Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

" አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።"
(ኢዮ 2: 12)
መልካሙን የምንሰማበት ቀን ይሁንልን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPY
አብሳሪው መልዓክ መጥፎ ነገር የማንሰማበት የተቀደሰ ቀን ያድርግልን መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ🙏🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
የህመሙ ምልክት ያለበት ሰው አይተን 8335 ደውለን ምን እንዳለችኘ Record የተደረገ እንዲህ ይባላል እንዴ ተጠጉና ጠይቁት ይባላል መተው ማየት የለባቸውም በዚ አይነትማ አለቅን ማለት አይደል ይሔ ነገር ችላ ይባላል እንዴ??
Morning is a perfect time
"2pray"🙏
"2love"😍
"2care"👍
"2smile"😃
"2relax"🕺
&
"to thank God"🙏🙏
For give us
One more day
Good morning everyone😍😍hav a nice SUNDAY 😊😄
AB PHOTOGRAPY
እራሳችንን እየጠበቅን እጃችንን በሳሙና መታጠብ አንርሳ.....ሰዎች ከተሰበሰቡበት ቦታ እንራቅ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPY
ፎቶውን ስለልኮትን ገልብጠው እንዲያዩት ይመከራል😍
መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤል በእለተ ቀኑ ከምንሰማው አስፈሪ ነገር ይጠብቀን
እራሳችንን እየጠበቅን እጃችንን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ አንርሳ.....ሰዎች ከተሰበሰቡበት ቦታ እንራቅ ስለምኖዳቸው ሰዎች ስንል እንጠንቀቅ
🙏 ስለሃገራችን ስለዓለም እንፀልይ🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
የሀበሻ ጀብዱ
ደራሲ:- አዶልፍ ፓርለሳክ

ተርጓሚ:- ተጫነ ጆብሬ መኮንን
እውነተኛ ታሪክ
በ348 ገፅ ብዛት በሚያምር አቀረራረብ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ እውነተኛ የአያቶቻችን የቅድመ አያቶቻችን ታሪክ
ሀበሻነት ኩራት ነው!!!
Canon 4000D
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
"ኢትዮጵያን ማንም አይረዳትም፡፡ ብቻዋን ናት!

ሞሶሎኒ ሀሳቡን እንደገና እንዲያይ የሩሲያ የማስፈራሪያ ቃል እንኳን አላቆመውም፡፡ ምን ያድርግ? ፈረንሳዮች እና እንግሊዞች አይዞህ ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ቅዱስ መብትህ ነው ብለውታል፡፡ አሜሪካ እንኳን ሳትቀር በተዘዋዋሪ ደግፋዋለች፡፡ አርፈሽ ተቀመጭ ይሔ ነፃነት ነፃነት የምትይው ትግልና መንፈራገጥ ለመላላጥ ነው ብላታለች፡፡ አይ ኢትዮጵያ!

በደብረታቦር ያለሁ ብቸኛ አውሮፓዊ መሆኔ ሲታወቀኘ ሀዘኝ ተሰማኘ፡፡ ወዲያው ለዚች ለተቀደሰች ሀገር ከነዚህ ምስኪን የገበሬ ወታደሮች ጎን በታላቅ ድፍረትና ጀግንነት መውደቅ በእግዚአብሔር የሚታደሉት ታላቅ ፀጋ መሆኑን ስረዳ ልቤ በደስታ ተሞላች፡፡ ከዚች ቅጽበት ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ፡፡ አዎ ያ ወጣት እንዳለው የሀገሬን ድንበር ጥሶ የሚመጣን ወራሪ እንደቆሎ እቆላዋለሁ እንደሙጃ እዘረጋዋለሁ አጭደዋለሁ፡፡፡

አዶልፍ ፓርለሳክ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መተው በንጉሰ ነገስቱ ፊት ቀርበው ትልቅ የሚባለውን የኢትዮጵያ የመኮንንነት ማዕረግ ተሾሙ፡፡ ከዚያም በካፒቴን ማዕረግ በጣልያን ወረራ ጊዜ በ(1935/1936 እ.ኤ.አ) በወቅቱ የሰሜኑ ጦር ጠቅላላ አዛዠ ከነበሩት ከራስ ካሳ ኃይሉ የሰላሌው ወታደራዊ አማካሪና በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩት ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ጎን ሆነው እስከአፍንጫው ታጥቆ የመጣውን ወራሪውን የሞሶሎኒ ጦር እስከመጨረሻዋ ቀን ድረስ የታገሉና ያታገሉ ታላቅ ጀግና የጦር መኮንን ነበሩ፡፡

እኚህ ጀግና ሰው በታላቅ ጀግንነት ወደር በማይገኘለት የሀገር ፍቅርና ወኔ የእናት ሀገር ፍቅሩን በደሙ ለከፈለው ለዚያ ጦር የታሪክ ገድል ሃበሻስካ ኦዴሳ(Habesska adyssea) የሃበሻ ጀብዱ የተባለውን እውነተኛ የታሪክ ማስታወሻ ጽፈው ታህሳስ 1 ቀን 1981ዓ.ም በቼኮዝሎቫኪያ ዋና ከተማ ፕራንግ አርፈዋል፡፡ "

በዚች እቤት በምናሳልፋት ጊዜ ይህን በተጫነ ጆብሬ መኮንን የተተረጎመውን ከሰባ አመታት በላይ ያለፈውን እውነተኛ የአያቶቻችን የቅድመ አያቶቻችንን ታሪክ እንድታነቡት ጋበዝኳችሁ የሀገር ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ ትማሩበታላቹ አብዝታችሁ ታተርፉበታላችሁ እውነት ሀበሻ በመሆኔ ኮርቻለሁ፡፡

ለአክቲቪስቶቻችን በቀን 10 ገፅ እንዲያነቡ ቢታዘዝላቸው ባይ ነኝ፡፡

ከመፅሀፉ የተመቹኝን በቅርብ ቀን....

እራሳችንን እንጠብቅ ቤታችን እንሁን እናንብብ
መልካም ጊዜ
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅ
አስተያየታችሁን አድርሱኝ @jahABP
AB PHOTOGRAPY
እራሳችንን እየጠበቅን
keep ur social distance
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
"Vision is the source and hop of life.

The greatest gift ever given to mankind is not the gift of sight but the gift of vision. Sight is a function of eyes, vision is the function of heart. "Eyes that look are common, but eye that see are rare." Nothing noble or noteworthy on earth was ever done with out vison.

No invention, development, or great feat was ever accomplished without the inspiring power of the mysterious source called............vision.

Vision is the key to unlocking the gates of what was and what is, to propelling us into the land of what could be, and has not yet been. Vision sets you can free from the limitations of what the eyes can see and allows you to enter into the liberty of what the heart can feel. It is vision that make unseen visible and the unknown possible.

It was the vision of flight that inspired the Wright brothers invent the airplane. Vision produced the great Axum civilization over thousand year & gave over rise of the towering obelisk that still amaze us today. It was the vision of light that possessed thomas Edison to invent the lightbulb. It was the vision of a desk-sized computer that motivated Stephen Jobs to invent the desktop computer. It was the vision of giving every person access to people-friendly software that inspired Bill Gates to develop and invent the Microsoft global empire. Vision is the energy of progress.

You were born to achive something significant, and you were destined to make a difference in your generation. Your life is not a divine experiment, but a project of providence to fulfill a purpose that your generation needs.

This personal purpose is the source of ur vision and gives meaning to your life. I therefore encourage you to believe in your daydream and to reconnect with your passion, your vision awaits your action. Your future is not ahead of you-it lies within you. See beyond your eyes and live for the unseen. Your vision determines your destiny."

Source: - From the book of

THE PRINCIPLE AND POWER OF VISION

BY:- DR. MYLES MUNROE.


For ur suggestion @jahABP
ባለፈው አመት የአጎቴ ልጅ ጋር ሔጄ ከተደረደሩት መፅሐፍት መካከል አንድ መፅሐፍ እይታዬን ሳበው እርእሱ ትልቅ ሆኖ ገዝፎ ታየኘ ከእርእሱ በበለጠ ደግሞ ቀልቤን የወሰደብኘ የመፅሐፋ ሽፋን ላይ ንስር አሞራ መኖሩ ነበር፡፡

ከዚያ በፊት በዚያን አመት ስለ ንስር አሞራ የተቻለኘን ለማንበብ እና የተለያዩ ቪዲዮዎችን ለማየት ጥረት አድርጌ ነበር እና ጥንካሬ ተስፋን ባለመቁረጥ አልሸነፍ ባይነት በስቃይ ውስጥ በትዕግስት ማለፍን ችግርን ለብቻ መጋፈጥን ሌላም ሌላም....ተጨማሪ አመታትን በደስታ ለመኖር የሚያደርጋቸው ተጋድሎዎች መሆናቸውን አውቄ ነበር እና ለንስር አሞራ የተለየ ቦታ ሰጥቼው ነበር....ግጥምጥሞሹ ገርሞኘ ያለምንም ማመንታት አነሳሁት ይሔን መፅሐፍ ማንበብ እንደምፈልግ ላጎቴ ልጅ ነገርኩት እሺ ግን ምወደው መፅሐፍ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርግለት አለኘ ሃሳብ አይግባህ አልኩት::

እንደገባሁ ጀመርኩት የተወሰኑትን የወደድኳቸውን እዚሁ ቻናል ላይ ለጠፍኩ እንግሊዘኛ ላይ ብዙም ስላልሆንኩ ንባቤ በአጭሩ ተቀጨ 🤦‍♂ መፅሐፋን መለስኩ፡፡ ዘንድሮ እራሴው ገዝቼው ድጋሚ ተፋጠናል የተቻለኘን ለማካፈል ጥረት እያደረኩ ነው፡፡

በዚ በእረፍት ጊዜ እንድታነቡት እጋብዛለሁ
ቤታችን እንሁን እራሳችንን እንጠብቅ እጃችንን በሳሙና በተደጋጋሚ እንታጠብ ለምኖዳቸው ስንል እንጠንቀቅ፡፡
ለአስተያየታችሁ @jahABP
"ሞት የሚያስፈራን ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን
ስለማናምን ነው"

ዉዲ አለን ታዋቂ አሜሪካዊ ኮሜዲያንና የፊልም ዳይሬክተር ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ፈላስፋም ነው ይላሉ፡፡ ሦስተኛውን ሃሳብ ከግምት ውስጥ አስገብተን በቀልዶቹ ውስጥ ያሉትን ፍልስፍናዎች እንቃኛለን፡፡

ዉዲ አለን የተወለደው እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 1/1935 ኒዎርክ ውስጥ ነው፡፡ እውነተኛ ስሙ አለን ስቴዎር ኮኒስበርግ ነው፡፡

ዉዲ አለን በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች እየተጋበዘ ልምዱን እና የህይወት ተሞክሮውን ለተማሪዎች እንዲያካፍል ተደጋጋሚ ግብዣ ይቀርብለት ነበር፡፡

ታዲያ በአንድ ወቅት በተጋበዘበት ዩኒቨርስቲ ለፍልስፍና ተማሪዎቹ ተሞክሮውን እየተናገረ በመካከል ትምርታቸው ፍልስፍና መሆኑ ታሰበውና ተዘጋጅቶ የመጣበትን ጉዳይ አቀረበላቸው፡፡

"አሁን አንድ ቀላል ምሳሌ አሳያችኋለሁ:- ይህ የምታዩት የማርማራታ ጠርሙስ ባዶ ነው ወይስ አይደለም?" አላቸው

ተማሪዎቹም በአንድ ቃል "ባዶ ነው" አሉት

የተማሪዎቹን መልስ እንደሰማ የጠረጴዛ ቴኒስ ኳስ በማንሳት ጠርሙሱን ይሞላው ጀመር ኳሶቹም የጠርሙሱ አፍ ሲደርሱ "አሁንስ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡

"አሁን ሞልቷል!"አሉት፡፡

አለን ግን ብዮች አንስቶ በጠርሙሱ ውስጥ አንስቶ መክተት ጀመረ ብዮቹም በኳሶቹ መኃል እየገቡ ቦታቸውን መያዝ ጀመሩ "አሁንስ?" አላቸው፡፡

ተማሪዋቹም በድጋሚ በአንድ ቃል "አሁን ሞልቷል!" አሉት፡፡


አለን አሁንም ደቃቃ አሸዋ ጠርሙሱ ውስጥ መክተት ጀመረ አሸዋውም ገብትቶ ቦታውን ያዘ "አሁንስ?" አላቸው፡፡

ተማሪዎቹም በእርግጠኝነት "አሁን ሞልቷል!" አሉት፡፡

አንድ ጠርሙስ ቢራ ከፈተና ማንቆርቆር ጀመረ ቢራውም ገብቶ ቦታውን መያዝ ጀመረ፡፡

ይህን ጊዜ ተማሪዎቹ መሳቅ ጀመሩ

"አሁንስ" አለ ዉዲ አለን የተማሪዎቹ ሳቅ ረገብ ሲል ጠብቆ

"ይህ የማርማራታ ጠርሙስ የእናንተን ህይወት የሚወክል ነው....

የጠረጴዛ ቴኒስ ኳሱ በህይወታችሁ ውስጥ እጅግ አስፈላጊውን ክፍል የሚይዝነው፡፡ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጤንነት፣ ልጆች በአጠቃላይ የምትወዱት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡

ብዮቹ ደግሞ ሁለተኛ የህይወታችሁ ጉዳይ ሲሆኑ ይኸውም ስራችሁ፣ ቤታችሁ፣ መኪናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

አሸዋው ደግሞ በሦስተኛ ደረጃ የሚያስፈልጋችሁ ጥቃቅን ነገር ነው፡፡.....

ነገር ግን በህይወታችሁ ውስጥ አስቀድማችሁ አሸዋውን ብትከቱ ለጠረቤዛ ቴኒስ ኳስና ለብዮቹ ቦታ አይኖራችሁም ነበር፡፡ ህይወታችሁን እንዲህ ይመስላል፡፡ ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ለጥቃቅን ጉዳይ ቅድሚያ ከሰጣችሁ በህይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ጉዳይ የሚሆን ቦታ አይኖራችሁም፡፡ ዋነኛ ትኩረታችሁ ለህይወት የሚጠቅማችሁ ጉዳይ ላይ ብቻ ይሁን። ከልጆቻችሁ ጋር ተጫወቱ፣ ጤንነታችሁን ጠብቁ፣ ከሚስቶቻችሁ(ከባሎቻችሁ) ጋር ተዝናኑ....... የወደፊት ህይወታችሁ በእነዚህ እና እነዚህን በሚመስሉ ጉዳዮች ላይ ይጠመድ፡፡

የሚያስፈልጋችሁን ካስቀደማችሁ በኃላ አሸዋውን የመጨረሻውን ክፍል ስጡት" አላቸው

በዚህ ጊዜ ከተማሪዎቹ መካከል አንዲት ወጣት እጇን አወጣችና " አለን! ሁሉንም ስትዘረዝረው ቢራውን እረሳኸው እኮ! ለመሆኑ ቢራው በህይወታችን ውስጥ የሚወክለው ምንድነው?" አለችው፡፡

አለን ፈገግ አለና፡- "አየሽ! የረሳሁትን አስታወስሽኝ፡፡ ህይወታችሁ የቱንም ያህል የሞላ መስሎ ቢታያችሁ በመጨረሻ ግን ለጥቂት ቢራዎች ደግሞ ቦታ እንዳለው እንዳትዘነጉ ለማስታወስ ያህል ያደረኩት ነው" አላቸው፡፡

ጥበብ ከጲላጦ ስብስብ ስራዎች(፩,፪,፫,፬)
( ኃይለጊዮርጊስ ማሞ )

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

በዚህ በእረፍት ጊዜያችን እናንብብ!
ቤታችን እንሁን!
እራሳችንን እንጠብቅ!
ለምኖዳቸው ስንል እንጠንቀቅ!!!
ለአስተያየታችሁ @jahABP
"እነሆ! ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወጣች÷ እስከዛሬም ታመዋለች"

እኔ ለሴት ልጅ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት አለኘ አብዛኛውም ጓደኞቼ ሴቶች ናቸው፡፡ እንዳትቀየሙኘ ግን በዚ በዕረፍት ጊዜ
መፅሐፍ ስቀራርም ያገኘኀትን ፈገግ ያስባለኘን በሴቶች ላይ የተነሱ ፍልስፍናዎችን እነሆ ልላችሁ ወደድኩ

