በግጭቶች ውስጥ አንዱ ትዕግስት ያጣና ክፋ ቃል ይናገራል ፣ ክፉ እርምጃ ይወስዳል፡፡ እርሱ ጀምሮታል ብለውም ሁለኛውን ክፋት ብዙዎች ይቀጥላሉ፡፡ አንተ ትዕግስት የምታጣው ወገን አንድ ክፉ ነገር ስትናገር ሁለት ክፉ ትሰማለህ፡፡
የዘራኸውን ስድብ አትረፍርፈህ ታመርታለህ፡፡ አንተ ክፉ ምላሽ የምትሰጥ እርሱ በጀመረው ላይ ስለቀጠልክ የማትጠየቅ እንዳይመስልህ የሚያስጠይቀው ቅደም ተከተሉ ሳይሆን ክፉ ማድረጉ ነው፡፡ ይልቁንም እረሱ ሲያደርገው የጠላኸው እንዴት እንዲጠጋህና እንዲገዛህ ትፈቅዳለህ? ለክፉ ክፉ ስትመልስ የተንኮል ደቀመዝሙር እየሆንክ ለክፋት ሠራዊት ተጨማሪ ወታደር እንደሆንክ ማሰብ አለብህ፡፡ እርሱ በእጁ ያለውን ድንጋይ ይወርውር ባንተ እጅ ያለውን ብርቱካን ወርውርለት፡፡ ድንጋዩ ሲያልቅበት መልሶ ብርቱካኑን ይወረውርልሃል፡፡ ክፉ ነገር ያልቃል ፣መልካም ነገር ግን አያልቅም፡፡ ብዙ ሀይለኞች ዛሬ ደክሟቸው የትንንሽ ልጆች መጫወቻ ሆነዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰራዊቶች ግን በዓመታት ውስጥ አይደክሙም፡፡ አንድ ታዋቂ መሪጌታ ነበሩ፡፡ እኚህ መሪጌታ ክፉ ገር ከአፋቸው ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ሰዎች፡- "እርሶ ግን መቼ ነው ተሳስተው ክፉ ነገር የሚናገሩት?" ቢሏቸው :-
"መልካሙ መቼ አልቆብኘ ነው ክፉ ምናገረው" አሉ ይባላል፡
መልካሙን እናስብ መልካሙን እንናገር መልካሙን እንስራ የዛሬ መልዕክታችን ነው፡፡
SHARE FOR YOUR FRIENDS
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
JOIN US ....
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD