AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
እናንተ ሰዎች ነው ያልከው??
አዎ ኡነቴን እኮ ነው ትገርሙኛላችሁ?? ለምሳሌ ይህን መስመር እየው አለኘ ወደ ወለሉ እያመለከተ ወለሉ ላይ ብዙ ቀጥ ያሉ መስመሮች አሉት፡፡ አየኻቸው አይደል ማንኛውም ሰው በህይወቱ እንደዚህ አይነት መስመሮች አሉት ግን ማንም ይሔን መስመር ጠብቆ መሔድ አይፈልግም በዚ መስመር ተጉዞ የፈለገበት መድረስ ይችላል፡፡ ግን የሌላው ያምረዋል ሌላውን ከመስመር አስወጥቶ እሱ ባቋራጭ ለመክበር ይፈልጋል የሱን መስመር ትቶ የሌላው መስመር ውስጥ ይገባል ሌላውን ከተሳካ አሽቀንጥሮ መጣል ካልሆነ ይዞ ማስቀረት ማዘግየት ይፈልጋል ጉልበት ያለው የሌለውን ይጨቁነዋል.....ታዲያ ሰው አይገርምም ትላለህ??
ሰው አይደለሁም ልልህ አይደለም ነኘ ያውም በሙሉ ጤነኘነት የተወለድኩ ግን አብዛኞቻችን እንደሰው መኖር አቅቶናል ልልክ ነው፡፡
ይኼማ ምንም ጥያቄ የለውም የሁላችንም ትልቅ ችግር ነው፡፡ አልኩት
በቀጣይ ስለማቀርብላችሁ መፅሐፍ አነሳሁለት ደራሲውን በጣም እንደሚወደው ነገረኘ ግን አህያዋን መፅሐፉ ላይ ማድረጉ ቅር እንዳለው ነገረኘ ለምነ?? ስለው፡፡
አህያ እወዳለሁ አሁን እያወራንበት ባለንበት ሰዓት አህያ ሆኜ ባወራህ ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ከhigh school ጀምሮ አህያን ፕሮሞት እያረኩ ነው የመጣሁት፡፡ አንዴ ጅማ ዩኒቨርስቲ በነበርኩበት ጊዜ አንድ ሰውዬ አህያውን በሆነ በር ሊያስገባው እየሞከረ አህያው አልቻለም በሀይለኛው መታው ሊያልፍ አልቻለም በድጋሚ ሌላ ዱላ አሳረፈበት አሁንም ሊያልፍ አልቻለም ሰውየው ዝቅ ብሎ ሲያይ ለኬ አንድ ብረት ነው አግዶ የያዘው ከዛ በኀላ ስለአህያ አብዝቼ ማሰብ ጀመርኩ አያሳዝንም?? አለኘ፡፡ ስለመፅሐፉም ብዙ ተባባልን፡፡
ቀላል ያሳዝናል አልኩትና በውስጤ የሀገራችንን አህዮች ስቃይ ሽው አለብኘ ከጥንት እስከ አሁን ፡፡
የምኞት ማደሪያ እያደር ሲለጠጥ ግድግዳና ጣሪያው ለበር የታሰበው ሽንቁር ሆነ ቀረ....ምትል የበውቄን ግጥም አለልኘ ስንኙን ተሳስቼ ይሆናል አለኘ ኡነት ገብቶት ነው የፃፈው ብዬ ሁሌ አስባለሁ፡፡ ከሆነ HE IS GREAT አለኘ፡፡
አያ ሙሌን ሳያውቀው በሱ ታሪክ ለመክበር የሚፈልጉ ሰዎች አሉ እንደጅብራ እላዩ ላይ ለመጣበቅ የሚፈልጉ አያ ሙሌን እወደዋለሀው ይሉኃል መከራውን ችግሩን ሳያውቅ ደቡብ ላይ አንድ ፍሬ አለ በጣም ይጣፍጣል ያን ለማግኘት ግን መተህ መስበር አለብህ ውስጡ ያለውን ጣፋጭ ነገር ምታገኘው ስለዚህ ስለ አያሙሌ በደንብ ልናውቅ ይገባናል መጎርጎር አለበት አለኘ፡፡....ግን ለወደቀ ልጁ አንድ ነገር ማድረግ አልቻለም😡(ስለአያሙሌ ህይወት በሰፊው እመለስበታለሁ)
የሀገራችን አስተሳሰብ ተበላሽቷል ሁሉም ነገር ተዛብቷል
እኛ ሀገር አምልኮ በዝቶል የሀይማኖት ሳይሆን የሰው አምልኮ ሔዶ የሆነ ሰው እግር ላይ አዳኜ ፈጣሪዬ ታዳጊዬ መውደቅ አንተ የፈጠረህ አምላክ አለህ የብርሃን አምላክ ስለዚህ ለምን ሰውን ትለምናለህ እሱጋር የጎደለ ነገር አለ አንተ ማሳየት ምትችለው አላስተዋልነውም እንጂ፡፡ ሰብአዊ ግንኙነት የተዛባው ለዛ ነው ይሔ የገዢና ተገዢ አካሔድ....
ፂምህን አሳድገህ ስካርፕ ማድረግ ፋሽን ነው ፓሽን?? ወይስ ሌሎቹ ስላደረጉት?? በወጉ የማይንቅ በወጉ አያከብርም ይላል በዕውቀቱ የሆነ ቦታ ላይ፡፡
በኡነት ነው ምልህ እዛ ፀሀዩ ላይ ሔጄ እንዲ ጠብታ እስክሆን ድረስ ብቀልጥ ደስ ይለኛል ግን አይሆንም ኬሚካል ሪአክሽን አይሰራም🤦♂🤷♂
አለኘ ከጃንቦ ብርጭቆው ላይ ላይ ጠብታ እያፈሰሰ ተስፋ ቆርጬ ምናምን አይደለም ሀገራችን ወደማይሆን ደረጃ እየሔደች ነው፡፡
ስብሃት ስለአማርኛ ቆንጅዬ ንግግር ተናግሯል እንደ አማርኛ ሀሳብን ለመግለፅ የሚሆን የለም ይላል፡፡
ወደፊት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ይህን ፖለቲከኛ ይተቹታል አለኘ
አው የሆነ መፅሐፋቸው ላይ ይህ ትውልድ የስልጣን ጥመኛ ነው ይሉታል አልኩት፡፡
በትክክል አለኘ
መፍትሔው ምንድነው ትላለህ አልኩት እንደራስህ ምታስቀምጠው
ስህተት ይፈልጋል የሰው ልጅ እንደእሳት
እስኪሰራ ድረስ ደግሞ እስኪሳሳት፡፡
የምትል የሆነ ሰው ግጥም አለልኘ የበውቄም ሊሆን ይችላል አላቅም🤷♂
ከሰራ በኀላ መሳሳቱን ያምንልሃል ካልሰራ ግን መቼምምምምም አያምንልህም ስለዚህ መስራት አለብን መሞከር መጣር አለብን ያ ወደ ምንፈልገው ቦታ ያደርሰናልና፡፡
አዲስ ነገር በሀይማኖታችን በባህላችን እንዴት አስማምተን ነው መጠቀም ያለብን የሚለው ላይ ትልቅ ስራ ሊሰራ ይገባል፡፡
ምን እየሰራህ ነው ግጥም እፅፋለሁ የተለያዩ ሀሳቦችን እየፈጠርኩ ሰዎችን አማክራለሁ ለሚሰሩት ነገር በዛ ጥሩ ገቢ አገኘበታለሁ ለምሳሌ ፒያሳ ሰራተኛ ሰፈር ጋር አዲስ የሚሰራ ቤት አለ ለዛ ስም ማወጣው እኔ ነኘ አሁን አልነግርህም ሲከፈት ሔደህ እየው አለኘ፡፡
እሺ በደስታ አልኩት
እንዳነበው ምጠቁመኘ መፅሐፍ??
