እጅግ የተጎሳቆሉ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ንፁህና ውብ መንደር የቀየረው ''የበጎነት መንደር"
በአዲስ አበባ ከተማ ከተከናወኑ ግዙፍ የልማት ስራዎች በተጨማሪ የላቀ ትርጉም ያለውና እጅግ የተጎሳቆሉ እና ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ንፁህ እና ውብ መንደር በመቀየር የብዙዎችን እንባ ያበሰ እና ከአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ያላቀቀ እንዲሁም ለሰው ክብር የሚመጥን አኗኗር ያጎናፀፈው ''በጎነት መንደር'' የላቀ ትርጉም ያለው ነው፡፡
''የበጎነት መንደር'' በተለይም የቤት እጥረት ችግርን በመቅረፍ በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ዜጎችን በዘላቂነት በማቋቋም ምቹ መኖሪያ አካባቢ በመፍጠር የነዋሪውን ማህበራዊ ግንኙነት ያጠናከረ እና የመደጋገፍ ባህልን ያደሰ ነው ፡፡
ለሰው ክብር ቅድሚያ በመስጠት የመኖሪያ ቤት ችግር በዘላቂነት መፍታት ያስቻለው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በልደታ፣ በአራዳ፣ በኮልፌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በየካ:በለሚ ኩራና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ሌሎች የበጎነት መንደሮች በመገንባት የጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለኑሮ ምቹ የሆኑ፣ ንጽሕናቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች፣ የጋራ መገልገያዎች እና የጋራ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ዘመናዊ፣ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎችና ሕፃናት ቦርቀው የሚጫወቱባቸው ምቹ የስፖርት ሜዳዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡
አስተዳደሩ በመጠለያ እጥረት፣ በከፍተኛ የኪራይ ውድነት እና ለኑሮ ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና አቅመ ደካሞችን በዘላቂነት ለማቋቋም ያስችል ዘንድ በርካታ ብሎኮችንና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ለተጠቃሚው እያስተላለፈ ይገኛል፡፡
የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ችግር በእጅጉ መቀነስ ያስቻለው ይህ የበጎነት መንደር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በበጎ ፈቃደኛ ዜጎች ባለሃብቶችና ተቋማት ትብብር በመገንባት የነዋሪውን ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር መቹ ለኑሮ ተስማሚ ከተማን መፍጠር ያስቻለ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ነው ፡፡

ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በጨረታ እንደሚሸጥ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በግልጽ ጨረታ ያቀረባቸውን ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ25/02/2019ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ሚድያዎች ምንጩ ያልታወቀና ያልተረጋገጠ የተዛባ መረጃ ኃላፊነት በጎደለዉ አግባብ ከማሰራጨታቸዉ በፊት ከትክክለኛዉ እና ኃላፊነት ከተጣለበት አካል መረጃ መጠየቅ ይገባቸዋል። መረጃ የማግኘት መብትም አላቸዉ ።
አዲስ አበባ በፈጣን የልማት ጉዞ ላይ ነች። ከተማዋ እያስመዘገበች ያለችውን የልማት እድገት ዓለም አቀፍ ተቋማት በራሳቸዉ መንገድ መረጃ እና ማስረጃ ሰብስበዉ ካረጋገጡ በኃላ እየተደነቁ እዉቅና እየሰጧት ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በመረጃ እና ማስረጃ በቀላሉ ማረጋገጥ ሲችሉ እውነታውን ወደ ጎን በመተው ኃላፊነት በጎደለዉ አግባብ አዛብተዉ ያሰራጫሉ።
