የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ጥቅም ወይስ ጉዳት/The effect of currency devaluation።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ (Devaluation) በጣም ጠቅሞናል! ይህንን ጉዳይ ለኢኮኖሚስቶች ካልሆነ በስተቀር ለመረዳት አዳጋች ነው! ስላሉት ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥቸበታለሁ፡፡
የብር የመግዛት አቅም መዳከሙ እድል ብቻ ሳይሆን ጉዳትም ይዞ መጥቷል ይህንን በምሳሌ በማነጻጸር የሚከተለውን ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
https://youtu.be/I-dH9SkOEvo

YouTube
የገንዘብ አቅም መዳከም ጥቅም እና ጉዳት/The effect of money devaluation
በኢኮኖሚያዊ ውሳኔ ጥቅም ብቻ ያለው ውሳኔ የለም! ጉዳዩ የፖሊሲው ውሳኔ በአመዛኙ ወዴት ይሄዳል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ በሀገራችን የገንዘብ የመግዛት አቅም እንዲዳከም በመደረጉ በተቃራኒው በጣም ተጠቃሚ ሆነናል! ሲሉ ለምክር ቤት አቅርበዋል።
ይህንን ጉዳይ ኢኮኖሚስቶች ካልሆኑ በስተቀር ለመረዳት አይቻልም! ስላሉት የDevaluation ጥቅም እና ጉዳት በምሳሌ ለማስረዳት ይህንን አስተማሪ…

አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
1.3 MB
Source AA mayor office
በኪራይ ቤት በመኖር እና በግል ቤት በመኖር መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልዩነት ምንድን ነው? አዲስ አበባ ውስጥ ተከራይ መሆን ለምን አስቸጋሪ እንደሆነ በመረጃ ተመልከቱ።
#ለምሳሌ፦ ተከታይቶ መኖር ከቤት ባለቤቶች ጋር ሲነፃፀር 3.5 እጥፍ ድሃ የመሆን እድል አለው!
ከዚህ ቀደም የሰራሁትን ጥሩ ጥናት አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
https://youtu.be/6Ad857-0wYk

ተከራይ መሆን የቤት ባለቤት ከመሆን አንፃር በ3.5 እጥፍ ድሃ ያደርጋል!
በኪራይ ቤት በመኖር እና በግል ቤት በመኖር መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልዩነት ምንድን ነው? አዲስ አበባ ውስጥ ተከራይ መሆን ለምን አስቸጋሪ እንደሆነ በመረጃ ተመልከቱ። ከዚህ ቀደም ለማስተርስ መመረቂያ የሰራሁትን ጥሩ ጥናት አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት። The Impact of Living in the Rented House on Household Welfare.
በሀገራችን ወጥ የሆነ የኢኮኖሚክስ ኮርሶች ናቸው የሚሰጡት? እስቲ በተማራችሁበት እና እየተማራችሁ ባላችሁበት የግልም ሆነ የመንግስት ኮሌጅም ሆነ ዩኒቨርስቲ በድግሪም ሆነ በማስተርስ የሚሰጡትን የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት ኮርሶች ፃፏቸው።
እኛ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ ስንማር ከተለመዱት በተጨማሪ
Economics of Marketing, Economics of Industry, Economics of Infrastructure, Public Finance, Financial Economics, Microfinance,
#Health_Economics, Monetary Economics, Labor Economics, Economics of Agriculture, Population Economics...እና ብዙ ሌሎች ነበሩ። የሌሎቻችሁስ?
ብዙዎቻችሁ ከምትገልጿቸው ከተመሳሳዬቹ ውጪ ያሉት
Economics for management, Business Economics, Engineering Economics, Behavioural and Institutional Economics, Energy Economics, Production Economics, Enterprenurship, Tourism Economics......ሁሉም ጋር የሚሰጡ የኢኮኖሚክስ ትምህርቶች አይመስሉም!
#ለምሳሌ፦ እኔ ድግሪ ላይ ከላይ የተጠቀሱ ኮርሶችን አልወሰድኩም!