ሁሉንም መፅሀፍ ግን ይኸ ትውልድ የብላታ ወልደጊዮርጊስ ስነምግባር ሚለውን መፅሐፍ ቢያነብ በጣም ተጠቃሚ ይሆናል ብዬ አስባለሁ አለኘ፡፡
መፅሐፉ እንዳጋጣሚ አንድሽ ስጦታ ተሰጥቶት በትንሹ የማንበብ አጋጣሚ ነበረኘየተወሰነ በፎቶም ያስቀረሁት ነበር አሳየሁት ሸጋ ነው አንብበው ብዙ ነገር ታተርፍበታለህ አለኘ እሺታዬን ገለፅኩኘ፡፡
ሰርገኞቹ መጡ እዚህ ነህ ስለው አዎ አለኘ መጣሁ ብዬው ወደሰርጉ ሔድኩ አጃቢ ነና ሞቅ ለማድረግ...🕺🕺🕺
ግን አሳዛኙ ነገር ግን ስመለስ ላገኘሁ አልቻልኩም የለም😢😢😔😳በራሴ በጣም ተናደድኩ ስልክ እንኳን ሳልቀበለሁ በጣም በሸኩኘ ግን ተመልሼ መጥቼ እንደማገኘሁ ለራሴ ቃል ገብቼ Final ፈተና ነበረብኘና ወደዛ ሔድኹኘ፡፡
"ተማሪ ካለ አስተማሪማ የትም አለ"
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
መልካም ምሽት ሀሳቡ የተቆራረጠ የሆነው እንደሰውየው አካሔድ እንደሆነ ልብ ይባልልኘ፡፡
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

እስኪ ደግሞ አንድ ምርጥ የሃገራችንን ፊልም ልጋብዛችሁ
ይህን ፊልም ያየሁት እንደወጣ ነበር 2006 ዓ.ም
ሁለት የትምሮ ጓደኞቻችን የሆነ ስራ ሰርተው ብር አገኙና ካልጋበዝናቹ አሉን ትምርት ባልነበረን ሰዓት ተቀጣጥረን ሰብሰብ ብለን ተገናኘን አቤት እንዴት ደስ ሚል ጊዜ እንዳሳለፍን ብታቁ፡፡
ግን ውስጥ ስንገባ ፊልሙ ሁላችንንም ቀየረን መሰጠን ጆሮ እና አይናችን ለሰከንድ ዞር ሳይሉ ተከታተልነው፡፡ ሲያልቅ ግን ሁላችንም በሀሳብ ፍጭት ጀመርን እንዲህ መሆን አልነበረበትም ነበረበት ምን ይፈጠር ታዲያ ያምሃል ወይ....ብቻ መንገዱን በክርክር እንደጨረስነው ትዝ ይለኛል በፊልሙ ከተበሳጩትም አንዱ ነበርኩ፡፡
😔የዛሬ ስድስት አመት በትዝታ ተጓዝኩ🤦♂
አንተ አንቺ እኛ ሁላችንም በሱ በሷ ቦታ ብንሆን ምን እናደርግ ነበር ጓደኛችን ብትሆን ቢሆንስ ምናመጣው መፍትሔ ምን ነበር??
አሁንም ድረስ እራሴን ደጋግሜ እጠይቀዋለሁ፡፡ ትላንት ማታ ደግሜ አየሁት የፊልም እይታዬ በእርግጥ ተቀይሯል፡፡ በሱ ሌቭል ለምን ሌላ ፊልም እንዳልተሰራም ግራ ገባኘ ሁሉም ነገሩ አንደኛ ነው ተዋንያን መረጣ ቦታመረጣ ድርሰቱ ዳይሬክቲንጉ ካሜራ እና ሲኒማቶግራፊው ድምፅ ማጀቢያ ሙዚቃ ግጥሞቹ ዜማዎቹ ቅንብሩ ሁሉም ነገሩ አንደኛ ነው ወድጄዋለሁ አምኜም ተቀብያለሁ ድሮ የዛኔ መናደዴ ቆይቶም ቢሆን መሳሳቴ ገብቶኛል ታሪኩ ልክ ነበርና፡፡
መጥፎ ነገሮች እንዳይፈጠሩ ጥረት ማድረግ አለብን ከተፈጠሩ ደግሞ ቶሎ ማስተካከል መቻል አለብን በማንም ችግር ከመፍረድም መቆጠብ አለብን፡፡ብልጥ ከሞኘ ይማራል አይደል ብሒሉ ከተሳሳቱ ሰዎች ብዙ ነገር መማር አለብን፡፡ መጥፎ ነገሮች በህይወታችን ከተፈጠሩ የኛ ህይወት ብቻ አይበላሽም የሁሉም ሰው እንጂ ተፈጥሮንም ህብር ጭምር......የሚሉ አያሌ ምክሮች ያሉበት ፊልም ነው እስኪ ወደ2006 ዓ.ም እንመለስ
የፊልሙን ርዕስና
ከፊልሙ የቀነጫጨብኳቸውን የተለያዩ ምርጥ ያልኳቸውን ሀሳቦችን አካትቼ እመለሳለሁ😍🙏
ቆዩልኘ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ

NATURE OF BEHAVIORAL ምን ይላል?
HUMANITY PERSPECTIVE ምን ይላል?
(በትንሹ ጎግል እናድርግ)
ወንድ አያስፈልገኘም ብቻዬኝ ተመችቶኛል ምናምን አትበይ ይህ እኮ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፡፡
ኡነት ብቻዬን ነው ምኖረው ብለሽ ነው ምታስቢው??
ሁሉም ሰው ብቻውን ነው፡፡
እናወራለን ሥንት ነገር እንባባላለን አንተ ግን እዛው ነህ፡፡
የባንዲራ እስራስ እዚህ አለ ተብዬ ነበር፡፡
እርሳስ....የኔ እመቤት እስራስ ሳይሆን እርሳስ ነው ሚባለው፡፡
ማስተዋል ካልቻልክ ስራህን መጉዳት ከጀመርክ ጥሩ አይሆንም፡፡
ጨካኘ ናት በጣም....ለነገሩ ትሻላለች የሚጥሉ አሉ አይደል፡፡
የኔ ታሪክ እነንደዛ ነው ተጥዬ ነው የተገኘሁት፡፡
ዛሬ ከመለያየታችን በፊት ታይኛለሽ አይደል
ቀና በይ እስኪ ደስ አልልም
ስለማታይኘ እኮ ነው፡፡
ቆይ ማነው አንተን የልብ ልብ የሰጠህ ማንም አይደፍረኘም እኮ
ያን ያህል አታስፈሪም እኮ፡፡
ማጨስህ ልክ ነው??....ካንተ አይጠበቅም
ምንድነው ከኔ ሚጠበቀው፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ....ስቀልድ አልነበረም ግን
ደባሪ ነህ አልሽኘ
ስርዓት አለህ ነው ያልኩት፡፡
ቆንጆ መኪና አለህ😍
THANK YOU🙏
አማርኛ የሚያኮራ ቋንቋ ነው፡፡ THANK YOU ላልከው የማይተናነስ አቻው አመሰግናለሁ አለው እና እባክህ ቋንቋህን አክብር አንዳች የሚያንሰው ነገር የለውም፡፡
አንዳንዴ ፈፅሞ አላረገውም ምትለውን ነገር ስታደርገው እራስህን ታገኛለህ....የሚያስገድዳቸው ነገር ይኖራል፡፡
320 ብር
ቆይ እኔ ልክፈል
አይ ቆይ.....
ሁለተኛ እንደዚህ እንዳታደርግ
ምንም ማለት አይደለም
ምንም ማለት አይደለም አትበል ገንዘብ ካለበት ቤት እንደመጣህ አውቃለሁ ብዙ ነገር ልትገዛልኘ ትችላለህ ግን አልፈልግም...ጓደኛሞች እስከሆንን ድረስ ደግሞ ማሎደውን፡ነገር ማወቅ አለብህ፡፡
በገነት መኖር ግነን ታምናለህ?? ከሞት በኀላስ ህይወት ያለ ይመስልኻል?
ይመስለኛል በዚህ ብቻማ አያበቃም በገሃነም መኖር ግን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ እንደ አዉ ይመስለኛል፡፡
አዉ ምነንድነው?? በልጅነትሽ አዉ ይበላሻልእንደዚ ካላረግሽ ምናምን....
እንዴ የሀብታም ልጅ አዉ ያውቃል እንዴ??😊
የሃብታም ልጅ ኢትዮጵያዊ አይደለም እነንዴ??🤔
እንደዛ ይመስለኛል በዘላለም እሳት መቃጠልን ፈርተን ጥሩ ልጆች እንድንሆን ብለው ይመስለኛል፡፡ ጥሩ በመሆን የሚገኘ ጥበብ እንዳያመልጠን አይመስልሽም??
ጥሩ በማድረግ ግን እንግባባለን
የራሷ ጥፋት ነው ሲበቃት ተወችኘ፡፡
የመጨረሻዬ ነው....ውሸቴን መስሎሽ ነው??
እንዲህ ቀላል ነው እንዴ ማቆም
ለኔ ነው፡፡ የማቆምበት ምክንያት ነበር ያጣሁት አሁን ግን አለኘ፡፡
ስም እንስጠው እስኪ ግንኙነታችንን
ችላ ተባብለን እንዳንተላለፍ
እኔ እና አንተ ልክ ነን፡፡
አምንሻለሁ ለማመን ገና ነኘ ግን አንቺን አምኜሻለሁ መጎዳት ግን አልፈልግም አንቺንም መጉዳት አልፈልግም የሰው ልብ በሰው ይሰበራል ባመነው በወደድነው ሰው ይሰበራል፡፡
የራሴ ህይወት የራሴ ሀላፊነት ነው፡፡
እስከመቼ ነው እንደማቶጂኘ ምታስመስይው
አሎድህም አላልኩም
ታዲያ የሚያስጨንቅሽን ለምንድነው ማትነግሪኘ
ይጎዳኻል...
ስለዚህ ደብቀሽኘ ትኖሪያለሽ??
ይሔን ዘፈን ወድጄዋለሁ
.......እኔ ማውቀው እኔ ማውቀው
ፍቅር እንዳስተማርኩሽ ነው፡፡
እኔ ማውቀው እኔ ማውቀው
መውደድ እንዳለመድኩሽ ነው፡፡
ቀና ብሎ ለመሔድ የወንዶችን አድናቆት የማትፈልግ በራሷ ምቶስን ጠንቃቃ ሴት ብዬ ነበር የመረጥኩሽ፡፡
አንተ አይደለህ እንዴ አብረኻት ካልሆንክ ብለህ ስተትጨቀጭቀኘ የነበረው.....
ግን ተጣድፈህ አግባት አላልኩህም
ምነድነው ያጣላችሁ ለምንድነው ማትነግሪኘ
የኔ እና የሱ ሚስጥር ነው
የእኔ እና የአንተ ሚስጥር አለ አይደል እንደዛ ማለት ነው፡፡
ልገልሽ ነበር 😔😊😍
መጨረሻ ላይ ያለውን ዘፈን ልብ ብላችሁ አድምጡልኘ ....መሳጭና ገራሚ ነው፡፡
የፊልሙ ርዕስ:- ቀሚስ የለበስኩለት
ደራሲ፡- ዘሪቱ ከበደ
ዳይሬክተር፡- ሔኖክ አየለ
ተዋንያን፡- ተዘራ ለማ ፣ ዘሪቱ ከበደ ፣ ቃልኪዳን፡ታደሰ ፣ እድልወርቅ ጣሰው ፣ዲበኩሉ ታፈሰ ፣ ሔኖክ መሃሪ ፣ ሙሉ ሰለሞን ፣ የዝና ወርቁ ፣ ውቢት ያረጋል.....እና ሌሎችም በብቃት ተጫውተውታል
ለአስተያየታችሁ @jahABP

ማንም ስልክ ላይ ባይደውልል
አንድ ስልክ ግን እንዲደወልልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡
ማን ለሚለው ተመልሼ እመጣለሁ🏃♂🏃♂🏃♂😀
አንድ ስልክ ግን እንዲደወልልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡
ማን ለሚለው ተመልሼ እመጣለሁ🏃♂🏃♂🏃♂😀
በጎ ነገር ማድረግን የመሰለ ምን ነገር አለ ሰውንም አንተ ባደረከው መልካም ነገር ሰው ሲድን ማየት ደግሞ ደስታህን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡
ምን መሰለህ ወዳጄ ማንም አስታዋሽ ባይኖርህ ደም መለገስ ጀምርማ፡፡
ደምህን ከለገስክ ልክ ሶስት ወር ሲሞላህ የሚገርመ ሰላም ያለው ድምፅ ወዳጃችን እንዴት ነህ ሁሉ ሰላም ነው የዛሬ ሦስት ወር ደምህን ለወገኖችህ ለግሰህ ነበር ጤኔኘነት የሚሰማህና ብቁ ነኘ ብለህ ካሰብክ ዛሬ ሶስት ወር ስለሞላህ ለመስጠት የምትችል መሆኑን ልንገልፅልህ እኖዳለን ይሉኻል፡፡ አቤት ትህትና🙏😍
አየህ አንተ ባታስበውም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ ያንተ መኖር የሚያኖራቸው አያሌ ሰዎች አሉ፡፡ ምንም የለኘም ምንም መስጠት አልችልም አትበል ያለህን ካሰብከው ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡
በዚ አስፈሪ ጊዜ ደግሞ የደም እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል አቅማችን የሚፈቅድ ሰዎች ሔደን የዚህ መልካም እና ቅዱስ ሐሳብ ተካፋይ እንሁን እላለሁ፡፡
ይኽን ክፉ ጊዜ በፍቅር በመተሳሰብ በጋራ ተባብረን እንለፈው፡፡😍🙏😍
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
መልካም ምሽት

ባለፈው ነው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ ሰፈር ንፋስ እየተቀበልን እየተጫወትን እየተሳሳቅን ነበር በመሐል እኔ አመሌ ተነሳና ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ፡፡
እነሱ ደቂቃ ይይዛሉ ወይኔ አመለጠህ አሁንስ አገኘኸው እስኪ አሳየን አሁን አመለጠህ ለጥቂት ይሉኛል፡፡
324 ፎቶዎችን አነሳሁ አንድም የተሳካ ፎቶ ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ ሁላችንም በጣም ብናዝንም እየተሳሳቅን ወደቤት ተመለስን፡፡
ማርያምን እላችኋለሁ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር የሆነ ቀን ሚገርም ፎቶ ከሰማዩ ላይ እንደማስቀር አውቅ ነበር፡፡
እና ዛሬ ማታ ምን ሆነላችሁ ወደ ሰማይ አንጋጥቼ 180 ፎቶዎችን አነሳሁ አንገቴን እስኪያመኝ ድረስ... የእውነት ግን አሞኛል..... ከዛማ ፎቶዎቹን ስታዩ እራሳችሁ ትፈርዳላችሁ....ሚገርመው አስተያየት እንዲሰጡኝ ጓደኞቼ ጋር ልኬላቸዋለሁ ሸጋ የሆነ አስተያየታቸውን ለገሱኝ፣ አበረታቱኝም ፎቶዎቹን ካዩት ሰዎች መካከል አንዲት ወዳጄ😍🙏የምወዳት😘 ከመቼው እንደጻፈችው ባላውቅም ገራሚ ግጥም ጻፈችለት በጣም ደስ ሚል ግጥም ነገ ከፎቶው ጋር ይለቀቃል፡፡
እባክህ ወዳጄ ሞክር ሞክር ሙከራዎች ወደ ትክክለኛው ቦታ ያደርሱሀል፡፡
ሩጫችን ከትላንት የተሻለ መሆን አለበት ከትላንት የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጥን!!!
@jahABP ነኝ ማንኛውንም አስተያየታችሁን አድርሱኝ

⚡️🔥ተቃጠለ🔥⚡️
ተቃጠለ ቢሉኝ ጎጆየን ነው ብዬ፣
ተቃጠለ ቢሉኝ ታዛየን ነው ብዬ፣
ለካስ ሰማይ ኖሯል ኧረ እናንተ ሆዬ!
እሱማ እሳት ነው የእሳተ መለኮት የጌታ መኖሪያ፣
በውሃና ነፋስ የተጠቀለለ የእግዜር የጥበቡ ትንሹ ማሳያ።
ከላይ ያለው እሳት ዝቅ ብሎ ከሆን ኋጥያቴ ሲበዛ፣
ነነዌ እንደሆነው ዮናሴ ሰብኮኝ እኔም ልብ ብገዛ፣
ፊቱን ይመልሳል ፈጣሪ ደግ ነው ምህረቱ የበዛ።
የተ.አ.ኢ (አል አይን)
24/09/ 2012 ዓ.ም
ከምሽቱ 2:25
ትዝታ © °°°°°
አብያችን ያነሳውን ፎቶ ካየሁ በኋላ የተጻፈ...
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
⚡️🔥ተቃጠለ🔥⚡️
ተቃጠለ ቢሉኝ ጎጆየን ነው ብዬ፣
ተቃጠለ ቢሉኝ ታዛየን ነው ብዬ፣
ለካስ ሰማይ ኖሯል ኧረ እናንተ ሆዬ!
እሱማ እሳት ነው የእሳተ መለኮት የጌታ መኖሪያ፣
በውሃና ነፋስ የተጠቀለለ የእግዜር የጥበቡ ትንሹ ማሳያ።
ከላይ ያለው እሳት ዝቅ ብሎ ከሆን ኋጥያቴ ሲበዛ፣
ነነዌ እንደሆነው ዮናሴ ሰብኮኝ እኔም ልብ ብገዛ፣
ፊቱን ይመልሳል ፈጣሪ ደግ ነው ምህረቱ የበዛ።
የተ.አ.ኢ (አል አይን)
24/09/ 2012 ዓ.ም
ከምሽቱ 2:25
ትዝታ © °°°°°
አብያችን ያነሳውን ፎቶ ካየሁ በኋላ የተጻፈ...
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
አስታውሳለሁ ምኒልክ 12 ክፍል እያለን ከትምህርት ቤታችን ዝቅ ብሎ በቢኒያም ፎቶ ቤት ወደቀኘ ታጥፎ ባለች ባለች የራሳችን በምትመስል ትንሽዬ ምግቤት እርጥብ ልንበላ ተቀምጠን ሳለ.......አንድ ጓደኛዬ አንዴ አብያ ብሎ ጮኸ ምንድነው አልነው ሁላችንም አንድ ላይ....የገጣሚ ስም ጠራ አትቀልድ አልኩት በኡነት እሱ ነው፡፡ ሔደ ብሎ እየሮጠ ወጣ........ተከተልኩት ኡነትም እሱ ነው የገጣሚ ወግ የሆነችውን ስካርፑን ጣል አድርጎ ገና ከእንቅልፉ መነሳቱ ነው መሰል አይኖቹ ትንንሽ ሆነዋል ፊቱን የወረረው ፂሙ ላይ የውሃ ጠብታዎች ይታያሉ በኢንቬሎፕ የታሸገ ዶክመንት ይዟል ሰላምታ ተለዋውጠን አድናቆታችንን ገልፀን ማስታወሻ ፎቶ ተነሳን ደስ ብሎን ነበር፡፡
አሁን ላይ ግን እናደዳለሁ ለምን ታክሲ ድረስ አብሬው አልሔድኩም ለምን ትንሽ እንኳን አላወራሁትም በጣም እበሽቃለሁ🤦♂🤦♂፡፡
ይህን እንዳነሳላችሁ ያስገደደኘ የዚህን ገጣሚ አጫጭር ልቦለዶች ትንሹ ወንድሜ እያነበበ አየሁት ሲያስቀምጠው አነሳሁና ርዕሱን አየሁ ፈገግ አስባለኘ ከጀርባ የደራሲው ቀደምት ስራዎች ተፅፈዋል ማውጫውን ስመለከት አይኔ አንድ ርዕስ ላይ አረፈ አስገረመኘ፡፡
የጋሽ ስብሃት አባባል ፊቴ ድቅን አለ
" አንዳንዴ የምታስበውን ነገር የሆነ ቦታ ተፅፎ ታገኘዋለህ የምትለዋን"፡፡
ገለጥኩና ማንበብ ጀመርኩ ተደነኩ የኔ ያንተ ያንቺ የኛ የሁላችንም ሃሳብ ይጋራል ብዬ አሰብኩና ስለወደድኩት ይኸው ላካፍላቹ ወደድኩ፡፡
ነገ ጠብቁኘ
ለማንኛውም አስተያየታችሁ @jahABP

ሃሳብ ... ማሰብ ... አሳቢነት
ወድቋል ማለት ይቀላል፡፡ አልጋው ላይ የተጣለ እንጂ የተኛ አይመስልም፡፡ ጥልቅ መጥፋት ውስጥ ነበር፡፡ ሕልምም ቅዠትም አላየም፡፡ ተኘቶ ብቻ ነው የተነሳው (ይቅርታ ተኘቶ ነው የነቃው)፡፡ አልጋው ላይ ወድቆ ነበር የተነሳው፡፡
ዓይኖቹን ገለጠ በስተግራ በኩል ካለችው ትንሽ ጠረቤዛ ላይ ከኮንዶም አጠገብ የተቀመጠ አንድ የሮዝማን ሲጋራ አንስቶ ለኮሰ፡፡ አሰበ፡፡ ማሰብ ማፍጠት ከሆነ እያሰበ ነው፡፡ (እዚህ ላይ አሰበ ያልኩት እኔ ነኘ ወይ እርሱ እያሰብኩ ነው አለ) መልካም አለም አላለም...እያሰበ ነው፡፡ :...እኔም ካልኩኘ እያሰብኩት ነው፡፡
በሌላ ሁኔታ ውስጥ በማናሰላሰስላት ነጥብ ላይ መብሰልሰል ማሰብከሆነ (በትላንቱ ሁኔታ ውስጥ መፀፀት ወይ መደነቅ) ማሰብ ከሆነ አድፍጧል ማፍጠጥ ማሰብ ተደርጎ ስለሚወሰደድ፡፡ ምናልባት ማሰብ ከመፃኢ ጊዜ ጋር ቂርኘነት ሊኖራት ይችላል፡፡ ወደኀላ ማሰብ ግን ስላልታሰበበት የማሰብ ያህል ነው፡፡ ማስታወስ የተሆነውን ወደኀላ የመተርተር ውጤት እንጂ በራሱ የአሁንታነት ሁኔታ አይመስለኘም፡፡
ሲጋራውን በረጅሙ ሳበ፡፡ በረጂሙ ተነፈሰ፡፡ ጢሱ ተበተነ ...የጢሱ ሽታ ትላንት ያሳለፈውን ሁኔታ መሰለው ትላንትን እያስታወሰ (እያሰበ) ሌላ ሃሳብ ታሰበው ...ከአንዱ ወደሌላው ሲሸጋገር የሚያውቀው ነገር አልነበረውም፡፡ (ካላወቀው እንዴት እያሰበ ነው፡፡) ማለት እንችላለን... ቢሆንም እያሰበ ነው...
....
ለመተኛት ማንቀላፋት ያስፈልጋል፡፡ ካንቀላፉ መውደቅ አለ፡፡ መውደቅ!!! ከወደቁ በኀላ የሞት ልምምድ( በእንቅልፍ) አለ፡፡ እንግዲህ በእንቅልፍ መሃል ነው ሕልም የሚታለመው... ሕልም ከሌለህ ቅዠት ፣ ከምንም ግን የሚሆነው ምንም ነው፡፡ ተኘቶ መንቃት ወድቆ መነሳት ብቻ፡፡ ያለህልም ያለ ቅዠት... ከወደቀበት ተነሳ፡፡ ወጣ
የሆቴሉን ደረጃ እየቆረጠ ወረደ፡፡ ሰባት ደረጃ ሥምንተኛው ወለል፡፡ ሰባት ነው አለ፡፡ ለራሱ ስምንተኛውንማ አልቆጥርም ብሎ በልቡ አሰበ፡፡ ሰባትን ስለሚወድ የእድል ቁጥሬ ሰባት ነው ይላል... ሥላሴ በሰባት ናቸው፡፡ ሰው የሰባት ነገሮች ውጤት ነው... የስጋው ክፍል አራት፡፡ ስጋ ጎዶሎ የሚሆነው ደካማ የሆነው ሙሉ ስለሆነ ነው፡፡ ነፍስ የሶስት ባህሪያት ውጤት ናት የማሰብ የመናገር የሕያውነት ÷ እኔ ከነፍስ ወገን ስለሆንኩ በሰባት አምናለሁ አለ... ሰባት ራሱ በራሱ ለራሱ የታመነለት ቁጥር ነው፡፡ ሲወጣ በልቡ እንዲህ ተናገረ....
"ወለሉን ሳይቆጥረው ደረጃው ሰባት ነው" ሲል፡፡
ከተማይቱ በብዙ የተጨነቁ መንፈሶች የተሞላች ናት፡፡ በከተማይቱ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ከህይወትና ከፊደል የተማሩ አዛውንቶች ሳይቀሩ... ሕይወታቸው በእንባና በሀዘን ማህበረሰብንም በማማረር የተሞላ ነው፡፡ ለከተማይቱ ነዋሪዎች ሕላዊ በጣራና በግድግዳ ላይ የተመሰረተ ሆኗል ከዚህ ከፍ እንዳይሉ ግራና ቀኙን አይተው እንዳያስተውሉ እንዳይጠነቀቁ የከተማዋ ድምፅ አልባ ሕግ አይፈቅድም፡፡
በዚህ ትንሽ እድሜ ጠገብ ከተማ ውስጥ ሕይወት በንድፍነት ደረጃ የተቀመጠ ሲሆን ቀለም አልተቀባም፡፡ የትኛውም ነዋሪ የሚጓዙበት ያለበትን አያውቀውም ÷ እዚች ድሃ ነገር ግን ውብ ከተማ ውስጥ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች በድንገተኘነት ላይ የተመሰረቱ ናቸውና የዚህ፡ከተማ የሕግ መፅሐፍ "ድንገትና ምናልባት" የሚል ነው፡፡
አየ፡፡
ሰማዩን ምድሩን የፊቱን የኀላውን ሁሉንም አየ ዓለም እንደከዚህ በፊቱ ናት፡፡ ወያላዎች የጠራሉ ፣ ሴቶች አጊጠዋል ፣ ካፌዎች ቡና መቁላት ጀምረዋል፡፡ እርሱም እንደትላንትጠዋቱ መጀመሪያውን ቡና ለመጠታት ካፍቴሪ ሊቀመጥ ነው...ዛሬ ጠዋት ደግሞ የትላንትናው ምሽት ይወራል ስለድራፍት ፣ ስለቢራ ፣ ስለውስኪ ፣ ስለፐብ ፣ ስለክለብ ፣ መጨረሻ መሐል መጀመሪያ ደግሞ ሴት ስለሴት ስለሴት የአንድ ቀለም ወግ፡፡ ተራ ወሬ ህይወት አልባ ድምፅ...ለነገሩ ምርጥ ሃሳብ ራሱ ወረቀት ላይ ካልሰፈረ ተራ የዓይን ደመና ነው፡፡ ደመናው በቀለም ረጥቦ ወረቀት ሜዳ ላይ ከዘነበ ተራና መናኛው ወሬ ትንሽ ሃሳብ መሆን ይችላል፡፡ ከወሬ ከፍ ያለ፡፡
ዓለም አሁንም በዓይኑ ፊት እንደትላንቱ ናት፡፡
ጠየቀ፡፡....
ትላንት የሞቱ ምን አመለጣቸው? በዛሬው እና በትላንቱ እንቅስቃሴ መሃል ምን፡ለውጥ አለ?? የዛሬው ሰው ከትላንቱ በምን ከፍ ይላል? የአምናው ጣዕም ከዘንድሮ በሚሻልበት ዓለም የዛሬ ምርጥነት ምኑ ላይ ነው? እየቀነሰና እየወረደና እየተዋረደ በሚገኘበት ሁኔታ ውስጥ ከትላንት ወደ ዛሬ የመገኘት በረከትነት ምኑ ላይ ነው? በሕይወት ያሉት ከሞቱት ዝቅ ካሉ በሙታን ቀናቶች ላይ ሕያዋን ቀናቶኞች ላይ ሕያዋን ቀናተኞች ከሆኑ የዛሬ ዛሬነት ምኑ ላይ ነው?
እናንተ አምና... ካቻምና... የዛሬ ሃያ አመት የሞታችሁ ሆይ... ቀናቶቻችሁን መልሱልን ቀኖቻችን ከእናንተ ይልቅ ብርሃናማ አይደሉምና፡፡
የሚያየውን ሰው ሁሉ ተፀየፈ፡፡ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ቀለም የተቀባ ብራና መሰለው ያውም ከባድ ቀይ የተቀባ...
አስተናጋጇ መጣች፡፡
ቡና አላት እንደወረደ፡፡ ቡና ሲያዝ አፉ በምራቅ ልቡ እንዲህ በማይለው ሐሴት ይሞላል...
ቡና ሊጠጣ ነውና ደስተኛ ነው፡፡
ቅድም ስለማሰብ ያሰበው ትዝ አለው፡፡ ማሰብ ምንድን ነው? ሰው በማሰቡ ከእንስሳት ይለያል ሲባልስ እንዴት ነው?... የሰው ልጅ ምንን ስላሰበ ነው ከእንስሳት የሚነጠለው? ወይስ እያሰበ መሆኑን (ማሰብ መቻሉን ማወቁ) ነው? ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው፡፡ እንስሳት ወደ ማይሆን አቅጣጫ ሲጓዙ እረኛቸው እንደሚያግዳቸው ሁሉ ማሰብ እረኛችን ትሆን? እንዲህ ከሆነ የሰው ልጅ መች እረኛውን ሰማ? ከኔ ጀምሮ፡፡ አሁን እኔ ውስጥ እዚህ ካፍቴሪያ የተሰበሰቡ ሰዎች የሉምን? ምክንያቱም ስለራሱ ሙሉ የሆነ ስለእርሱም አይሳሳትም፡፡ Period
ውሸት???
ማሰብ ከእንስሳት የተለየንቀት ሳይሆን ከአራዊት ይልቅ አውሬነታችን የተገለጠበት ከትንኘም በታች ቅንጣት ያከልንበት ሁኔታ ነው፡፡ ማሰብ ነውራችንን አደባባይ ያሰጣብን ከእኔነታችን ያጣላን ከእንስሳት ዝቅ ያደረገን ነገር ነው፡፡ ቡናው እስኪቀርብ እነዚህን እያሰበ ነበር...
ቡና ቀረበለት፡፡
የመጀመሪያው ቡና፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስራውን በእጅጉ እንደያዘ ከደረሰበት ቀጠለ...
"ዘሎ ገደል የገባ እንስሳ የትኛው ነው? የሰው ልጅ ብቻ፡፡ መውደቅ አውቆ ማጥፋት አስቦ ማጥቃት አስቦ መጥፋት የሰው ልጅ ብቸኛ መለያ ነው... የማያስብ እንስሳ ጥፋት ኪሚያስብ የሰው ልጅ አጥፊነት አናሳ ከሆነ የሚያስብ የሰው ልጅ ጥፋት በማያስብ እንስሳ ካልተደረገ ከሁለቱ አናሳው ማን ነው? ያሰበውስ? የደመነ-ነፍስ እውቀት ከነፍሳዊ እውቀት ከተሻለ ሰው ክብሩን ለእንስሳ ሊለቅ ይገባዋል፡፡ በእርሱ የተደረገ ጥፋት በእርያዎች የለምና..."
ወደ ራሱ ተመለሰ የቡናውን ስኒ አነሳ...አልቋል ስኒው ውስጥ የዕድፍ መስመር አየ.....የአቧራ መንገድ የሚመስል ብዙ አቋራጭ መንገድ መሳይ ነገር ከንፈሩ በነካበት የስኒው የውስጠኛ ክፍል ደግሞ ሰፊ የአቧራ ሜዳ ወይም የሸርተቴ መጫወቻ መሳይ ነገር ይታያል...
ይቀጥላል🏃♂🏃♂🏃♂

ራሱን ወቀሰ "ወደማልኩበት እንዴት ተመለስኩ?"
ትላንት እርሜን ስጎርስ ለምን አላፈርኩኘም? ሐፍረቴን ለመግለፅ የማይራራልኘ "የሰው ልጅ ያስባል" የሚል ማፈሪያዬን እንዴት እመካበታሁ? አለማሰብ ባይቻልም ማሰብን መመኪያ ለማድረግ የሰው ልጅ እጅግ ብዙ
ይቀረዋል፡፡ ይቺህ ውብ አለም እናስባለን በሚሉ ደናቁርቶች ጠፍታለች፡፡ ረሃብ የሰው ልጆችን የተንኮል ቀመር ነው፡፡ ጦርነት የሰው ልጆች ያለማሰብ ውጤት ነው በሽታ በሰው ልጆች ተቦክቶ ይጋገራል... የዋሆች ይመገቡታል ፈጥነውም ይሞታሉ፡፡ ይህ የሰው ልጅ የማሰብ ውጤት ነው ግን፡፡ ይህ ዓይነት ጭካኔ በእንስሳት አልተደረገም፡፡ ስለዚህ ከሚያስበው፡የሰው ልጅ እንስሳቶች በለጡ፡፡ የተበለጠ ጎበዝ የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡ ያሸነፈ ተሸናፊ፡፡
ድጋሚ ካዘዘው ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ ፉት አለ ጥቁረቱ ደስ ይላል፡፡...
ቡና ባይኖር ዓለም ምን ትመስል ነበር? አለ በውስጡ
ራሱ ቡናን ትመስል ነበር፡፡
በቡና ጥቁረት ስር የሃሳባዊነት ብርሃን ተሸሽጓል፡፡
እዚህ ቤት ያለው የቡና ጣዕም የሚወደው አይነት የቡና ጣዕም ነው፡፡
ምላሱ ላይ ያለውን ቡና እያሰበ ቀና አለ የቤቱ መግቢያ ላይ በቢጫ ፕላስቲክ ላይ የተለጠፈውን ጥቅስ አየ... ስለቡና ይህንን ጥቅስ አየ... ስለቡና ይህንን ጥቅስ እልፍ ጊዜ አንብቦታል የሚካኤል ባልዛክ "When you drink a cup of coffee, ideas comes marching in your brain"
የመጨረሻውን የቡና ጨመቅ ወሰደ ቡናውን ምላሱ ላይ አሽከረከረ፡፡ አሁን አንተ ምን ታስባለህ? አለ ራሱን፡፡ የቡና ጣዕም ለመለየት ከማሰብ ብቻ በመልካም ወይም መጥፎ ጣዕም ሊታወቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አሁን ማሰብ በጣዕም ላይ የምትደረግ ትኩረት ናት እንጂ ሌላ ጨዋታ አይደለችም፡፡
ለምሳሌ...
ሰው ያስባል በማሰቡም ተዋርዷል እያልኩ እያሰብኩ ነው እንበል (አሁን) እንስሳው ደግሞ ስለ አለማሰቡ ምንም አያስብም አያውቅምም፡፡
እኔ ስላሰብኩ ምን ይፈጠር?...ይህ ምላሽ ትንሽ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን እኔ ስላሰብኩ ምን ይፈጠር?... የሚለው ምላሽ የጥያቄው ምላሽ ብቻ አይመስለኘም ከጥያቄው በኀላ የመጣ አንድ የሃሳብ መስመር ይመስለኛል፡፡ስለዚህ
"ሰው ያስባል ነገር ግን በማሰቡ ተዋርዷል"
እነንዲህ ከሆነ ደግሞ አልታሰቀም ማለት ነው(ራሱን)፡፡ ምክንያቱም ከዛ በኀላ የታሰቀው "እኔ ስላሰብኩኘ ምን ይፈጠር ስለሆነ፡፡"
ሁለት፡፡...
እንስሳው ስለ አላሰበ አይደለም ያላጠፋው፡፡
እንዳያስብ ሆኖ በሆነ (በተፈጠረ) ነገር ላይ እሻላለሁ ይሻላል ፣ እበልጣለሁ ይበልጣል ቅሎ መፃረር አለመሻል ይመስላል፡፡ ምክንያቱም አልሻልም አልችልም አይደለሁም ማለት የማይችል እንደሆነ ከሚኖር ነገር ጋር መሆንን ሲሻ ከማይሆን ከአለመሆን ጋር የሚስማማ የሰው ልጅ ሁኔታውን ከሚኖር እንስሳ ጋር በምን ይለያል? ምክንያቱም እንስሳው የማያጠፋው ስለማያስብ ሳይሆን ሁኔታውን ስለሆነ ነው፡፡ የሚያጠፋውም እንዲያ ስለሆነ ነው፡፡
ማሰብ የምክንያት አይደለም፡፡ መሆን ግን አብዛኛው ጊዜ የማሰብ ሳይሆን የመፈለግ ውጤት ናት...አስበን አንፈልግም የፈለግነውን፡እናስባለን እንጂ፡፡ እውነት ነው የቃላት ጨዋታ ሊመስል ይችላል ግን የምናወራው (የምፅፈው) (የምታነበው) ስለ ማሰብ የምትታሰብ የወረቀት ወሬ ናት፡፡ ቅድም እንዳወራነው ወደ ኀላ ልትተርትና የአፍ ደመና ዝናብ መሆን ባትችል እንኳ ካፍያ እናድርጋት ትንሽ ወሬ፡፡ በብራና ላይ ቅንጣት ብርሃን መሆን ስለምትችል የምናስበው በቃል ስለሆነ የቃል ጨዋታ ብሎ ነገር የለም፡፡ ቅድም ከተናገርኩት ጋር በመጠን የተቃረንኩት ይመስላል... ከዚያ ምልከታ በኀላ ይኼኛውን ከተቀበልኩስ የቃላት ወንዝ በሃሳብ እዚህ ካደረሰኘ የቃል ጨዋታ ያልሆነ ስለሌለ ሁሉም "ንድፍ" የቃል ውጤት ነው፡፡ መስመር እራሱ ሳይቀር...፡፡
ጠረቤዛ ላይ ባዶ ሲኒ... ሲኒው ሲዞር ዜሮ መሳይ የቡና ስኒ ማስቀመጫ ላይ ፣ የስኒ ማስቀመጫው ስኒውን ተሸክሞ ዜሮ ቅርፅ ጠረቤዛ ላይ ይታያል፡፡
አስተናጋጇ መጣች
ስኒውን ልታነሳ መስሎኘ ነበር፡፡ ነገር ግን ከአጠገቤ ካለው ጠረጴዛ ላይ ያሉትን ጥንዶች ለመታዘዝ ነበር፡፡ አመጣጧ ለካ የምትንጎራደደው ስራዋ ስለሆነ ነው፡፡ መንጎራደድ ከጠረጴዛ ጠረጴዛ እዚህ ቤት ብዙ ደስ የሚሉ ዜሮ ነገሮች ይበዛሉ...ይህንን ያልኩት የአስተናጋጇ ዳለሰ ስለሚያምር ነው ምርጥ ቅንፍ አላት ()
እዚህ ቤት ስገባ ይህንን ሃሳብ ራሱ ሳያሳስበኘ አይቀርም፡፡ እንደ ምርጥ ባለ ቅኔ ውብ ስንኞች፡፡ ሳይታሰቡ እንደሚፈሱ ግጥሞች፡፡ እንደ ባለተሰጦዖ ቀልደኛ ቀልዶች፡፡ ተፃፈ፡፡ በድንገት እኔ የዚች ፈገግታ የተለያት የተወዳጇ ኑሮ ወደጎን ያዘመማት ከተማ ነዋሪ ነኘ ከተማችን እንብርት ላይ የተፃፈው ሕግም ተገዢ ነኘ የከተማዋ ቁልፍ ሕግም " ድንገትና ምናልባት" የሚል ነው፡፡
ይህ ሕግ የሕዝቡ ሕይወትና ኑሮ አማክሎ የወጣ እነንደሆነ የከተማዋ "ጭቃ ሹሞች" ይናገራሉ...እንዲህ ሲሉ...
"የህዝቡ ሕይወት የሚመራው በምናልባት ነው...ድንገት ተነስቶ የሚኖር ህዝብ ስለሆነ በድንገት ለሚመራ ህዝብ የምናልባት ስርዓት ሊጨመርበት (ለት) ይገባል...ምናልባት ለሚሆነው ነገርም...የድንገት ህግ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ እኔም የዚህ ከተማ ሕግ ተገልጋይ ነኘና እዚህ ካፍቴሪያ ይህን ጽሁፍ ጻፍኩት ድንገት፡፡
መፍሰስ መልካም ነው፡፡ ወደ ሃሳብ ወንዞች ወደ ፍላጎተት ውቅያኖስ የመሆንን ተራራ ባያቅፉትም እየዳሰሱ፡፡ በእውነት ሸለቆ ባይኖሩም እየተሽለኮሎኩ፡፡ ወንዙ ወደሚያደርሰን እየታጠፍንም ቁልቁል እየተወረወርንም በፀጥተኛው ሜዳ ላይ እንደማይጓዝ ለጥ ብለን እነንደ አሸዋ በልባችን እየተሳብን አንዳንዴም በአሸዋማ ሜዳዎች ላይ ውለታ ቢስ ለመሆን ቁልቁል እያደረግን መፍሰስ እስከመዳረሻችን...ለመተኛት መውደቅ ለመውደቅ ማንቀላፋት... ለሕልም ...ለቅዠት ምንምንም ላለማየት ተኘቶ ለመነቃት፡፡ ወድቆ ለመነሳት መውደቅ... መውደቅ...መውደቅ...
ቅድም ሆቴሉ ውስጥ ወድቆ ሲነሳ... አንቀላፍቶ ሲነቃ ያሰበውን አሁንም አሰበ፡፡ አንዳንድ ሃሳቦች እነንዲህ ናቸው...አይለቁም...ይኖራሉ...ብቅ...ይላሉ...
ድንገት
የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ከኤፍሬም ስዩም
ህዳር 2007ዓ.ም
ቤታችን እንሁን እናስብ🤔🤔👊

አባትክ/አባትሽ መክሮሽ ያውቃል??
😂😂ፈገግ ያስብላል አይደል😂👊
እስኪ እንደዚህ ብሎ መክሮኻል/መክሮሻል
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂😜😜
በዚህ ፅሁፍ ተገርሜበታለሁ......
ብዙ ታተርፉበታላችሁ
@jahABP ነኘ
😂😂ፈገግ ያስብላል አይደል😂👊
እስኪ እንደዚህ ብሎ መክሮኻል/መክሮሻል
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂😜😜
በዚህ ፅሁፍ ተገርሜበታለሁ......
ብዙ ታተርፉበታላችሁ
@jahABP ነኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
አንፃር
አባቴ ነው፡፡...
.....ቀና ብለህ ከግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ፎቶዬን ተመልከት አለኘ፡፡ አባቴ ከእናቴ ጋር ሲጋቡ የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ የአባቴ ፀጉር ከብዛቱ ርዝመቱ ጉድ ያሰኛል፡፡ የገረጣ ጠይም ፊት ነው፡፡ መካከለኛ ቁመና ፣ ሥጋ ያልበዛበት አካል ይታያል፡፡ አባቴ ከሰላሳ አመት በፊት የተነሳው ፎቶ፡፡ ፎቶው ላይ ያለው ምስል የአባቴን ዘመን የአለባበስ ስርዓት ያሳያል ፣ ቬል የረዘመ ሱሪ ፣ ኮሌታው የሰፋ ኮት በነጭ ስፖርት ሸሚዝ ይታያል፡፡ አባቴ በእኔ እድሜ እያለ የተነሳው ፎቶ..
"አየህ አይደል? እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ንፋሱን እጨብጥ ባህሩር እጨልጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ንፋሱም ከእጄ የለም ፣ ባህሩም ሆዴን አልሞላም፡፡ ከንቱ የወጣትነት ምኞት ነበርና፡፡
እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ከአባቴ ምክር ይልቅ የራሴን ስሜት የማዳምጥበት ወቅት ነበር፡፡ ከአያትህ መሬትነት ይልቅ የኔን እሳትነት እመካበት ነበር፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ እያለሁ"
አለኘ አባቴ፡፡
ፀጉሬን እየፈተልኩ አባቴ የደረሰባትን የዘመን እውነት በልቤ እያሽሟጠጥኩባት እሰማ ጀመር..
"ታሪክ እራሱን ይደግማል ማለት እንግዲህ ይህ ነው፡፡ የምትመካበት አዲስ ነገር ምንድነው? እኔ ያላደረግሁት አንተ የምታደርገው ምን አለ? ተመልከት ፎቶዬን <ፀጉሬ ጎፈሬ ነበር፡፡ የአንተም ፀጉር አፍሮ ነው፡፡ እኔ ለጎፈሬዬ ከኀላ ኪሴ የእንጨት ሚዶ አይለየኘም ነበር፡፡ አንተም እንደኔው ለአፍሮህ ትጨነቃለህ፡፡ አፍሮህ ሲያድግ ደሞ ትገምደዋለህ፡፡
ሲሻህ ደግሞ ትሾርበዋለህ፡፡ይሔ ሁሉ ግን ከእኔ ከአባትህ የተረፈ ነው፡፡ ከኔ ያላገኘኸው ምንም ነገር የለም፡፡ እኔ በጎፈሬዬ የሀገሬን ጠላት ማጥፋቴን ፣ ማንነቴን መጠበቄን መሰከርኩበት፡፡ አንተ ግን በሹሩባህ መጀመሪያ ራስህን ፣ ቀጥሎ ቆነጃጅቶችኝ ጠለፍክበት፡፡
አንተ በፒያሳ እንደምትሆነው ሁሉ እኔም በውቤ በረኃ ዘምቻለሁ፡፡ <ይኼ ሁሉ የአባቴ ምክር ነበር፡፡
አሁንም እጄ ከፀጉሬ ላይ አልተለየም ÷ ሦስቱ ጣቶቼ ፀጉሬ ላይ ይፈትላሉ አባቴም ያወራል፡፡
<ይሄ ሁሉ ግን ጥላ ነው፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ የሚዳሰስ አካል ይመስለኘ ነበር፡፡ አይደለም፡፡
ወጣትነት ፍቹ እንደሌለው ህልም ነው፡፡ ታየዋለህ ፣ እንደ ነፋስ ሽውታም ያመልጥኻል፡፡ ወጣትነት ፊደል ነው፡፡ ፣ ቃል ግን አይደለም፡፡
ልጄ ሆይ ምክሬን ስማ ወጣትነትና ሕሊና ባዶ ናቸው፡፡
ሕሊና ፀፀትን እንጂ እርምትን አይወድም፣ ወጣትነት እና ሕሊና አንድ ናቸው፡፡ ሕሊና ፀፀት እንጂ እርምትን አይወድም ፣ ወጣትነትም እንደዚያው ነው፡፡ ብዙ ምኞትና ብዙ ከንቱነት፡፡"
ቀና ብዬ አይኑን አየሁት...ዓይኔን ወደመሬት መለስኩት፡፡ ቢጨርስና ቤቱን ጥዬው ብወጣ ደስታዬ ነበር፡፡ የአባቴ ምክር ወሬውን ቀጠለ...
"እስካሁን ከነገርኩህ በላይ የምነግርህ ቢኖር ዕድሜህ በአንተ ላይ ታዛለች እንጂ ፣አንተ በዕድሜህ ላይ መብት የለህም፡፡ እስካሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበትን ስልጣን በራስህ የለህም ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ደግም እርጅናዬን ታስንቅኃለች ፣ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡
ምናልባት፡- ዛሬ አንተ ከእኔ አባትህ የበለጥክበት ጊዜ እንደሚመስልህ ሁሉ አንተ በተራህ በልጅህ የምትበለጥት ጊዜ ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ልጄ ይበልጠኛል ለማለት አትችልም ÷ ልጅህ ከአባቴ እበልጣለሁ ይላል እንጂ፡፡ ያን ጊዜ የልጄን ልጅ ሰባት እጥፍ እወደዋለሁ ÷ የአያቱ ተበቃይ ነውና፡፡ አባቶች የልጆቻቸውን ልጆች የሚወዱበት ምክንያት ለማወቅ ከፈለግህ ፎቶዬን ተመልከተው ÷ አንተ ስወልድ ዕድሜዬ እንዳንተ ነበር፡፡
አንተ በእኔ ዕድሜ ስትሆን እኔ ወደ አያትህ እየሔድኩ ነው፡፡ ሕይወት ታሳሳለች ÷ አባት ስትሆን ደግሞ ልጅህ እያካለለ ሲያሮጣት ታያለህ ያኔ ለልጅህ ጠላቱ ልጁ ነውና የልጅህን ልጅ ትናፍቃለህ፡፡ የልጅህንም ልጅ ከልጅህ ይልቅ ሰባት እጥፍ ትወደዋለህ፡፡ ተበቃይህ ነውና፡፡" ብሎኘ ሽበት የወረረውን ወጉሩ ላይ ባርኔጣውን ጥሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ወጣ፡፡
እኔም አባቴ ከተናገራቸው ብዙ ቁም ነገሮች መካከል ያስገረመችኘና ያስፈገገችኘ እያሰብኩ ወደ ቀጠሮዬ ተነሳሁ......
"አሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበት ስልጣን በራስህ የለህም፡፡ ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ትሰማለች እነንጂ አታስተውልም፡፡ ጉብዝናህ እርጅናዬን ታስንቅኃለች ÷ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡"
የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ከኤፍሬም ስዩም
ህዳር 2007
ቤታችንእንሁን ቤተሰቦቻችን የሚሉንን እናዳምጥ