የከተማ አስተዳደሩ በመሬት አስተዳደር ዘርፍ ሲታዩ የነበሩ የቢሮክራሲ እንግልቶችን፣ የአሠራር መዘግየቶችን፣ ሕገ-ወጥ ደላላነትንና ለብልሹ አሠራር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ክፍተቶችን ለማስወገድ በርካታ የሪፎርም ሥራዎች አከናውኗል። ሪፎርሙም ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እንግልት መቀነስ ያስቻለ ከመሆኑም ባሻገር፣ የሕዝብና የመንግስትን ውስን ሀብት ከብክነትና ከሕገ-ወጥነት ለመጠበቅ አስችሏል።
✅ ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የፎርቹን ጋዜጣ በህትመቱ ኃላፊነት በጎደለው አግባብ የተዛባ መረጃ ካሰራጨ እና ብዙዎች እንዲወዛገቡ ካደረገ በኃላ መሳሳቱን ሲያዉቅ አርሟል።
ስህተትን አመኖ እርምት ማድረግ ተገቢ ቢሆንም እንደ አንድ የመረጃ ምንጭ የመረጃዎችን ትክክለኛነትና ታአማኒነት አስቀድሞ ከምንጩ ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
በቅርቡ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባሳለፈው ውሳኔ የተወሰኑ ነባር አሠራሮች የነበሩባቸውን ሂደት ማሳጠር እንጂ ከመሬት አሰጣጥ ደንብ ፣ወይም መመሪያ አልወጣም።
ነገር ግን በሰነድ አልባ መሬትና በካቢኔ የተወሰኑ የመሬት ጉዳዮችን የማከፋፈል ኃላፊነትን ከዚህ ውሳኔ ጋር በማያያዝ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከውሳኔው ይዘት ጋር የማይገናኝ እና ሕብረተሰቡን ሊያደናግር የሚችል ነው።
✅ የውሳኔው ዋነኛ ዓላማ፦ እንግልት እና መዘግየትን መቀነስ ነዉ!
ከውሳኔው ዋነኛ ይዘቶች አንድ ሕጋዊ ይዞታ ወደ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ይዞታ እንዲከፈል የሚቀርብ ጥያቄ የካቢኔ ስብሰባን መጠበቅ ሳያስፈልግ አሳማኝ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥምና በመሬት አስተዳደር ቢሮ ተረጋግጦ ሲቀርብ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ፀድቆ እንዲፈጸም የሚያስችል አሠራር ነው።
ይህ አሠራር የተዘጋጀው ዕለት ተዕለት ለሚከናወኑ መደበኛ የመሬት አገልግሎቶች ሳይሆን፣ አልፎ አልፎ በግለሰቦች ወይም በባለመብቶች ጥያቄ ሲቀርብና ሲያጋጥም በጥንቃቄ የሚተገበሩ ውስን ጉዳዮችን ብቻ የሚመለከት ነው። ምክንያቱም ሕጋዊ ይዞታዎችን ያለበቂ ምክንያት መከፋፈል የሕዝብን ሀብት ለሕገ-ወጥ ተግባርና ለግል ጥቅም ለማዋል የሚያስችሉ ክፍተቶችን ሊፈጥር ይችላል።
ስለዚህ በዚህ ዓይነት ውሳኔዎች ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ የግለሰቦችን መብት ለመጠበቅ፣ ሕገወጥ የመሬት ንግድን ለመከላከልና ተገልጋዮች በሕጋዊው መንገድ ብቻ ያለ አላስፈላጊ እንግልት አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የተወሰደ ማሻሻያ ነው።
✅ የተዛባ መረጃ ሕብረተሰቡን እንዳያደናግር!
በዚህ ሁኔታ የአሠራሩን ይዘት በማዛባት፣ በተሳሳተ መንገድ በማቅረብና ያልወጡ ደንቦችን እንደወጡ በማስመሰል የሚሰራጩ መረጃዎች ተገልጋዩን ለግራ መጋባትና ላላስፈላጊ እንግልት ሊዳርጉ ስለሚችሉ ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን።
በተለይም የመሬት አስተዳደርን በተመለከተ በሕጋዊ መረጃ ፋንታ በወሬና በደላላ ትርክት ላይ ተመስርቶ መንቀሳቀስ ሕብረተሰቡን ለተጨማሪ ወጪ፣ ለጊዜ ብክነትና እንግልት ይዳርጋል። ስለዚህ ማንኛውም የመሬት አስተዳደር ጉዳይ ሲኖር በተቋሙ የሚሰጡ ግልጽ ማብራሪያዎችን መከታተል ወይም ከሕጋዊ የመንግሥት የመረጃ ምንጮች ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
✅ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሚሰራው ሪፎርም የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው!
ስለዚህም ሕብረተሰቡም በተዛቡ መረጃዎች እንዳይደናገር፣ በደላሎች ተጽዕኖ ሥር እንዳይወድቅና ማንኛውንም ጉዳይ በህጋዊ መንገድ እንዲያስፈጽም ጥሪ እናቀርባለን።
የሕዝብ ሀብትን የመጠበቅ ኃላፊነት የአስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ግዴታ ነው።
የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ከ1997- 2007 ዓ/ም ባለዉ ጊዜ ውል ተይዞላቸዉ የተገንቡ እና አገለግሎት እንዲሰጡ የተደረጉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጥራት ጉድለት ሰለታየባቸዉ በጥናት ተለይቶ ነዋሪዎች ላይ ምንም ጉዳት ሳይፈጠር የሙያዊ እርምት ሥራ ሊደረግ ነው።
አዲስ አበባ፦ ከ1997- 2007 ዓ/ም በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተስተዋሉ የግንባታ ጥራትና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት በጥናት የተለዩ ሕንፃዎች ላይ የማስተካከያ ሥራ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከ1996- 2007 ዓ.ም ድረስ በተገነቡ ሕንፃዎች ላይ የታዩ የግንባታ ጥራትና መሰል ችግሮችን ለመለየት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።
በጥናቱ የችግሮቹ ዓይነትና ደረጃ ተለይቶ ቅድሚያ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ሕንፃዎች ተለይተዋል። በዚህም ከነዋሪዎች ጋር በመግባባት፣ የሥራ ተቋራጮችን በመመደብና የማስተካከያ ሥራዎችን ለመጀመር ዝግጅ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አመልክቷል።
በተጨማሪም በጥናቱ የተመለከቱ ጉድለቶችን በተመለከተ አስፈላጊውን የሰነድና የማስረጃ ዝግጅት በማድረግ፣ በውል ግዴታ መሠረት ተጠያቂነትን ለማስፈንና ተገቢውን የሕግና የውል እርምጃ ለመውሰድ እየተሠራ መሆኑን አሳውቋል።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል ::
በ2018 በጀት ዓመት በተለያዩ ሳይቶች የተጀመሩ ቤቶች የግንባታ ጥራታቸውን በመጠበቅ፣ የሥራ ፍጥነትን በማሳደግና ዲዛይኖችን በማሻሻል ለነዋሪዎች ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ አካባቢዎችን ለማቅረብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ የመማክርት ጉባዔ በቀጣይ በሚከናወኑ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው በቤት ልማት፣ በመንግሥት ቤቶች አስተዳደር እንዲሁም በቤት ጥናትና መረጃ አያያዝ ረገድ የሚሰጣቸውን የተቀናጁ አገልግሎቶች በማዘመን፣ ፍትሐዊና ቀልጣፋ አሠራር ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል። የመማክርት ጉባዔውም የቀጣይ ሥራዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን በሚያስችለው የድጋፍና ክትትል ዕቅዱ ላይ መክሯል፡፡
የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ የድጋፍና ክትትል ሥራውን አስፈላጊነት ሲያስረዱ፤ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ፍትሐዊና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ማድረግ ዋነኛው ግብ መሆኑን ገልጸዋል። አሠራሩ መንግሥትንና ሕዝብን የበለጠ በማስተሳሰር የመንግሥትን ቅቡልነት ለማረጋገጥና የታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ ለመሙላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ታምኖበት የተዘጋጀ መሆኑንም አክለዋል።
የቢሮው የመማክርት ጉባዔ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ተከተል ተጋፋው በበኩላቸው፤ የተቀናጀና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሰፍን ጉባዔው በተጨባጭ መሥራት እንዳለበትና ይህም ከሁሉም አባላት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
የውይይት መነሻ ዕቅዱን ያቀረቡት የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ኃይለማርያም ጌታነህ ሲሆኑ በቤት ግንባታ ሳይቶች ፣ ከማዕከል እና በክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም