The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
198 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፦ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ አድርጓል።

ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ÷

- ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣

በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19 ከ02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።

ነገር ግን ኢኮኖሚው በነዳጅ ድጎማም ሆነ የድጎማ ማሻሻያ ሲገጥመው ሁኔታው ምን ሊመስል ይችላል የሚለውን በዚህ https://www.youtube.com/watch?v=pVL9RdHBPeU ቪዲዎ እንመለከታለን! (ከዚህ ቀደም የተሰራ ቪዲዮ ለማስታወስ)።
የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት/Feasibility Study አዘገጃጀት! ከብቶች ማድለብ እና መኖ ዝግጅት ቢዝነስ ያዋጣል?

የራሳችሁን ቢዝነስ ለመጀመር ካላችሁ ካፒታል እና ለመስራት ካሰባችሁት ዘርፍ አንፃር አዋጪ ስለመሆኑ እንዴት ታረጋግጣላችሁ?

ዛሬ ላይ ሆናችሁ ከ10 ዓመት በኋላ ቢዝነሱ የሚደርስበትን ደረጃ እንዴት ትለካላችሁ?

ለመስራት ያሰባችሁት ቢዝነስ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች (Risk Analysis) እንዴት ቀድመው ያሰላሉ።

የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) እንዴት የተሳካ መሆኑን ማወቅ ይችላሉ።

ቢዝነስ ለመስራት ባለሃብት መሆን ግዴታ ነው? የቢዝነስ ምንጭ (30% ከራስ እና 70% የባንክ ብድር) እንዲሁም 30% የሆነውን መነሻ ካፒታል ሽርክና በማድረግ አዋጪ ቢዝነስ በጥናት መጀመር አይቻልም?

ይህንን በተመለከተ ሰፊ በምሳሌ የተደገፈ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ቢዝነስ ለመስራት ለምታስቡ፤ ተማሪ ለሆናችሁ፤ ቢዝነስ ለምታማክሩ እና የሰነድ ግምገማ ለምታደርጉ ሰዎች አዘጋጅቻለሁ ተመልከቱት ለሰዎችም እንዲደርስ አድርጉ።

https://youtu.be/GZoZ9jcmIJs
#ለክርክር፦ መንግስት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወራት እድሜ ለመጨረስ ማቀዱ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ በመፍጠሩ ዙሪያ እና የዋጋ ንረት ላለበት ኢኮኖሚ እና #በቀጥታ ምርትን ወደ ገበያ ለማያመጡ ፕሮጀክቶች ቢሊየን ብሮችን በወራት እድሜ (በአጭር ጊዜ) ወደ ኢኮኖሚው መልቀቅ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ስጋቶች መፈጠር ዙሪያ ክርክር ቢነሳ የቱ ሚዛን ይደፋል?
የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ስሌት፦ በኢትዮጵያ የ6 ትሪሊዮን ብር ወይም የ111 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) አለ። የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር 117 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል የሚለውን ትንበያ ብንወስድ የነፍስ ወከፍ ገቢው በብር እና በዶላር ምን ያህል እንሆነ እና እንዴት እንደሚሰላ እንመልከት።

https://youtu.be/70s6v8Ybb0g
ብዙዎቻችን በግለሰብ እና በቤተሰብ ደረጃ መሰረታዊ ከማይባሉ ወጪዎች እየራቅን ያለነው ለምን ይመስላችኋል? አንድ የደለቡ በሬዎችን ለገበያ የሚያቀርብ ወዳጄ ሰሞኑን ገበያ እንዴት ነበር? ብዬ ስጠይቀው "በዚህ በዓል ብዙም ጠያቂ የለም!" አለኝ ለምን ይመስልሃል? ስለው "ሸማቹ ስጋን እንደ ቅንጦት ወስዶታል መሰለኝ!" አለኝ በተመሳሳይ ከበዓል በፊት አንድ ጋዜጠኛ ደውሎልኝ "የገበያ ዳሰሳ ስናደርግ ነጋዴዎች መሰረታዊ የማይባሉ ቁሳቁሶች ሽያጫቸው እየቀነሰባቸው እንደሆነ እየገለጹ ነው! ለምን ይመስልሃል?" ብሎኝ ነበር፡፡