"እግዚአብሔር ሔዋንን የፈጠረበት ብቸኛው ምክንያት የአዳም ጥያቄ ነው" የሚሉን ምዕራባዊያን ፈላስፎች "ለነገሩ ሔዋን ሳትፈጠር አስቀድሞ ብዙ ተባዙ ስላለን ምድርን ለመሙላት የእሷ መምጣት እምብዛም አፈላጊ አልነበረም፡፡ የሚገርመው ግን ከጎኑ አጥንት ወጥታ ተመልሳ የአዳም የጎን ውጋት መሆኗ ነው" ይላሉ፡፡ ፈላስፎችም አክለውም
"እግዚአብሔር በመጀመሪያ ዓለምን ፈጠረ፡፡ በቀጣዩ ቀን ሰውን ፈጠረና ከስራው ሁሉ አረፈ፡፡ በማግስቱ ሴትን ፈጠረ፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔርም ሆነ ሰው እረፍት አላገኙም" ይሉናል፡፡

ይህንና የሌሎችን ፈላስፎች ምን አሉ የሚለውን ነገ በሰፊው እንመለስበታለን፡፡
ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች(፩,፪,፫,፬)
(ከኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

አስተያየታችሁን አድርሱኘ @jahABP

እራሳችንን እንጠብቅ መልካም ምሽት🙏
AB PHOTOGRAPY
መልካም እለተ ሰንበት
መልካሙን የምንሰማበት የተቀደሰ ቀን ይሁንልን🙏🙏
ምን ማድረግ እንደምትችል አሳይተኸናልና አቤቱ ቁጣህን መልስልን🙏😔🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Audio
እሁድ አይደል ይቺን ተጋበዙልኘ am in lop with u voice ሲስቱ😍😍😘😘👏
AB PHOTOGRAPHY
የድንግል ማርያም ልጅ መድኀኔዓለም ይቺን ቀን ስለጨመረልኘ አመሰግነዋለሁ

ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው ፪፬ አመት ሞሎቶኛል በዚህ እድሜዬ ከቤተሰቦቼ ከሰፈሬ ከጓደኞቼ በወረስኳቸው የመልካም መንገድ መስመሮች በመከተል በተቻለኘ መጠን ጥሩ ሰው ለመሆን ሞክሪያለሁ የተሳካልኘ ባይመስለኘም፡፡
ከናንተ በተጨማሪም የማነባቸው መፅሐፍ እኔነቴ ላይ ትልቁ ድርሻ ይወስዳሉ( አንባቢ ነኘ ለማለት ባልደፍርም)
መልካም እንሁን በኡነት አሁንም መልካም እንሁን @jahABP
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አራዳ ላይ ብቻ

ሰባ ነገስታትን ፣ ሲያስጨንቅ የነበር
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ
"ፒያሳ" በሚሏት ፣ በአራዶች ሀገር
የቢራ ቆርኪ ላይ ፣ ምስሉ ታትሞ
የጠርሙስ ልብ ላይ
ድራገኑን ሲገል ፣ እያየሁት ቆሞ
"አራዳነት ማለት....
አጽድቆ ማርከስ ነው" ፣ እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
እዛው አራዳ ላይ
ፒያሳ አደባባይ
ሚሔድ የሚመስል ፣ የማይሔድ ፈረሱ
ሁሌ እዛው ቦታ
ስሔድ የማላጣው ፣ ሚኒልክ ንጉሱ
ሀውልቱ ታትሞ
ከፈረሱ ጋራ ፣ እያየሁት ቆሞ
"አራዳነት ማለት
ሲሔዱ መቆም ነው" እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡
ደግም
ደግሞ
ደግሞ
እዛው አራዳ ላይ
ፒያሳ ላይ ያለ ፣ ሌላው አደባባይ
ነቅለው የተከሉት ፣ የእምነት አቡኑ
"አትገዙ "ብሎ!
ገዝ'ቶን ያለፈ ፣ ጴጥሮስ ካህኑ
በሰንሰለት ታስሮ
ከመትረየስ ጋራ ፣ እያየሁት ቆሞ
"አራዳነት ማለት....
ፈቺውን ማሰር ነው" እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
እዛው ፒያሳ ላይ ፣ ያራዳ የደም ስር
ማ'ሙድ ሙዚቃ ቤት...
ሁሉ መቃጠሪያው ፣ ያደረገው ቅጥር
የልብስ መሸጫ
ሆኖ እያየሁት ፣ ዜማውን አቁሞ
"አራዳነት ማለት....
"ለብሶ መደንቆር ነው" ፣ እላለሁ ባ'ርምሞ፡፡

በላይ በቀለ ወያ
ኩል እና ጥላሸት 2012 ዓ.ም
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
" ህይወቴ እንደተከፈተ መጽሐፍ ነው"

ጋንዲ አለም በታሪኳ ካየቻቸው መሪዎች ፣ ፈላስፋዎች ፣ ሃይማኖተኞች...ወዘተ የላቀ ዕውቀትና ጥበብ የነበረው ብቻ ሳይሆን÷ አንድ ሰው የህይወትን መንገድ ከተረዳ በኀላ በዚያ መንገድ ለመሄድ የሚያስፈልገውን መስዋዕትነት ለመክፈል ምን ያህል ብቃት በውስጡ እንዳለ ያሳየ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡

ስለጋንዲ ህይወት የማይታወቅ ነገር የለም ማለት ይቻላል "ህይወቴ እንደተከፈተ መጽሐፍ ነው ፤ ሚስጥር የለኝም ፤ ሰዎችም ሚስጥር እንዲኖራቸው አላደፋፍርም...." የሚለው ሞሐንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2 ቀን 1869 ካቲህዋር በምትባለው የህንድ ግዛት ተወለደ፡፡ ለቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ የነበረው ጋንዲ አባቱ በህንድ የሚገኙ ሦስት ግዛቶችን በተለያዩ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል። በልጅነቱ ከቤተሰቡ እየተደበቀ በህንድ እምነት የተከለከለውን ስጋ ይበላ የነበረ ጋንዲ በአንድ ወቅት ግን ይህንኑ ድርጊቱን አቆመ። "ስጋ መብላት ያቆምኩት ሃጢያት ሆኖብኝ ሳይሆን ወላጆቼን መዋሸቱ የከበደ ሃጢያት ሆኖ ስላገኘሁት ነው" የሚለው ጋንዲ በ19 አመቱ ወደ እንግሊዝ አገር ተጉዞ አትክልት ተመጋቢነቱን በዚያ ጀመረ፡፡

በእንግሊዝ ሀገር የህግ ትምህርቱን ተከታትሎ ሲጨርስ ወደ ሙምባይ ተመልሶ የህግ አርቃቂ ሆኖ ይሰራ እንደነበር ከታሪኩ እንረዳለን፡፡ ይህ የሕግ አርቃቂነት ሥራው አንድ የሕግ ብርሃንን በውስጡ አበራለት.... ይኸውም የዘር መድሎ በሕንድ ስር የሰደደ መሆኑን መረዳቱና ይህንንም ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ነበር፡፡

ከሕንድ የእምነትና ፍልስፍና መፃሕፍት በተጨማሪ የመፅሐፍ ቅዱስና የቁራን ጥልቅ ዕውቀት እንደነበረው የሚነገርለት ጋንዲ ከምንም በላይ ግን ለራሺያው ደራሲ ቶልስቶይ ታላቅ ፍቅርና ክብር እንደነበረው በሕይወት ዘመኑ በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡ በተለይም ቶልስቶይ "the kingdom of GOD is within you" በተባለው ሥራው እጅግ ተማርኮ እንደነበር ታሪኩ ይነግረናል፡፡ ጋንዲ ስለ ቶልስቶይ ሲናገር.... "ውስጣዊው እኔነቴ ላይ ታላቅ ተፅዕኖውን አሳርፉል" ብሏል፡፡

ጋንዲ ስለእውነት ከነበረው እምነት ብንነሳ.... "በዚህ ምድር ስኖር ከእውነት በቀር የፈለኩት ነገር የለም፡፡ መንገዱን አግኝቼዋለሁ ብዬ አሰብሁ ፤ እውነትን ለማግኘት የማያቋርጥ ትግልና መፍጨርጨር አደረግኹ ፤ የተረዳሁት ግን እውነትን ማግኘት ማለት ራስን ማወቅና መድረሻንም መረዳት ማለት እንደሆነ ነው፡፡ ይህም በአጭር ቃል ሲጠቃለል ፍፁም መሆን ማለት ነው፡፡ ሕሊናዬ ግን ፍፁም አለመሆኔን ሲረዳ ያመዋል፡፡ ፍፁም ለመሆን ብርታትና ኃይሌን በሙሉ ተጠቀምኩ፡፡ ለመሆን ግን አልቻልኩም፡፡ እንደማንኛውም ሰው ፍፁም የማያደርግ ድክመት ነበረኝ...." ብሏል

ጋንዲ በማከል እንዲህ ይላል "....ለእኔ ፈጣሪን መፈለግ ማለት እውነትን መፈለግ ነው ፤ እውነትን ለማግኘት ሕይወቴን መስዋዕት ማድረግ ቢያስፈልግ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ፡፡ እውነትን የሚፈልግ ሰው ደግሞ ከትቢያ ባነሰ ደረጃ ራሱን ያዋረደ (ትሁት) ይሁን፡፡ ዓለም ትቢያን በእግሩ ጫማ ይረግጠዋል፤ እውነትን የሚፈልግ ሰው ግን በትቢያ የተረገጠ ሆኖ ራሱን ያዋርድ፡፡ ያን ጊዜ የእውነት ጭላንጭል ይበራለታል፡፡"

ጋንዲ በዘመኑ ሁሉ በሰው ልጅ ዘንድ እንደ ቅዱስ ይታይ እንጂ የራሱን ቅዱስ መሆን "ፈፅሞ አይቀበለውም..... በአንፃሩ ቅዱስ ሳልሆን ምናልባት በሥርዓት የታነፅኩ ሰው እንደሆንኩ እንጂ" ይላል፡፡ "እኔን ቅዱስ ማለት ቅድስናን አለማወቅ ወይም ማርከስ ነው" ባለራዕይ ነኝ ብዬም አልዋሽም... ቅዱስ ነህ የሚሉኝንም አይደለሁም እላለሁ.... እኔ ከምድር የወጣሁ ምድራዊ ነኝ....እንደእናንተው ለብዙ ድክመቶች ተጋልጫለሁ....ነገር ግን ዓለምን አይቻታለሁ። ዓለምን በተከፈቱ ዓይኖቼ አስተውያታለሁ.... በሰው መንገድ የተወረወሩ ፍላፃዎች በእኔም መንገድ በተደጋጋሚ ወድቀዋል....የዚህ ሁሉ ድምር ግን በሥርዓት አንፆኛል...." ብሏል፡፡

ጋንዲ ታሪክን መማር የማይጠቅም መሆኑን ይናገራል፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠው የታሪክ ትምህርት ስለ ጦርነት ብቻ የሚነገር በመሆኑ "ይህ ታሪክ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም" በማለት ያሳስባል፡፡

ጋንዲ በተደጋጋሚ በሃሳቡ የማይስማሙ ሰዎች ቢያጋጥሙትም.... "በሃሳብ አለመስማማት ማለት ጥላቻ ማለት አይደለም......ጥላቻ ቢሆን ኖሮ ከሚስቴ በላይ ጠላት ባልኖረኝ ነበር ፤ ቢያንስ በአንድ ሃሳብ የማይለያዩ ሁለት ሰዎች እስከዛሬ አጋጥመውኝ አያውቁምና" ብሏል፡፡

"ገነትን በምድር ማምጣት ከተፈለገ 'እኔ' የሚለውን ቃል ከፖለቲካ ፣ ከኢኮኖሚ ፣ ከሃይማኖት.... ወዘተ ውስጥ መፋቅ ያስፈልጋል" ይላል ጋንዲ ስለሰው ልጅ ደህንነት ፣ ሰላም ፣ ብልፅግና ፣ ፍቅር.... ከማንም በላይ ያስተማረና ፣ የሰበከ ራሱንም አርአያ አድርጎ ያቀረበ ጋንዲ ታሪኩን የሰሙ ፣ ያነበቡና የተረዱ ሰዎች በዚህ ሐቅ ይስማማሉ፡፡

ጋንዲ ጃንዋሪ 30/1948 ዓ.ም የምሽት ጸሎቱን ለማድረስ ወደ መቅደስ በመጓዝ ላይ ሳለ ከጠላቶቹ በተተኮሰ ጥይት ተገደለ፡፡

ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች/፩-፪-፫-፬/
(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

ለማንኛውም አስተያየታችሁ @jahABP አድርሱኝ፡፡
AB PHOTOGRAPY
ኤሊያና ሮቤል ቤታችን እንሁን እያለች ነው፡፡
HOME CHALLENGE
CANON 4000D
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD