Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY


ሊያመልጠኘ ነበር እኮ አገኘሁት
📷Samsung j4 core

@ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ለልደቴ ከተሰጡኘ ስጦታዎች አንዱ የአሌክሶ አጥቢያ መፅሐፍ አንዱ ነበር፡፡ ታዲያ ይህን ድንቅ ስራ አንብቤ ስጨርስ አራት ኪሎ ያነሳኀቸው ፎቶዎችን ሳገላብጥ ይሔን አገኘሁት😄.....አራት ኪሎ ከብዙ ትዝታዎች ጋር😍😍🙏
📷sony cybershoot

@ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABOGD @ABPGD
Ab photograohy & graphic design

"የተሻልክ ሳይሆን የበለጥህ ሁን፡፡"

"ከቢጤዎችህ ጋር አትምከር የሚነግሩህ የምታቀውንና የትብዕቢት ምክር ነው፡ የቀድሞ ወዳጆችህን አትርሳ፣ የአባትህን ወዳጅ ጠይቅ፡፡ የተሾመን ሰው አውቀዋለው ብለህ አትናገር፡፡ ካልፈለገህ በቀር ደጅ አትጥናው፡፡ ካልፈቀደልህም ስለ ጠባዩ ስለ ኑሮው ለማንም አትናገር፡፡ ሁለት ጆሮ ያለህ አንተ እንኳን የምትባለውን ትሰማለህ ሺ ጆሮ ያለው ሹም የሚባለውን አይሰማም ብለህ አትሞኘ፡፡ የዕድሜ እና የእውቀት እጥር ካለባቸው ጋር አትምከር፡፡ ባለጌን ስለወደደህ ብቻ አታቅርበው፡፡ የሚሰድበው ያጣ ቀን አንተን ያዋርድሃልና፡፡ ብልግና ሱስ ነው፣ ሱሰኛ ዘመድ አይሆንም፡፡
ፊት የልብ አደባባይነውና ሁሉን ቅሬታህን ፊትህ ላይ አታስነብብ፡፡ ጠላቶችህ ፊትህን እንጂ ልብህን እንዲያዩ አትፍቀድ፡፡ ለስድባቸው ስድብን አትመልስ ይህን ሰምቻችኀለሁ ማለት ነውና፡፡ ምንም ቢሆን አሁን የተሰማልን አትናገር፡፡ ከራስህ ጋር ሳትመክር ከሰው ጋር አትመካከር፡፡ ለአንድ ሀሳብ የሶስት ቀን እድሜ ስጠው፡፡ ባዕድ ባለበት ስለቤትህ አታውራ፡፡ ለግቢህ አጥር ፣ለቤትህ በር፣ለህይወትህ ሚስጥር ይኑርህ፡፡ የተሻልክ ሳይሆን የበለጥህ ሁን፡፡
የዛሬን ድል ከፈለክ ዛሬ መሸነፍ ትችላለህ፣ የነገን ድል ከፈለግህ ዛሬን ተሸነፍ፡፡
በትልቅ አደባባይ ስለትንንሾች አትናገር፡፡ በስኬትህ በጣም አትደሰት፣ በውድቀትህም በጣም አትዘን፡፡ ሁኔታዎች ይለወጣሉ ደስታና ሀዘን ስሜት ናቸውና ያልፋሉ፡፡ እውነት ግን ፀንቶ ይኖራል፡፡ ብዙ ሰው የሚሰማው የምትናገረውን ሳይሆን ራሱ የሚያስበውን ነው፡፡ ስለ ጠብ እያሰበ ከሆነ ስለ ፍቅር እየተናገርክ የሚሰማው ጠቡን ነው፡፡ ስለ መንደር እያሰበ ከሆነ ስለአለም እየተናገርክ የሚሰማው ያንን ነው፡፡"
እኔም እላለሁ
ሁሉም ሰው አንድ አይደለምና ምርጫህን አስተካክል፡፡
AB @jahABP ነኘ
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን የደስታ ቋጠሮ
ለንባብ እንዲመች አድርጌ የቀነጨብኩት፡፡
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች

በውስጥ መስመር Pdf መፅሐፍ እንዴት እናገኛለን ብላችሁ ነበር ይኸው ቀጣይ ያለውን ሊንክ በመጠቀም ብዙ መፅሐፍቶችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
@Rovibook @Rovibook @Rovibook
@Rovibook @Rovibook @Rovibook
@Rovibook @Rovibook @Rovibook
@Rovibook @Rovibook @Rovibook
አስተያየታችሁ አይለየን
🙏🙏🙏🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY


በቃ ለዚ ነበር ይሔ ሁሉ ግንባታ😂😂😂😂😜😜😜

@ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABOGD @ABPGD
AB graphic design


21........እናቴ መልካም ቀን

@ABPGD @ABOGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABOGD @ABPGD
AB graphic design

ከእዮባ ተወዳጅ ስራዎች ለፕሮፋይል

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


አድዋ በዓል ላይ የነበረኘ አንድ ፎቶ ነበር እሱም ካሜራዬን ይዤ እጄ ብቻ የሚታይበት ነው፡፡ እንዴት ሌላ ፎቶ እንዳልተነሳሁ ለራሴም ግራ ገብቶኘ ነበር፡፡ከወራት በኀላ ሶፋኒት ሽፈራው የምትባል ጓደኛዬ በማህበራዊ ድህረገፅ በፌስቡክ ይህን ቆንጅዬ ፎቶ ላከችልኘ የኡነት በጣም ወድጄዋለሁ😍
ይህን ፎቶ ለማንሳትም ብዙ እንዳስቸገርኳት ነገረችኘ😄😄በጣም አመሰግናለሁ ይህን ቆንጆ ፎቶ ስላነሳሽኘ ሲቀጥልም አፈላልገሽ ስለላክሽልኘ🙏😊😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


መልካሙን የምንሰማበት የተቀደሰ ቀን ይሁንልን
መርካቶ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሀይማኖት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB graphic design

Hulk bog down in the coffee😂😂😂
stay home stay safe😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


ረጅሙ ፋፋቴ ደብረ ሊባኖስ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

DEADPOOL 3
TRIP TO HAWASSA

RUN DEADPOOL RUN RUN

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Ab photography & graphic design

ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ እንድትጓዝ ያደርጉኻል፡፡

እኔም ባገኘኋቸው አጋጣሚዎች ከላይ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ወደ ህልሜ የማደርገውን ሩጫ እንዳላቆም የሚያደርጉ አያሌ ተሞክሮዎችን እና ተነሳሽነትን አግኝቻለሁ፡፡

እንደእኔ አስተሳሰብ ዋነኛ አለምን የሚለውጡ ሰዎች አንባቢዎች ናቸው፡፡ ጨጓራችን የሚፈጨው ምግብ እንደሚፈልግ ሁሉ አይምሮአችንም የሚያወጣውና የሚያወርደው ሀሳብ ያስፈልገዋል አለምን በተለያየ አቅጣጫ ለማየት ደግሞ ዋነኞቹ አቅጣጫ ጠቋሚዎች መጽሐፍት ናቸው፡፡

አውቃለሁ ጎበዝ አንባቢ አይደለሁም ግን በተቻለኝ አቅም መጽሐፍትን ለማንበብ እጥራለሁ፤ የለውጡ አካል መሆን እፈልጋለሁ። እኔ ከመጽሐፍት ላይ ያገኘኋቸው እውቀቶች አያሌ ናቸው፡፡ ካነበብኳቸው መጽሐፍቶች ደግሞ እኔ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የሰጠኋቸው 3 መጽሀፎች አሉ። እነዚህን መጽሐፍቶች አንብቤ ብቻ አልተውኳቸውም እየኖርኳቸውም ጭምር ነው። ድሮ እኔን የሚያውቁኝ ሰዎች "አንተ እኮ እንዲህ አልነበርክም በጣም ተለውጠሀል" ይሉኛል፤ አሁን የሚያውቁኝ ደግሞ ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል (ጥሩ ነኝ ለማለት ባልደፍርም)፡፡

እውነታው ግን ለእኔ መለወጥ የእነዚህ መጽሐፍት ሚና እጅጉን ላቅ ያለ ነው እውነት ለመናገር መጽሐፍቶቹን ከማንበቤ በፊት እና ካነበብኩ በኋላ የተለየሁ ሰው ሆኛለሁ፤ ለእራሴ እስኪደንቀኝ እራሴን ተለውጦ አግኝቼዋለሁ። ያሉኝ ጥቂት መጽሐፍት ባለችኝ ትንሽዬ መሳቢያ ስር ተደርድረው ይቀመጣሉ። እነዚህ ሶስቱ መጽሐፎች ግን ሁሌም አልጋዬ ትራሴ አጠገብ ይቀመጣሉ። ሁል ጊዜም እንደ አዲስ አንስቼ አነባቸዋለሁ፤ ሁልጊዜም ለኔ ቅርብ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ጉዞ ስሄድ ከተቻለ ሶስቱንም ካልተቻለ አንዱን ይዤ መሄዴ የማይቀር ጉዳይ ነው።

ብዙ ጊዜ በኑሮዬም ሆነ በንግግሬም ላይ ከእነዚህ መጽሐፍት ያገኘኋቸው እውቀቶች ነፀብራቅ ይታያል። የፈጣሪን ትልቅነት፣ የተረጋጋ ሰው መሆንን፣ ለሰው ችግር መድረስን፣ ሰውን ካለበት አለማዊ ሀሳብ ማንቃትን፣ ያለውን የውስጥ ችሎታ አውጥቶ እንዲጠቀም ማድረግን፣ ያላስተዋላቸው የህይወት መርሆችን መጠቆምን፣ ችግርን ከስር መሰረት መቅረፍን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ታጋሽነት፣ ለማንኛውም ችግራችን መጀመሪያ እራስን ተጠያቂ ማድረግን፣ ለፍርድ አለመቸኮልን፣ በፍቅር ሁሉንም ማሸነፍን፣ ሰላም ለማምጣት ዝቅ ማለትን፣ ሰዎች መጥፎ ሲያደርጉብን ምላሻችን ሁሌም መልካም መሆን እንዳለበት፣ ራዕይ ያለን ልንሆን እንደሚገባ፣ አመሰግንሃለሁ/ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ማለትን፣ ለጥፋታችን ቶሎ ይቅርታ መጠየቅን፣ በእያንዳንዱ ውድቀታችን መማር መቻልን፣ ከምንም ተነስተን ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደምንችል፣ የምንፈልገውን ነገር ተስፋ እስካልቆረጥን ድረስ ማሳካት እንደምንችል፣ በህይወት አጋጣሚ የምናገኛቸው ሰዎች ለእኛ መማሪያዎቻችን መሆናቸውን፣ የምናደርገው መልካም ነገር በቀጥታ ባይሆንም በተዘዋዋሪ እኛኑ መጥቀሙ የማይቀር መሆኑን፣ ደስታ ከመቀበል ይልቅ በመስጠት ላይ መሆኑን፣ እውተኛ ስጦታም ከተረፈን ላይ ሳይሆን ካለን ላይ መሆኑ፣ ዛሬን ከትላንት የተሻለ አዲስ እና የተሻለ ማድረግ እንዳለብን እና እንደምንችልም ............. ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አስተምረውኛል ያስተምሩኛልም። ያስተምሩኛል የምላችሁ ሁልጊዜም ሳነባቸው አዲስ ነገር ስለማገኝባቸው ነው፡፡

ሶስቱን መጽሐፍ አንብቤ በጨረስኩበት ወቅት ይህን የፎቶግራፊ ቻናል አልከፈትኩም ነበር። ነገር ግን ለራሴ እንዲህ ብዬ ነግሬው ነበር ቻናል ሲኖረኝ ሰዎች እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ እጋብዛለሁ ብዬ ነበር....ገና ቻናል ሳልከፍት..... አሁን ግን 3.1k ሰዎች ያሉበት ቻናል ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት እየተናገርኩ ነው። ራዕይ ነበረኝ አሳካሁት ማለትም አይደል? ነገም ደግሞ ከዚህ የበለጠ ሰዎች ፊት ስለነዚህ መፅሐፍት እናገራለሁ። ነገ በትልልቅ ሚዲያዎች ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት አወራለሁ። ደራሲዎቹን በደንብ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁ.... እኔ እነዚህን መፅሐፍት እየኖርኳቸው ነው፡፡ በእውነት እላችኋለሁ ጥሩ ሰው እንድሆን አድርገውኛል፣ በጥሩ አንፀውኛል፤ እናም እነዚህን መጽሐፍት እንድናነባቸው ለጻፉልን ጸሐፊዎች በእናንተ ስም እጅግ እጅግ ታላቅ የሆነውን ፍቅርና አክብሮቴን ላደርስ እወዳለሁ፡፡

እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ የጋበዝኳቸው ሰዎች አባቴን አቶ አንዷለምን ጨምሮ ለሰጠኋቸው መጽሐፍት አድናቆታቸው ላቅ ያለ ነበር። እንዲያነቡት ስለጋበዝኳቸውም ለእኔም ምስጋናቸውን ችረውኛ።

የመጽሐፍቶቹ ርዕስ ምንድነው???

ደራሲዎቹስ እነማን ናቸው???

በመጀመሪያ የመጽሐፉን ርዕስና የደራሲውን ማንነት ሳልጠቅስ ከሶስቱም መጽሐፍ የተወሰነ ቀንጭቤ ለንባብ አቀርባለሁ ከዛም መጽሐፍቶቹንም የደራሲዎቹንም ስም እለጥፋለሁ፡፡

@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ፡፡

ቤታችን እንሁን!
እናንብብ!
ቤተሰብን አካባቢን ሀገርን እንዲሁም አለምን እንለውጥ!!! ❤️❤️❤️
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


አንቺ ጨረቃ ታምሪያለሽ በጣም😍😍😱😱

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Phenomenal pictures & graphic design pinned «Ab photography & graphic design ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ…»
በቀጣይ ከሦስቱ መፅሐፎች ከአንዱ ቀንጨብ እናድርግ