#ለምሳሌ፡- ለበዓል ቤት የሚያድሱ፤ አዳዲስ የቤት እቃ ለበዓል የሚያስገቡ፤ አዳዲስ ልብስ እና ጫማ የሚፈልጉ፤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቡድን ወጥተው የሚዝናኑ፤ ወዘተ ሰዎች እየቀነሱ ነው እንደማለት ነው፡፡

በኢኮኖሚክስ የሰዎች ገቢ ሲከፋፈል ግብር ከመቆረጡ በፊት ያለ ገቢ (Gross Income)፤ ግብር ከተቆረጠበት በኋላ የሚቀረው ገቢ (Disposable/Net Income) እና ጠቅላላ መሰረታዊ ወጪዎችን ሸፍኖ የሚቀረው ገቢ (Discretionary Income) በመባል ይከፋፈላል፡፡

በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ ሰዎች ከግብር በኋላ የሚያገኙት ገቢ (Disposable Income) በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ እንደ የኢኮኖሚ የእድገት መለኪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ገቢያቸው ከመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ተረፈ ማለት (Discretionary Income) ይቆጥቡታል፤ ለትልልቅ ወጪዎች ያውሉታል (ቤት ወይም መኪና ለመግዛት) ወይም ኢንቨስት ያደርጉታል ተብሎ ይታመናል፡፡

አሁን እኛ እያጣን ያለነው Discretionary Income ነው! እንዴት? መሰረታዊ የሚባሉት የቤት ኪራይ ወጪ፤ የምግብ ግብዓት ወጪ፤ የትምህርት ወጪ፤ የትራንስፖርት ወጪ፤ የመብራት ወጪ፤ ወዘተ ከፍተኛ ከመሆናቸው የተነሳ የአብዛኛው ሰው ገቢ ከመሰረታዊ ወጪ እየዘለለ አይደለም፡፡

የመንግስት ሰራተኞች ገቢያችሁ ስንት ነው? ሲባሉ #እጄ_ላይ_የሚደርሰኝ? ይላሉ! ምን ማለት ነው? ማንም ማውራት የሚፈልገው በቀጥታ ለሸመታ ስለሚያውለው (Disposable/Net Income) በመሆኑ ነው፡፡ #ለምሳሌ፡- የ10ሺ ብር ደሞዝተኛ የሆነ የመንግስት ሰራተኛ የጡረታ ቁጠባ ሳይቀነስ ከግብር በኋላ በእጁ የሚደርሰው 8ሺ ብር አይሞላም (የገቢዎች ዌብሳይት ላይ ስሌቱን ማየት ይቻላል)፡፡

በተመሳሳይ አንድ ሰው በውድድር በሽልማት መልክ ወይም ሎተሪ ቆርጦ አንድ ሚሊየን ብር ቢያገኝ፡ ሰዎች የሚያውቁት የአንድ ሚሊየን ብር (Gross Income) ባለቤት እንደሆነ ነገር ግን ተሸላሚው በእጁ የሚያገኘው ከታክስ በኋላ 850ሺ ብር (Disposable/Net Income) ሊሆን ይችላል፡፡

በአንድ ሀገር ውስጥ የኑሮ ውድነት እየጨመረ ሲመጣ ገቢያቸው በዛው ልክ ማሳደግ ከሚችሉ ሰዎች ውጪ ያለው ማህበረሰብ የሚያደርገው ነገር የወጪ ድልድል መስራት ነው፡፡ ስለሆነም ያለውን የተጣራ ገቢ መሰረታዊ የሚባሉ ወጪዎች ላይ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ መሰረታዊ የሚባሉ ወጪዎች በዋጋ ንረት እያደጉ በመሆናቸው መሸፈን ስለሚቸገር ከመሰረታዊ ወጪ የተረፈ የሚባል ገንዘብ እጁ ላይ አይኖረውም፡፡ ስለዚህ ወደደም ጠላም  መሰረታዊ የማይባሉ ቁሳቁሶችም ሆነ የአገልግሎት ገበያ ውስጥ ላይገኝ ይችላል፡፡