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ከንቲባ_አዳነች፦ "አዲስ እየተገነባ ያለ ህገወጥ ቤት ተመልክተን ይፍረስ ስንል ገንቢው የፍርድ ቤት እግድ አሳየን! ቤቱ ከመገንባቱ በፊት በባዶ ቦታ ላይ ልክ ቤት እንዳለው አስመስለው የፍርድ ቤት እግድ በማስወጣት ግንባታ የሚያደርጉ ሰዎች አሉ"።
በለው!!! ሙስና እንደዚህ #ተቋማዊ ሲሆን መፍትሄው ሙስናን መጠየፍ ከሚል መፈክር በላይ መሆን እንዳለበት ይሰማሃል።

#በጣም_ይገርማል!
ከብዙ ዩኒቨርስቲ ከ100 በላይ ሰዎች በትምህርት ዘመናቸው የወሰዷቸውን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ኮርሶች የላኩትን ስመለከት በሀገራችን ባሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በየዓመቱ የሚመረቁ የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች የተለያየ ኮርስ ወስደው ነው።
ጥሩ ኢኮኖሚስት መፍጠር መቻል አንድ ጉዳይ ሆኖ ነገር ግን በቀላሉ በአንድ ሀገር ውስጥ ኢኮኖሚክስን ለማወቅ ተመሳሳይ ትምህርት እንኳን መማር ግድ ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሚመራውም ሆነ ትምህርት ሚኒስትር ይህንን ጉዳይ ቢፈትሹት መጥፎ አይደለም!

ብዙዎቻችን የተማርንበትን ዩኒቨርሲቲ አንመስልም! ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ ላይ ካላቸው ተጽዕኖ በላይ ተማሪው ራሱ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ከባድ ነው።
https://youtu.be/dEkkFrQb22c
https://youtu.be/dEkkFrQb22c
YouTube
ብዙዎቻችን የተማርንበትን ዩኒቨርሲቲ አንመስልም!
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ ላይ ካላቸው ተጽዕኖ በላይ ተማሪው ራሱ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ከባድ ነው።
#ዩኒቨርስቲው_ወይስ_ተማሪው?፦ አንዳንዶች ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርስቲ የሚያወዳድሩት #ግሬድ በቀላሉ ይሰጣል ወይም አይሰጥም.....
ጥቂቶች በዩኒቨርሲቲው የተሟላ ቤተ-መፅሃፍ መኖርን፤ በቂ መፅሃፍት መኖራቸውን፤ የተሟላ የኮምፒውተር እና የሳይንስ ላብራቶሪ መኖርን.....
አንዳንዶች ዩኒቨርስቲው አዲስ የተከፈተ መሆኑን፤ በዩኒቨርሲቲው የመምህራን አቅም እና ቅጥር አካባቢያዊ መሆንን.....ወዘተ ነው።
እዚህ ሀገር ጥሩ ነጥብ ያመጣ ጎበዝ ተማሪ ህንድ እና ቻይና ሃገር ተጨማሪ ከፍተኛ ትምህርት ተምሮ ሲመጣ "ደሞ ህንድ! ደሞ ቻይና!" ብለው የሰውየውን ጉብዝና ረስተው የሚተቹም አታጡም! "እገሌ ዶክተር ነው! ግን የራሽያ እና የኩባ ነው" የሚል ማጣጣል ሰምታችሁ አታውቁም?
በበለፀጉ ሀገራት ተምሮ መጥቶም ደካማ አታጡም! ጋና ተምሮ መጥቶም ጎበዝ አታጡም (ዴንማርክ መማርም ሆነ ጋና መማር ተማሪው በሚኖረው የ2 እና የ3 ዓመት ቆይታ ውስጥ ያለ ተማሪው የራስ ጥረት እሴት ላይጨምሩበት ይችላሉ)።
ስኮላርሽፕ አግኝተው አውሮፓም ሆነ እስያ የተማሩ የማውቃቸው ሰዎች ጋር ስናወራ ከቻይና/ከህንድ ይልቅ አውሮፓ መማር የሚመርጡት አውሮፓ ውስጥ በየወሩ የሚሰጠውን የኪስ ገንዘብ፤ አውሮፓ ውስጥ የትርፍ ጊዜ ስራዎች መኖር እና ክፍያው ሃሪፍ መሆኑ፤ የአውሮፓ ከተማ ለመጎብኘት እንጂ #የመጀመሪያው ምክንያት የአውሮፓ ትምህርት ከቻይና/ከህንድ ትምህርት በጥራት ይበልጣል ብለው ስላወዳደሩ አይደለም።
በርግጥ በዓለም ላይ ጥራት ያለው ተማሪ በመቀበል ጥራት ያለው ተማሪ የሚያወጡ ባወጡትም ተማሪ የሚኮሩ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ ሃርቫርድ፤ MIT፤ ኦክስፎርድ፤ ወዘተ በኩራት እኛ ጋር የተማረው እገሌ የሀገር መሪ ሆነ ይላሉ።
#ለምሳሌ፦ ጥሩ በሚባሉት አስተማሪዎች ባሉበት ዩኒቨርሲቲ በበቂ አይቷቸውም ሰምቷቸውም የማያውቀውም፤ በበቂ መፅሃፍ የተሞላ ላይበራሪ እያለ አንድም ቀን ብቅ ብሎ ያላነበበውም፤ ኮርጆ ሴሚስተር የሚያልፈውም፤ ወዘተ እዚህ ዩኒቨርሲቲ በመማሬ እኮራለሁ ይልሃል።
ሌሎች በየዩኒቨርሲቲው ያለውን ትንሽም መፅሃፍ፤ ላብራቶሪ፤ ኢንተርኔት፤ አስተማሪዎች፤ የተሻሉ ጎበዝ ተማሪዎች እንዲሁም ሙሉ ጊዚያቸውን ለትምህርታቸው በመጠቀም ድንቅ ተማሪ ይሆናሉ። ነገር ግን የተማርከው እኮ "እንትን ዩኒቨርሲቲ" በመሆኑ ደካማ መባል አይችልም።
#ለምሳሌ፦ ድሮ ከሀረር በዩኒቨርስቲው የተበታተንን ተማሪዎች በክረምት ተመልሰን ስንገናኝ "እንትን ዩኒቨርሲቲ የገባ ተማሪ አይደለም አህያ እንኳን ትመረቃለች፤ እንትን ዩኒቨርሲቲ የገባ ተማሪ መንገድ ሲያቋርጥ መኪና ካልገጨው በስተቀር ሳይመረቅ አይቀርም"፤ ወዘተ የሚል መፈራረጅ ነበር።
ጥሩ መፅሃፍ ከአጥኚ ጋር ካልተገናኘ ዋጋ አለው? ጎበዝ አስተማሪ ለማወቅ የሚጥር ተማሪ ከሌለ ዋጋ አለው?
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጥረቱ አንደኛ የወጣ ተማሪ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ገብቶ ቢሆን ኖሮ በደረጃ ላይወጣ ነው? (ልዩነቱ አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች ከመለያየታቸው ብቻ የሚመጣ ነው)፤ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በጥረቱ የሰቀለ ተማሪ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተፎካካሪ ላይሆን ነው?
ነጥብ የእውቀት ብቸኛው መለኪያ አይደለም! ነገር ግን ለብዙዎች (ቀጣሪ መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ) መመረቂያ ነጥብ የእውቀት መለኪያ በመሆኑ ግሬድን ፍታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ እና የማይሞክሩ የዩኒቨርሲቲ አባላት በሰዎች አይምሮ ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎቹ ደረጃ እንዲወጣላቸው ያደርጋሉ።
የትምህርት መርህን ጥሰው በቀላል መመዘኛ ትልልቅ ነጥብ በሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ የተማረም ሆነ ነጥብ በፉክክር እና በፍትሐዊነት መሰጠት አለበት በሚል ዩኒቨርሲቲ የተማረም ተማሪ እራሱን እንጂ ዩኒቨርሲቲውን ሙሉ ለሙሉ አይወክልም።
በርግጥ ኢፍትሃዊነት ባለበት ዩኒቨርሲቲ 4 ነጥብ ያመጣ እና ፍትሃዊነት ባለበት ዩኒቨርሲቲ 3 ነጥብ ያመጣ ተማሪ ተመሳሳይ ጥረት የእውቀት ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ።
አንድ ወዳጄ ሲነግረኝ ስራ ለመቅጠር ብዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው የተነሳ (4 ነጥብ ያላቸው በጣም ብዙ ተማሪዎች አመልክተው ነበር አለኝ!) አሰራሩ ባይፈቅድም በውስጥ ለመለየት ያህል የነባር ዩኒቨርሲቲ 3.2 ነጥብ ያመጣ ተማሪን እና የአዳዲሶቹን ዩኒቨርሲቲዎች 4 ነጥብ ያመጣ ተማሪን አቻ እናደርግ ነበር ይለኝ ነበር።
ዩኒቨርስቲ የሚለካው በነጥብ ፍትሃዊነት አሰራሩ እና በፋሲሊቲው እንጂ በተማሪው የግል ስንፍናም ሆነ ተማሪው በእድሜው ባከማቸው እውቀት ዩኒቨርስቲው ሊለካ አይችልም።
የተወሰኑ የትምህርት መስክ የሚማሩ ተማሪዎች አቅሞቻቸው ከዩኒቨርሲቲው ጋር ቀጥተኛ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። #ለምሳሌ፦ ህክምና ሳይንስ፤ ኢንጂነሪንግ፤ ኮምፕዩተር ሳይንስ፤ ግብርና፤ ወዘተ። በዋናነት እኔ የማወራው ስለ ማህበራዊ ሳይንስ በተለይ ደግሞ ስለኢኮኖሚክስ ዘርፍ ነው።
የውይይት መነሻ ሃሳብ ነው! ውይይት ክርክር መለማመድ አለብን!

ኢኮኖሚክስን የማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የሚያስመድበው ዋናው ምክንያት ኢኮኖሚክስ የሰዎችን ባህሪ/Behaviour ስለሚያጠና ነው። የሰዎች ባህሪ ደግሞ ተገማች ያልሆነ እና የማያልቅ ነው።
#ለምሳሌ፦ በሳይንስ ረገድ አለም በብዙ መለኪያ ወደመስማማት ተቃርቧል! አውሮፕላን ከተፈጠረ በኋላ መሰረታዊው የአውሮፕላን አመራረት እና አበራረር ተጠንቶ አልቋል፤ የኮምፒውተር አሰራር አዲስ ባህሪ ሊፈጥር አይችልም፤ በሽታዎች እና መድሃኒቶች ዙሪያ የተደረሰበት ምርምር ደረጃው ይታወቃል፤ መኪና መሰረታዊ አሰራሩ ተመሳሳይ ነው፤ የሂሳብ ቀመሮች በፍጥነት የሚለዋወጡ አይደሉም፤ የGPS ፈጠራም አጠቃቀምም ተበርብሩ የተደረሰበት ነው፤ ወዘተ። ነገር ግን ኢኮኖሚክስ ላይ ያለ ክስተትም ሆነ መፍትሄ ተበርብሮ ያለቀም ተገማችም አይደለም!
#ለምሳሌ፦ ሰዎች ለዋጋ ያላቸው ውሳኔ፤ ሰዎች ለጥራት ያላቸው ውሳኔ፤ ሰዎች የኢንቨስትመንት ውሳኔ ለማድረግ ያላቸው ውሳኔ፤ ሰዎች የቤተሰብ ቁጥርን ለመወሰን ያላቸው ውሳኔ፤ ወዘተ ቁርጥ ያለ መልስ የለውም!
አለም አርማታ ለመስራት ምን ያህል አሸዋ እና ምን ያህል ሲሚንቶ መደረግ እንዳለበት የተስማማበትን ቀመር ያህል ሀገራት በኢኮኖሚ ለማደግ ማድረግ ስለሚኖርባቸው ዘዴ አልተስማማም።
በድርድርም ሆነ በቁርጥ ዋጋ ለመሸመት የተዘጋጀ ሸማች የውሳኔውን እርግጠኝነት ከግምት የዘለለ አያውቅም ወይም ሻጭ በድርድር ለሚሸጠው ዋጋ ማረፊያ ዋጋውን ከህሊናው ጋር ወስኖ አይጨርስም።
ሸማች የተጠራለትን ዋጋ የሚቀበለው እንደሸማቹ ገቢ፤ መረጃ እና ፍላጎት ነው፤ ሻጭ ይዞ ለወጣው ቁስም ሆነ አገልግሎት ዋጋ የሚወስነው እንደጥሬ እቃው ተገማች ዋጋ፤ እንደ ሸማች አቅም/ጉጉት፤ ሻጭ በፍጥነት ለማደግ ካለው ጉጉት፤ እንደ በገበያው ያለው የሌሎች ቁሶች እና አገልግሎት ዋጋ፤ ወዘተ ተመርኩዞ ነው።
አለም የማይመልሰው ይህ ከላይ የዘረዘርኳቸው የሸማችም ሆነ የሻጭ ምክንያቶች እንደ አለም ህዝብ ቁጥር ብዙ በመሆኑ ተመሳሳይ ቀመር የለውም።
ኢኮኖሚክስ የግራፎ እና የGDP ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሸማች ውሳኔ አሰጣጥም ጥናት ነው።

ሰፋ ባለ መልኩ የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ትንታኔ ለማግኘት ይህንን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://youtu.be/v1kao07I_aU
https://youtu.be/v1kao07I_aU
YouTube
ስለ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በጥልቀት ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው በሙሉ የተከፈተ ቻናል!
If you are passionate about Economics, This page is for you!
The leading source of economic analysis!
Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
Telegram:- https://t.me/wasealpha

የገበያ መረጃ እስከሌለ ድረስ ሻጭን #እባክህ ብሎ ለምኖ እና ተለማምጦ ዋጋ ማስቀነስ የሸመታ ታክቲክ እንጂ የክብር ጉዳይ አይደለም!
በኢኮኖሚክስ መርህ የሸማች ግብ ካለው ገቢ ላይ ዝቅተኛውን ወጪ በማውጣት የመጨረሻ አነስተኛ በሚለው ዋጋ የሚፈልገውን መጠን ያህል ሸምቶ ፍላጎቱን ማርካት ነው (Utility Maximization)።
የሻጭ ግብ ከፍተኛ በሚለው ዋጋ የሚፈልገውን ያህል መጠን ሸጦ የትርፍ መጠኑን ማሳደግ ነው (Profit Maximization)።
ሸማች ሻጭ ቢወርድ ዝቅተኛ የሚለው የትርፍ መጠን (Profit Margin) ላይ ለመቆም እንጂ ከስሮ ለመሸጥ አለመሆኑን ያውቃል። ነገር ግን የሻጭ የመጨረሻ የትርፍ ጣሪያን ስለማያውቅ ጥልቅ ድርድር ለማድረግ ቢወስን የእርካታ/Utility ግቡን ለማሳካት ነው።
#ለምሳሌ፦ አንዳንድ ሰዎች "ስኬታማ ከመሆኔ በፊት የማልፈልገውን ስራ ሳይቀር ሳልጠየፍ የማልመው ግቤ ላይ ለመድረስ ሰርቻለው" ሲሉ ይሰማሉ። ስኬት ላይ ከደረሱ በኋላ ያለፉት ሂደት ለትችት አይቀርብም።
ስለዚህ ሸማች ካለው ገቢ አንፃር የሚፈልገውን መጠን በዝቅተኛ ዋጋ ለመሸመት የሚሸምተው ነገር ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋው ድረስ የቱንም የድርድር እና ዋጋ የማስቀነስ (እባክህ ቀንስ ብሎ መለመንን ጨምሮ) ስልት ቢጠቀም የሸመታ ግቡን በማሳካት እርካታ ላይ (Utility Maximization) ለመድረስ ስላደረገው ሎጂካል ነው።

ሙስና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ያለ ገንዘብ ማግኘትን ከባድ ከማድረጉም በላይ የሃገር እና የህዝብ ሃብት በጥቂቶች እጅ እንዲከማች እያደረገ ነው!
https://www.youtube.com/watch?v=VFQLyK2Y5h4
https://www.youtube.com/watch?v=VFQLyK2Y5h4
YouTube
#Shorts ሙስና ጥቂቶች የብዙሃንን ሃብትእንዲያከማቹ ያደርጋል!
#Shorts ሙስና ሰዎች አገልግሎቶችን በገንዘባቸው እንዲገዙ እያደረገ ነው።
ሲጃራ ማጨስ ለጤና እንደሚጎዳ በሲጃራ ማሸጊያ ላይ እንዲለጠፍ እያስገደድክ ብቸኛ የሲጃራ ፋብሪካህን የማትዘጋበት እንቆቅልሽ #ኢኮኖሚክስ ይባላል!
አዲስ እና ጥሩ የጥናት ርዕስ ለማግኘት ለተቸገራችሁ ሰዎች በዚህ ወቅት ብትሰሩባቸው ጥሩ እና በብዛት ያልተሰሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ 10 ርዕሶችን ልጠቁማችሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
https://youtu.be/lSK51l3_pLw
https://youtu.be/lSK51l3_pLw
YouTube
10 ምርጥ እና አዲስ የጥናት ርዕሶች (10 Best research titles)
አዲስ እና ጥሩ የጥናት ርዕስ ለማግኘት ለተቸገራችሁ ሰዎች በዚህ ወቅት ብትሰሩባቸው ጥሩ እና በብዛት ያልተሰሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ 10 ርዕሶችን ልጠቁማችሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
ሰፋ ባለ መልኩ የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ትንታኔ ለማግኘት ይህንን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://youtu.be/v1kao07I_aU
https://youtu.be/v1kao07I_aU
YouTube
ስለ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በጥልቀት ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው በሙሉ የተከፈተ ቻናል!
If you are passionate about Economics, This page is for you!
The leading source of economic analysis!
Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
Telegram:- https://t.me/wasealpha
The leading source of economic analysis!
Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
Telegram:- https://t.me/wasealpha
የኢትዮጲያ ጠቅላላ ምርት/GDP በ111.27 ቢሊየን ዶላር ከሰሃራ በታች ሶስተኛው ትልቁ ነው! ነገር ግን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚው በምግብም ሆነ ከምግብ ውጪ በሆነ የድህነት መለኪያ (የፀጥታ እና የደህንነት ዋስትናን ጨምሮ) ባለብዙ ጉድለቶች ነው።
ዓለም አቀፍ የገቢ ልዩነቶችን እንመልከት.....
1. ዝቅተኛ ገቢ/Low income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ1,046ዶላር በታች የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ 54ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር 4,500 ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
2. ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ/Lower-middle income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ1,046 እስከ 4,095ዶላር መካከል የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ54ሺ ብር እስከ 212ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ4,500 ብር እስከ 17ሺ ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
3. ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ/ Upper-middle income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ4,095 እስከ 12,695 ዶላር መካከል የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ212ሺ ብር እስከ 660ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ17ሺ ብር እስከ 55ሺ ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
4. ከፍተኛ ገቢ/ High income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ12,695 ዶላር በላይ የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ660ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ55ሺ ብር በላይ የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
#ጥያቄ፦ ኢትዮጵያ #ዝቅተኛ ወይስ #ዝቅተኛ_መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ነች?
