ይኸው መመሪያ" መመሪያ ቁጥር 1023/2017" ይሰኛል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች?

የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡

1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-

ሀ/ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ ወይም ለህብረሰሰቡ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ :

- የትምህርት ተቋማት፣
- የጤና ተቋማት፣
- የሕጻናት፤ የሴቶች፤ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች

ለ/ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች

2. ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደአገር እንዲገቡ የተፈቀደ እቃዎች።

3. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሰረት ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት መሳሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና አክሰሰሪዎች፡፡

4. በብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች፡፡

ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች ከማህበራዊ ቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ #አይችሉም።

ሀ/ ከ8 መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎች  እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ለ/ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።

ሐ/ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች።

በዚህ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ እቃዎች ማስረጃዎች ማቅረብ የግድ ይላል።

ምን አይነት ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው?

1. እቃዎቹ በእርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የእርዳታ የምስክር ወረቀት።

2. የእቃዎቹን ዝርዝር እና ዋጋ የሚያሳይ ኢንቮይስ፣

3. እቃዎቹ ለተገለጸው አላማ የሚውሉ መሆኑን እንዲሁም ስለእቃዎቹ አጠቃቃም ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑ የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው ከመንግስት መስሪያ ቤት የተጻፈ የድጋፍ ድብዳቤ።
ዝርዝር መረጃ (የገንዘብ ሚኒስትር አዲስ መመሪያ)...

ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት #ቀረጥ_ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

የቀረጡ አይነት፤ የቀረጡ መጠን፤ ከቀረጥ ነፃ የሆኑ እና ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው? የሚለውን መረጃ ተመልከቱ... https://youtu.be/9nkBrhjziQs
#መረጃ

ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚችል አስታዉቋል።

የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰቡን ተቋሙ ገልጿል።


የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ሁሉም ደንበኞች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ አንጨምርም ነገር ግን የደንበኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ በአንድአንድ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ብለዋል።

#Capital
በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ምክንያታዊ መሆን ያሉባችሁ 4 ጉዳዮች.....


ነጋዴ፤ ስራ ፈጣሪ፤ ውጤታማ ገበሬ የሚያደርግ ድግሪ የለም! ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስትወጡ ውጤታማ ለመሆን በምክንያት ማሰብ እና መወሰን ያሉባችሁ ተጨማሪ ጉዳዮች አሉ!


ወደ ዩኒቨርስቲ የምትገቡ እና በዩኒቨርስቲ እየተማራችሁ ያላችሁ ተማሪዎች ሁለቴ ማሰብ ስላሉባችሁ 4 ወሳኝ ጉዳዮች ከልምድ በመነሳት በምሳሌ አስረዳለሁ! ወጣቶች ትጠቀሙበታላችሁ ብዬ አምናለሁ......https://youtu.be/IlgmPrz8mh4
ኢትዮጵያ እዳ የመክፈል አዝማሚያ ተሻሽሏል (ከCC ወደ CCC+ አድጓል)! እዳ የመክፈል አቅም ከየት አገኘች? (S&P Credit Rating Report)!


ታዋቂው የእዳ ደረጃ አውጪው ተቋም S & P (Standard and Poor's) Credit Rating በታህሳስ 2016 ኢትዮጵያ ከነበረችበት CC በዚህ ሳምንት ወደ CCC+ እንደተሸጋገረች አሳውቋል (Reuters በዋና ዜናው አውጥቷል)!

S&P ኢትዮጵያ በቅርቡ የውጪ እዳ ከማይከፍሉ ተርታ (SD: Selective Default ምድብ) ልትወጣ እንደምትችል ገልጿል።

የኢትዮጵያ አዲሱን እዳ የመክፈል ደረጃ እና መሰረታዊ ምክንያቶች በዚህ ቪዲዮ ታገኛላችሁhttps://youtu.be/6kbWIl54EW4
#ለማስታወስ!

ኢትዮጵያ የውጪ ብድር ዕዳ መክፈል ያለመቻል አመክንዮ እና ስጋት ምንድን ነው? የተሰጣት የብድር መክፈል ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ቀጣይ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም አቀፉ የዕዳ ጫና ዝርዝር በሚያወጣው ፊች የተሰጣት ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም ሀገራት የውጪ ዕዳ የመክፈል አቅም ደረጃ (ከAAA እስከ D) እንዴት ይመደባሉ?

የኢትዮጵያ መንግስት የውጪ ዕዳ ባለመክፈል የሚፈጠርን ጫና ለመቋቋም ምን አይነት ተገማች እርምጃዎች ሊወስድ ይችላል?

በጥልቀት ያለውን ትንታኔ እና መረጃ ከሚከተለው https://youtu.be/OsbhuVpYosw ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ እና ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!
ኢትዮጵያ ውስጥ ደንበኛ የሆኑበት ባንክ ቢከስር ወይም ቢዘጋ የቆጠባችሁት ገንዘብ እንደሚመለስላችሁ ታውቃላችሁ?


እስከ 100ሺ ብር የቆጠቡበት ባንክ በሆነ ምክንያት ቢከስር ወይም ቢዘጋ 100% የቆጠቡት ገንዘብ በ90 ቀናት ውስጥ እንደሚመለስላችሁ ታውቃላችሁ? የዚህን መድን ዋስትና የሚሰጠው በብሄራዊ ባንክ ስር የተቋቋመው የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ነው (በ2016 ከ6.51ቢሊየን ብር በላይ ለዋስትና ሰብስቧል)።


ዘርዘር ያለ መረጃ አቅርቢያለሁ https://youtu.be/o-uFMRiM2ZE
ከፍተኛ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል (የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን)! በአገልግሎቶች ላይ ከ566% እስከ 75% የታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።


ከመጭው ሰኞ መስከረም 20/2017 ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። https://youtu.be/aX-ybBpHD4Y
#ለመረጃ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ዳርቻ የተገነባው ግዙፉ የለሚ ብሔራዊ ሲሚንቶ ፈብሪካ ዛሬ ተመርቆ በይፋ ሥራ ይጀምራል።

ይህ ፋብሪካ በ125 ቢሊየን ብር (2.2 ቢሊየን ዶላር) ወጪ በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ  ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ያስገነባው ሲሆን ፋብሪካው ተጠናቆ ዛሬ ሊመረቅ ነው።

ለሚ ሲሚኒቶ ፋብሪካ በቀን ከ10ሺ ቶን በላይ ሲሚንቶ የሚያመርት ሲሆን የኢትጵያን የሲሚንቶ ፍላጎት በሚገባ የሚሸፍን ይሆናል (If Other Things Remaining Constant)።
IMF በኢትዮጵያ ተገኝቶ በመጀመሪያ ውይይት 345 ሚሊየን ዶላር ፈቅዷል!


IMF ከሪፎርም በኋላ ለኢትዮጵያ ቃል የገባው የ3.4 ቢሊየን ዶላር የ4 ዓመት የብድር ስምምነት እንዳለ ይታወቃል። ይህ ቃል የተገባ ስምምነት በሂደት የተከናወኑ ተግባራትን እየገመገመ ብድሩን እንደሚለቀው ይታወቃል።

ስለሆነም ከሃምሌ ወር በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የደረሰበትን የሪፎርም ደረጃ ገምግሞ በቀጣይ ሳምንት ቃል ከገባው 10% (345 ሚሊየን ዶላር) ለመልቀቅ ማሰቡን ገልጿል።

የIMF ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ባደረገው ውይይት የሰጠውን 6 መሰረታዊ ነጥቦች ተከታተሉ.
https://youtu.be/_fRZNLBGNLM