ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂጃለሁ። ውይይታችን በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ነበር። በተጨማሪም፣ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳየውን የመደመር መጽሐፌን የሩሲያኛ ዕትም ለፕሬዚዳንት ፑቲን አበርክቼላቸዋለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ባለፉት 5 ዓመታት በመዲናችን 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች ማስተላለፍ የተቻለዉ አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ ነዉ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል ::
ከተማ አስተዳደሩ በቤት ግንባታ ልማት ሂደት ዉስጥ የመንግስት ሚና ቀዳሚ በማድረግ የተለያዩ የግንባታ አማራጮችን በመዘርጋት ቤት አልሚ ሪል እስቴቶች፤የግል አልሚዎች ህብረት ስራ ማህበራት እና በጎ ፈቃደኞች ተቀናጅተዉ በመኖሪያ ቤት ልማት ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡
በተለይም ከተማ አስተዳደሩ የአጭር ጊዜ እቅዶችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ ስራዎችን በመተግበር ላይ ሲሆን በተጨማሪ በዘንድሮው ሩብ አመት ብቻ የመርካቶ በጎነት መንደርን ጨምሮ ከ4 ሺ 200 በላይ ቤቶች በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
እነዚህ የቤት ግንባታዎች ንጹህ የመኖሪያ አካባቢን የፈጠሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ምቹ አካባቢ በመፍጠር የልጆች መጫወቻ የተሰራላቸው ሰው የሚንቀሳቅስባቸው አና የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ ስፍራ የተሟላላቸው የዜጎችን ክብር የሚመጠኑ መኖሪያ መንደሮች ናቸው፡፡
በአጠቃይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ተነሺዎችን፤ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉን፤አረጋዉያንንና የሃገር ባለዉለታዎችንና ሌሎች ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አካታች የሆነ የልማት ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር የ70 ግራም ዳቦ ዋጋ ላይ ቅናሽ አደረገ።
የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር በነፃ ገበያ የሚሸጥ የ70 ግራም ዳቦ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።
ማህበሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ እንዳሳወቀው፣ ከክፍለ ከተሞች ዳቦ አምራች ማህበራት አመራሮች ጋር በዳቦ ዋጋ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ ቀደም ሲል በነፃ ገበያ 15 ብር ይሸጥ የነበረው 70 ግራም ዳቦ አሁን 13 ብር እንዲሸጥ ውሳኔ አሳልፏል።
የዋጋ ማስተካከያው በነፃ ገበያው ዋጋቸውን በራሳቸው ወስነው ሲሸጡ የነበሩ የግል ዳቦ ቤቶችን ብቻ የሚመለከት መሆኑንም የማህበሩ አመራሮች ገልጸዋል። ቅናሹ የሸገር ዳቦን፣ የብርሃን ዳቦን እንዲሁም በመንግስትና የግል አጋርነት ዳቦ እያመረቱ የሚገኙትን 29 የዳቦ ፋብሪካዎችን እንደማይመለከት ገልጸዋል።
በዚህ መሠረት አንድ 70 ግራም ዳቦ በሸገር ዳቦ 5 ብር ከ50 ሳንቲም፣ በብርሃን ዳቦ 5 ብር እንዲሁም በመንግስትና የግል አጋርነት የሚሠሩ ማምረቻዎች ላይ በ8 ብር መሸጡን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። እነዚህም በምግብ ዋስትና እና ምርታማነት፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ እንዲሁም በክህሎት እና በዕውቀት ሽግግር ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው።
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት ነው። ይህንን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን።
ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኃይል አማራጮቻችንን ከማስፋት ባለፈ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት ትስስር ከምንጊዜውም በላይ የሚያጠናክር ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)