Ab photography & graphic design
ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ እንድትጓዝ ያደርጉኻል፡፡
እኔም ባገኘኋቸው አጋጣሚዎች ከላይ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ወደ ህልሜ የማደርገውን ሩጫ እንዳላቆም የሚያደርጉ አያሌ ተሞክሮዎችን እና ተነሳሽነትን አግኝቻለሁ፡፡
እንደእኔ አስተሳሰብ ዋነኛ አለምን የሚለውጡ ሰዎች አንባቢዎች ናቸው፡፡ ጨጓራችን የሚፈጨው ምግብ እንደሚፈልግ ሁሉ አይምሮአችንም የሚያወጣውና የሚያወርደው ሀሳብ ያስፈልገዋል አለምን በተለያየ አቅጣጫ ለማየት ደግሞ ዋነኞቹ አቅጣጫ ጠቋሚዎች መጽሐፍት ናቸው፡፡
አውቃለሁ ጎበዝ አንባቢ አይደለሁም ግን በተቻለኝ አቅም መጽሐፍትን ለማንበብ እጥራለሁ፤ የለውጡ አካል መሆን እፈልጋለሁ። እኔ ከመጽሐፍት ላይ ያገኘኋቸው እውቀቶች አያሌ ናቸው፡፡ ካነበብኳቸው መጽሐፍቶች ደግሞ እኔ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የሰጠኋቸው 3 መጽሀፎች አሉ። እነዚህን መጽሐፍቶች አንብቤ ብቻ አልተውኳቸውም እየኖርኳቸውም ጭምር ነው። ድሮ እኔን የሚያውቁኝ ሰዎች "አንተ እኮ እንዲህ አልነበርክም በጣም ተለውጠሀል" ይሉኛል፤ አሁን የሚያውቁኝ ደግሞ ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል (ጥሩ ነኝ ለማለት ባልደፍርም)፡፡
እውነታው ግን ለእኔ መለወጥ የእነዚህ መጽሐፍት ሚና እጅጉን ላቅ ያለ ነው እውነት ለመናገር መጽሐፍቶቹን ከማንበቤ በፊት እና ካነበብኩ በኋላ የተለየሁ ሰው ሆኛለሁ፤ ለእራሴ እስኪደንቀኝ እራሴን ተለውጦ አግኝቼዋለሁ። ያሉኝ ጥቂት መጽሐፍት ባለችኝ ትንሽዬ መሳቢያ ስር ተደርድረው ይቀመጣሉ። እነዚህ ሶስቱ መጽሐፎች ግን ሁሌም አልጋዬ ትራሴ አጠገብ ይቀመጣሉ። ሁል ጊዜም እንደ አዲስ አንስቼ አነባቸዋለሁ፤ ሁልጊዜም ለኔ ቅርብ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ጉዞ ስሄድ ከተቻለ ሶስቱንም ካልተቻለ አንዱን ይዤ መሄዴ የማይቀር ጉዳይ ነው።
ብዙ ጊዜ በኑሮዬም ሆነ በንግግሬም ላይ ከእነዚህ መጽሐፍት ያገኘኋቸው እውቀቶች ነፀብራቅ ይታያል። የፈጣሪን ትልቅነት፣ የተረጋጋ ሰው መሆንን፣ ለሰው ችግር መድረስን፣ ሰውን ካለበት አለማዊ ሀሳብ ማንቃትን፣ ያለውን የውስጥ ችሎታ አውጥቶ እንዲጠቀም ማድረግን፣ ያላስተዋላቸው የህይወት መርሆችን መጠቆምን፣ ችግርን ከስር መሰረት መቅረፍን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ታጋሽነት፣ ለማንኛውም ችግራችን መጀመሪያ እራስን ተጠያቂ ማድረግን፣ ለፍርድ አለመቸኮልን፣ በፍቅር ሁሉንም ማሸነፍን፣ ሰላም ለማምጣት ዝቅ ማለትን፣ ሰዎች መጥፎ ሲያደርጉብን ምላሻችን ሁሌም መልካም መሆን እንዳለበት፣ ራዕይ ያለን ልንሆን እንደሚገባ፣ አመሰግንሃለሁ/ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ማለትን፣ ለጥፋታችን ቶሎ ይቅርታ መጠየቅን፣ በእያንዳንዱ ውድቀታችን መማር መቻልን፣ ከምንም ተነስተን ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደምንችል፣ የምንፈልገውን ነገር ተስፋ እስካልቆረጥን ድረስ ማሳካት እንደምንችል፣ በህይወት አጋጣሚ የምናገኛቸው ሰዎች ለእኛ መማሪያዎቻችን መሆናቸውን፣ የምናደርገው መልካም ነገር በቀጥታ ባይሆንም በተዘዋዋሪ እኛኑ መጥቀሙ የማይቀር መሆኑን፣ ደስታ ከመቀበል ይልቅ በመስጠት ላይ መሆኑን፣ እውተኛ ስጦታም ከተረፈን ላይ ሳይሆን ካለን ላይ መሆኑ፣ ዛሬን ከትላንት የተሻለ አዲስ እና የተሻለ ማድረግ እንዳለብን እና እንደምንችልም ............. ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አስተምረውኛል ያስተምሩኛልም። ያስተምሩኛል የምላችሁ ሁልጊዜም ሳነባቸው አዲስ ነገር ስለማገኝባቸው ነው፡፡
ሶስቱን መጽሐፍ አንብቤ በጨረስኩበት ወቅት ይህን የፎቶግራፊ ቻናል አልከፈትኩም ነበር። ነገር ግን ለራሴ እንዲህ ብዬ ነግሬው ነበር ቻናል ሲኖረኝ ሰዎች እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ እጋብዛለሁ ብዬ ነበር....ገና ቻናል ሳልከፍት..... አሁን ግን 3.1k ሰዎች ያሉበት ቻናል ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት እየተናገርኩ ነው። ራዕይ ነበረኝ አሳካሁት ማለትም አይደል? ነገም ደግሞ ከዚህ የበለጠ ሰዎች ፊት ስለነዚህ መፅሐፍት እናገራለሁ። ነገ በትልልቅ ሚዲያዎች ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት አወራለሁ። ደራሲዎቹን በደንብ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁ.... እኔ እነዚህን መፅሐፍት እየኖርኳቸው ነው፡፡ በእውነት እላችኋለሁ ጥሩ ሰው እንድሆን አድርገውኛል፣ በጥሩ አንፀውኛል፤ እናም እነዚህን መጽሐፍት እንድናነባቸው ለጻፉልን ጸሐፊዎች በእናንተ ስም እጅግ እጅግ ታላቅ የሆነውን ፍቅርና አክብሮቴን ላደርስ እወዳለሁ፡፡
እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ የጋበዝኳቸው ሰዎች አባቴን አቶ አንዷለምን ጨምሮ ለሰጠኋቸው መጽሐፍት አድናቆታቸው ላቅ ያለ ነበር። እንዲያነቡት ስለጋበዝኳቸውም ለእኔም ምስጋናቸውን ችረውኛ።
የመጽሐፍቶቹ ርዕስ ምንድነው???
ደራሲዎቹስ እነማን ናቸው???
በመጀመሪያ የመጽሐፉን ርዕስና የደራሲውን ማንነት ሳልጠቅስ ከሶስቱም መጽሐፍ የተወሰነ ቀንጭቤ ለንባብ አቀርባለሁ ከዛም መጽሐፍቶቹንም የደራሲዎቹንም ስም እለጥፋለሁ፡፡
@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ፡፡
ቤታችን እንሁን!
እናንብብ!
ቤተሰብን አካባቢን ሀገርን እንዲሁም አለምን እንለውጥ!!! ❤️❤️❤️
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

Phenomenal pictures & graphic design pinned «Ab photography & graphic design ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ…»
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ተጨማሪ ሙከራ
ትዕግሥት ማለት ያልተሸበረ መንፈስና የማይበርድ ተስፋ ነው፡፡ ትዕግስት ከዚህም ያለፈ ትርጉም አለው፡፡ "ተጨማሪ ሙከራ ማድረግ ነው፡፡" ትዕግሥት እጅና እግርን አጣጥፎ ጊዜን ወይንም እግዚአብሔርን መጠበቅ ማለት አይደለም፡፡ ትዕግሥት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሁላችንም እንደሚገባን የወደቀ ሰው ዳግመኛ ለመነሳት የሚያደርገው መፍጨርጨር ፣ የከሰረው ሰው እንደገና ውጤታማ ለመሆን የሚያደርገው ሩጫ ትዕግሥት ወይም ውስጣዊ ብርታት ነው፡፡
ብዙዎቻችን ተጨማሪ ሙከራ ማድረግን አንፈልግም፡፡ ለሰበባችን አንድ ነገር እንድናደርግ በቃ አልሆነም ምንም ማድረግ አልችልም እንላለን፡፡ ራሱ ማድረግ የማይፈልግ ሰው ግን ሌሎቹ እንዲያደርጉለት ይሻል፡፡ በሌሎች ልፋት መብላት ፣ በሌሎች መጋፈጥ ተጋርዶ መኖር ይሻል፡፡ ይህ ግን ራስን ለማኝና አካለ ስንኩል ማድረግ በራስ ላይም ውድቀትን መፍረድ ነው። የምንኖርበት ዓለም የሙከራ ዓለም ነው፡፡ ጠዋት የሚጎርፈው ሠራተኛ ሁሉን ማግኘት ተስፋ አድርጎ ብቻ ሳይሆን ከትላንቱ ዛሬ እንደሚሻል አምኖ ይወጣል፡፡ ይህንንም ባያምንም የቀኑን ፀሀይ እንኳን ለማየት ባልደፈረ ነበር፡፡ ዛሬ ባይሳካም ነገ ደግሞ በማለዳ ለመውጣት ያስባል፡፡ ሙከራዎች ከስኬት ላይ ያደርሳሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ የመኖር ፍላጎት ይጨምራሉ፡፡ ሙከራዎች ከጠራ ነገር ያደርሳሉ፡፡
እንዳንሞክር ፈተና የሚሆንብን..... የመውደቅ ፍርሃት ፣ የትላንት ክፉ ገጠመኝ ፣ ተስፋ መቁረጥ ናቸው፡፡ ሕፃን ልጅ በእግሩ ፀንቶ የሚቆመው ብዙ መውደቅ መነሳትን በማየትና ተስፋ ባለመቁረጥ ነው፡፡ ከዚያም ደጋፊዎችን በመያዝ መንገዱን ይለማመዳል፡፡ በሁለት እግር የሚሔድ ሰው ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ በአራት እግር የሚሔዱ እንስሳት ግን በተወለዱ ቀን ይቆማሉ፡፡ በሁለት እግር በኩራት መሔድ ከባድ ነው፡፡ ከልምምድና ከሙከራ በኀላ ግን በሁለት እግር መሔድና መሮጥ ይቻላል፡፡ ዓላማችን መቆም ከሆነ እስክንቆም ድረስ መሞከር አለብን። ዓላማችን ውድቀት ከሆነ ግን አለመሞከር እንችላለን፡፡ መሞከር ብቻ ሳይሆን በመራመድ የቀደሙን መያዝ ወይንም ምክራቸውን መቀበል ያስፈልገናል፡፡ በመራመድ የቀደሙን ሰዎች በአካል ብቻ ሳይሆን በመፅሐፋቸውና በምክራቸው ይደግፉናል፡፡ በእውቀት ለመቆም አዋቂዎችን በትሕትና መቅረብ ፣ በሀብት ለመቆም አዛዦቻችንን በአክብሮት ማገልገል ይገባናል። አዋቂዎችን የምንፈልገው ባወቅነው ላይ ማገልገል ይገባናል፡፡ አዋቂዎችን የምንፈልገው ባወቅነው ላይ ጨምረው እንዲነግሩን ከሆነ ምንም አናገኝም፡፡ ራሳችንን ባዶ አድርገን ካልቀረብን አዋቂዎች ሊቀርቡን አይችሉም፡፡ እኛም የሚነግሩንን ልንይዝ አንችልም፡፡ እንዲሁም መታዘዝን ያላወቀ አዛዥ መሆኖ አይችልም፡፡
ዕለቱን ተወልዶ ዕለቱን ብቁ የሚሆን ተግባር የለም፡፡ የተፈጥሮ ጊዜውን ሲጠብቅ ግን ደስታው እንደ ፀሀይ ብርሃን እየፈካ ይመጣል፡፡ መሠረት ያለው በመሆኑ ፀንቶ ይቆያል፡፡ ደክመንበታል ደስ ያሰኛል፡፡ ተአምር ናፋቂዎች ብንሆንም ተፈጥሮም የተአምራት አካል ነውና ሂደትን ማክበር ይገባናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀስ በቀስ አደገ እንጂ አምላክ ነኝ ብሎ ዕለቱን አላደገም፡፡ የተፈጥሮን እድገት ሥርዓት ጠበቀ፡፡ ቀስ በቀስ ማደግ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡
ብዙ ትልልቅ ሰዎች ለደረሱበት ከፍታ የበቁት ከብዙ ትዕግስት ወይም ሙከራ በኋላ ነው፡፡ ከብዙ ሙከራ በኋላ ትልቅ የሆኑ ሰዎች ፣ ጊዜ ካነሳቸው ደግሞም ገጠመኝ ካገነናቸው ዝነኞች ይልቅ ክብራቸውን እንደጠበቁ ማለፍ ችለዋል፡፡ ለትዕግሥተኞች የዛሬ አለመሆን ሌላ አቅጣጫ እንዲያዩ ማስተዋላቸውን ያድሰዋል እንጂ መሬት ላይ ተቀምጠው ስለ ውድቀታቸው እንዲተክዙ አያደርጋቸውም፡፡ የአብርሃም ሊንከንን ታሪክ ብንመለከት ትዕግስት ብዙ መከራ እንደሆነ በመጨረሻም ድልን እንደሚያተርፍ ያስተምረናል፡፡ ስለአብርሃን ሊንከን ያነበብኩትና አሁንም ድረስ የሚመስጠኝ ታሪክ አለ፡፡
አብርሃም ሊንከን፡-
በ32 ዓመቱ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ35 ዓመቱ ፍቅረኛው ከዚህ አለም በሞት ተለየችው፡፡
በ36 ዓመቱ በነርቭ በሽታ ተያዘ፡፡
በ38 ዓመቱ ለአስመራጭነት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ40 ዓመቱ ለምርጫ ቀርቦ ሳይሳካለት ቀረ፡፡
በ48 ዓመቱ በኮንግረስ ምርጫ ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ50 ዓመቱ ለሕግ መወሰኛ ም/ቤት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ56 ዓመቱ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ58 ዓመቱ እንደገና ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
ተስፋ ሳይቆርጥ ታግሦ በመጨረሻ በ1860 ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ተመረጠ፡፡ የጥቁሮችን መብት ያስከበረና አሜሪካን አንድ ያደረገ ትልቅ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነ፡፡ አብርሃም ሊንከን በ32 ዓመቱ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ እንደ ወደቀ በቃኝ ለእኔ ያልተሰጠ ነው ማለት ይችል ነበር፡፡ የሚወዳት አፍቃሪው በሞት ስትለየው ዓለም ለምኔ ብሎ ሁሉን ነገር መተው ይችል ነበር ፡፡ በአደባባይ የሚታወቁ ዘጠኝ ሙከራዎቹ መልሳቸው ውድቀት ነበር፡፡ በዐስረኛው ሙከራ ግን ከአሰበው ላይ ደረሰ፡፡ ለእነዚያ መከረኛ ጥቁሮች መብት ቆመ፡፡ የእርሱ ጅምር ዛሬ ከፍፃሜ ላይ ደርሶ አሜሪካ በማይታመን መልኩ በጥቁር ለመመራት በቃች፡፡
ወድቆ ለመቅረት ካለን ምክንያት ለመነሳት ያለን ምክንያት ይበልጣል፡፡ እግዚአብሔርና ደጋግ ሰዎች እየጠበቁን ነውና፡፡
ትዕግስት..... ተጨማሪ ሙከራ...... ወድቆ መነሳትን መልመድ...
የመጀመሪያው መጽሐፍ ይሄ ነው!
ይህችን እያነበባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገድ ጀምሩ እንደመጽሐፉ እየኖራችሁ ያላችሁም በርቱልኝ...
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አይለየኘ

በቀጣይ ከትላንቱ መፅሐፍ ትንሽ እንቆንጥር🏃♂🏃♂🏃♂🙏🙏
ቀጥታ ከመፅሐፉ ስለምወስደው እባካችሁ
እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ፈጣሪ ወይም አላህ .....ብላችሁ እንድታነቡት እመክራለሁ የመፅሐፉ ዋና አላማ ህይወትን መቀየር ነውና፡፡
ቀጥታ ከመፅሐፉ ስለምወስደው እባካችሁ
እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ፈጣሪ ወይም አላህ .....ብላችሁ እንድታነቡት እመክራለሁ የመፅሐፉ ዋና አላማ ህይወትን መቀየር ነውና፡፡
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ይችለናል
ቀላል ሰው የሰማውን እስኪናገር ምጥ ይይዘዋል። የእግዚአብሔር ሰው ግን የእግዚአብሔርን ባህርይ ስለሚካፈል ያየውን ክፉ የማያሳይ ፣ የሰማውን ክፉ የማያሰማ ፣ መልካሙን እንጂ ክፉውን የማያውጅ ፣ የበደለውን ወንድሙን በር ዘግቶ የሚወቅስ ፣ ጥቅምን ሳይሆን ፍቅርን የሚያስብ ፣ ጭካኔ ድል ነስቶ ርህራሄን ገንዘብ ያደረገ ነው፡፡ ይህን መስፈርት የሚያሟላ የእግዚአብሔር ሰው ያለ ባይመስለን እንኳን እግዚአብሔር ግን አለ፡፡ ዛሬ ለክፋት የጨከኑ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ለበጎ ነገርም የጨከኑ የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ፡፡ ምናልባት በአደባባይ ሳይሆን በእልፍኝ በከተማ ሳይሆን በገዳም ስላሉ እነዚህን ሰዎች ማየት እንቸገር ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን መልካም ሰዎችን እንድንፈልግ ብቻ ሳይሆን መልካም ሰው እንድንሆንም ነው፡፡ ሰዎች በስብዕና የሚያደርጉትን እኛ በመንፈሳዊነት ማድረግ ካልቻልን ቆም ብለን እራሳችንን መመርመር ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰማውን የማያሰማብን ፣ የነገርነውን ምስጢር የማይዘራብን እውነተኛ አባት ነው፡፡ ዛሬ የሰው ነውር ዜና ተብሎ ብዙህ ሺህ ብር ከሚሸጥበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የሚደብቅንል ሰው የምንደብቅለትም ወዳጅ የሌለበት የመካሰስ ዘመን ላይ ነን፡፡
የምንባረከው በመሸፋፈን እንጂ በመገላለጥ አይደለም፡፡ የወዳጃችንን ሐፍረት ከሌሎች እየሰወርን ለመለወጡ ግን ተግተን መምከር አለብን፡፡ እኛ ያየነውንም ያላየነውንም እናወራለን። እግዚአብሔር ግን ከመነሻው እስከ ፍፃሜ ያለውን ታሪክ እያወቀ ዝም ይላል፡፡ አንዳንዴም ሰውየው ንስሐ የገባበትን በደል ሳይቀር እናወራለን፡፡ ሰይጣን እንኳን በደልን በመመዝገብ ትጋቱ ንሰሐ የተገባበትን ኃጢያት ሲፅፍ አይውልም፡፡ እኛ ግን እንዲህ ስናደርግ ከሰይጣን መባሳችንን አንረዳም፡፡
እኛ ምህረትን በመስጠት መአትን ማውረድ አንችልም፡፡ ሁላችንም በታላቅ ችሎት ፊት አንድ ቀን እንቆማለን፡፡ እግዚአብሔር መዓቱም ምህረቱም በእጁ ሆኖ ይታገሰናል፡፡ ዛሬ አብረን እየበላንና እየጠጣን የወዳጃችንን ወንጀል ለአንድ ቀን እናጠራቅማለን፡፡ ይልቁኑም ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ለማዋረድ ስንት ፋይል ከፍተን እናሰባስባለን፡፡ አላወቅነውም እንጂ የወንድማችን ውርደት የኛም ውርደት ነው፡፡
እግዚአብሔር ለሁሉም እንደስራው ይሰጠዋል፡፡ እርሱ ሲፈርድ የእኛን ሰነድና ምስክርነት አይፈልግም፡፡ የሁሉም ጥፋት ከየግንባሩ ላይ ያነበዋል፡፡ በክርስቶስ ፊት ስንቆም የራሳችን እንጂ የሌሎች በደል አይታየንም፡፡እግዚአብሔር ቢቀጣን ምክንያታዊ ነው፤ ኃጢያተኞች ነንና፡፡ ነገር ግን የመዳን ምክንያት እንዲሆነን ምህረቱን አቁሞልናል፡፡ ሁላችንም "የአንድ ቀን ሥልጣን ቢኖረኝ" እንላለን በአንድ ቀን ሥልጣናችን ያንን ሁሉ ክፉ ሃሳባችንን ለመፈጸም ፤ በዘላለም ሥልጣኑ እኛን የሚያኖር ጌታ ትዕግስቱ እንዴት ሰፊ ነው!! እግዚአብሔር በፀጋው ስለሚያስተዳድረን ይኸው "አለን" ለማለት በቅተናል፡፡
እግዚአብሔር ያየብንን ቢያሳይብን ፣ የሰማብንን ቢያሰማብን ኖሮ እንደ ሰው እንኳን የማንቆጠር ፣ አንድም ቀን ለማደር የማይፈቀድልን ሰዎች በሆንን ነበር፡፡ የህሊናችንን ቁልፍ በራሱና በእኛ እጅ ስላደረገው እንኳን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ የምናስበው ሁሉ ቢገለጥ ከማን ጋር እንኖር ነበር??? እግዚአብሔር ብቻ ይችለናል የእኛ ነገር የማይገርመው እርሱ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ የነገርነውን ሌላ ሰው ጋር አናገኘውም፡፡ ሰዎች የምንናገረውን በማዳመጥ ይወዱናል፡፡ የምናስበውም ግን አያውቁም፡፡ ቢያውቁ ሊጠሉን ይችላሉ፡፡ አውቆ የሚወደን ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ የቀደሙ አባቶች እንደሚሉት "እርሱ ልብ ያወጣውን ኩላሊት ያጤሰውን ያውቃል" ይህ አምላክ አንድ አላማችን ፣ አንድ አይናችን ፣ አንድ ተስፋችን ነውና ተጠንቅቀን ልንይዘው ይገባል፡፡ ከሰው የታጣ በእርሱ ይሞላል፡፡ ከእርሱ የጎደለ ግን በማን ይሞላል??? ሰው ቢሸሸን እግዚአብሔር ዘመድ ይሆነናል÷እግዚአብሔር ቢርቀን ግን ማን ዘመድ ይሆነናል???
ሰዎች ፍቅራችንን ቢችሉት በደላችንን ግን መቻል አይሆንላቸውም፡፡ መስጠታችንን ቢወዱትም ሁልጊዜ ተቀባይ መሆናችንን ግን አይፈልጉትም እግዚአብሔር በኃጢያታችነ በፍላጎታችን ይችለናል፡፡ እርሱ እንዳየ ሰዎች ቢያዩን እርሱ እንደሰማ ሰዎች ቢሰሙን እንደ እኛ ክፉ ፍጥረት ባልነበረ፡፡ እርሱ ግን እንደኃጢአታችን አላደረገብንም እንደበደላችንመ አልከፈለንም፡፡
ያለንበት ዘመን ለእውነት ተቆርቋሪ የሚመስለውም ሆነ በአቋም የሚዋሸው ሁሉም አንድ የሆነበት ዘመን ይመስላል፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ደግሞ በራቸውን ዘግተው የመጣውን መዓት እስኪያልፍ አቤቱ አቤቱ እያሉ ነው፡፡ በዛሬው ዘመን ያለው እውነተኝነት በእውነት ተከልሎ የጠሉትን ለማጥቃት እንጂ የጠፋውን ለመመለስ አለመሆኑ ያሳዝናል፡፡ ለዚህም ድራማችን እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ድንበር ይሰጠዋል፡፡ ጥበብም ፣ ሃብትም የማያልፈው ቁርጥ ቀን ቀርቧል፡፡ ይችህ ቀን የምታልፈው ያለ ግብዝነት የምትቀርብ ፀሎትና እውነተኛ ንስሐ ብቻ ናት፡፡
ከእርሱ ጋር ያለነው በአንድ እድል ቢሆን ኖሮ ሰው ለመሆን ባልበቃን ነበር፡፡ "ከሎሌ ጥፋት ከጌታ ምህረት" እንዲሉ እኛ ከመበደል እግዚአብሔር ይቅር ከማለት ያረፍንበት ዘመን የለም። እግዚአብሔር ለመጨረሻ ጊዜ ነው ምቀበላችሁ ቢለን ምን እንሆን ነበር??? እርሱ ከእንግዲህ ወዲህ በቃኝ ቢለንስ ማን ይሸከመናል???
የማይለወጥ ፍቅሩ፣
የማይናወጥ ባሕርዪ፣
የማያልቅ ቸርነቱ፣
የማይሰለች ምህረቱ፣
የማይወሰን ይቅርታው፣
የማይጠብ ትዕግስቱ.......
ከኛ ያላራቀ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን
ከመጀመሪያው መፅሐፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተቀነጨበ፡፡
ይችህን እያነበባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገጅ ጀምሩ እንደመጽሐፉም እየኖራችሁ ያላችሁ በርቱልኝ.....
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

በቀጣይ ከመጀመሪያው መፅሐፍ የመጨረሻ ፖስት፡፡
ትንሽ ረዘም ስለሚል ሁለት ቦታ ከፍለን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻም ፖስት ላይም የመፅሐፉን ርዕስና የደራሲውን ስም ምናሳውቅ ይሆናል፡፡
😊🙏😍🙏 ቤታችን እንሁን
ትንሽ ረዘም ስለሚል ሁለት ቦታ ከፍለን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻም ፖስት ላይም የመፅሐፉን ርዕስና የደራሲውን ስም ምናሳውቅ ይሆናል፡፡
😊🙏😍🙏 ቤታችን እንሁን
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ይቅር ባይ እንሁን
የሀሳብ መለያየት ተፈጥሮ ነው፡፡ ተፈጥሮን መሻር አይቻልም፡፡ ተፈጥሮ ግን በመወያየት ይታረቃል፡፡ ባል እና ሚስት እኮ የሚያዋህዳቸው የተፈጥሮ ልዩነታቸው እንጂ አንድነታቸው አይደለም፡፡ ጾታቸው የተለያየ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን የአንድነት ምክንያት ነው፡፡ ልዩነት ወደ አንድነት ያመጣል፡፡ ፍቅር ነው፡፡
የሀሳብ መለያየት እንደጠላት እያስተያየ ማጋደሉ ዛሬም ድረስ ዘልቋል፡፡ ቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር እየተባባሉ በጎዳና ሲቀላሉ የኖሩ የአንድ እናት ልጆች አመለካከትን ማስታረቅ አቅቷቸው ነው፡፡ የአሳብ ልዩነትን እንደጠላት ማስተያየቱ አሳዛኝና ኀላ ቀርነትም ነው፡፡
በግጭቶች ውስጥ አንዱ ትዕግስት ያጣና ክፋ ቃል ይናገራል ፣ ክፉ እርምጃ ይወስዳል፡፡ እርሱ ጀምሮታል ብለውም ሁለኛውን ክፋት ብዙዎች ይቀጥላሉ፡፡ አንተ ትዕግስት የምታጣው ወገን አንድ ክፉ ነገር ስትናገር ሁለት ክፉ ትሰማለህ፡፡
የዘራኸውን ስድብ አትረፍርፈህ ታመርታለህ፡፡ አንተ ክፉ ምላሽ የምትሰጥ እርሱ በጀመረው ላይ ስለቀጠልክ የማትጠየቅ እንዳይመስልህ የሚያስጠይቀው ቅደም ተከተሉ ሳይሆን ክፉ ማድረጉ ነው፡፡ ይልቁንም እረሱ ሲያደርገው የጠላኸው እንዴት እንዲጠጋህና እንዲገዛህ ትፈቅዳለህ? ለክፉ ክፉ ስትመልስ የተንኮል ደቀመዝሙር እየሆንክ ለክፋት ሠራዊት ተጨማሪ ወታደር እንደሆንክ ማሰብ አለብህ፡፡ እርሱ በእጁ ያለውን ድንጋይ ይወርውር ባንተ እጅ ያለውን ብርቱካን ወርውርለት፡፡ ድንጋዩ ሲያልቅበት መልሶ ብርቱካኑን ይወረውርልሃል፡፡ ክፉ ነገር ያልቃል ፣ መልካም ነገር ግን አያልቅም፡፡ ብዙ ሀይለኞች ዛሬ ደክሟቸው የትንንሽ ልጆች መጫወቻ ሆነዋል የእግዚአብሔር ሰራዊቶች ግን በዓመታት ውስጥ አይደክሙም፡፡
አንድ ታዋቂ መሪጌታ ነበሩ፡፡ እኚህ መሪጌታ ክፉ ነገር ከአፋቸው ተሰምቶ አይታወቅም። ታዲያ አንድ ቀን ሰዎች፡- "እርሶ ግን መቼ ነው ተሳስተው ክፉ ነገር የሚናገሩት?" ቢሏቸው :- "መልካሙ መቼ አልቆብኝ ነው ክፉ ምናገረው" አሉ ይባላል፡፡
ለብዙዎቻችን ጠላታችንን ይቅር ከማለት ወዳጃችንን ይቅር ማለት ይከብደናል፡፡ የመዋደዳችን ፍፃሜ መጠላላት ለምን ሆነ? ከመጀመሪያው ፍቅር የኋላው ይቅርታ ይሻላል፡፡ አዎ "የሰዎችን በደል ሲረገጥ በሚጠፋው ፣ ነፋስ በሚሸፍነው አሸዋ ላይ መጽሐፍ ይገባናል። መልካምነታቸውን ግን በማይጠፋው ዓለት ላይ በልባችን ላይ መቅረፅ ይገባናል፡፡"
እኛ ግን የምናደርገው በተቃራኒ ነው፡፡ አንገት የተሰጠን ለጌጥ አይደለም ፣ ዞር ብለን ለማየትም ነው፡፡ ስለዚህ ያለፈውን መልካም ጊዜ ዞር ብለን ማየት አለብን፡፡ ለክፋት ሳይሆን ለመልካም ነገር ዋጋ መስጠት አለብን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት ፣ የእሳት ፍንጣሪ የምታህል ምግባር ዋጋ አላት፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ የመልካም ነገር ዋጋው ብዙ ሲሆን በሰው ዘንድ ግን የክፉ ነገር ሚዛኑ ከፍ ያለ ነው፡፡
የራሳችንን ደካማነት ስንረዳ የሌሎቹን ደካማነት ለመረዳትና ይቅርታ ለማድረግ ዝግጁ እንሆናለን፡፡ ሰው ማነው? ለሚለውን ጥያቄ ምላሽ ካገኘን ይቅርታ የማይከብደን ሰዎች እንሆናለን፡፡ እውነተኛ ፍቅርም በክፋት ተሸንፎ ቂመኛና በቀለኛ የሚሆን ሳይሆን በመልካም አሸንፎ በዳዩን ሰው ለንሰሐ የሚጋብዝ ነው፡፡ በዓለም ላይ ከሰዎች ጋር የማንነካካበት ኑሮ ስለሌለን አስተውለን ካየነው የብዙ ሁከታችን ምንጩ የይቅርታ ሕይወት ማጣት ነው፡፡ ይቅርታ የከበደው ልብ ሁሉም ነገር ይከብደዋል፡፡
ሰዎችን ከማኩረፍና ከመሸሽ በላይ የምናስተምራቸው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ማድረግ የወደቀው እንዲነሳ እድል መስጠት ነው፡፡ በአለም ላይ ትልልቅ ስራ የሚሰራው ከተዓምራት ይልቅ በይቅር ባይነት ነው፡፡ በክፋት እየመረረች ያለችው አለማችንን የሚያጣፍጡ ይቅር ባይና አፍቃሪ ሰዎች ከሌሉ የሰው ሕይወት ፈፅሞ ተስፋ የሌለው ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይቅር ባይ እንሁን!! ይቅር ያልናቸው ሰዎች ከበደሉን በላይ ይክሱናል፡፡ ይቅርታ ሰው ያበላሸውን እንዲያስተካክል ዕድል መስጠት ነው፡፡
ህፃን ልጅ ወድቆ የሚነሳው ዙሪያውን አይቶ የሚጠብቁት ሰዎች ድጋፍ ከሰጡት በኋላ ነው፡፡ ተስፋ የሚያደርገውሰው ከሌለ ለመነሳት አያስብም፡፡ እዚያው እንቅልፍ ይይዘዋል። ሰዎችም ከስህተታቸው የሚመለሱት የወዳጆቻቸውን ይቅርታ ሲያገኙ ነው፡፡ አሊያ እንደወደቁ ይቀራሉ፡፡ ሌባ የሚባሉት የሚሰርቁትን ንብረት ጠብቁ ስንላቸው ከደህነኛ ሰው በላይ ይጠብቃሉ፡፡ ፀጥታ ሲጠፋ የበጥባጮቹን አለቃ አደራው ላንተ ነው ሲባል ሌት ተቀን ተግቶ ሰላምታን ያስከብራል፡፡ ሰዎች ባመናቸው መጠን ይታመኑልናል፡፡ ይቅርታ የወደቁትን ሰዎች እንዲነሱ እድል መስጠት ነው፡፡
አንድ አባት "ልጄ በአንድ አፍ ውስጥ የሚኖሩትን ጥርስና ምላስ አስታውስ፡፡ እነዚህ አካላት ተፈጥሮአቸው የተለያየ ነው፡፡ ጥርስ ነጭ ነው ፣ ምላስ ቀይ ናት፡፡ ጥርስ ጠንካራ ስለታም ነው፡፡
ምላስ በጣም ለስላሳ ናት፡፡ አፍ ሲከፈትላት ምላስ ትወጣለች፡፡ ሲከደን በገዛ ጎረቤቷ ላለመጎዳት ትሸሻለች፡፡ ጥርስ ያደማውን እጅ ምላስ ትልጣለች፡፡ ጥርስ ሲያኘክ ምላስ ታርስለታለች፡፡ የፊት ጥርስ ማኘክ ሲከብደው ወደመንጋጋው እህሉን በመውሰድ ትራዳለች፡፡ ግን በአንድ ቤት ይኖራሉ፡፡ እኛም መልካችን ፣ አቅማችን ፣ የሥራ ድርሻችን የተለያየ ፣ አንዳችን ስለታም አንዳችን ለስላሳ ብንሆንም ተቻችለን መኖር ይገባናል " አሉኝ። አዎ እሾህ ያላቸው ጃርቶች ተጣብቀው ይሔዳሉ፡፡ አንዱ ያንዱን ሙቀት ለማግኘትና ብርዱን ለመከላከል መወጋጋታቸውን ይችላሉ፡፡ እኛም ባልተለወጠ ማንነት ውስጥ እንደመኖራችን ሁላችንም ያልተነቀለ እሾህ አለን፡፡ ተገልለን ለመቀመጥ የዓለሙ ብርድ ይገድላል፡፡ ከመሞት መቁሰል የተሻለ ነውና ልንጠጋጋ ይገባናል፡፡ ድካማችንን እንደ አደጋ ከመቁጠር ተፈጥሮ መሆኑን ማሰብ ያበረታናል፡፡ ክፉ ጠባይ ባለቤቱም እየጠላው አብሮት ይቆያል፡፡ እግዚአብሔር ግን ይለውጣል፡፡ ተሰርተን እስከምናልቅ መሸካከም ይገባናል፡፡
.....ይቀጥላል....

በቀጣይ
ከመጀመሪያው መፅሐፍ ቀሪውንና የመጨረሻውን ክፍል ይዘን እንቀርባለን መፅሐፉን ገዝታችሁ እንደምታነቡት ባለሙሉ ተስፋ ነኘ፡፡ አስተያየታችሁን እየሰጣችሁኘ ስላላችሁም ደስተኛ ነኘ አሁንም ይቀጥል እላለሁ፡፡
ቤታችን እንሁን እናንብብ

ቀጣይ እና የመጨረሻ ክፍል
.....ይቅርታ በነበረን ታሪክ ላይ ያልነበረንን አዲስ ታሪክ በህይወታችን ላይ ይጨምርልናል፡፡ የበደለንን ብናስፈርድበት ይህ ለዓለም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይቅር ብንለው ግን አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በይቅርታ ሊማሩ የማይፈልጉ ሰዎችን እናስተምርበታለን፡፡ በእውነት የሚከብደን ይቅር ማለት ብቻ ሳይሆን ይቅርታም መቀበልም ይከብደናል እግዚአብሔር ይጎብኘን፡፡
አዎ እግዚአብሔር በኃጢያታችንና በድካማችን ተሸክሞናል፡፡ ራርቶም ይቅር ብሎናል፡፡ ይህ ትዕግስቱ ከማረከን እኛም ይቅር ባዮች ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በድካማችን ብቻ ሳይሆን በፍላጎታችንም ተሸክሞናል፡፡ እኛም የሰዎችን በደላቸውን ብቻ ሳይሆን ፍላጎታቸውንም በትዕግስት ልናሟላላቸው ይገባናል፡፡
አንድ ሰው፡- "በዚህ ዓለም ላይ ያለኝ ወዳጄ ልብስ ሰፊዬ ነው፡፡ እርሱ ብቻ በትላንቱ አይለካኝም" ብሏል ልብስ ሰፊ ትላንት ለክቶን እንደሆነ ዛሬም ስንሔድ ይለካናል እንጂ በትላንቱ ልኬት ተረጋግቶ አይቀመጥም፡፡ እውነተኛ ወዳጅም በትላንትናው ማንነት የማይለካ ዛሬም በመለወጣችን የሚያምንብን ነው፡፡ የአገራችን ሰው፡- "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደሚል የአንድ ቀን ስህተት የሁልጊዜ ስህተት ፣ የአንድ ቀን ጥፋት የሁልጊዜ ጥፋተኘነት አድርገን መውሰድ በእውነት ሀጢያት ነው፡፡ ሰው ይለወጣል ሰው እንደሚለወጥ ካላመንን ሰውነታችንን እያጣን ነው፡፡ እኛም እንደቀድሞው አይደለንም፡፡ ሰዎችም እንደቀድሞ አይሆኑም፡፡ ይህ ዓለም በየዕለቱ ትምህርት አለውና፡፡
የሰዎችን የቀደሙ ስህተታቸውን ልንረሳላቸው አልቻልንም፡፡ ንሰሐ ገብተውበት ይሆናል፡፡ እኛ ግን ይቅርታውን ሳይሆን ስህተቱን ስናወድስ እንኖራለን፡፡ ታላላቅ ሰዎችም ቢሳሳቱ ሊገርመን አይገባም፡፡ ታላቅነታቸው ሰው መሆናቸውን አያስቀረውምና፡፡ ደካማ ሰዎች ግን በታላላቆቹ ስህተት ሲሳለቁ ይኖራሉ፡፡ ቃሉም "እንደ ቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ይለናል፡፡
ሰዎች የጣሉትን ሸክም እኛ ተሸክመንላቸው እየተበሳጨን እንዳይሆን እግዚአብሔር ይግለጥልን፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ይቅር እንባባል፡፡ እናቶቻችን የቂም ሙዳዮች ፣ እንዳይበሰብስ የሚጠብቁት ናቸው፡፡ እገሌን በዓይኔ አያሳየኝ የሚሉት ምክንያቱ ምንድነው??? ብንላቸው በመንግስቱ ንዋይ ግርግር ጊዜ እንዲህ አድርጋኝ ነበር ይላሉ፡፡ እስከዛሬ በዚያ ክስተት ይበሳጫሉ፡፡ በደሉ የተፈፀመው ግን 1953 ዓ.ም ነው፡፡ ቂምን መንከባከብ አረም ስንዴ ላይሆን መልፋት ነው። ይልቁንም በዛሬው ዘመን የሀይማኖት ሰዎችን ከማስታረቅ ዓለማውያንን ማስታረቅ እስኪቀል ድረስ መራሮች ሆነናል ይቅር እንባባል፡፡
በእውነት ትዕግሥትን ገንዘብ በማድረግ ይቅር ባይ እንሁን፡፡
የመፅሐፍ ርዕስ:- የእግዚአብሔር ትዕግስት
በዲ/ን አሸናፊ መኮንን
2002ዓ.ም
ከመጀመሪያው መፅሐፍ የመጨረሻ ፅሁፍ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
ከጻፍኩት ያልጻፍኳቸው አያሌ ምክሮች አሉበትና ገዝታቹ ታነቡት ዘንድ ስጋብዛችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በእውነት አብዝታችሁ ታተርፉበታላችሁ ትለወጡበታላችሁም ህይወታችሁን አንድ ደረጃ ከፍ ታደርጉታላችሁ ትዕግስተኛ እና የይቅርታ ሰው ትሆኑበታላችሁ .....በእርግጠኝነት ከራሳችሁ አልፎ የሌላ ሰውንም ህይወት ትቀይሩበታላችሁ፡፡
መጽሐፉን አንብባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገድ ጀምሩ እንደመጽሐፉ እየኖራችሁ ያላችሁ በርቱልኝ
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኝ
ጊዜዋን አጣባ የኔን አያሌ ስህተቶች ሳትሰለች አርማ እናንተ ጋር በአማረ መልኩ እንዲደርስ ለረዳችኘ ለትዙ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡
😍🙏😍🙏😘

ከንባብ አለም ረፍት ስናደርግ ደሞ እስኪ አንድ ፊልም ልጋብዛችሁ
የምንማረው ለምንድነው??
እየተማርንስ ያለነው የፍላጎታችንን ነው ወይስ ሰዎች የመረጡልንን?? ፍላጎታችነ ምንድነው
እየሰራን ያለነው የምኖደውን ስራ ነው?? የምኖደው ስራ ምንድነው??
ከሆነ አመት በኀላ ወይኔ ያኔ እኮ ያንን እድል ብጠቀምበት ያን ትምህርት ብማር ይሔን ስራ ባልሰራ ማለት ትፈልጋለህ.....?? በእርግጠኘነት አትፈልግም የምቶደውንስ እንዴት ማግኘት አለብን??.......አለማዊ ትምህርቶች ብቻ ናቸው ለሰው ልጅ ጠቃሚ?? ተፈጥሮስ የምትችረን ነገር የለም?? እኔ ብቻ ነኘ ልክ ሚለውስ ምን ያህል እየጎዳን ነው?? ጓደኞቻችንንስ እንዴትነው መርዳት ያለብን ወደ ተፈጠሩበት አላማ እንዲጓዙ?? እውነት መናገርስ አይጠቅመንም??እኛ ከፍ ምንለውስ ሌሎቹን ዝቅ በማድረግ ነው?? በነገራችን ላይ አሜሪካን ፊልም አይደለም እንዲህ እንዲህ እያለ እራሳችንን እንድንጠይቅ በሳቅ እየተዋዘ የቀረበው በራጅኩማር ሒራኒ ዳይሬክት የተደረገውን 3 idiots የተሰኘ በ2009 የተለቀቀ ኮሜዲ/ድራማ ዘውግ የቀረበ ምርጥ የህንድ ፊልም ነው፡፡
በትወናው ቦማን ኢራኒ ፣ አሚር ከሃን ፣ካሪና ካፑር፣ ሻርማ ጆሺ፣ ማድሃቫን፣ኦሚ ቫዲያ፣ አሊ ፋዛል.....በብቃት ተጫውተውታል፡፡ ርዝመት 2:50ደቂቃ
በመጨረሻም ትልቅ የተማርኩበትን ነገር ወዲህ ልበልላችሁ.....
ዳይሪክተሩ ተማሪዎቹን ይጠይቃል
★......."ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ማነው??
★........ኒል አምስትሮንግ
★.........ሁለተኛስ
★...ዝም
★........አያቹ ሁለተኛ ከሆናቹ ብዙ ሰው ቁብ አይሰጣችሁም ሁሌም አንደኛ ለመሆን ሞክሩ፡፡"
ከትላንት የተሻልን መሆን አለብን የተሻልን ሳይሆን የበለጥን...ሩጫችን ከትላንትናው ማንነታችን ጋር አንደኛ ለመውጣት አለብን ባይ ነኘ፡፡

ወደ ሁለተኛው መፅሐፍ ከመሸጋገራችን በፊት እሲኪ የወደድኩትን አንድ ትልቅ ሰው ላስተዋውቃችሁ.....😊
"ታላቅነት የሚመጣው ባለመውደቅ ሳይሆን ከውድቀት በመነሳት ነው"
ኮንፊሺየስ በቻይና ታሪክ ትልቁን ሥፍራና ድርሻ የያዘ ሰው ነው፡፡ እውነተኛ ስሙ ኮንግ ኩዊ ሲሆን ውልደቱም የመሳፍንት ዘር ከሆነው ከኮንግ ጎሳ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ551 እንደ ነበር ይታመናል፡፡
ጥንታዊ የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱት የኮንፊሺየስ አባት ሉ የተባለችው ግዛት ገዢ እንደነበርና ኮንፊሺየስ በተወለደ በ3 አመቱ እንደሞተ ያትታሉ፡፡ የአባቱ መሞት ኮንፊሺየስን ጨምሮ ቤተሰቡን ለከፋ ድህነት የዳረገ ሆነ። ይሁንና በድህነት ውስጥም ቢሆን ኮንፊሽየስ በዘመኑ የተሻለ የተባለውን ትምህርት ለማግኘት የታደለ ሆኖ አድጓል፡፡ በ19ኛ ዓመቱ መግቢያ ላይ ትዳር መስርቶም ኮንፊሺየስ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆችም አባት ነበር፡፡
ኮንፊሽየስ በዘመኑ የደከመበት ጉዳይ ቢኖር ጥንታዊውን የቻይና ታሪክ በማንሳት በእሱ ዘመን ትውልድ ውስጥ ሕያው እንዲሆን የከወነው ጥናት ነበር፡፡ በዚህም ጥናቱ ጥንታዊ የቻይና ስነ-ጽሑፍ ተመልሶ እንዲያንሰራራ ታላቅ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን አልፎም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍበት የመማሪያ መጽሐፍም ሆኖ አገልግሏል፡፡ ምንም እንኳን እራሱ ኮንፊሽየስ ለልዕለ ተፈጥሮአዊ አካል(አምላክ) ያለው እምነት እጅጉን አናሳ ቢሆንም እሱ ግን በሚሊዮኖች ተከታዮቹ ዘንድ እንደመንፈሳዊ ሰው እየታየ ሲታመንበት ኖሯል፡፡
ኮንፊሺየስ የፍልስፍና ስራዎቹን አላስተላለፈም፡፡ ነገር ግን እሱ ተናግሯቸዋል ፣ አስተምሯቸዋል የተባሉት ቁም ነገሮችና በተለይም የፍልስፍና እሳቤዎች በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት እየተጻፉ ትውልድና ዘመንን እየተሸጋገሩ እዚህ ደርሰዋል፡፡
የኮንፊሺየስ ትምህርቶች ከሃይማኖታዊ ይዘታቸው ይልቅ በተግባራዊ የሕይወት ልምምድና በሥነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ የጥንቱን ግብረ-ገባዊ ዕውቀት በእሱ ትውልድ ሊመልስ የተነሳና በተለይም በአምስቱ መልካም ተግባራት በሚላቸው (ርኅሩኅነት ፣ ጻድቅነት ፣ ትሁትነት ፣ ጥበበኛነት ፣ ታማኝነት) የሰው ግዴታዎች ላይ አስተምሮቱን መስርቶ ነበር፡፡
ወላጅን መታዘዝና ለሕያዋንና ለሙታን ክብርን መስጠት ቁልፍ የትምህርቱ ሐሳቦች ነበሩ። ስለመንግስትም የነበረው አመለካከት ወላጅ ከልጁ ጋር ከሚያደርገው ግንኙነት ጋር የተዛመደ ነበረ፡፡ ዜጎችም መንግስት የሚፈልጉባቸውን ግዴታ በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ይመክር ነበር፡፡ የመሪዎች ታላቅነት በሚመሩት ሕዝብ ሕይወት የሚታይ ነው፡፡ የሚመሩበት የሞራል ሕግ ሲኖራቸው መንግስታቸው ዜጎቹን ወደ እሱ መሳቡ አይቀሬ ነው በማለት የወቅቱን የሀገሩንና የሕዝቡን አደጋ ለመመለስ ይጥር ነበር። እነዚህንና ሌሎችን ትምህርቶች በቻይና ቀጣይ ዘመናት ውስጥ የፍልስፍናዋ የታሪኳ መሰረት ሆኖ በሰፊው ታይቷል፡፡
የኮንፊሽየስ ተማሪ አንድ ቀን የጥበብን መማሪያ ይነግረው ዘንድ ጠየቀው፡፡ ኮንፊሺየስም፡- "ጥበብን በሦስት አይነቶች መንገድ መማር ትችላለህ፡፡ የመጀመሪያው በማንፀባረቅ ሲሆኑ እሱ ታላቅ መማሪያ ነው ፤ ሁለተኛው በማስመሰል ሲሆን ይኸ ደግሞ ቀላሉ ነው ፤ ሦስተኛው በልምድ ሲሆን እሱ መራር ነውና አትሞክረው" ብሎታል፡፡ "እየተማረ የሚያስብ እሱ ጠፍቷል ፣ እያሰበ የማይማር ደግሞ እሱ ታላቅ አደጋ ላይ ነው" የሚለው ኮንፊሺየስ ዕውቀትን መያዙ ሳይሆን በተግባር መገለጡ ዋነኛ እሳቤ ሊሆን እንደሚገባ ይናገራል፡፡ "ዕውቀት የሌለው ሰው ዕውቀት ማጣቱን ቢናዘዝ አዋቂ ሆነ ማለት ነው" በማለት ኮንፊሺየስ ለአላዋቂም የሚመክረው ቁም ነገር አለው፡፡
"የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለፀው በተግባሩ እንጂ በንግግሩ አይደለም" የሚለው ኮንፊሺየስ የተግባር መሠረቱ ደግሞ ጽኑ ፍላጎት መሆኑን አበክሮ ይናገራል፡፡ ለዚህም ነው፡- "የአንድ ተራ ሰው ጽኑ ፍላጎት ከውስጡ ከመውሰድ ፣ የአንድ ታላቅ ሃገርን የጦር አዛዥ መማረክ ይቀላል" የሚለው፡፡ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ዓይነቱን ጽኑ ፍላጎት በውስጣቸው ሲተክልና ሲኮተኩት ኖሯል፡፡
በሌላ ቀን አንድ ደቀመዝሙሩ፡- ከጥሩ ጓደኛ መቅረብ ፣ ከመጥፎ ጓደኛ ደግሞ መራቅ ተገቢ አይደለምን?" በማለት ሲጠይቀው ኮንፊሺየስም መልሶ፡-"ከሁለቱም መራቅ ተገቢ አይደለም፡፡ ከጥሩ ጓደኛ ጥሩነቱን ስቀዳ ከመጥፎው ደግሞ መጥፎነቱን ተመልክቼ ራሴን ማስተካከያ አደርገዋለሁ" ብሎታል፡፡
"ሰዎች እያወሳሰቧት እንጂ ሕይወት ቀላል ናት" የሚለን ኮንፊሺየስ ሰዎች በጨለማው ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሸማ ቢለኩስ ለጨለማው ችግራቸው በቀላሉ መፍትሔ እንደሚያገኙ ይመክራል፡፡
ሰዎች ስለራሱ ይናገር ዘንድ ተጠይቆም ከሰዎች በአንደኝነት ነገር ብቻ የላቀ መሆኑን ይናገራል፡- "በድርጊቴም ይሁን በምግባሬ ከእኔ ጋር የሚስተካከሉ እጅግ ብዙዎች አሉ ፤ ከሌሎች ለመማር ባለኝ ፍላጎት ግን ማንም አይስተካከለኝም" ብሏል፡፡
ኮንፊሺየስ ተማሪዎቹን በጥበብ ፣ በርኅራሔ የተሞሉ ይሆኑ ዘንድ ይመክራል፡- "በጥበብ የተሞላ ሰው ክፉና ደጉን የሚለይ ሁለት አእምሮ አለው ÷ ርኅሩኅ ሰው ስለነገ አይጨነቅም÷ ጽኑ ሰው ደግሞ በምንም አይፈራም ፣ አይታወክም" ይላል፡፡
ከችግር ማምለጫው መላ በተማሪው የተጠየቀው ኮንፊሽየስ፡- " ዕውቀት በአእምሮ መሙላት ፣ ሳይታክቱ መማርና ሳይሰለቹ ደግሞ ማስተማር የችግር የማምለጫ መንገዶች ናቸው" ብሏል፡፡
"ታላቅ ሰው ችሎታውን ለማሳየት አይሽቀዳደምም" የሚለው ኮንፊሺየስ የታላቅን ሰው ችሎታ አላዋቂ ሊሸፍነውና ዝቅ ሊያደርገው ብቃቱ እንደሌለው ይናገራል፡፡ እንዲያውም ለተማሪዎቹ ሲናገር፡- "የአላዋቂን ሰው ስንፍናን ልኩን የሚያውቀው አዋቂ ሰው ብቻ ነው፡፡ እናም በሌሎች ዘንድ ለመታወቅ ከመድከም ይልቅ ልታወቅ የሚገባኝ ነኝ በሚለው እምነትህ ውስጥህን ሞልተህ ተቀመጥ፡፡ የዕውቀት አንዱ ጥቅሙ በራስ መተማመንን ማምጣቱ ነው ይላል፡፡
የኮንፊሺየስ ድንቅ ምክር ተደርጋ የምትወሰድለት ደግሞ እነሆ፡- "አለምን ሥርዓት ለማስያዝ በመጀመሪያ ሀገርን ሥርዓት ማስያዝ ያስፈልጋል ፤ ሀገርን ሥርዓት ለማስያዝ ደግሞ ቤተሰብን ሥርዓት ከማስያዝ ይጀምራል ፤ ቤተሰብን ሥርዓት ለማስያዝ የራስን ህይወት ሥርዓት ማስያዝ ይጠይቃል ፤ የራስን ህይወት ሥርዓት ለማስያዝ ደግሞ ልብን መግራት ያስፈልጋል፡፡ "ስለዚህም በኮንፊሺየስ አባባል የዓለም ነገር መነሻውና መጨረሻው ዞሮ ዞሮ ልባችን ነው፡፡ ልባችን ሥርዓት ሲያጣ ዓለም ላይ ይገለጣል እንደማለት ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው "የሀገር ጥንካሬ ከቤተሰብ ብርታት ይጀምራል" የሚለው፡፡
"ታላቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ታላቅነቱ ባለመታወቁ የማይናደድ ሰው እሱ በእርግጥ ታላቅ ነው" የሚለው ኮንፊሺየስ በዘመኑ ሁሉ ታላቅነቱን በተግባር ለመግለጥ እንጂ ለሰዎች ታይታ በመሮጥ ሲደክም ያልተገኘ ሰው ነበር፡፡ ኮንፊሺየስ አብዛኛውን ዘመኑን ጥንታዊ የስነ ጽሁፍ ቅርሶችን በመመርመርና በእነሱም ዙሪያ በማስተማር ያሳለፈ ነው፡፡
"አንድን ነገር መቼም ላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው ፤ ስታውቀው ደግሞ ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው" የሚለው ኮንፊሺየስ በቻይና የፍልስፍናም ሆነ የእምነት ታሪክ ውስጥ እስከዛሬ ጉልህ ሥፍራን እንደያዘ ዘልቋል፡፡
ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች/፩ ፪ ፫ ፬/
ከኃይለጊዮርጊስ ማሞ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
ለአስተያየታችሁ @jahABP አድርሱኘ