#Window_Shopping
ስንቶቻችሁ ዋጋን ከተለያየ ሱቅ ካጣራችሁ በኋላ ለመግዛት ትወስናላችሁ?
በሀገራችን ዋጋ ንረት ፈጣን በሆነበት ሁኔታ አምና እና የዛሬ ደሳምንት በጠየቁበት ዋጋ አንድን ቁስም ሆነ አገልግሎት እርግጠኛ ሆኖ ማግኘት ያስቸግራል! ምክንያቱም የዋጋ መጨመር ገበያውን #ተገማች እንዳይሆን ስላደረገው ነው!
ገበያን እና ዋጋን ማጥናት ልምድ መሆን ያለበት ነገር ነው! #ለምሳሌ፡- አሁን ላይ ሰዎች የእረፍት ጊዚያቸውን ምንም የሚገዙት ነገርም ባይኖር በዘመናዊ #ሞሎች እና በገበያዎች በመዞር የማንኛውንም ቁሳቁስም ሆነ አገልግሎት የተለያየ ዘዴን በመጠቀም ዋጋን በቦታ ከፋፍለው መጎብኘት እና መጠየቅ የተለመደ ነው! ይህ ሁኔታ የገበያ ጥናት ይባላል!
በሀገራችን ከተለመደ ሱቅ የተጠራን ዋጋ (ጨመረ እንዴ? አልያም ቀነሰ እንዴ? በሚል ከሻጮች ብቻ ከሚወሰድ ማረጋገጫ ወስኖ መግዛት የተለመደ ነው!) የዚህ አይነቱ አካሄድ ተመሳሳይ እቃን ተመሳሳይ ሰፈር ውስጥ ቢሆንም ከተለያየ ሱቅ የተለያየ ዋጋ አውጥቶ ለመግዛት ይዳርጋል!
#ለምሳሌ፡- አንድን ቁስ ከሁለት እና ከሶስት ሱቅ ቢጠየቅ የተለያያ ዋጋ የሚኖራቸው እድል ይኖራል (ልታረጋግጡት ትችላላችሁ!) አንዳንዴ ሻጮች የገዢውን ሁኔታ በመመልከት ከፍ እና ዝቅ የማድረግ አዝማሚያ የምትመለከቱባቸው ትክክለኛውን ዋጋ የዘለለ ግምት በእቃው ላይ እንደሚያስቀምጡ ያሳያል (ላንተ ብዬ! ላንቺ ስል! በሚሉ ቃላቶች የተወሰነ ዋጋ ዝቅ የማድረግ ልምድ አለ! ይህ ልምድ ነጋዴ ካስቀመጠው የትርፍ መጠን ለማንም ሲል እየወረደ ሳይሆን ገበያው በመረጃ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑን ስለሚረዳ ነው!)፡፡
በተለይ እንደወቅቱ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚከሰትበት ጊዜ የዋጋ ጥናት እያደረጉ የሚገኝ እድልን (Opportunity Cost) መጠቀም ወሳኝ ነው! #ለምሳሌ፡- አትክልትን ከሰፈር ውስጥ መግዛት ትልቅ ገበያ ሄዶ ከመግዛት ጋር ሲነጻጸር በኪሎ ያለውን ቅናሽ፤ ገበያው ድረስ ለመሄድ የሚያስወጣውን ወጪ በመቀነስ ተጠቃሚ የሚያደርግ ከሆነ ከገበያ ሄዶ በመግዛት ወጪዎችን መቆጠብ ይቻላል፡፡
በልምድ ደረጃ ደንበኛ የሚለው አስተሳሰብ እና እምነት በዋጋ መሸወድን የሚፈጥርበት እድል አለ! ስለዚህ በትክክል ደንበኛ የሆናችሁበት ሱቅ ከሌሎች አጎራባች ሱቆች የተለየ የዋጋ ለውጥ እንዳለው የማጣራት ልምድ ማዳበር፤ የሌሎች ሱቆች ዋጋ መረጃ እንዳላችሁ ማሳወቅ፤ ከባለሱቁ ጋር ያላችሁን ማህበራዊ ግንኙነት በማይጎዳ መልኩ ደንበኝነትን መምራትም ያስፈልጋል (አበዳሪያችሁ ከሆነ በችግር ጊዜ ሊቀጣችሁ ይችላል!)፡፡
እኔ ለምሳሌ አንድ ቁስ ለመግዛት ሳስብ (ተከራይ ስለሆንኩ ደንበኛ የሚባል ነገር የለኝም!) ከጫፍ ሱቅ ጀምሮ እስከ ጥግ ድረስ ካሉት ላይ በመደዳ እየጠየኩ እሄድ እና የዋጋ ለውጥ ያስተዋልኩበት ጋር ስደርስ እገዛለሁ! እንድ ብር እና ሁለት ብር የመቀነስ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ገበያ እና ዋጋ ማጥናት ልምድ መሆን ስላለበት ነው! ሁለት ብር ያላከበረ ኢኮኖሚስት ትምህርቱን መናቅ ነው የያዘው!
አስቤዛን በጅምላ ወይም በጥቅል ገዝቶ መጠቀም የነጠላ ቁስ ዋጋ ስንት እንደሆነ እና ባላፈው ጊዜ ከገዛችሁበት ዋጋ የተፈጠረውን ለውጥ ልትረዱ አትችሉም! ስለዚህ የመሰረታዊ ሸቀጦቻችሁን ዋጋ በደንብ መረዳት ጥሩ ነው።
አሁን ላይ የገበያ ጥናት አማራጩ ሰፊ ነው! Online በሚገኙ ገበያዎች ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ቁሶች እና አገልግሎቶችን ዋጋ የእግር ጉዞ ሳያደርጉ ለማወቅ ያግዛል! በተመሳሳይ የዋጋ ጥናት የሌለበት ግብይት መደበኛ ወጪ ያለበትን ሁኔታ አለመረዳት፤ አላስፈላጊ ወጪ መፍጠር እና መሸወድ እና መዋከብን የሚፈጥር በመሆኑ በዝና ከሚያውቁት ገበያ ብቻ ዋጋን ሳያጣሩ ከመሸመት እና ከመጠቀም ለመከላከል ሲባል ዓለም ሁሉ የሚጋራውን የገበያ ጥናት(Window Shopping) ወስኖ ከመሸመት በፊት መለማመድ ተገቢ ነው።

#Window_Shopping፡ የተሻለ ዋጋ ፍለጋ የተለያየ ገበያ ማጥናት ማለት ነው!
ዛሬ ስልካችሁን አውጥታችሁ የዕለቱን የምንዛሬ ዋጋ አጣሩ!
በእርግጠኝነት የተሻለ የገበያ የምንዛሬ ዋጋ ያለበት ገበያ ያገኛሉ!
#ለምሳሌ: በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጠውን የሮሃ የግል የምንዛሬ ቢሮን የጥቅምት 11/2018 የምንዛሬ ዋጋ ተመልከቱ!
ምክንያታዊውን ምረጡ! ወስኑ! የተሻለ ምንዛሬ ኢንቨስትመንት ነው!
የየለቱን የምንዛሬ ዋጋ ለመከታተል👇
ቴሌግራም፡ https://t.me/roohaforex
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/share/19hCtXhSH3/?mibextid=wwXIfr
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/rooha-forex-bureau/