The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
198 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመረጡትን የትምህርት መስክ 100% የመማር መብት እና እድል ቢኖራቸው የሰራተኛ ገበያው ላይ የትኛውም የትምህርት መስክ የሚበዛ ይመስላችኋል?
በግለሰብ ደረጃ ስለነበሩት ውሳኔዎች ስህተት እና ጥንካሬ፤ ስለሌሎች ሃገራት ተሞክሮ እና ውድቀት፤ ስለመጪው ጊዜ እድል እና ስጋት ለሚያስተምረው ኢኮኖሚክስ እና ይህንን ለተማሩ ኢኮኖሚስቶች "ስለወደፊቱ በመጨነቅ የምታሳልፈው ደቂቃ ወይም ስላለፈ ነገር ተፀፅተህ የምታሳልፈው ደቂቃ ልክ እንደጠፋ ይቆጠራል፣ ምክንያቱም በእውነት መኖር ያለብህ አሁን ብቻ ነው" የሚለው የኢካርት ቶል ታዋቂ ምክር እንዴት ይታያል?

#ለምሳሌ፡- በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ሸማቾች ለሚያደርጉት የሸመታ ውሳኔ እንዲሁም አምራቾች ወጪን በመቀነስ ለማሳደግ ለሚፈልገው ትርፉ ሲሉ የሚያደርጉት ውሳኔ ምክንያታዊ (Rational) ነው ይላል፡፡ ኢካርት ቶል ደግሞ "The Power of Now" ላይ ሰዎች በቀደመ ጊዜ ባደረጉት እና ባለፈ ውሳኒያቸው ላይ በሚፈጥሩት ያልተገባ ጸጸት ወይም በመጪው ጊዜ ላይ ይበልጥ በመጨነቃቸው ምክንያት አሁን ላይ ምክንያታዊነታቸው ይቀንሳል ይላል፡፡

የቀደመ ጊዜ ውሳኔም ሆነ የመጪው ጊዜ ትንበያ በጣም አስፈላጊ ነው በሚለው እና ያለፈ ጉዳይ አልፏል መጪው ጊዜው ሲደርስ ዛሬ መሆኑ ስለማይቀር ስለዛሬ እንዲያውም ስለአሁኗ ቅስፈት ብቻ መጨነቅ ይገባል በሚሉት ሁለት አስተሳሰቦች ላይ ምን ትላላችሁ?
ነጭ፤ ግራጫ፤ ጥቁር እና ቀይ ገበያ ማለት....

ነጭ ገበያ (White Market)፡- ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ በህጋዊ ስርዓት ውስጥ የሚካሄድ የግብይት ስርዓት ሲሆን በመንግስት ተመዝግቦ የሚታወቅና በግብር ስርዓት ውስጥ ያለ ነው፡፡ እዚህ ግብይት ውስጥ ገዢም ሻጭም ምርቱንም ሆነ አገልግሎቱን ለመለዋወጥ ሙሉ ህጋዊ መብት አላቸው:: #ለምሳሌ፡- የንግድ ፍቃድ ካለው አካል ምንም አይነት እቃ መግዛት ወይም መሸጥ፤ ህጋዊ ሆስፒታል ሄዶ መታከም ወይም ማከም፤ ወዘተ፡፡

ግራጫ ገበያ (Gray Market)፡- ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ አንድን እቃ መግዛት ወይም መሸጥ እየቻልን በህገወጥ መንገድ እቃውን ወይም አገልግሎቱን ስንገበያይ ማለት ነው:: #ለምሳሌ፡- የስኳር መድሃኒት በህጋዊ መንገድ ገዝቶ መጠቀም ይፈቀዳል ነገር ግን በተለያየ ምክንያት (የአቅርቦት እጥረት ብዙ ግዜ ምክንያት ይሆናል!) ከህጋዊ ስርዓቱ ውጪ ባለ የንግድ ስርዓት ገዝተን ወይም ሸጠን ስንገኝ ማለት ነው፡፡

ጥቁር ገበያ (Black Market)፡- ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ አንድን እቃ ወይም አገልግሎት መግዛትም ሆነ መሸጥ ክልክል በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ገዝቶ ወይም ሸጦ መገኘት ነው (መንግስት ብቸና አስመጪ፤ አምራች እና ሻጭ ወይም አከፋፋይ የሆነባቸው ቁሶች አልያም አገልግሎቶች ሊሆኑ ይችላሉ):: #ለምሳሌ፡- የመሳሪያ ሽያጭ፤ የውጪ ምንዛሬ ሽያጭ፤ አደንዛዥ እጽ ሽያጭ፤ የእንሰሳት አካል፤ ወዘተ መግዛት ወይም መሸጥ ማለት ነው፡፡

ቀይ ገበያ (Red Market)፦ አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ስኮት ካርኒ ካደረገው ጥናት በመነሳት በ2011 በጻፈው "The Red Market" መጽሃፍ ሰው ያሉትን የሰውነት ክፍሎች #ለምሳሌ፡- ኩላሊት፤ ልብ፤ አይን፤ ሳንባ፤ ጉበት፤ መቅኔ፤ ደም፤ አጥንት፤ የዘር ፍሬ፤ ጥርስ፤ ወዘተ አውጥቶ በቁሙ አልያም ሞቶ ቢሸጥ እስከ 250ሺ ዶላር ያወጡለታል ይላል፡፡ ለዚህ ነው #ደም የሚፈስበት የሰውነት ክፍል ሽያጭ በመሆኑ "Red Market" የተባለው፡፡

ለጥቁር ገበያ ዋነኛው ምክንያት #ድህነት ነው እንደሚባለው ለቀዩ ገበያ ድህነት ዋናው ምክንያት ነው፡፡ ምን ማለት ነው? ድሆች ውድ የሰውነት ክፍል ተሸክመን የምንበላው የምናጣበት ሁኔታ ልክ አይደለም! ስለዚህ ሸጠን እንጠቀማለን ይላሉ፡፡ ካርኒ በመጽሃፉ እንደሚገልጸው ህንድ ውስጥ ባለ አንድ የስደተኞች (በ2004ቱ የሱናሜ አደጋ የተፈናቀሉ ናቸው) ካምፕ ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች ኩላሊታቸውን አውጥተው ከመሸጣቸው የተነሳ ስደተኞች ካምፑ Kidney Ville የሚል ቅጽል ስም ወቶለታል ይላል፡፡

አንድ ልጇን ለማስታመም 1ሺ ዶላር በማጣት ኩላሊት የሸጠች ህንዳዊቲ ምስክርነት ስትሰጥ ተጎሳቁለህ ሲያዩህ ደላሎች ቀርበው ያዋሩሃል ትላለች 'When You're At Your Most Desperate Place ... The Brokers Come In'፡፡ እንዳትረሱ ገበያው በዓለም ላይ (ኢትዮጲያን ጨምሮ) ህጋዊ አይደለም፡፡ ከሞተ ሰው በፍቃደኝነት የሚወሰድ የዓይን ብሌን እና በቤተሰቦች መካከል በፍላጎት የሚሰጥ ኩላሊት የህግ አሰራር አለው።

ቀላሉ ምሳሌ የጸጉር ገበያ Human Hair የተለመደ ስሙ "#Black_Gold." ሆኗል! በዓለም ላይ በዓመት ከ900ሚሊየን ዶላር በላይ ልውውጥ ይደረግበታል (በሀገራችን ትክክለኛው Human Hair ውድ ከመሆኑ የተነሳ የሃብት መገለጫ ሲደረግ ይታያል)፡፡ በጋዜጠኛው ጥናት የወንዶች ጸጉር ለገበያ ቀርቦ ይቆረጥ እና በኬሚካል ካምፓኒዎች ተቀነባብሮ ወደ አሚኖ አሲድ (L-cystine) ይቀየር እና ለማጥቆሪያነት አገልግሎት ላይ ይውላል ይላል፡፡

ደላሎች በበኩላቸው የሰው ልጅ የሰውነት ክፍሎች የሚተኩ አልያም በፋብሪካ የሚመረቱ ባለመሆናቸው ያለን አማራጭ በቁሙ ካለ ሰው መውሰድ/መግዛት አልያም በቅርቡ ከሞተ ሰው መውሰድ ነው ይላሉ (የዓለም ህዝብ ቁጥር (8 ቢሊየን) የኩላሊት አቅርቦት ባለበት ዓለም ሰው ለምን በኩላሊት እጥረት ይቸገራል ሲሉ ይከራከራሉ)፡፡

በቱርክ በተደረገ አንድ ጥናት ደላሎች በዓለም ላይ የተለያዩ ኔትዎርኮችን በመጠቀም ከአፍሪካ፤ ከእስያ እና ከአውሮፓ የሰበሰቡትን ኩላሊት Medical Tourist’s በሚበዙበት በጀርመን፤ በካናዳ፤ በእስራኤል እና በፖላንድ ገበያዎች እስከ 100ሺ ዶላር ይሸጣሉ (በሽፋን ከበጎ ፍቃደኛ የተለገሱ ተብለው ነው የሚቀርቡት)፡፡

የአለም የጤና ድርጅት (በዓለማችን በዓመት ከ10ሺ በላይ ኩላሊት ይነቀላል ይተከላል) ከዚህ ውስጥ 10% የሚሆነው የሰውነት ክፍሎች ንቅለ ተከላ ህገ ወጥ ነው ይላል፡፡

ታዋቂው VICE News (The Business of Crime በሚለው ዶክመንተሪው ሲያስረዳ 1 ቢሊየን ዶላር የሚዘዋወርበት የሰውነት ክፍል ሽያጭ (ጥሩ ሳንባ 130ሺ፤ ጥሩ ኩላሊት 100ሺ፤ የአይን ብሌን 30ሺ ዶላር) የሚቸበቸብበት የተደራጀ የህገ ወጥ ማዕከል ሆኗል ይላል፡፡ በንግድ ሰንሰለቱ ለጋሹን/ተሰራቂውን የሚያመጡ እና የሚያጓጉዙ ደላሎች፤ የሰውነቱን አካል አውጪ ዶክተሮች እና ንቅለ ተከላውን የሚያከናውኑ የጤና ተቋማት ናቸው፡፡

የሰውነት ክፍሎችን ማሰባሰብ በሻጭ ፍላጎት ብቻ የተመሰረተ አይደለም! ከፍተኛ የሰዎች እገታ በማድረግ (በተለይ ስደተኞች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች)፤ በተለያየ ምክንያት ለሌሎች ህክምና ከሄዱ ሰዎች በመስረቅ፤ ወዘተ ነው፡፡
ለመማር የትምህርት ዘርፍ (Department) የምትመርጡበት መስፈርት ምንድን ነው? ተጨማሪ ድግሪ ለመያዝ ምክንያታችሁ ምንድን ነው?


ድግሪ ወይም ማስተርስ ለመያዝ፤ ኢንጂነር አልያም አካውንታንት ለመሆን ድርሻ ነበራችሁ? በሰዎቾ፤ በቤተሰብ አልያም በመንግስት ፍላጎት የትምህርት እና የሙያ ታሪካችሁ አልተወሰነም?


በአጋጣሚ የተገኘውን የትምህርት ዘርፍ መርጦ መማርም ሆነ ተጨማሪ ትምህርት ለመማር በቂ ምክንያት አለማቅረብ በህይወት ወስጥ ዋጋ አስከፋይ ነው።


በዚህ ዙሪያ ከልምዴ በመነሳት ያዘጋጀሁትን ምክር ልስጣችሁ!


https://youtu.be/eGHAvTNi5rQ
በቅርቡ ቢሾፍቱ ቡና በምጠጣበት ቦታ ሁለት የባንክ ሰራተኞች ሂሳብ ካልከፈትክ በሚል ለማሳመን የሞከሩባቸውን ነጥቦች ጨርሰው ረጅም ልመና፤ ዛሬ በስራ ቦታዬ ላይ የሌላ ባንክ ሰራተኞች ከ20 ደቂቃ በላይ ሂሳብ ካልከፈትክ የሚል ረጅም ተማጽኖ ("እባክህ!፤ ለኔ ስትል!፤ ብትከፍት ምን አለበት?")….

ለሰራተኞቹ ሂሳብ ማስከፈት የሚለኩበት ስራቸው እንደሆነ አውቃለሁ እንዲሁም ለባንኮቹ የሂሳብ ክፈቱ ዘመቻ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችልም አምናለው (ባንኩ የሂሳብ ደብተሩን ለማሳተም ያወጣውን ወጪ ብቻ መሸፈን የሚችል ብር ብቻ ያለባቸው ብዙ የሂሳብ ደብተር በየባንክ ቤቶች አሉ)!......

ነገር ግን በመንገድ ላይ በፍጥነት የሚጓዝ ሰው፤ እረፍት ፈልጎ ለተቀመጠ ሰው፤ ቢሮው ላይ በስራ የተጠመደን ሰው፤ የሂሳብ ደብተር ለመክፈትም ላለመክፈትም በቂ ምክንያት ላለው ሰው፤ ደብተር አለኝ የሚለውን እስቲ የታለ ደብተሩ አሳየኝ በሚል ንትርክ ማስጨነቅ ሳይሆን ሁኔታዎችን መምረጥ እና ፋይዳውን በተለየ Approach መመልከት መጀመርም ተገቢ ይመስለኛል፡፡
በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በዓለም ላይ የተለያዩ ገበያዎች አሉ! መንግስታት ሁሉንም የግብዓት ስርዓት የመቆጣጠር አቅም የላቸውም! በዋናነት በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ያለው ልዩነት ምንድን ነው? በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ምን አይነት ቁሶች እና አገልግሎት እንደሚገበያዩ፤ ለምን ገበያዎቹ እየሰፉ እንደሆነ የሚከተለውን የመረጃ ዳሰሳ ጥናት ላይ በምሳሌ የተደገፈ ትንታኔ አቅርቤላችኋለሁ። እስከመጨረሻው ተከታተሉት።

https://youtu.be/QM_w7F5axNU
ከ2 ወር በፊት በነዳጅ የሚሰራ መኪና ከውጪ ለማስገባት ብሄራዊ ባንክ የLC ፍቃድ ሲከለክል የመኪና መሸጫ ቦታዎች ጭር የሚሉ ይመስል ነበር! ነገር ግን አሁን ላይ የመኪና መሸጫ ቦታዎች ላይ አዳዲስ መኪኖች በብዛት አሉ! ለምን ይመስላችኋል?
Washington Consensus ታዳጊ ሀገራት ብድር እና እርዳታ ለማግኘት የሚጠየቁት 10 መስፈርቶች!


Washington Consensus የብዙዎቻችንን ህይወት የመንካት አቅም ያለው የፖሊሲ ቅድመ ሁኔታ ነው! በነጻ ገበያ ሰበብ ታዳጊ ሀገራትን በነጻ ከመርዳት ይልቅ ቅድመ ሁኔታ በማዘጋጀት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፤ የዓለም ባነክ (World Bank) እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት (U.S. Treasury) በጋራ በመሆን ያዘጋጁልን 10ቱ ትዛዛቶች ናቸው፡፡ ሀገራት ትዛዛቱን ካሟሉ ይረዳሉ ወይም ብድር ያገኛሉ፡፡ እነዚህን 33 ዓመታት ያስቆጠሩ አስሩንም ትዛዛት ወይም ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር ተከታተሉ።


https://youtu.be/sB8tWKxTCyc
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፦ "መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ ነው"። የዚህ አይነት መግለጫ በየዓመቱ መሰጠቱን ስመለከት መንግስት ህዝቡን "ቢያንስ ለበዓል እንዳይከፋችሁ!" የሚል ነው የሚመስለኝ።


መሰረታዊ የአቅርቦት ስራ መስራት የሚቻል ቢሆን በዓመት ውስጥ የሚመጡ ጥቂት በዓላት የሚፈጥሩት የሸማች እና የመንግስት ጭንቀት ይቀንስ ነበር።



የማስታመም እርምጃ የለመደው የኢትዮጵያ ገበያ በበዓላት ወቅት የመንግስትን ውስን የገበያ ጣልቃ ገብነትን ባይጠላም ሸማቹም ለበዓል ሸመታ ምክንያታዊ ለመሆን መጣር አለበት።
ሀገራት ብራቸውን ለምን በብዛት አያትሙም? ሀገራት የራሳቸውን ገንዘብ የማተም መብት አላቸው? ሀገራት ለምን ገንዘባቸውን በሌሎች ሀገራት እዲታተም ያዛሉ? ኢትዮጲያ ገንዘቧን የት ነው የምታሳትመው? ይህንን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትንታኔ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡ https://youtu.be/AjAMg_NgH70
ዶላር ለምን የዓለም ጠንካራ መገበያያ እና የክምችት ገንዘብ ሆነ? ሀገራት ለምን የአሜሪካንን ዶላር ያከማቻሉ? ዶላር ለምን እስከአሁን በሌሎች ገንዘቦች አልተተካም? በቅርብ ዶላር መተካት ይችላል? ሰዎች እና ሀገራት በእጃቸው ያለውን ዶላር ለምን ይተማመኑበታል?

 ይህንን በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ ሰፊ ትንታኔ አቅርቢያለሁ እስከ መጨረሻ ተከታተሉት።

https://youtu.be/_X6UzWi8p1w
"በጥቁር ገበያ ውጪ ሀገር ያለ ሰው አንድ ዶላር በ100ብር ይልካል ነገር ግን በባንክ በኩል የሚልከው ሰው በ53ብር ይመነዝራል በዚህ ምክንያት አብዛኛው ሰው በአንድ ዶላር 47ብር ከሚያጣ በጥቁር ገበያ ለመላክ ይገደዳል፡፡ ይህ ደግሞ መንግስት በቂ የውጪ ምንዛሬ እንዳያገኝ ያደርገዋል! ስለዚህ መንግስት በበዓል ወቅት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ስለሚላክ በዋጋ ሰበብ ጥቅሙን ከሚያጣ ለበዓል ወቅት ለምን በባንክ ያለውን የአንድ ዶላር ምንዛሬ ወደ 100ብር በማሳደግ በዓል ካለፈ በኋላ ወደ 53ብር ቢመልሰው የውጪ ምንዛሬን ለማግኘት መፍትሄ አይሆንለትም ወይ?" ሲል አንድ ሰው ጠየቀኝ………

ከውጪ ሃገር በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ገንዘብ የሚልኩ ሰዎች ለረጅም ጊዜ በቋሚነት ይህንን የጥቁር ገበያ እና ገንዘብ ላኪ ኤጀንቶች ስለሚጠቀሙ ለአንድ ጊዜ በሚል ብቻ ወደ መደበኛ ባንኮች የመምጣታቸው እድል ዝቅተኛ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

በብሄራዊ ባንክ እና በጥቁጥር ገበያ መካከል ያለው የምንዛሬ ልዩነት መሰረታዊ ምክንያቱ በውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ነው! ስለዚህ ገበያው በቀላሉ ገበያው የሚፈልገውን የውጪ ምንዛሬ ማቅረብ እስኪችል (Exchange Rate Equilibrium Point) መንግስት ምንዛሬ ከፍ ባደረገ ቁጥር የጥቁር ገበያው ከፍ ማለቱ አይቀርም ስለዚህ ልዩነቱ ይቀጥላል እንጂ አይጠብም! ይህ ደግሞ አደጋ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው?

#ለምሳሌ፡- ብሄራዊ ባንክ አንድ ዶላር በባንኮች በ100ብር ይመንዘር ቢል፡ የጥቁር ገበያው በነበረበት 100ብር ሊቀጥል አይችልም በቅስፈት ውስጥ ከ100ብር በላይ በማድረግ የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እና ፍላጎት የሚመጣጠኑበትን መጠን (Equilibrium Point) እያሳደጉት ይሄዳል፡፡ ምክንያቱም የጥቁር ገበያው የውጪ ምንዛሬውን ማገላበጥ ስለሚፈልግ እና መንግስት ለበዓል ሰሞን ገንዘቡን በማዳከም የሚሰበስበውን የውጪ ምንዛሬ በቀላሉ ለግሉ ባለሃብት በፈለገው መጠን እና ጊዜ ሊለቀው እንደማይችል ስለሚረዳ ምን አልባት ጥቁር ገበያው አንድ ዶላርን ወደ 150ብር ከፍ አድርጎ ሊጠብቅ ይችላል ብሎ ማሰብ መጥፎ አይደለም ማለቴ ነው፡፡

አሁንም ድረስ በውጪ ምንዛሬ ላይ ያለው አቅርቦት እና ፍላጎት በክምችት እስካልተቀራረቡ ድረስ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ከውጪ ምርቶችን ለማስገባት ከብሄራዊ ባንክ የሚጠየቀው LC ሆነ ከጥቁር ገበያ በከፍተኛ መጠን ምንዛሬ ተገዝተው ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ዋጋ ማደጉ አይቀርም (Imported Inflation) ምን ማለቴ ነው?

#ለምሳሌ፡- የውጪ ምንዛሬ በብሄራዊ ባንክ አንዱን ዶላር በ53ብር የተጠየቀ አስመጪ ምንዛሬው ለአጭር ጊዜም ቢሆን 100ብር ቢደረግ በአንድ ዶላር የተጨመረበትን 47ብር በቀጥታ ወጪ ላይ ስለሚደምረው ከውጪ ሃገር የሚገባው ምርት በሀገር ውስጥ ገበያ ውድ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መንግስት አንድ ዶላርን ለአጭር ጊዜም ቢሆን 100ብር ማድረሱን ተከትሎ ጥቁር ገበያው (Exchange Rate Equilibrium Point) ፍለጋ አንድ ዶላርን ወደ 150ብር ቢያሳድገው አስመጪው የተጨመረበትን 50ብር ወጪ ላይ ስለሚደምረው ከውጪ ሃገር የሚያስገባው እቃ በግዴታው ቢሆን በሀገር ውስጥ ውድ ይሆናል፡፡

ብሄራዊ ባንኩ በዓል አልፎ ምንዛሬውን ወደ 53ብር ዝቅ እሲኪያደርግ LC ባይፈቀድ ወይም ለጊዜው ከውጪ ምንም ባይገባ ሊባል አይችልም! ምክንያቱም የውጪ ምንዛሬ ክምችት የሌለው ኢኮኖሚ እና ከፍተኛ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ከውጪ ሸምቶ ለሚያስገባ ኢኮኖሚ አንድ ቀን ብዙ ነው)፡፡

በተጨማሪ የውጪ ምንዛሬ ተመን የሚሰራው በአመክንዬ ነው! ማለትም የገንዘብን ዋጋ በገበያ መሠረት መተመን (Floating Exchange Rate)፣ የገንዘብ ዋጋ መጠን በማዕካለዊ ባንክ የሚወሰንበት (Fixed Exchange Rate) እና አሁን ላይ የኢትዮጲያ መንግስት የሚመራበት ማዕከላዊ ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ጣልቃ የሚገባበት (Managed Floating Exchange Rate) ናቸው። ስለዚህ ከአመክዮ ውጪ ለጥቂት ቀን (ለበዓል ወቅት) የገንዘብ የመግዛት አቅምን በእጥፍ ማዳከም የሚል ውሳኔም አሰራር ሊኖር አይችልም!
አንድ ሰው "መንግስት በጣም አዋጪ ለሆኑ ፕሮጀክቶቹ ገንዘብ በብዛት አትሞ በፍጥነት ቢሰራበት ችግሩ ምንድን ነው?" አለኝ፡፡ ገንዘብ #እንደፈለጉ በማተም የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መሸፈን ይቻላል! ነገር ግን አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ኢኮኖሚው ከሚሸከመው የገንዘብ መጠን በላይ ከሆነ (መታተም ካለበት ዝቅተኛ መጠን ከበለጠ) እና ገንዘቡ ታትሞ የሚያርፍበት ሴክተር እና የአዲሱ ገንዘብ የስርጭት ሂደት ያልተጠና ሲሆን ነው አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ችግር መሆን የሚጀምረው፡፡


በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ገንዘብ በዘፈቀደ ሊታተም እና ሊሰራጭ አይችልም (በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ አስተዳደር ደካማነት ብዙ ገንዘብ ማተም የፈለገ ሀገር መብቱ ነው! ነገር ግን በዋጋ ንረት ዋጋ የሚከፍለው ኢኮኖሚው ነው)፡፡ ገንዘብ ለአንድ ኢኮኖሚ አስፈላጊም አደጋም ነው! ለዚህም ሲባል የገንዘብ ፖሊሲ (Monetary policy) በጠንካራ ተቋማት (በዋናነት በብሄራዊ ባንክ) በከፍተኛ ክትትል እንቅስቃሴው እንዲመራ ይደረጋል፡፡


በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት የተቀበለው ድንቁ ኢኮኖሚስት Milton Friedman በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ የገንዘብ አቅርቦት ማደግ ያለበት በየዓመቱ ከጠቅላላው ምርት GDP ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መጠን ወይም ፐርሰንት ነው (ስርዓቱ K-Percent Rule ይባላል) ስለዚህ የገንዘብ ኖት መጠን የሚወሰነው ጠቅላላ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሚኖረው እድገት እና እንቅስቃሴ አንጻር ከ3 ከመቶ ያልበለጠ ህትመት እንዲሆን ይመክራል፡፡


ጥያቄውን ያነሳልኝ ልጅ ኢኮኖሚክስን የተማረ ስላልነበር ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አለብኝ (እንዲሁም ኢኮኖሚክስን ላልተማራችሁ ሰዎች የሚረዳ ከሆነ) ጥያቄውን ለመመለስ ያህል……

የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በገበያው ያለው የቁሳቁስ እና የአገልግሎት አቅርቦት ከሰዎች የመግዛት ፍላጎት እና አቅም ጋር እየመዘነ ኢኮኖሚው በፈጠረው ሃብት አንጻር ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ገበያው በተለያየ መንገድ መልቀቅ አለበት፡፡

ነገር ግን በተለይ የዋጋ ንረት ላለበት ኢኮኖሚ (ነባሩ የዋጋ ንረት ከገንዘብ ፈሰስ አንጻር የተባባሰ ከሆነ) ተጨማሪ ገንዘብ ተጨማሪ የሸማች አቅም በመጨመር ምርት በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ገበያ ሳይመጣ ፉክክር እና ፍላጎትን በመፍጠር ያለው ምርት ላይ ዋጋ እንዲጨመር ሊያደርግ ይችላል (የዚህ አይነቱ አጋጣሚ በአንደኛው እና በሁለተኛው ጦርነት ወቅት በተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት፤ አፍሪካ ውስጥም በዝምባብዌ፤ በላይቤሪያ፤ ወዘተ ሆኖ ያውቃል)፡፡


#ለምሳሌ፡- መንግስት ግዙፍ የመስኖ ግድብን በመስራት 200ሺ ሄክታር የስንዴ ማሳን እስከማልማት የሚደርስን የፕሮጀክቱን ወጪ 20ቢሊየን ብር አትሞ ቢያዘጋጅ ብለን እናስብ፡፡ ቀጥታ ለመስኖ ግንባታ (ሲሚንቶ (የተወሰነ ግብዓት)፤ ብረት (የተወሰነ ግብዓት)፤ የግንባታ ማሽነሪ፤ ወዘተ) እና ለሰብል ዝግጅት (ምርጥ ዘር፤ የአፈር ማዳበሪያ፤ ለማጓጓዣ ነዳጅ፤ ጸረ-ሰብል መድሃኒት፤ ወዘተ) ኢኮኖሚው በብር ገዝቶ ማቅረብ ይችላል?


ስለዚህ ብር የሚያገለግለው ለሀገር ውስጥ ግብዓት (የውጪ ምንዛሬ ለማይጠይቁ ግብዓት ፍጆታ ካላቸው) እና የባለሙያ ክፍያ/የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ነው፡፡ ምክንያቱም የውጪ ምንዛሬ ለሚጠይቁ የፕሮጀክት ወጪዎች ብርን በቀጥታ መጠቀም ስለማይቻል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በቂ የውጪ ምንዛሬ በሌለበት ብርን በማተም ብቻ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ለማጠናቀቅ ከባድ ነው፡፡


ፕሮጀክቶች ለመጠናቀቅ ረጅም ጊዜ የመውሰድ ልምድ ስላላቸው እና አሁን በሀገራችን የሰዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ በማሽኖች ስላልተተካ በየፕሮጀክቶቹ እና ለፕሮጀክቱ ግብዓት የሚያቀርቡ ተቋማት ከፍተኛ የሰው ሃይል ስለሆነ የሚጠቀሙት ከፍተኛ ክፍያ (በደሞዝ እና በስራ ማስኬጃ) በጠቅላላ ሂደቱ በሙሉ ይወጣል፡፡


ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ለስራ ማስኬጃ የሚወጣው ወጪ ገበያ ውስጥ ለሸመታ በሚል ስለሚወጣ አቅርቦት እስካልተሻሻለ ያለው አነስተኛ አቅርቦት ላይ ገንዘብ ያላቸው ሸማቾች ሲጨመሩ ፉክክሩ እቃዎችን ከእጥረት የተነሳ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡


#ለምሳሌ፡- ይህ ፕሮጀክት እስኪጠናቀቅ ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 10ሺ በቤታቸው/በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ በቤት ያለስራ ተቀምጠው የነበሩ ወጣቶችን በወር የ5ሺ ብር ደሞዝተኛ ቢያድርግ፡ እነዚህ ሰዎች በየወሩ የ5ሺ ብር የአገልግሎትም ሆነ የቁሳቁስ ሸመታ ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ! ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ምርት ወደ ገበያ ከማምጣቱ በፊት ወጣቶቹ ወደ ሸመታ በመግባታቸው ፉክክሩን በመጨመር ዋጋዎችን ከፍላጎት በተነሳ ምክንያት (Demand Pull Inflation) ውድ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡


በሌላ ጎን እነዚህ የ5ሺ ብር አዳዲስ ደሞዝተኞች የባንክ ደብተር አውጥተው በወር አንድ አንድ ሺ ብር ማስቀመጥ ቢጀምሩ ባንኮች የተቀበሉትን ቁጠባ በኢንቨስትመንት መልኩ ቢያበድሩት ድጋሚ ገንዘብ ወደ ገበያው ፈሰስ ሆኖ ተመሳሳይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ በተለይ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብነት መያዝ ለለመደ ማህበረሰብ ከባንኩ ቁጥጥር ውጪ የሚውለውን ገንዘብ መጠን ስለሚጨምረው የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባቱ ሲባባስ በተለያዩ የMonetary ዘዴዎች ገንዘቡን ወደ ማዕከላዊ ባንኩ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡


አስተውሉ የታተመው ገንዘቡ ወደ ገበያ ሳይሰራጭ ለፕሮጀክት ብቻ ማዋል የሚባል አመክንዬ ሊኖር አይችልም! እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳይ ሲወራ ስለጥቂት ሰዎች ሳይሆን ስለድምር ተጽዕኖው ነው የሚወራው፡፡ ምን ማለቴ ነው ? በቀላሉ ከላይኛው ምሳሌ በመነሳት ፕሮጀክቱ ሊኖር የሚችለው አንድ ቦታ ላይ ነው፡ ሰዎቹም 10ሺ ናቸው የሚል ክርክር ቢነሳ ጠንካራ አይደለም! ምክንያቱም የማክሮ ኢኮኖሚውም ሆነ የዋጋ ንረት የሚሰላው የየአካባቢዎቹን አማካይ ጥቅል ውጤት ተወስዶ ነው፡፡
በኪራይ ቤት በመኖር እና በግል ቤት በመኖር መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልዩነት ምንድን ነው? አዲስ አበባ ውስጥ ተከራይ መሆን ለምን አስቸጋሪ እንደሆነ በመረጃ ተመልከቱ።


#ለምሳሌ፦ ተከታይቶ መኖር ከቤት ባለቤቶች ጋር ሲነፃፀር 3.5 እጥፍ ድሃ የመሆን እድል አለው!


ከዚህ ቀደም የሰራሁትን ጥሩ ጥናት አቅርቤላችኋለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት።


https://youtu.be/6Ad857-0wYk
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ።
የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት/Feasibility Study አዘገጃጀት! ከብቶች ማድለብ እና መኖ ዝግጅት ቢዝነስ ያዋጣል?


የራሳችሁን ቢዝነስ ለመጀመር ካላችሁ ካፒታል እና ለመስራት ካሰባችሁት ዘርፍ አንፃር አዋጪ ስለመሆኑ እንዴት ታረጋግጣላችሁ?


ዛሬ ላይ ሆናችሁ ከ10 ዓመት በኋላ ቢዝነሱ የሚደርስበትን ደረጃ እንዴት ትለካላችሁ?


ለመስራት ያሰባችሁት ቢዝነስ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች (Risk Analysis) እንዴት ቀድመው ያሰላሉ።


የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) እንዴት የተሳካ መሆኑን ማወቅ ይችላሉ።


ቢዝነስ ለመስራት ባለሃብት መሆን ግዴታ ነው? የቢዝነስ ምንጭ (30% ከራስ እና 70% የባንክ ብድር) እንዲሁም 30% የሆነውን መነሻ ካፒታል ሽርክና በማድረግ አዋጪ ቢዝነስ በጥናት መጀመር አይቻልም?


ይህንን በተመለከተ ሰፊ በምሳሌ የተደገፈ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ቢዝነስ ለመስራት ለምታስቡ፤ ተማሪ ለሆናችሁ፤ ቢዝነስ ለምታማክሩ እና የሰነድ ግምገማ ለምታደርጉ ሰዎች አዘጋጅቻለሁ ተመልከቱት ለሰዎችም እንዲደርስ አድርጉ።


https://youtu.be/GZoZ9jcmIJs