በባህሪያቸው መሰረታዊ ወጪዎች የቤት ኪራይ፤ የምግብ ወጪ፤ የትምህርት ቤት፤ የመብራት፤ የትራንስፖርት፤ ወዘተ የሚዘለሉ ባለመሆናቸው ሸማቾች አዳዲስ ልብስ ከመግዛት እና ከመዝናናት እየሸሹ ይመጣሉ፡፡ ለበዓል ጭንቀቱ የበዓል የምግብ እና የመጠጥ ወጪዎችን መሸፈን እንጂ አዲስ መጋረጃ መቀየር አይሆንም እንደማለት ነው፡፡

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ በችግር ሲመታ ከሚታዩ ምልክቶች መካከል አንዱ ይሄ ነው! ስለዚህ ኢኮኖሚስቶች ወይ የመንግስት ግብር መጠን እንዲቀንስ ወይም ኢኮኖሚው በገፍ በማምረት የዋጋ ንረትን ወደታች እንዲያወርድ ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱም…….

ግብር ቀነሰ ማለት ገቢ ጨመረ ማለት ነው! ገቢ ጨመረ ማለት ከመሰረታዊ ሸመታ የሚተርፍ ገቢ ይኖራል ማለት ነው! በተመሳሳይ በገበያው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ቀነሰ ማለት ወጪ ቀነሰ ማለት ነው! ወጪ ቀነሰ ማለት ከመሰረታዊ ወጪዎች የሚተርፍ ገቢ ተገኘ ማለት ስለሆነ ነው፡፡

ሰዎች በመዝናኛ ቦታ የሚዝናኑ ሰዎች፤ መኪና የሚለዋውጡ ሰዎች፤ ቤት ለመግዛት የሚሻሙ ሰዎች ስለተመለከቱ ጠቅላላ ኢኮኖሚው እና ሸማቹን የሚወክሉ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ በየጎዳናው፤ በመንደሩ እና በየቤቱ መሰረታዊ የሚባለውን ወጪ ለመሸፈን በመቸገር ከመሰረታዊ በጣም መሰረታዊ ወደሚባል ልኬት የገባው ብዙ ነው፡፡ ይህንን ሀቅ ሸማች፤ ነጋዴም ሆነ መንግስት እየተረዱ መሄድ እና መፍትሄዎችን ማሰብ አለባቸው፡፡
የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካከል ያለው ልዩነት!

አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካሄድ ማለት ለማከናወን ያሰቡትን የቢዝነስ አይነት (በተለይ አዲስ ቢዝነስ) ጠቅላላ ሁኔታ መዳሰስ ሲሆን ለሚሰራው ቢዝነስ በዛ ያሉ አማራጮች ስለመኖራቸው ማሳየት እና የሚታሰበው ፕሮጀክት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው የሚያጣራ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ከብት ማደለብ የሚባል ቢዝንስ ስለማዋጣቱ ቢጠና እስካልተተገበረ ድረስ ሃሳባዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጪነት ጥናት ከዳታ በመነሳት፤ የቀደሙ አቅርቦት እና ፍላጎትን በመለካት፤ የፖሊሲ አማራጮች መኖራቸውን ማጣራት፤ በመጪው ጊዜ አቅርቦት፤ ፍላጎት እና ዋጋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ትንበያ መስራት፤ ቢዝነሱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መለየት፤ የሚጠበቁ መፍትሄዎችን ማሳየት፤ የፕሮጀክቱን ማህበራዊ ቅቡልነት ማረጋገጥ፤ ቢዝነሱ በገበያ ያለውን ተፎካካሪነት መለካት፤ ወዘተ ነው፡፡

ነገር ግን ፕሮጀክቶች (Business Plan) ገንዘቡ ከየት ተገኝቶ፤ ምን ያህል ሰዎች ተቀጥሮ፤ የት አካባቢ አምርቶ፤ ምን አምርቶ፤ እንዴት ሸጦ፤ እንዴት ማስታወቂያ አሰርቶ፤ እንዴት ምርቱን አከፋፍሎ፤ ስንት ሸጦ፤ በስንት ሸጦ፤ ወዘተ የሚሉ የታክቲክ እና የስትራቴጂ ስልቶችን በመንደፍ ከኢኮኖሚ አንጻር አትራፊ/አዋጪ ማድረግ እንደሚቻል የሚሰራ ሰነድ ነው፡፡

ከብት ማድለብ አዋጪ መሆኑ ሳይጣራ ከብት ለማድለቢያ መኖ የሚገዛበት ቦታ ሊመረጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) የሚሰራው የቢዝነሱ አዋጪነት (Feasibility Study) ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ኢንቨስትመንት ፍቃድ፤ የቦታ ጥያቄ ወይም ብድር ለመጠየቅ የሚሰራው ጥናት የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ፕሮጀክት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንዲሁም በፖሊሲ የሚደገፍ መሆኑን በማጣራት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቢዝነስ ፕላን ቢዝነሱን ላሰበው ሰው ብቻ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ዋና አላማው ኢኮኖሚያዊ አዋጪ (ትርፋማ) መሆኑ ብቻ ነው፡፡

በዚህ ዙሪያ በጥልቀት ያቀረብኩበትን ቪዲዮ https://youtu.be/GZoZ9jcmIJs
#Research_Gap ማውጣት የምትችሉባቸው 9 አማራጮች፦ አዲስ ጥናት ለመስራትም ሆነ ከዚህ በፊት ከተጠኑ ጥናቶች በመነሳት አዲስ ነገር ለመጨመር እና ጥሩ ጥናት ለማከናወን Research Gap የሚለይባቸው በርካታ አማራጮችን አስቀምጫለሁ እስከመጨረሻው ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙ አጋሩ።

https://youtu.be/yxh5T8vbI5o
ትናትን መማሪያ ብቻ በማድረግ ዛሬን ከነሙሉ ቀልቡ በንቃት የተጠቀመ ሰው ነገ ይዞ የሚመጣውን በሙሉ ለመቀበል አይቸገርም። ውጤታማ ቀን ይሁንላችሁ።
Channel photo updated
የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካከል ያለው ልዩነት!

አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካሄድ ማለት ለማከናወን ያሰቡትን የቢዝነስ አይነት (በተለይ አዲስ ቢዝነስ) ጠቅላላ ሁኔታ መዳሰስ ሲሆን ለሚሰራው ቢዝነስ በዛ ያሉ አማራጮች ስለመኖራቸው ማሳየት እና የሚታሰበው ፕሮጀክት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው የሚያጣራ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ከብት ማደለብ የሚባል ቢዝንስ ስለማዋጣቱ ቢጠና እስካልተተገበረ ድረስ ሃሳባዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጪነት ጥናት ከዳታ በመነሳት፤ የቀደሙ አቅርቦት እና ፍላጎትን በመለካት፤ የፖሊሲ አማራጮች መኖራቸውን ማጣራት፤ በመጪው ጊዜ አቅርቦት፤ ፍላጎት እና ዋጋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ትንበያ መስራት፤ ቢዝነሱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መለየት፤ የሚጠበቁ መፍትሄዎችን ማሳየት፤ የፕሮጀክቱን ማህበራዊ ቅቡልነት ማረጋገጥ፤ ቢዝነሱ በገበያ ያለውን ተፎካካሪነት መለካት፤ ወዘተ ነው፡፡

ነገር ግን ፕሮጀክቶች (Business Plan) ገንዘቡ ከየት ተገኝቶ፤ ምን ያህል ሰዎች ተቀጥሮ፤ የት አካባቢ አምርቶ፤ ምን አምርቶ፤ እንዴት ሸጦ፤ እንዴት ማስታወቂያ አሰርቶ፤ እንዴት ምርቱን አከፋፍሎ፤ ስንት ሸጦ፤ በስንት ሸጦ፤ ወዘተ የሚሉ የታክቲክ እና የስትራቴጂ ስልቶችን በመንደፍ ከኢኮኖሚ አንጻር አትራፊ/አዋጪ ማድረግ እንደሚቻል የሚሰራ ሰነድ ነው፡፡

ከብት ማድለብ አዋጪ መሆኑ ሳይጣራ ከብት ለማድለቢያ መኖ የሚገዛበት ቦታ ሊመረጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) የሚሰራው የቢዝነሱ አዋጪነት (Feasibility Study) ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ኢንቨስትመንት ፍቃድ፤ የቦታ ጥያቄ ወይም ብድር ለመጠየቅ የሚሰራው ጥናት የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ፕሮጀክት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንዲሁም በፖሊሲ የሚደገፍ መሆኑን በማጣራት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቢዝነስ ፕላን ቢዝነሱን ላሰበው ሰው ብቻ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ዋና አላማው ኢኮኖሚያዊ አዋጪ (ትርፋማ) መሆኑ ብቻ ነው፡፡

በዚህ ዙሪያ በጥልቀት ያቀረብኩበትን ቪዲዮ https://youtu.be/GZoZ9jcmIJs
በቅርቡ በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች እንዲሰበስቡ የተወሰነው የንብረት ታክስ ምን ማለት እንደሆነ፤ እንዴት እንደሚሰላ፤ የትኞቹን ቋሚ ንብረቶች ከግምት እንደሚከት፤ ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው እድል ወይም ስጋት በተመለከተ ያቀረብኩትን ቪዲዮ https://youtu.be/pU3tVqBuBjI ተከታተሉት።
በቅርቡ የገንዘብ የመግዛት አቅሙ ሊዳከም ይችላል? የኢትዮጵያ ብር ትክክለኛ ዋጋው ስንት እንደሆነ ለማወቅ ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሬ ተመን መለኪያው ነው። ታዲያ አንድ ዶላር በስንት ብር መመንዘር እንዳለበት ብሄራዊ ባንክ በገንዘብ ፖሊሲው በኩል ይወስናል።

በዚህ ቪዲዮ የገንዘብን የመግዛት አቅም ማዳከም (Devaluation) ማለት ምን ማለት እንደሆነ? ብር ከዶላር አንፃር በየቀኑ የሚፈጥረው መዳከም (Depreciation) ምን ማለት እንደሆነ! የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የብርን የመግዛት አቅም ሊያዳክም ስለሚችልበት እና ስለማይችልበት ምክንያት? የገንዘብ መዳከም ኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል እና ስጋት ምንድን እንደሆነ! ወዘተ ላይ ትንታኔ አለ።

https://youtu.be/hCZCFlmo_3Q
#የቀብድ ግብይት አዋጪ ነው! በዋጋ ንረት ወቅት ያለወለድ አበዳሪ አካል ተጎጂ ነው። ለወዳጃችሁ የዛሬ ዓመት ያበደራችሁትን ገንዘብ ዘንድሮ ሲከፍል ያንኑ ነው። በማህበራዊ ምክንያት የገንዘቡ የመግዛት አቅም ስለተዳከመ ወዳጅ ወለድ አስቦ አይሰጥም! አበዳሪ ለማካካሻ ወለድ አይጠይቅም።

በተመሳሳይ ቀብድ ቀድሞ ተቀባይ በማህበራዊ ተፅዕኖ የዋጋ ለውጥ ላለመፍጠር ይገደዳል። በተቃራኒው ቀብድ ቀድሞ በመክፈል የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ ስምምነት ውስጥ የወደቀ ሸማች ነባር ዋጋ ለመክፈል እድል ያገኛል።

#ለምሳሌ፦ ዛሬ 3ሺ ብር ለተባላችሁት እቃ ከወር በኋላ 3ሺ ብር ይዛችሁ ብትመጡ 4ሺ ብር ቢገባ ዋስትና የላችሁም! ነገር ግን በማህበራዊ ዋስትና ዘዴ ባንዱ #ቀብድ ከወር በፊት 1ሺ ብር ከፍላችሁ ቢሆን ከወር በኋላ 4ሺ ብር ዋጋ ላይ ላትወድቁ ትችላላችሁ።

ሻጮች የእጅ በእጅ ክፍያ እና የቀብድ ክፍያ መካከል ረጅም የጊዜ ልዩነት እና የዋጋ ልዩነት ላይፈጥሩ ይችላሉ የሚለው ታሳቢ ተደርጎ #እድሉ_ያላችሁ ሰዎች ለመሸመት ለወሰናችሁት ቁስ ፈጣን ውሳኔ ከሌላችሁ የዋጋ ንረት ተገማች ስላልሆነ በቀብድ መገበያየት መጥፎ አይደለም።

የዋጋ ንረት የመቀነስ ባህሪ ባለው ገበያ ላይ የቀብድ ተጠቃሚ ሻጭ ነው። በቀብድ 4ሺ ብር ያሰረው ዋጋ በገበያ ተመን 3ሺ ብር ቢወርድ ዋጋ ለመቀነስ ላይገደድ ይችላል።

የዋጋ ንረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ካልቀረ ለመሸመት ያሰቡትን በፍጥነት መሸመት ወይም እድሉ ካለ በቀብድ የጊዜ የዋጋ ለውጥን መቀነስ ይቻላል።

በቅርቡ አንዲት ልጅ ፈርኒቸር ቤት ትከራከራለች። "የዛሬ ወር ጫማ መደርደሪያ 2,800ብር እንዲሰራልሽ 500ብር ቀብድ ስጪ ሲለኝ ስላልወሰንኩ ዛሬ ላይ ያንኑ ምርት 4,000ብር ገብቷል አለኝ" ትላለች ሻጭ "ያንቺ ጥፋት ነው! ያኔ ወስነሽ ቢሆን በቅናሹ ይሰራልሽ ነበር! አሁንም ካልወሰንሽ በቀጣይ የሚደርስበትን የግብዓት ዋጋ አላውቅም" ይላል።
በቅርቡ የገንዘብ የመግዛት አቅሙ ሊዳከም ይችላል? የኢትዮጵያ ብር ትክክለኛ ዋጋው ስንት እንደሆነ ለማወቅ ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሬ ተመን መለኪያው ነው። ታዲያ አንድ ዶላር በስንት ብር መመንዘር እንዳለበት ብሄራዊ ባንክ በገንዘብ ፖሊሲው በኩል ይወስናል።

በዚህ ቪዲዮ የገንዘብን የመግዛት አቅም ማዳከም (Devaluation) ማለት ምን ማለት እንደሆነ? ብር ከዶላር አንፃር በየቀኑ የሚፈጥረው መዳከም (Depreciation) ምን ማለት እንደሆነ! የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የብርን የመግዛት አቅም ሊያዳክም ስለሚችልበት እና ስለማይችልበት ምክንያት? የገንዘብ መዳከም ኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል እና ስጋት ምንድን እንደሆነ! ወዘተ ላይ ትንታኔ አለ።

https://youtu.be/hCZCFlmo_3Q
የቢዝነስ አዋጪነት መለኪያዎች/NPV, IRR, CBR, Payback Period ትርጉም ምንድን ነው? እና እንዴት ይሰራል?

1. Net Present Value
2. Internal Rate of Return
3. Benefit Cost Ratio
4. Payback Period

ለመጀመር ያሰባችሁት ቢዝነስ በቀጣይ ዓመታት አዋጪ ስለመሆኑ እና አዋጪ ስላለመሆኑ ከመጀመሩ በፊት ለመለካት የሚያስችሉ መሰረታዊ ነጥቦችን አቅርቤላችኋለሁ። በጣም የሚጠቅም እና በቀላሉ በምሳሌ የቀረበ በመሆኑ እስከመጨረሻው ተከታተሉት ለሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩ።

https://youtu.be/VpmcOTD90h8
🤔1

በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?፦ በቀላሉ ሁሉንም መስፈርት ባሟላ መልኩ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል በምሳሌ በ100ሺ ብር የሚሰራ የምርጥ ቡና ቢዝነስ ፕላን በአማርኛ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተመልከቱት፤ ናሙናውን በመጠቀም ወደ የምትፈልጉት ቢዝነስ አይነት መለወጥ እንዲሁም ለሌሎች ማጋራት ትችላላችሁ።

https://youtu.be/7R9GyixR59s
የ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን.pdf
355.1 KB
የቢዝነስ ፕላን/ 4 Pages Business Plan
እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ።