The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
198 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
1. የዋጋ ንረት/የኑሮ ውድነት በቤተሰቦች ሸመታ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ። (The effect of inflation on household consumption/expenditure bundle)።


2. የድህነት መለኪያ ከገቢ እና ከወጪ አንፃር (Difference between income and expenditure poverty measurement)።


3. የዋጋ ንረት/የኑሮ ውድነት በማህበራዊ ኑሮ/ግንኙነት ላይ ያለው ተፅዕኖ (The impact of inflation on social life)።


4. የተማሪዎች ምገባ በቤተሰቦች ላይ ያመጣው ተፅዕኖ (The impact of school feed on household welfare)።


5. በድርድር እና በቁርጥ ዋጋዎች ላይ የሸማች አስተሳሰብ እና መተማመን (Perspective and public confidence on negotiation and fixed price)።


6. የቤተሰብ ቁጥር መጠን ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች (The determinant of family size decision) ወይም

ትዳር ለመመስረት የሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች (The determinant of marital status decision)።


7. ግጭት በሰዎች መተማመን ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ (The impact of conflict on public confidence)።


8. ጡረታ የወጡ ሰዎች የወጪ እና የሸመታ ሁኔታ (The trend of retirement consumption/expenditure)። #ለምሳሌ፦ ባደጉ ሃገራት የጡረተኛ ቤተሰብ የሸመታ መጠን ከፍተኛ ነው በተለይ የጤና እና የመዝናኛ በኢትዮጵያስ?


9. የጥቁር ገበያው ተፅዕኖ (The impact of black market)።


10. የመንግስት ሰራተኞች/ማንኛውም ሰራተኞች የስራ ቦታ ውጤታማነት ተፅዕኖዎች (The effect of civil servant engagement/job performance)።


የጥናት መነሻዎች በሞዴል (Explanatory) እንዲሁም በሀተታዊ (Descriptive) መሰራት የሚችሉ ናቸው። የነዋሪዎች ችግር በማይክሮ ደረጃ ወርዶ (Cross sectional) መስራት ለሚያስቡ ሰዎች በየአካባቢው እና በቤተሰብ ደረጃ የሚታዩ ሁኔታዎች ጥናት መሆን እንደሚችሉ ለማየት ያህል ነው።


ከላይ የተጠቀሱ ነጥቦች መነሻ ቢሆኑም ሌሎች የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ለመፈተሽ እና የጥናት ስራ ለመስራት ካነሳሳ በሚል ነው።


ስለ የጥናት መነሻዎች (Thematic Area) ዘርዘር አድርጎ ለመፃፍ ስለማይመች በቪዲዮ https://youtu.be/lSK51l3_pLw የገለፅኩ ቢሆንም መስተካከል ያለበት የመሰላችሁን እያስተካከላችሁ በራሳችሁ ያዘጋጃችሁት የሚታዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ካሉ ርዕሶች ላይ ካስተማሪ፤ እርስበርስ ወይም ያውቃል ከምትሉት ሰው ጋር በመወያየት መርጦ ለመስራት መሞከር መጥፎ አይደለም።


የረጅም ጊዜ (Time series) በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ጥናት ለመስራት የተለመዱ መለኪያዎች (Variable) ስላሉ እነሱ ላይ ብዙ ሰዎች የጥናት ርዕስ ለማግኘት ሳይሆን ሞዴል ለመምረጥ፤ የረጅም ዓመታት የማክሮ ዳታ ለማግኘት እና የመተንተን ችግር ብቻ ነው የሚኖርባቸው።
Channel photo updated
#አምርተዉ_እንጂ_ገዢ_አታጣም! "Say's Law"
****

የክላሲካሎች ዘመን (Classical School) እየተባለ በሚታወቀው (1776--1871) ሳይንሳዊ መርህን በተግባር በተፈጥሮ እና በሰው ዘር ላይ ምርምር ማድረግ በተጀመረበት፤ በተለይም በአውሮፓ በ17ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ የብርሀን ዘመን (Age of Enlightment) በኢኮኖሚው ዘርፍ እውቁ የኢኮኖሚ ባለሙያም Jean Baptiste Say በ1803 "A Treatise on Political Economy" በሚለው ስራው እንድ ድንቅ ሀሳብ ይዞ ብቅ አለ፣ እሱም "ምርት ፍላጎትን ይፈጥራል" (Supply Creates Its Own Demand) የሚል ነበር።


በየትኛውም ገበያ ውስጥ ስለምርትህ ፈላጊዎች ወይም ተጠቃሚዎች ሳትጨነቅ ወይም ፈላጊ  መኖር አለመኖር ሳታረጋግጥ ምርትህን አምርተህ ለገበያ ብታቀርበው የሚገዛህ አታጣም እንደማለት ነው። ይህም ህግ (Say's Law) በመባል ይታወቃል።


#ለምሳሌ፡- በቀላሉ ዛሬ ላይ በእያንዳንዳችን እጅ የሚገኘውን የሞባይል ስልክ ከመፈጠሩ በፊት የሞባይል ስልክ እንዲኖረን ፍላጎት አልነበረንም! ዛሬ ላይ መኪናን የገዙ ሰዎች መኪና እንፈልጋለን ብለው አልነበረም መኪና የተፈጠረው! በዲጅታሉ ዓለም እንኳን ብናየው የኢንተርኔት ፍላጎት በዚህ ደረጃ ይሆናል ተብሎ አልነበም ኢንተርኔት የተፈጠረው። ወዘተ…


ነገር ግን ሞባይሉም መኪናውም ኢንተርኔቱም ተፈጠረና ለዓለም ገበያ መቅረብ ሲጀምር (Supply Created First) የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ስራውንና ኑሮውን ምን ያክል እንደሚያቀልለት ስለተረዳ ገዝቶ መጠቀም ጀመረ (Demand Created Second)።


የSay's Law ተግባራዊነትን የሚደግፉና ስራ ፈጣሪዎች ወይም አምራቾች ስለምርታቸው የገበያ ፍላጉት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ግን ይመከራል።


በሌላ መልኩ ደግሞ በ1930ዎቹ ታላቁ የኢኮኖሚ ቀውስ (Great Depression) ጊዜ ምርቶች ገዢ አጥተው ነበር። ምክንያቱም ስራ የለም፣ ስራ ከሌለ ገቢ የለም፣ ገቢ ከሌለ ፍላጎት (Demand) የለም። ስለዚህ በ Say's Law አልስማማም የሚል አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ በ1930ዎቹ ብቅ ብሏል። እሱም John Maynard Kenes ነበር።


Kenes ፍላጎት ሲኖር ነው ምርት መመረት ያለበት ወይም ፍላጎት ምርትን ይፈጥራል (Demand Creates Its Own Supply) በማለት በGreat Depression ጊዜ የተፈጠረውን እንደማሳያ በማቅረብ በ Say's ህግ አልስማማም/አይሰራም በማለት መተቸት ጀመረ።


ፋብሪካዎች ማምረት አቁመዋል/ተዘግተዋል፣ ሰራተኞቻቸውን ቀንሰዋል/በትነዋል። ነገር ግን ፋብሪካዎቹ አሉ፣ ማሽኖቹም አሉ፣ የተፈጠሩት ቴክኖሎጅዎቹም እንዳሉ ናቸው። ስለዚህ ኢኮኖሚው ከአቅም በታች (Below Full Production Capacity) እያመረተ ቀውሱ የተባባሰው ፋብሪካዎች ምርት ለገበያ ማቅረብ ስላልቻሉ ሳይሆን ለምርታቸው ፍላጎት በመቀነሱና በዚህም አምራቾች የማምረቻ ወጫቸውን እንኳን መሸፈን ስላልቻሉ ነው! በማለት Kenes ይከራከር ነበር።


#ለምሳሌ፡- በሆቴል ቤቶች አካባቢ ስጋ ፈላጊዎች በብዛት ስለሚኖሩ ከሆቴል ባለቤቶች ጋር በመነጋገር ነጋዴዎች ስጋን ያቀርባሉ። ሆስፒታሎች አካባቢም የመድሀኒት ፍላጎት ስላለ የመድሀኒት ቤቶችን በብዛት እናያለን። እኛ ሰፈር እንኳን ብዙ ወንደላጤ ተከራዮች ከመኖራቸው የተነሳ ብዙ እናቶች በየሱቁ እንጀራን ያቀርባሉ። ወዘተ…


ስለዚህ የትኛው ህግ ነው ትክክል Say's Law ወይስ Kenes's Law? ካላችሁ፣ መልሱ ሁለቱም ነው። ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የሁለቱንም ተግባራዊነት በግልፅ እናያለን።


Say እና የእሱን ሀሳብ የሚያራምዱት (Classical School's) አጠቃላይ አቅርቦት (Agregate Supply) ላይ ትኩረት በማድረግ የኢንቬስትመንት መነሻው ቁጠባ ነው። ቁጠባ ካለ ኢንቬስትመንት አለ፣ ኢንቬስትመንት ካለ ስራ አለ፣ ስራ ካለ ገቢ አለ፣ ገቢ ካለ የመግዛት ፍላጎት አለ፣ ስለዚህ ምርት ፍላጎትን ይፈጥራል ይላሉ።


አምራቾች ወይም ስራ ፈጣሪዎች ጥረው ግረው አምርተው ገበያው ተቀዛቅዟል የሚገዛን አጣን ሲሉ እንሰማለን። ስለዚህ ቀድመው በገበያ ጥናታቸው ከማምረታቸው በፊት ለምርታቸው በቂ ፈላጊ እንዳለና እንደሌላቸው ስለማያረጋግጡ ሊሆን ይችላል። የKenes ህግን ስላልተከተሉ ማለት ነው። ፍላጎት የፈጠረው አምራች መሆን ስለነበረባቸው።


በቀላሉ ብዙ ሰዎች መብራት እንፈልጋለን፤ ውሀ እንፈልጋለን፤ መንገድ እንፍልጋለን እያሉ በሚያነሱት ሰፊ ፍላጎት መንግስትም እነዚህን አገልግሎቶች ሲያቀርብ እናያለን። ፍላጎት የፈጠረው አቅርቦት ማለት ነው። Kenes እና የእሱን ሀሳብ የሚያራምዱት (Kenessian School's) አጠቃላይ ፍላጎት (Agregate Demand) ላይ ትኩረት በማድረግ ኢንቬስትመንት ካላ ምርት አለ። ምርት ካለ ስራ አለ፣ ስራ ካለ ገቢ አለ፣ ገቢ ከለ ቁጠባ አለ፣ ቁጠባ ካለ መልሶ ኢንቬስትመንት አለ፣ ብለው ያምናሉ።


እናንተስ ከኢንቬስትመንት እና ከቁጠባ የትኛው መቅደም አለበት? ትላላችሁ! ሰዎች መጀመሪያ በረጅም ጊዜ ቆጥበው ወደ ኢንቬስትመንት መሸጋገር አለባቸው ወይስ ተበድረው ኢንቬስት አርገው ከኢንቬስትመንቱ ከሚያገኙት እየቆጠቡ ብድራቸውን መክፈል?


ከ2 ዓመት በፊት ከአማኑኤል አሰፋ ጋር በሰፊው የተወያየንበት ሃሳብ ነበር! እናንተ  በየትኛው ሃሳብ ትስማማላችሁ? ፍላጎት ወይስ አቅርቦት መሪው?


👉Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour


👉YouTube፦ https://youtu.be/v1kao07I_aU
ችግር በታወቀ ጊዜ ከተፈታ ቢዘገይም ዘገየ ተብሎ አይጣጣልም! አሁን ላይ በሀገራችን ችግር መሆናቸው እየታወቀ እና ወደፊት ከፍተኛ ችግር እንደሚያመጡ እየታወቀ ቸል የሚባሉ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዋጋ እያስከፈሉ ነው! ለዘላቂው ኢኮኖሚ ሲባል #ተንከባላይ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ካልታረሙ አላስፈላጊ ዋጋ ማስከፈላቸውን ይቀጥላሉ።
#Information_Failure!
****

በ2001 በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን በጥምረት ያገኙት George Akerlof፤ Joseph Stiglitz እና Michael Spence ዓለምን ያነቃት አንድ ሃሳብ ገነቡ፣ እሱም Adverse Selection ማለትም ሻጭ ስለሚሸጠው ቁስ ዋጋ እና ጥራት በቂ መረጃ ኖሮት: ነገር ግን ሸማች ምንም መረጃ ሳይኖረው (Information Failure) በሚያደርጉት መገበያየት ሸማች እንዴት ነው ጥራቱን የጠበቀ እቃ በተገቢው ዋጋ መግዛቱን የሚያውቀው? የሚል ነበር፡፡ ሻጭም ሆነ ሸማች እኩል ስለሚሸጡት እና ስለሚገዙት ቁስ ጥራትም ሆነ ተገቢው ዋጋ ስንት እንደሆነ ሲያውቁ Symmetric Information በገበያው ተፈጥሯል ስለዚህ ሸዋጅም ተሸዋጅም የለም ይባላል፡፡


#ምሳሌ1፡- የሰራ መኪና ለመግዛት በሚደረግ ድርድር ሻጭ ከገዢ በተሻለ የመኪናዋን ልፋት፤ ጥራት፤ የሚገባትን ዋጋ ያውቃል ነገር ግን ገዢ በቴክኒሺያን ቢያስፈትሽም በቂ እና የተሟላ መረጃ ስለማይኖረው መጥፎ ወይም አክሳሪ ውሳኔ ሊወስኑ ይችላሉ (George Akerlof በሰራው The Market for "Lemons" ጸሁፍ በደንብ አብራሮቶታል)፡፡ ከዚህ ኪሳራ ለመዳን #የመደራደር አቅም ወሳኝ ነው ይላል፡፡


#ምሳሌ2፡- በተመሳሳይ የህይወት ኢንሹራንስ የሚሰጡ የመድህን ድርጅቶች ኢንሹራንስ ስለሚገባው ሰውዬ የስራ፤ የጤና፤ የአኗኗር ሁኔታ፤ ወዘተ ከግምት ይከታሉ፣ ምክንያቱም መረጃ ሳይኖራቸው በቀን 50 ሲጃራ የሚያጨስን ሰው ከማያጨሰው ሰው እኩል ዋስትና ሰጥተው ኪሳራ ላይ መውደቅ አይፈልጉም፡፡ ዋስትና ገዢ (አጫሹ ሰውዬ ስለጤናው መረጃ አለው) ነገር ግን ዋስትና ሰጪ ስለሰውየው ካላጣራ በስተቀር በቂ መረጃ አይኖረውም ይህንን ሁኔታ Adverse Selection ይሉታል፡፡ ስለዚህ አደጋውን ለመቀነስ ድርጅቶቹ የዋስትና መጠኑን ይቀንሳሉ አልያም ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል ያደርጋሉ፡፡


#ምሳሌ3፡- አዲስ ሰራተኛ በሚቀጠርበት ወቅት ሰውየው ስለተማረው ትምህርት እና የስራ ልምድ እንጂ ስለስራ ተነሳሽነቱ፤ ስለታዛዥነቱ፤ ስለሰው አክባሪነቱ፤ ስለስራ ወዳድነቱ፤ ስለሱሰኝነቱ፤ ወዘተ ተቀጣሪ እንጂ ቀጣሪ ድርጅቱ ስለማያውቅ Michael Spence እንደሚለው Adverse Selection መፈጠሩ አይቀርም ይላል (Cumulative GPA 4 ማምጣቱን እና በማዕረግ መመረቁን አይተህ ስራ ቀጥረህው የስራ ተነሳሽነት የሌለው ሰው ሆኖ ስራን በማንጓተት ሊከርም ይችላል)፡፡


አሁን ላይ በሀገራችን ላይ የሚስተዋለው ድንገታዊ የዋጋ መጨመር ሸማቾችም ሆነ የመንግስት ባለስልጣናት የገበያው ሁኔታን የሚገልጽ በቂ መረጃ ስለሌላቸው ነው! (ባልታወቀ ምክንያት!፤ ምርት በቂ ነው ግን እጥረት ተከስቷል!፤ ገበያው በአሻጥር ተሞልቷል፤ ወዘተ የሚሉ መልሶች ተከታታይ የገበያ መረጃን ካለመያዝ የሚመነጩ ናቸው) ስለዚህ ትክክለኛውን የዋጋ መጨመር መረጃ መንግስት እና ሸማች ከሌለው መንግስት ገበያውን ለማረጋጋት ያልተረጋገጡ እርምጃዎች መውሰድ እና ህዝቡ የሚቀርብለትን ዋጋ ተቀብሎ በውድ መግዛት አይነት ሁኔታዎች ይከሰታሉ! እየተከሰቱም ነው።


የሀገራችን ገበያ በመረጃ እጥረት የታወቀ ነው! መንግስት ስለ ገበያው፤ አምራች ስለ ሸማች፤ ሸማች ስለ ገበያ አማራጭ፤ አርሶ አደር ስለ ከተሜው ገበያ፤ ወዘተ በቂ የመረጃ ልውውጥ መንገዶች እና የመረጃ ማዕከላት እጥረት በመኖሩ በንግድ ሰንሰለቱ ውስጥ መረጃ መደበቅ እና መልቀቅ ብቻ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ መሰረት የሌለው ትርፍ የሚያገኙ ደላሎች እና ሌሎች ተዋናዮች እየተበራከቱበት ነው።


👉YouTube፦ https://youtu.be/v1kao07I_aU


👉Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
የማይበገር/Resilient ኢኮኖሚ ማለት ምን ማለት ነው? የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ የማይበገር/Resilient ነው?


የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥሙት ለመቋቋም በሚያደርገው ጥረት ጥንካሬው ይለካል፡፡ በአስቸጋሪ ወቅቶች የማክሮ ኢኮኖሚ የማገገም አቅም በሁለት መንገድ ይለካል፡፡ እነሱም…..


ኢኮኖሚው ቅጽበታዊ ችግሮችን ተከትሎ የሚፈጠሩ የምርት እጥረት፤ የስራ አጥነት፤ የበጀት እጥረት፤ የንብረት ኪሳራ፤ ወዘተ ኢኮኖሚው ላይ (ህዝቡ ላይ) ከፍተኛ ኪሳራ ከመፍጠራቸው በፊት የመገደብ አቅም ስለመኖሩ……


ኢኮኖሚው ላይ (ህዝቡ ላይ) ከተፈጠሩ አሉታዊ ተለዋዋጭ ችግሮች ኢኮኖሚው በፍጥነት የማገገም ችሎታ ስለመኖሩ እንዲሁም ኢኮኖሚው የተፈጠሩ ክስረቶችን እንደገና በፍጥነት የመገንባት አቅም ስለመኖሩ...


ይህንን በተመለከተ ይህንን https://youtu.be/zbMGzP0gSlI ቪዲዮ እስከመጨረሻው ተመልከቱት።
የኑሮ ውድነቱ ሁሉንም የሚፈትን ቢሆንም የመንግስት ሰራተኛውን ግን በተለየ ያጠቃዋል። ምክንያቱም የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በጥቂቱ ለመጨመርም ዓመታትን መቆየት አለበት ነገር ግን ሰራተኛው ለኑሮ የሚያስፈልገው ወጪ በየቀኑ ይጨምራል።


መንግስት ለሰራተኞች ደሞዝ መጨመር በገበያው ሊፈጥር የሚችለውን የዋጋ ንረት በመስጋት (ግምታዊ!) ለውጥ ላለማከናወን ብዙ ምክንያት ቢደረድርም ሰራተኛው አማራጭ ባለማግኘቱ የመኖር አቅሙን አዳክሞታል።


የደሞዝ ጭማሪ እንደሚባለው የዋጋ ንረቱን እንደሚጨምረው እና እንደማይጨምረው እንዲሁም ደሞዝ ጭማሪን ሊተካ የሚችል የደሞዝ ማካካሻ (Wages) እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ይህንን https://youtu.be/MpcR2trnJX0 ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
ኢትዮጲያ ውስጥ ከፍተኛ ስራ አጥ ህዝብ አለ! ታዲያ ለምን አሰሪዎች/ቀጣሪዎች በዝቅተኛ ደሞዝ የፈለጉትን ሰው ቀጥረው አያሰሩም?


ኢኮኖሚ ውስጥ አራት ገበያዎች አሉ፣ እነሱም፡- የቁሳቁስ ገበያ (Goods Market)፤ የአገልግሎት ገበያ (Service Market)፤ የገንዘብ ገበያ (Money Market)  እና የሰው ሃይል ገበያ (Labor Market) ናቸው፡፡ ሁሉም አብዛኛውን ግዜ ዋጋቸው የሚወሰነው በአቅርቦት እና በፍላጎት አማካኝነት ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- በቁሳቁስ ገበያ የሙዝ ፍላጎት ሲያድግ የሙዝ ዋጋ መጨመሩ አይቀርም፤ በአገልግሎት ገበያ የማሳጅ አገልግሎት ፍላጎት ሲጨምር የማሳጅ ዋጋ መጨመሩ አይቀርም፤ በገንዘብ ገበያ የወለድ ምጣኔ (Interest Rate) ሲጨምር የገንዘብ ፍላጎት መቀነሱ አይቀርም በተመሳሳይ በሰው ሃይል ገበያ ብዙ ኢንጂነር ሲኖር ለኢንጂነሮች የሚከፈለው ደሞዝ ዝቅ ማለት ነበረበት! ነገር ግን ብዙ ተመራቂ ኢንጂነሮች በገበያው ሞልተው (ሌላው ቀርቶ በዝቅተኛ ደሞዝ የመቀጠር ፍላጎት ያላቸው) የሚቀጥራቸው አላገኙም! ለምን?


የስራ ልምድ፡- ሰራተኛ ልምድ እስኪያገኝ የትኛውም ቀጣሪ ከፍሎ ማሰልጠን እና መጎዳት አይፈልግም፣ ስለዚህ በቂ የስራ ላይ ልምድ ያለውን ሰራተኛ በከፍተኛ ደሞዝ ቢቀጥር ይመርጣል (የኢትዮጲያ አየር መንገድ እና ባንኮች በተወሰኑ ዘርፎች ላይ ጀማሪ ሰው ቀጥረው በማሰልጠን የማሰራት ልምድ አላቸው)፡፡


በኢትዮጲያ ሁኔታ ካየነው ከፍተኛው ሰራተኛ ቀጣሪ ድርጅት መንግስት እራሱ ነው! መንግስት ደግሞ አሰራሩ ያስቀመጠለትን ዝቅተኛ የደሞዝ ጣሪያ ቀንሶ መቅጠር አይችልም! #ለምሳሌ፡- ለአንድ ጀማሪ ሲቪል ኢንጂነር ክፍት ቦታ 200 ሰው ተመዘገበ እንበል! የተቀመጠው የደሞዝ እስኬል 5ሺ ብር ነው! ታዲያ 200 ሰው መኖሩን አይቶ ደሞዙን 3500 ብር ነው ቢል የሚቀጠርለት በፍጹም አያጣም፣ ነገር ግን ከአዋጅ በታች መቅጠር ስለማይችል 5ሺ ብር መክፈሉ ግዴታ ነው!


የሰራተኛ ማህበራት ተጽኖ፡- አንድ ድርጅት ከዚህ ቀደም የቀጠራቸውን ጀማሪ ኢንጂነሮች 5ሺ ብር ይከፍላቸው ነበር እንበል! ነገር ግን አዳዲስ ብዙ ኢንጂነሮች መመረቃቸውን ተመልክቶ እና በ3500 ብር የሚቀጠር አይጠፋም በማለት ነባሮቹን ሊያባርር ቢያስብ የሰራተኛ ማህበራት በፍጹም አይፈቅዱም! ሌላው ቀርቶ ከውጪ በቀላሉ በ3500 ብር መቅጠር ስለምችል ደሞዛችሁን ከ5ሺ ወደ 3500 ቀንሱ ቢላቸው (እሺ የሚል አይጠፋም!) የሰራተኞች ጉዳይ የሚከታተሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የሰራተኛ ማህበራት በፍጹም አይፈቅዱም!


በአዳዲስ ተመራቂዎች የእውቀት ጥራት ላይ መተማመን ማጣትም ቀጣሪዎች ያላቸውን ሰራተኛ ይዘው ተጨማሪ ተግባራትን እንዲያከናውን በማድረግ ከፍተኛ ደሞዝ እየከፈሉ ማሰራት እንጂ ከተትረፈረፈው አዲስ ስራ ፈላጊ የመቅጠር ጉጉት አያድርባቸውም!


በተጨማሪ አሁን ላይ የአንድ የጉልበት ሰራተኛ (የቀን ሰራተኛ) ዝቅተኛው የቀን ዋጋ 150 ብር ነው፡፡ በተመሳሳይ ከላይ በዘረዘርነው ምክንያት ቀጣሪ በቀን ከ150 ብር በታች ማድረግ አይችልም! ምክንያቱም ዋጋው የተቀመጠው ቀጥተኛ በቀን ሰራተኞቹ የቀን ወጪ ግምት ተሰልቶ ነው (ቀጣሪ በቀን 100ብር ቢል ጭራሽ የሚሰራለት ላያገኝ ይችላል)፡፡


በደሞዝ ሁኔታ ሰራተኞች የመደራደር አቅማቸው የሚጨምረው ከ Formal Sector ይልቅ በ Informal Sector ላይ ነው ብዬ አስባለሁ! #ለምሳሌ፡- ባንክ ቤት ከሚቀጠር አካውንታንት ይልቅ ሰፈር ውስጥ ለሚሰራ ቤት ቆርቆሮ ለመምታት አንድ አናጺ የሚከፈለውን ዋጋ እራሱ የመወሰን አቅም አለው፡፡


👉YouTube፦ https://youtu.be/v1kao07I_aU


👉Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ሁለት ፕሮጀክቶች የፈቀደው የ745 ሚሊየን ዶላር ፋይዳ!


የዓለም ባንክ የ745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የኢትዮጵያን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ያቃልላል? የዓለም ባንክ ከድጋፉ መካከል የተወሰነው በሶስተኛ ወገን የሚተገበር የፕሮጀክት ፈንድ ነው ሲል ምን ማለቱ ነው?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ትንታኔ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት https://youtu.be/a9G6jXkoTsQ
በምዕተ ዓመቱ ከተፈጠሩ 12 ስራ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ነው፤ በ2008 'Top 100 Global Thinkers' ከሚባሉት ውስጥ በደረጃ 2ኛው ነበር! በ2006 የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት አግኝቷል፤ በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት በዓመት አንድ ቀን በስሙ መታሰቢያ "January 14 Muhammad Yunus Day" ተሰይሟል፤ ለመሆኑ ይህ ኢኮኖሚስት ለዓለም ምን ሰርቶ ነው?


በዓለም ላይ ብዙ ኢኮኖሚስቶች ከድህነት እንዴት መውጣት እንደሚቻል ቢያስተምሩም ያወሩትን እራሳቸው አድርገውት አይገኙም ነገር ግን ሙሃመድ የኑስ በ100 ሀገራት የሚተገበር የአነስተኛ ብድር አቅርቦት ተቋም በማቋቋም ሚሊዮኖችን ከድህነት ለማውጣት በቅቷል፡፡


የኑስ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሃል 1940 በባንጊላዲሽ ቤተሰቦቹ ከወለዷቸው 9 ልጆች መካከል 3ኛው ሆኖ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በ20 ዓመቱ የመጀመሪያ ድግሪ፤ በ21 ዓመቱ የማስተርስ ድግሪ እንዲሁም በ31 ዓመቱ የዶክትሬት ድግሪውን በኢኮኖሚክስ ጨርሷል፡፡


"ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ሃሳቦችን ባስተምርም በርሃብ ለሚጠቁ ዜጎች ወዲያው ምንም ጠብ የሚል ነገር አለመኖሩ ያስቆጨኛል" የሚለው የኑስ፤ በ1976 አስተማሪ ሆኖ በሚያገለግልበት ዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኝ ሰፈር ውስጥ ወክ በሚያደርግበት ወቅት በቀርከሃ ንግድ የተሰማሩ የሰፈሩ ድሃ ሴቶች ቀርከሃ ለመግዛት አራጣ እንደሚበደሩ እና ያገኙትን ገቢ በአብዛኛው ላበዳሪ እንደሚከፍሉ ይመለከታል እንዲሁም በተመሳሳይ ባንክ ቤቶች መያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሰዎች ብድር እንደማይሠጡም አወቀ፤ በዚያ ወቅት ለድሆች ገንዘብ ቢሰጣቸው በእምነት እንደሚመልሱ በማመን ያለውን 27ዶላር ለ42 ሴቶች በ2 ሳንቲም ወለድ ያበድራቸዋል፤ ያኔ አነስተኛ ብድር (Microcredit እና Microfinance) አገልግሎትን ሀ ብሎ ጀመረ፡፡


ከባንክ በመበደር ለድሆች ያለ ምንም ወለድ ማበደሩን ቀጥሎ በ6 ዓመት ውስጥ 28ሺ አባላትን ማፍራት የቻለው የኑስ ስራውን ወደ ድርጅት አሳድጎ የመንደር ውስጥ ባንክ ማለትም Grameen Bank አቋቁሟል፤ ማህበረሰቡ ሙስሊም በመሆኑ ብድር ያለመውሰድ እምነት ስለነበራቸው ፈተና ሆኖበት የነበር ቢሆንም በ2007 (ከተቋቋመ በ31ዓመት ውስጥ) 6.38 ቢሊዮን ዶላር ለ7.4 ሚሊዮን ሴት ድሆች ብድር አቅርቧል፡፡ ይሄ ሁሉ ብድር ያለምንም መያዣ እርስ በርስ በመተማመን "Solidarity Groups" ብቻ የተሰጠ ነው፡፡ የግራሚን ፕሮጀክቱ እያደገ በግብርና፤ በአሳ ማርባት፤ በመስኖ፤ በሶፍትዌር፤ በሞባይል እና በኔትዎርክ አገልግሎቶች በመሳተፍ በባንጊላዲሽ ትልቅ የግል ኩባንያ ሆኗል፡፡


የግራሚን ስኬት ዛሬ ላይ 100 ታዳጊ ሀገራት ሌላው ቀርቶ አሜሪካንን ጨምሮ በሌሎች ያደጉ ሀገራት ጭምር ተስፋፍቶ ከ94% በላይ ደንበኞቹን ሴቶቸ በማድረግ ሚሊዮኖችን ከድህነት አላቋል፡፡ በዚህም ተግባሩ ሙሃመድ የኑስ እና ያቋቋመው ግራሚን ባንክ በጋራ የ2006 የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የኑስ በኖቤል ሽልማት ያገኘውን 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለድሆች ተመጣጣኝ ምግብ ለሚያቀርብ ድርጅት ማቋቋሚ እና በባንጊላዲሽ ለድሆች አገልግሎት የሚሰጥ የሃይን ሆስፒታል ለማቋቋሚያ አድርጓል::


በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት ከ2008 ጀምሮ በዓመት አንድ ቀን በስሙ መታሰቢያ ማለትም "January 14 Muhammad Yunus Day" በተጨማሪም የኑስ ከ20 ሃገራት 50 የክብር ዶክትሬት እና ከ26 ሀገራት 113 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተበርክቶለታል፡፡ በ2010 ዓለማችን ካፈራቻቸው 50 ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል 40ኛው የኑስ ነው፡፡ ዛሬ ላይ የኑስ ጡረታ በመውጣት አለም አቀፍ መድረኮች ላይ በመገኘት ትምህርቶችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡


የዓለም የተባበሩት መንግስታት አነስተኛ ብድር (Microcredit እና Microfinance) ድርጅትን በየሀገሪቱ በመመስረት በተለይ የሴቶች ድህነትን መቀነስ እንደሚቻል በማመኑ በ100 ድሃ ሀገራት (ኢትዮጲያን ጨምሮ) እንዲስፋፋ አድርጓል፤ ብዙዎቹም ተለውጠዋል የዚህ ሁሉ ባለውለታ ደግሞ የኑስ ነው።


👉YouTube፦ https://youtu.be/v1kao07I_aU


👉Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
በሀገራችን የባንክ ወለድን በመጨመር የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል?


በርካታ የዓለም ሀገራት እየተፈጠረ ያለውን ከፍተኛ #የዋጋ_ንረት ለመቋቋም በባንኮች ያለውን #የወለድ_መጠን በመጨመር ላይ ናቸው! ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተመሳሳይ ምክረ ሃሳብ ከኢኮኖሚስቶች እየተሰጠ ነው! እውነት በኢትዮጵያ የባንክ ወለድን በመጨመር በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት ይቻላል?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://youtu.be/hxMcsOOLkKA ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።
አፍሪካ አሜሪካን ፊት እየነሳች ያለችው ለምንድን ነው? አፍሪካ ከአሜሪካ ይልቅ ወደ ቻይና ፊቷን እያዞረች ያለችው ለምንድን ነው? Why is Africa turning away from the United States? Why is the US role in Africa shrinking?

በ2021 አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ 64 ቢሊየን ደላር ብቻ ሲሆን ቻይና ከአፍሪካ ጋር የ261 ቢሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ በ2021 አከናውናለች፡፡ አሜሪካ ከቻይና በአምስት እጥፍ ያነሰ የንግድ ልውውጥ ውስጥ የገባቸው ለአፍሪካዊያን ያላት ንቀት ነው! አሜሪካ አፍሪካዊያን እርዳታ ፈላጊዎች ብቻ መሆናቸውን ማሰብ እና ሁሌም አፍሪካዊያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የመንገር መብት እና ሃላፊነት እንዳለባት አይነት አመለካከቷን ካልቀየረች የአፍሪካ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር ያላቸው የንግድ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያዘነብለው ቻይና አፍሪካ ግንኙነት ማዘንበሉ ሊቀጥል ይችላል፡፡

#ለምሳሌ፡- "በቅርቡ የአሜሪካ አፍሪካ ጉባዬ (U.S-Africa Summit) ላይ የተጠሩ 49 የአፍሪካ መሪዎች (ኢትዮጲን ጨምሮ) ስለሚወያዩበት አጀንዳ እንኳ ሳይነገራቸው ለስብሰባ መጠራታቸው የአሜሪካ መንግስት ለአፍሪካ መሪዎች ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው! ስለዚህ የአሜሪካ መንግስት እንደ ቅርጫት ኳስ ጨዋታ እረፍት ጠይቆ ቆም ብሎ ሊያስብበት ይገባል" (የዩኤስ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አሪካና ቺሆምቦሪ-ኳኦ)፡፡

ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከአፍሪካ ጋር ለመስራት የምታስባቸው እቅዶቿን ለአፍሪካዊያን በተናጥል እና በህብረቱ በኩል የማወያየት፤ በመርህ ላይ የተመሰረተ የብድር እና እርዳታ ስምምነት ማድረግ፤ በአፍሪካዊያን የውስጥ ጉዳይ ጠልቆ ባለመግባት እና ግንኙነቶች የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ በማድረጓ በዚህ ወቅት ለአፍሪካዊያን ከአሜሪካ ይልቅ ቻይና ተመራጭ እየሆነች ነው፡፡

የሚከተሉትን ሁለት የአልጀዚራ ትንታኔዎች ተመልከቷቸው፡፡
Why is Africa turning away from the United States?
https://www.youtube.com/watch?v=UfLxnIqi4Uc
Why is the US role in Africa shrinking?
https://www.youtube.com/watch?v=_uwAS7anNwU
#Harrod_Domar_Model
*

ምርታማነት ሲያድግ የሰዎች ገቢ (በቂ የስራ እድል ስለሚፈጠር) ስለሚያድግ አጠቃላይ ፍላጎት ያድጋል ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲመጣ ኢንቨስትመንት በመጀመሪያ ማደግ አለበት፤ እሱን ተከትሎ የሰዎችም የመሸመት ፍላጎት ተያይዞ ማደግ ይኖርበታል፤ በተመሳሳይ ኢንቨስትመንት ሲያድግ ምርታማነት ያድጋል (አቅርቦት አደገ ማለት ነው!) የኢንቨስትመንት ማደግን ተከትሎ የስራ እድል ስለሚሰፋ የሰዎች የመግዛት አቅም ያድጋል (ፍላጎት አደገ ማለት ነው!) ስለዚህ Equilibrium ይፈጠራል ይላል አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት Domar፡፡

የመንግስት ጣልቃ ገብነት እና የውጪ እርዳታ ሳይኖር (Closed-Economic) በሀገር ውስጥ በሚደረግ ቁጠባ በመታገዝ፤ በቂ የሰው ሃይል ጉልበትን (Full Employment) በመጠቀም ሀገርን ማሳደግ ይቻላል!፡፡ ምርታማነት እንዲጨምር ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ የካፒታል አቅም (Capital Accumulation) እና የሰው ሃይል መካከል ያለውን ግንኙነት መሰረታዊ ሲሆን በተቃራኒው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት Harrod (1939) አጠቃላይ የካፒታል አጠቃቀም በጠቅላላ የምርት መጠን (Output) ላይ ያለውን ግንኙነት አጥንቷል፡፡

በአጭሩ Domar (1946) ኢንቨስት ስለማድረግ ብቻ ሲጨነቅ Harrod ደግሞ ኢንቨስትመንትን ከሚያስገኘው የትርፍ ገቢ አንጻር ኢኮኖሚያዊ እድገትን መመልከት እንዳለብን ያስረዳል፤ የሁለቱ አስተሳሰብ አንድ ላይ ሲዋሃድ Harrod-Domar Model ይባላል፡፡ ሃሳቡም ለኢኮኖሚ እድገት መሰረታዊው ነገር ቁጠባ እና ካፒታልን በአግባቡ መጠቀም ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ያስረዳል (የKeynesian ቅጂ ነው!)፤ በዋናነት የDevelopment Economics ትምህርት አካል ቢሆንም የሚከተሉት ድክመቶች አሉበት!

ያደጉ ሀገራት ከሚፈጠርባቸው የስራ አጥነት ችግር እንዴት መውጣት እንደሚችሉ እንጂ ለታዳጊ ሀገራት የሚሆን ምርጫ አይደለም (በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ዛሬም በታዳጊ ሀገር ቁጠባ የማይቻል ፈተና ነው!)፤ ቁጠባ በሀገር ውስጥ ቢጠፋ ከውጪ ብድር ክፍተትን መሙላት ስለሚቻል ቁጠባ ብቸኛ አማራጭ አይሆንም፤ ኢንቨስትመንት ሲጨምር ከግብዓት የሚገኝ ተጨማሪ ትርፍ እንደሚቀንስ በሚያስረዳው በ The law of diminishing returns ህግ አግባብ ሞዴሉ ድክመት አለበት እና Full Employment ወይም ሁሉም ለስራ ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን ወደ ስራ መሰማራት አለባቸው የሚለው አስተሳሰብ የማይሳካ (ምክንያቱም ስራ አጥነት በጭራሽ ዜሮ አይመጣም) በመሆኑም የHarrod-Domar Model የሚተችበት ጉዳይ ነው፡፡


👉YouTube፦ https://youtu.be/v1kao07I_aU


👉Facebook፦ https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour
አከፋፋይ ምረጡ ማለት እና ዋጋ ተምኜላችሁ ሽጡ ማለት ነፃ ገበያ ማለት አይደለም!

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ፦ ከዛሬ ጀምሮ ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት #በነጻ_ገበያ ይካሄዳል። ስለዚህ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው! የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ #በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ገልጿል።

#አማካይ_የሲሚንቶ_ዋጋ
- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.3ብር
- አሁን ፋብሪካዎች ያስገቡት የመሸጫ ዋጋ ➤ 1014.6ብር
- እንዲሸጡ የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 758.1ብር

ታዲያ ይህ ማለት እኮ መባል ያለበት ሲሚንቶ አምራቾች አከፋፋይ መርጣችሁ በተተመነላችሁ ዋጋ ሽጡ እንጂ በትርጉም ደረጃ #ነፃ_ገበያ ማለት አይደለም!
ከሚታወቅ (Finite) ቁጥር እና ከማይታወቅ (Infinite) ቁጥር ናሙና እንዴት ይወሰዳል? በተለያዩ የናሙና ፎርሙላዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 95% confidence level እና በ90% confidence level ናሙና አመራረጥ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ክፍልፋይ (Proportion sample) እንዴት ይወሰዳል? ናሙና ቁጥር ስሌት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችኝ የሚመልስ ምርጥ የተግባር ቪዲዮ ሰርቻለው እስከመጨረሻው ተከታተሉት ለሌሎች ጥናት ለሚሰሩ እና ለሚማሩ ሰዎች አጋሩት።


https://youtu.be/5hetXEeAnJY
በጥናት ስራ ወቅት የኮተሪን/C.R. Kothari ስም አለመስማት አይቻልም! በተለይ ናሙና እንዴት እንደሚወጣ በደንብ በሚያስረዱት ፎርሙላዎቹ ብዙዎቻችሁ ታውቁታላችሁ፡፡

ይህ መጽሃፍ የጥናት ርዕስ እንዴት እንደሚለይ፤ ጥናት የሚገነባበት ስልት (Research Design)፤ ናሙና አወሳሰድ፤ መረጃ አተናተን፤ መላምት እንዴት እንደሚለካ (Testing of Hypotheses) እና የሞዴል ውጤት እንዴት እንደሚተነተን ትረዱበታላችሁ፡፡ ይህንን መጽሃፍ ስላጋራኋቹ ደስ ብሎኛል!

ያለንበት ዲጂታል ወቅት ከአስተማሪ ብዙ እና በቂ የሚጠበቅበት ነው ብዬ አላምንም! (ለብዙዎች በአግባቡ አለመማር፤ ሳይገባቸው መጨረስ፤ በአድቫይዘር በቂ ድጋፍ ያለማግኘት፤ ከስራ ጋር በመማር በክፍል አለመገኘት፤ ጊዜ ማጣት፤ ወዘተ) የሚነሱ ችግሮች ናቸው፡፡

ስለዚህ ወቅቱ ማንም የፈለገውን በኢንተርኔት ታግዞ ማንበብ እና ማየት የሚችልበት በመሆኑ ሰበብ ከመደርደር ይልቅ ወሳኝ የሚባሉ እና ለትምህርት እና ለስራችሁ የሚያስፈልጋችሁን ጽሁፎች በቀን ውስጥ በምትገኝ #ተባራሪ_ደቂቃ በሞባይልም ቢሆን ማንበብ መለማመድ ግድ ነው፡፡ ይህ ልምድ በአስተማሪ፤ በአድቫይዘር፤ በጊዜ ላይ የሚኖሩንን ሰበቦች ይቀንሳል የሚል ግምት አለኝ፡፡
በመኪና ንግድ ላይ አላግባብ ንሮ የነበረው #የትርፍ_መጠን መቀነስ የጀመረበት ምክንያቱ ምንድን ነው? (እኔ በግሌ ከመገመት በስተቀር ትክክለኛው ምክንያት ምንድን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልኩም)።
ሰዎች ከታች ያለውን ስላይድ ሲልኩልኝ አላምንም ብዬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉትን ንግግር ከEBC ዩቱብ ላይ ሙሉ ንግግሩን ስሰማ ከ17፡34 እስከ 17፡49 ደቂቃ ላይ አገኘሁት፡፡ በየትኛውም አመክንዬ ለመረዳት ቢሞከር አንኳን ሃሳቡ ያስደነግጣል (በምዕራብ አፍሪካ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች ሙስና አወንታዊ ጎን አለው በሚል ለማሳመን እንደሚሞክሩት ጥናት አይነት ነው!)፡፡
የሲሚንቶ ዋጋ በተመን አይቀንስም!

በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ገበያ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ሲመራ በዋጋም ሆነ በአቅርቦት ሲፈተን ኖሯል። አሁን ላይ የመንግስት ቁጥጥር በጥቂቱ ይላላል መባሉን ተከትሎ ዋጋው ሊስተካከል ይችላል ቢባልም በቀጣይ የሲሚንቶ ዋጋም ሆነ አቅርቦት ለመሻሻል የሚቸገርበትን ምክንያት በተመለከተ የሚከተለውን ቪድዮ https://youtu.be/fhY0OvsFi34 ተመልከቱ።