The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
#ወሳኝ_መረጃ!

ፍራንኮ ቫሉታ ተፈቀደ! ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች ውጭ ሁሉም ዕቃዎች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተፈቅዷል! (ይህ ውሳኔ በገበያ በሚወሰን የምንዛሬ ተመን ስርዓት ውስጥ ተጠባቂ ነው)::
#ለማስታወስ

Fixed Exchange Rate እና Floating managing Exchange Rate ስርዓት ባለበት ፍራንኮ ቫሉታ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው የችግር ጊዜ ውሳኔ ነው በሚል ክርክር ነበረ! በገበያ በሚወሰን Floating Exchange Rate ስርዓት ባለበት የጥቁር ገበያን ለማቀጨጭ እና አቅርቦት ለማሻሻል አዎንታዊ ሚና ሊኖረው ይችላል!

የዛሬ 2 ዓመት https://www.youtube.com/watch?v=xUb-q2QzJBs
#የፍራንኮ_ቫሉታ (ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በሰፊው መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በሰርኩላር አሳውቋል!

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የፍራንኮ ቫሉታ በሰፊው መፈቀዱ የሚኖረው እድል እና ስጋት ምን ሊሆን እንደሚችል እንመልከት https://youtu.be/LnhNtC-omYw

ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ #የውጪ_ምንዛሬ የደም ስር ነው! በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ #ከዶላር ተፅዕኖ ውጪ የሆነ ጉዳይ የለም!

በቆሎ እሸት ጠብሶ የበላ ሰው ከዶላር ጋር ንኪኪ አላደረገም ብላችሁ ታስባላችሁ?

አንዳንድ ሰዎች ከውጪ ምንዛሬ ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ጉዳይ የለም ይላሉ.....

አንዳዶች ደግሞ ምንም ከውጪ ምንዛሬ ጋር  የማይገናኝ የሀገር ውስጥ ምርት የማክሮ ኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ሁኔታን ተከትሎ ዋጋው ለምን ይለዋወጣል ይላሉ....

የአፈር ማዳበሪያ ለመሸመት የውጪ ምንዛሬ የሚፈልግ ኢኮኖሚ በስንዴ ምርት ዘርፍ የውጪ ምንዛሬ ጥገኝነቴን ቀንሻለሁ ሊል ይችላል?

መሰረታዊ ተፅኖውን በምሳሌ እንመልከት.....https://youtu.be/xKeKi-9kExs?si=hWChZ3OLYDLL6I8i
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከIMF ጋር ከሰራው ሪፎርም በኋላ በቀጣይ 4 ዓመታት ማክሮ-ኢኮኖሚው ምን እንደሚመስል የተዘጋጀውን እቅድ እንመልከት!

የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማድረግ ለIMF የሪፎርም የድጋፍ ጥያቄ አቅርቦ ሲገመገም ቆይቶ ሰነዱ ፀድቆ የ4 ዓመት የድጋፍ እና የተግባር እቅድ (144 ገፅ እቅድ) መተግበር ጀምሯል።

IMF ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፍ (ብድር እና እርዳታ) ማድረግ ጀምሯል! አፈፃፀሙን የሚከታተልበት የ4 ዓመት የኢኮኖሚ መለኪያዎች (የኢኮኖሚ እድገት፤ የዋጋ ንረት፤ የበጀት እና የንግድ ጉድለት፤ FDI፤ የውጪ እዳ፤ የገንዘብ ፈሰስ፤ የሀገር ውስጥ ገቢ እና ወጪ፤ የንግድ ሚዛን) በተመለከተ ከ2025-2029 ድረስ ትንበያ አስቀምጧል።

በዚህ ሰነድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለምን ሪፎርም እንደሚያስፈልገው እና ከሪፎርሙ ስለሚጠበቁ ውጤቶች በዝርዝር አስቀምጧል።

መንግስት ከሪፎርም ሰነዱ በመነሳት ለውጦች ማድረግ ጀምሯል (ነፃ ምንዛሬ፤ የግብር እና የቀረጥ ማሻሻያ፤ የድጎማ አይነት፤ የወለድ ተመን፤ የገበያ ቁጥጥር፤ ወዘተ)።

የIMF ድጋፍ በየዓመቱ አፈፃፀም እየተለካ የሚለቀቅ በመሆኑ ለውጦች በመንግስት ቁጥጥር ስር ብቻ መሆን አይችሉም!

በዚህ ቪዲዮ ሰነዱ የያዘውን እቅድ እና IMF ከሪፎርሙ በኋላ ይመዘገባል በሚል ያስቀመጠው ትንበያ በዝርዝር እንመለከታለን። https://youtu.be/M1IxocN6HNY
#ለመረጃ!

የወርቅ መግዣ የዋጋ ማሻሻያ መመሪያ! ከነሐሴ 21/2016 ዓ.ም. ጀምሮ በማዕከልና በክልሎች ባሉ የወርቅ መግዣ ቅርንጫፎች በኩል የሚገዛውን ወርቅ በተመለከተ የተሻሻለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከIMF ድጋፍ ሳይጠብቅ ሪፎርም (በዋናነት Floating Exchange Rate) ማድረግ ይችል ነበር?

የIMF ዋስትናን ተማምኖ የኢኮኖሚ ሪፎርም ያደረገው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቃል የተገባለትን የውጪ ድጋፍ ቢያጣ ምን ይገጥመዋል?

እስካሁን ባለው ሂደት የIMF የሪፎርም ድጋፍ ለመንግስት ምን አይነት እድል ሰጥቷል?

መንግስት ከIMF የተገባለት ድጋፍ እንዳይቋረጥ ምን አይነት እርምጃዎች ላይ ትኩረት እያደረገ ነው? ወደፊትስ ምን ላይ ትኩረት ይሰጣል?

ከላይ ለተዘረዘሩ ቁልፍ ጥያቄዎች መልስ የሰጠ ትንታኔ በመሆኑ እንዲመለከቱት ተጋብዘዋል!https://youtu.be/TCTKIILscV8

ቀላሉ ኢንቨስትመንት አክሲዮን መግዛት ቢሆንም አክሲዮን ለመግዛት ከግምት መግባት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ!

የአክሲዮኑ አይነት፤ የሚገዛበት ምክንያት፤ የሚገዛው መጠን፤ የሚገዛበት ወቅት፤ የመረጃው ምንጭ፤ ወዘተ....

በዚህ ወቅት (ከፍተኛ የዋጋ ንረት እየተጠበቀ) አክሲዮን መግዛት ምን ያህል ያዋጣል?

ይህንን ትንታኔ ተጠቀሙበት...https://youtu.be/PddDimDUf00

የአዲሱ_የታሪፍ_ማስተካከያ_መረጃ.pdf
2.6 MB
#መረጃ

#EEU : የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያደረገው የታሪፍ ጭማሪን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ በዚህ ፋይል ተያይዟል።

ፋይሉን ከፍተው በዝርዝር ይመልከቱ! መረጃው ከ@tikvahethiopia ነው
የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ የሚጨምረው ኢኮኖሚው ወይስ ፖለቲካው?

ደሞዝ በመጨመር እና የደሞዝ ግብር ባለመቀነስ መካከል ያለው ተቃርኖ....

በጀት እና ደሞዝ የፊስካል ፖሊሲ መሳሪያዎች ቢሆኑም ውሳኒያቸው ፖለቲካል ነው.....

በዓለም ላይ ከፍተኛ  (ሲዊዘርላንድ ቀዳሚ ነች) እና ዝቅተኛ ደሞዝ (ኢትዮጵያ ቀዳሚ ነች) የሚከፍሉ 10 ሀገራት ዝርዝር.....

ከምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ በኋላ መንግስት የሰራተኞችን ደሞዝ ለመጨመር ወስኗል! የውሳኔው ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ አመክንዮ....

ይህንን ትንታኔ ይመልከቱት.....https://youtu.be/cnnlajub0GQ
#መረጃ

የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል! 

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።