መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ባይሆንም ውሳኔው ግን መጥፎ አይደለም!
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ
ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል።
ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል።
መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ ይከፈለዋል።
በውጭ አገራት ገንዘብ ግብይት መፈጸምም ሆነ በህገወጥ መንገድ ይዞ መገኘት አይቻልም።
ወርቅን በህገወጥ መልኩ ቤት ውስጥ ማከማቸት የማይቻል ሲሆን በህገወጥ መልኩ ወርቅን ያከማቸ ግለሰብ ለጠቆመ ግለሰብ ባንኩ በወቅቱ ባለው ግብይት የ15 በመቶ ወረታ ይከፈለዋል።
በህገወጥ የሃዋላ የውጭ አገራት የተሰማሩ አካላትን ለጠቆመም እስከ 25 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።
በህገወጥ ገንዘብ ህትመት የተሰማሩ አካላትን ያጋለጠም ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።
ጠቋሚዎች ወረታውና ሽልማቱ የሚበረከትላቸው #ደህንነታቸው እና #ሚስጥራዊነታቸው በተጠበቀ መልኩ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱ የገንዘብ፤ የወርቅ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለጠቆመ ወሮታ የሚያሰጠው መመሪያ ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው ስጋት ወይስ መፍትሄ?
ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ https://youtu.be/tEm4dopFmcs እስከመጨረሻው ተከታተሉት።

YouTube
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱ የገንዘብ፤ የወርቅ እና የውጪ ምንዛሬ መመሪያ ስጋት ወይስ መፍትሄ? National Bank of Ethiopia's new plan!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲሱ የገንዘብ፤ የወርቅ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ለጠቆመ ወሮታ የሚያሰጠው መመሪያ ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው ስጋት ወይስ መፍትሄ? እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
የዚህ ዓመት የመንግስት ኢኮኖሚያዊ ትኩረት የታክስ ገቢን ማሳደግ መሆኑን ገልጿል! ስለዚህ የኑሮ ጫናን በጊዚያዊነት ለማቃለል ለመንግስት ሰራተኞች በጊዚያዊነት የገቢ ግብር ቅናሽ ወይም የተወሰነ ወር የግብር እፎይታ ቢሰጥ ያልነው ምክረ ሃሳብ ተስፋ ያለው አይመስልም!
ኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ የመላክ ደረጃ ላይ ነች?
የምግብ የዋጋ ንረት ከፍተኛ በሆነበት ወቅት በሀገር ውስጥ ገበያ በቂ ያልሆነ ምርት ወደ ውጪ ሀገር ገበያ የሚላክበት ምከንያት ምንድን ነው? ለአንድ ሀገር የውጪ ንግድ ጉዳይ የተወሳሰበ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲኖረው ሊያስገድድ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች የኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ መነሳት ምክንያታዊነት ላይ ጥያቄ አላቸው! ይህን በተመለከተ የኢኮኖሚክስ አስተምሮት ሃሳብ፤ የሃገራት ልምድ እና የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ ባህሪ ላይ የሚከተለውን https://youtu.be/Dn09ffzDzfU ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉት፡፡

ኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ የመላክ ደረጃ ላይ ነች? Ethiopia will start exporting wheat!
የምግብ የዋጋ ንረት ከፍተኛ በሆነበት ወቅት በሀገር ውስጥ ገበያ በቂ ያልሆነ ምርት ወደ ውጪ ሀገር ገበያ የሚላክበት ምከንያት ምንድን ነው? ለአንድ ሀገር የውጪ ንግድ ጉዳይ የተወሳሰበ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲኖረው ሊያስገድድ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች የኢትዮጲያ ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ መነሳት ምክንያታዊነት ላይ ጥያቄ አላቸው! ይህን በተመለከተ የኢኮኖሚክስ አስተምሮት ሃሳብ፤ የሃገራት ልምድ…
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ሪፖርቱን አውጥቷል፡፡ የኑሮ ውድነትን መቋቋም በሚል ርዕስ የወጣው ሪፖርት የዓለም ኢኮኖሚ በከፍተኛ ዋጋ ንረት ሰበብ በዚህ ዓመት እንደሚቀንስ እና የኑሮ ጫና ለበርካታ የዓለም ያደጉም ያላደጉም ሃገራት መገለጫ እንደሚሆን አቅርቧል፡፡
የዓለም ኢኮኖሚ ከባለፈው ዓመት ዘንድሮ በእጥፍ እንደሚቀንስ (በ2021 ከነበረው የ6 ከመቶ እድገት በ2022 ወደ 3.2 ከመቶ እንደሚቀንስ አሳይቷል በተጨማሪም በቀጣይ ዓመት እድገቱ ወደ 2.7 ከመቶ ዝቅ ይላል ሲል ትንበያ ሰጥቷል)፡፡ ይህ የእድገት መቀነስ ላለፉት 20 ዓመታት ያልታየ ነው፡፡
የዓለም ዋጋ ንረት አምና ከነበረበት የ4.7 ከመቶ ደረጃ በዚህ ዓመት ወደ 8.8 ከመቶ ያደገ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ውስን ቅናሽ በማሳየት 6.5 ከመቶ ሊሆን ይችላል ብሏል፡፡
የኢትዮጲያ ጠቅላላ ምርት በ2022 በ3.8 ከመቶ ሊያድግ የሚችል ሲሆን በ2023 እድገቱ ወደ 5.3 ከፍ ሊል ይችላል ሲል ትንበያ ሰጥቷል፡፡ የዋጋ ንረት አሁን ካለበት የ33.6 ከመቶ በቀጣይ ዓመት ወደ 28.6 ከመቶ ዝቅ ሊል ይችላል የሚል ተስፋ ሰጪ ትንበያ ሰጥቷል፡፡
#ለምሳሌ፡- መንግስት የዋጋ ንረቱን ዘንድሮ በ25 ከመቶ እቀንሰዋለሁ የሚል እቅድ አስቀምጦ ተጋኗል ስንል የነበረውን IMF በትንበያው ዘንድሮ መጨረሻ የኢትዮጲያ የዋጋ ንረት ቢያንስ በ5 ከመቶ መቀነስ ሊኖር ይችላል ብሏል፡፡
የዓለም ኢኮኖሚ እና የዜጎች የኑሮ ጫና እንዲሻሻል የዓለም ሀገራት የገንዘብ ፖሊሲን ማስተካከል፤ የፊስካል ፖሊሲን ማስተካከል እንዲሁም ምርታማነትን ማሳደግ እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ማስተካከል የሚችሉ ስትራክቸራል ስራዎችን መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የ2022 የኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚ ይፋ ሆኗል፡፡ የኖቤል ሽልማት ከ1901 ጀምሮ በኬሚስትሪ፤ በስነ-ጽሁፍ፤ በሰላም፤ በፊዚክስ፤ በህክምና ዘርፎች ላይ ሽልማት ሲሰጥ ቆይቶ ከ1968 ጀምሮ ኢኮኖሚክስን አካቷል፡፡ ከ1969 ጀምሮ እስካሁን 54 ጊዜ የኢኮኖሚክስ የኖቤል ሽልማት ሲሰጥ 92 ግለሰቦች በተናጥል እና በጋራ ተሸልመዋል፡፡
የዘንድሮ አሸናፊዎች Ben S. Bernanke፤ Douglas W. Diamond እና Philip H. Dybvig (ሶስቱም አሜሪካዊያን ኢኮኖሚስቶች ናቸው) ባንኮች በኢኮኖሚው ውስጥ ስላላቸው ሚና በተለይ የፋይናንስ ቀውስ በሚከሰትበት ወቅት የባንኮች ሚና ምን እንደሚመስል በሚያሳየው ጥናታቸው “for research on banks and financial crises” ነው።
ጥናቱን ላለፉት ከ30 ዓመታት በላይ በተናጥል ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን በፋይናንስ ቀውስ ወቅት ባንኮች እንዴት እንደሚጎዱ እና የባንኮች ውድቀት የፋይናንስ ቀውሶችን እንዴት እንደሚያባብስ አብራርተዋል፡፡
በተለያየ አጋጣሚ ሰዎች ገንዘባቸውን በባንክ ያስቀምጣሉ በተመሳሳይ በፈለጉ ጊዜ ለማውጣት ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ይህንን የቆጣቢዎች ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ ባንኮች ቆጣቢዎች ገንዘባቸውን በፈለጉ ጊዜ እንዲወስዱ የማስቻል እና የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ብድር የማቅረብ ስራን አቻችለው ሊሰሩ የሚችሉበትን ዘዴ ጠቁመዋል፡፡
#ለምሳሌ፡- በእኛ ሀገር ባንኮች ቆጣቢዎች ብራቸውን በሰፊ የማውጣት ፍላጎት ቢያሳዩ የመክፈል አቅም አላቸው? "ትንሽ ቆዩ! " እና "ከዚህ ብር በላይ ማውጣት አይቻልም! " የሚሉ ክልከላዎች በባንኮች እና በቆጣቢ ደንበኞች መካከል ቅሬታ ሲፈጥሩ አትመለከቱም?
ያቀረቡት ጥናት የሚያጠነጥነው የቆጣቢዎችን ከፍተኛ ፍላጎት ለማርካት እና የብድር አቅርቦትን ላለመቀነስ ሲባል ባንኮች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የመውደቅ አደጋ ይፈጠርባቸዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ለመቋቋም የመንግስት (ብሄራዊ ባንክ) የተቀማጭ ካፒታል ዋስትና ማሳደግ ወይም ባንኮች የመጨረሻ አማራጫቸው ያላቸውን ካፒታል አበዳሪ ብቻ ሆነው እንዲቆዩ ሊያስገድድ ይችላል፡፡ የዚህ አይነት አደጋን ለመቀነስ ባንኮች አዋጪ የሆኑ የብድር ጥያቄዎችን/ኢንቨስትመንቶችን የመለየት አቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡
በኢኮኖሚክስ የኖቤል ተሸላሚን ለመለየት ሂደቱ በመስከረም ወር የእጭዎች ዝርዝር መሙያ ፎርም ይበተናል (እስከ 3ሺ ፎርም ይበተናል) እና ለስድስት ወር ሰዎች እና ተቋማት በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ያሸልማል ያሉትን ስራ እያቀረቡ እጩ መለያ ይሆናል፤ መጋቢት ወር የተመረጡ እጭዎችን (እስከ 250-350 እጩ ይለያል) የማሳወቅ ስራ ይሰራል፤ በነሃሴ ስለተመረጡ እጭዎች ዝርዝር ይጻፋል፤ በመስከረም የመጨረሻ እጭዎችን ይለያሉ፤ በጥቅምት ወር አሸናፊ ይለያል እንዲሁም በታህሳስ ወር ዳጎስ ያለ ሽልማት ይሰጣል፡፡

ጥሩ እርምጃ!
38 አይነት ምርቶች ኤል ሲ ተከፍቶላቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በጊዚያዊነት ታገዱ!
በተደጋጋሚ የዚህ አይነት ውሳኔ ኢኮኖሚው (ብሄራዊ ባንክ) እንደሚያስፈልገው ሲገለጽ ቆይቷል! ስለዚህ ብሄራዊ ባንክ ዘግይቶም ቢሆን ወስኗል ሙሉ ለሙሉ መልካም የሚባል የኢኮኖሚ ውሳኔ የለም በብዙ መለያ ግን ይህ ውሳኔ ጥሩ ጎኑ የሚያመዝን ውሳኔ ነው፡፡
እገዳ የተጣለባቸው መጠጦች (ውስኪ ወይም ቢራ እና ሌሎች አልኮል መጠጦች)፣ ማስቲካ፣ ቸኮሌት፣ ውሃ፣ ሲጋራ፣ ሰው ሰራሽ ማጌጫዎችና መሰል ቁሳቁስ ሲሆኑ በግለሰቦች ኤል ሲ ተከፍቶባቸው የሚገቡ መኪናዎችንም እገዳው ይመለከታል ።
በምርቶቹ ላይ እገዳ የተጣለው ቁሳቁሶቹ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆነው ስላልተገኙና የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ገቢ እቃዎች በቂ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

የቁሳቁስ ከውጪ እንዳይገባ ክልከላ ሲደረግ ቀድመው በሀገር ውስጥ ገብተው የነበሩ አሁን ላይ የተከለከሉ ቁሶች የመሸሸግ እጣም ሆነ ዋጋቸው ከፍተኛ መሆኑ አይቀርም እንዲሁም በቀጣይ ወራት ምርቶቹ ወደ ጥቁር ገበያ እና ኮንትሮባንድ ስርዓት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ!
ነገር ግን የክልከላ ዓላም ምርቱን ከሀገር ውስጥ ገበያ በተዘዋዋሪ ማጥፋት ስለሆነ በአጭር ወራት ገበያው ከሸቀጦች ዝርዝር በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የተከለከሉ ቁሶችን ጭራሽ ባይሆንም በብዛት ስለሚያስወጣቸው ቅስፈታዊ የዋጋ መጨመሮች በሂደት መስተካከላቸው አይቀርም።

መንግስት 38 ምርቶች ከውጪ እንዳይገቡ እገዳ መጣሉ ለኢኮኖሚው ምን ፋይዳ አለው? የምርቶች ከውጪ እንዳይገቡ መታገድ በጥቁር ገበያ ዋጋ፤ በዋጋ ንረት እና በጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተጽኖ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚዳስስ https://youtu.be/tfV5HsQLBRM ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
YouTube
ምርቶች ከውጪ እንዳይገቡ እገዳ መጣሉ ለኢኮኖሚው ምን ፋይዳ አለው? Import Restriction in Ethiopia
የምርቶች ከውጪ እንዳይገቡ መታገድ በጥቁር ገበያ ዋጋ፤ በዋጋ ንረት እና በጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተጽኖ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚዳስስ ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት
ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ችግር መፍትሄ ሰፊውን ድርሻ የሚወስደው ፖለቲካው ፈጣን መልስ ካልሰጠ ችግሮች ልምድ እየሆኑ ይመጣሉ ባይ ነኝ! https://www.youtube.com/watch?v=Z3qi4oGd5Fc
መኪና ከውጪ እንዳይገባ መከልከሉ ፍታዊ የሚሆነው በመንግስት ተቋማት የሚታዩ በጣም #ውድ_መኪኖችም መግባት ሲያቆሙ ነው!
ፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔ ቢሆንም ላለው አነስተኛ ጥቅም ሲባል የሚተገበረው ለምን ይመስላችኋል?
ብሄራዊ ባንክ በቅርቡ የፍራንኮቫሉታ በጥቁር ገበያው ላይ እየፈጠረ ያለውን አደጋ በመረዳት በፍራንኮቫሉታ ቁሶችን ከውጪ ለማስገባት የባንክ ስቴትመንት መስፈርት የመደረግ አዝማሚያ እንዳለው ገልጿል።
ነገር ግን ፍራንኮቫሉታ የጎላ ጉዳት ቢኖረውም ውሳኔው ለኢኮኖሚው በተለይ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ጥቅም አለው በሚል እሳቤ ቀጥሏል! ታዲያ የሚታይ ጉዳት ያለው የፍራንኮ ቫሉታ ውሳኔ እንዲቀጥል የሚደረግበት መሰረታዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ይህንን ቪዲዮ https://youtu.be/xUb-q2QzJBs ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ውሳኔ.......! The impact of Franco Valuta in Ethiopia!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለሚጠቁሙ ወሮታ የሚከፈልበትን መመሪያ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በቅርቡ ብሄራዊ ባንክ 4 ህገወጥ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲያደርግና ጥቆማ ለሚያደርጉ ዜጎችም #ወሮታ እንደሚከፍል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ከተፈቀደ በላይ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ ማከማቸት፤
2. ሀሰተኛ የገንዘብ ህትመት መፈፀም፤
3. የወርቅ ክምችት፤
4. ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያለፈቃድ ማስተላለፍ በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ዜጎች ጥቆማ እንዲሰጡ እና ዜጎች ለሚሰጡት ጥቆማ ወሮታ እንደሚከፈላቸው ገልጾ ነበር።
- በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣
- የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣
- ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ይከፈላቸዋል።
ለግለሰቦች በቀን ከ100 ሺህ ብር በላይ መያዝ፣ ለተቋማትም በቀን ከ200 ሺህ ብር በላይ መያዝ የተከለከለ ነው።
ይህን መመሪያ የተላለፈን ግለሰብ ወይም ተቋም ለጠቆመ #ምስጢራዊነቱን በተጠበቀ መልኩ ወሮታው ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል።
ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ በከባድ የኢኮኖሚ ወንጀል እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ነው የተመላከተው።
ጠቋሚዎች በስልክ ቁጥር 0118133960፣ በኢ.ሜል አድራሻ tikoma@nbe.et፣ በፋክስ ቁጥር 0115514366 እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፖ.ሣ.ቁጥር 5550 ላይ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።