#ለምሳሌ፡- በኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ በመንግስት ሪፖርት 1,212ዶላር (ማለትም #ዝቅተኛ_መካከለኛ_ገቢ ደረጃ) ሲሆን በአለም ባንክ ግምት(የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ 117 ሚሊዮን ቢደርስ የሚለው ግምት ተሰርቶ) በኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 960 ዶላር (ማለትም #ዝቅተኛ_ገቢ ደረጃ) መሆኑን ያሳያል እንዲሁም የአለም ባንክ ኢትዮጲያ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ የመሰለፍ ውጥን አላት ይላል (በቅርቡ መንግስት ባወጣው መረጃ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ደርሰናል ብሏል)፡፡
የነፍስ ወከፍ ገቢ የሚሰላው ኢኮኖሚው በዓመት ውስጥ ካንቀሳቀሰው ጠቅላላ ሃብት (GDP) ለጠቅላላ ህዝቡ ሲካፈል የሚመጣው ቁጥር ቢሆንም የመጣው ስሌት ለሁሉም ሰው ይደርሰዋል ማለት አይደለም! የነፍስ ወከፍ ገቢው ትልቅ ሆኖ ጥቂቶች ሃብታም ሆነው ብዙዎች ድሃ የሆኑበት ኢኮኖሚ ሊኖር ይችላል፡፡
የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን የኢኮኖሚ እድገትን በቀጥታ አያሳይም! ምክንያታዊ የሃብት ክፍፍልን አያመለክትም። በነገራችን ላይ የገቢ ደረጃ መጠን በየአመቱ ይከለሳል። ከላይ የተጠቀሰው ደረጃ በ2021 መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው።
#ለምሳሌ፦ ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ /Upper-middle income የሚለውን ብንመለከት በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ4,095 እስከ 12,695 ዶላር ቢያገኝ (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ212ሺ ብር እስከ 660ሺ ብር) በሚለው መነሻ እና ከፍተኛው መካከል የ8ሺ ዶላር ወይም የ400ሺ ብር ልዩነት አለ።
ስለዚህ የአለም ባንክ እንደሚለው ሀገራት የተለያየ መጠንን ይጠቀማሉ። የአውሮፓ ሀገራት መካከለኛ ገቢ እና የአፍሪካ ሀገራት መካከለኛ ገቢ ወሰን ሊለያይ ይችላል። (በአውሮፓ መለኪያ ድሃ ሰው በአፍሪካ መለኪያ ሃብታም ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው!)።
የነፍስ ወከፍ ገቢ ስሌት በዓመት ቢሊየን የሚያገኘውንም ሃብታም በዓመት ያለምንም ገቢ በሰዎች ድጋፍ የሚኖረውንም ድሃ እኩል ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ ጠቅላላ ሃብት (GDP) እንዲሁም ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ባለበት ሃገር ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ኑሮ ምንም መሻሻል የሌለው ሲሆን Poverty Paradox ይባላል፡፡
በዚህ መለኪያ ኢትዮጵያ Poverty Paradox ውስጥ አይደለችም?

ጥሩ ኢኮኖሚስት ለመሆን የሚያስፈልጉ 10 ክህሎቶች። ጥሩ የኢኮኖሚክስ ተማሪ ወይም ጥሩ ኢኮኖሚስት ለመሆን የሚያስፈልጉ ክህሎቶች አሉ።
ምክንያቱም ኢኮኖሚክስ ስለወደዱት ብቻ የሚማሩት ሳይሆን የተሻሉ ክህሎቶች ይፈልጋል። ስለዚህ ኢኮኖሚክስን ለመማር ለምታስቡ ሰዎች የተወሰኑ ጠቃሚ ሃሳቦችን አጋርቻለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት።
https://youtu.be/CulW61TmCfI

ጥሩ ኢኮኖሚስት ለመሆን የሚያስፈልጉ 10 ክህሎቶች/Best characteristics of good economists/
ጥሩ የኢኮኖሚክስ ተማሪ ወይም ጥሩ ኢኮኖሚስት ለመሆን የሚያስፈልጉ ክህሎቶች አሉ። ምክንያቱም ኢኮኖሚክስ ስለወደዱት ብቻ የሚማሩት ሳይሆን የተሻሉ ክህሎቶች ይፈልጋል። ስለዚህ ኢኮኖሚክስን ለመማር ለምታስቡ ሰዎች የተወሰኑ ሃሳቦችን አጋርቻለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት።