በድሮ ዘመን አንድ ነጋዴ ወደ ከተማ ይመጣል በከተማውም እንደ ድንቅ ነገር ይታይ የነበረው መስታወት ነበርና ለሚስቱ ለመስጠት በታላቅ ፍቅር ይገዛላታል፡፡
ወስዶም ለሚስቱ ይሰጣታል፡፡ ሚስቱም ገልጣ ብትመለከተው የራሷን መልክ አየችው፡፡ ከዚህ በፊት መስታወት አይታ አታውቅም ነበርና ባሏ ከተማ ሲሔድ የወደዳት ልጃገረድ መስላት በብስጭት ታስቀምጠዋለች፡፡ነገሩን ታግሳመቆየት አልሆንልሽ ሲላት ያሳደጓት ከአያቷ ዘንድ ሔዳ አያቴ ባልተቤቴ ከኸተማ ዘልቆ አንዲት ሴት ወዶ መጣይባስ አልበቃ ብሎት ፎቶዋን ይዞልኘ መጣ ከዚህ በኀላ እኔ እና እሱ ከንድ ቤት አንኖርም ብላ እያለቀሰች ትነግራቸዋለች፡፡
አያትየውም እስኪ አምጫት ልያት ብለው መሽታወቱን ይቀበሏታል ሲያዩ የራሳቸውን መልክ ይመለከታል ውይይ ልጄ ይቺማ ጭርጭስ ያለች አሮጊት አይደለች እንዴ ነገ ትሞትልሻለች ባልሽም ወደቤትሽ ይመለሳል አሏት ባልሽም ወደቤት ይመለሳል ስለዚህ አትዘኚ አታልቅሺ አሏት ይባላል፡፡
ለመልካም የተደረገው ነገር ባለማወቅ እንዴት ክፋ ነገር እንደሆነ ይሔ ታሪክ ይነግረናል፡፡
መልካሙን መልካም የሚል እግዚአብሔር ብቻ ነው የሰው ልጅ አመሉ ብዙ ነው ግጅ ሳኖሞት መልካም ነገርን መስራት ማቆም የለብን፡፡
እኛ ሁላችን እንደታየን እንፈርዳለን እግዚአብሔር ግን በትግስቱ ና በዕውቀቱ ይፈርዳል፡፡
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን የእግዚአብሔር ትዕግስት ከሚለው መፅሐፉ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
መልካም ቀን
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
JOIN US ....
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD