AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ትላንት ከውጭ ወደቤት ስገባ አልጋዬ ላይ የሆነ መፅሔት አገኘሁ፡፡ ማን አምጥቶልኘ ነው ስል ያንተ እኮ ነው አሉኘ መፅሔቶችን ስለምሰበስብ አይ የኔ እንኳን አይደለም ካሱ ያመጣልን ይሆናል አልኩኘ፡፡
ካሱ ምጣድና ስቶቩ የሚሰሬ የድሮ አራዳ ነው ቤት ሲመጣ ይደንስልናል🕺🕺 ይዘፍንልናል🎤🎷🎺🎸🎹...የባህል ህክምናንም ይሞክራል ብዙ ነገሮችንም ያወራናል ከትንሹ ወንድሜ ጋር ደግሞ በጣም ይዋደዳሉ፡፡
እና አንባቢ ነው ሲመጣ የድሮ መፅሐፍቶችና መፅሔቶችን ጋዜጦችን ይዞልን ይመጣል፡፡ ደሳስ ሚሉ ፅሁፎች ያሉባቸው እና አያሌ እውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ እኛም እያነበብን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ይህን መፅሔትም እሱ እንዳመጣው ጥርጥር የለኘም፡፡ ምክንያቱም የኔ ዕቃዎች ያሉት እቃ ማስቀምጥበት ቦርሳ ውስጥ ነው ካለኔ ማንም አይነካም እማ እራሱ ብትሆን፡፡
እሱ ነው ያመጣሁ ያልኩበት ምክንያት መፅሔቱ
የሰኔ 2009 ዓ.ም ህትመት ቁምነገር የተሰኘ መፅሔት ነው፡፡
ጉስቁል ብሏል አነሳሁት የመፅሔት ገፅ ከዚህ በፊት ቆጥሬ ባላቅም ገፆቹን ቆጠርኳቸው 6 ገፅ ነው ያለው እስከ ስምንት በተራው ይሔድና በመሐል ብዙ ገፆች ጎድለውት ገፅ 29 ድጋሚ ይጀምርና ገፅ32 ላይ ያልቃል፡፡
አነሳሁት የገለጥኩት ገፅ ላይ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደሰ ስለተባሉ የሃገራችን ፕሮፌሰር የህይወት ተሞክሮ ያስቃኛል ግን አይጨርሰውም ተበሳጨው፡፡
ጥቂት ቢሊኒየሮችና ብዙ ምንዱባኖች የሚል ርዕስ አለ ግን ፅሁፉ ተቆርጧል🤦♂፡፡
ቀጠልኩ የስፔናዊው የፈርናዶ ቶሬዝ ከፍታ እና ዝቅታ ይላል፡፡ ገርበብ አደረኩት ለካ ቶሬዝ ፊልም ሰርቷል 😂😂😂 ዛሬ ነው ማቀው🤦♂👊👊
ገለጥ ሳደርግ ለባለትዳሮች ይልና ወሲብ አልባ ትዳር ይላል ይሔን አንብቤ ቻናል ላይ ማካፈል አለብኘ አልኩና ንባቤን ገታሁ ልብስ ቀያይሬ መፅሔቱን ይዤው ወጣሁ ብና ከጠጣሁ በኀላ ወደ ንባቤ ተመለስኩ ስላነበብኩ አዲስ ነገር አውቄያለሁ ፅሁፏ አጭር ነች መፅሐፍ አለብኘ የለብኘም እያልኩ ወደሌላ ገፅ ተሸጋገርኩ ወደ መጨረሻው ገፅ
በትልቁ "ሽማግሌው" ይላል
ማክሲም ጎርኪይ ፅፎት
መኩሪያ መካሻ ተርጉሞታል ይላል...
አነበብኩት በጣም ደስ ይላል በጣም የላይኛውን ፅሁፍ ልዝለላችሁ እና ይሔን ላካፍላቹ ወደድኩ ባለትዳሮች እንዳትቀየሙኘ ይሔም ፅሁፍ ስታነቡም ይቅርታ እንደምታደርጉልኘ አልጠራጠርም ልታገቡ ያሰባችሁ እስኪ ይቺን ፅሁፍ ገርበብ አድርጓት ሲንግል የሆናችሁም እራሳችሁን ታዘጋጁበታላችሁ፡፡
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂
ለአስተያየታችሁ @jahABP ነኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

ሽማግሌው
ከሮምና ከጄኖዋ መሃል የሚገኘ አነስተኛ የባቡር ጣቢያ ነው፡፡ አስተናጋጁ የነበርንበት ክፍል በረገደ፡፡ አንድ ዓይናና ድንክዬው ሽማግሌ የመሸከም ያህል ደግፎ አስገባው፡፡ ቆቅ፡የሆነ ሽማግሌ ነው፡፡ የረዳውን ሰው ለማመስገን እጆቹን አውለበለበ ÷ ዘባተሎ ባርኔጣውን አንስቶ እጅ እየነሳ ትህትናን በሚረጭ ጥልቅ ዓይኑ ተሳፋሪውን ቃኘ፡፡ " ትፈቅዱኛላችሁ?! ሲል በእፎይታ እጆቹን ጉልበቶቹን ላይ አሳረፈ፡፡ ጥርስ የለሽ ፈገግታውን ረጨ፡፡
"ሩቅ ነው የሚሔዱት አባቴ?" ሲል ጓደኛዬ ጠየቃቸው፡፡ "አይደለም ÷ ሶስተኛው ጣቢያ ላይ ነው የምወርደው፡፡ ቀጥሎም ቆይት ታሪኩን ይተረትረው ጀመር - ንፋስ እንደሚያወዛውዘው ቅርንጫፍ በቆመበት እየተወዛወዘ፡፡
እኔ ሊንጎሪያዊ ነኘ፡፡ እኛ ሊንጎሪያዊያን ጠንካሮች ነን፡፡ ለምሳሌ ያህል እኔ ውሰደኘ፡፡ 13 ወንዶችና አራት ሴቶች ልጆች አሉኘ፡፡ ምን ያህል የልጅ ልጆች እንዳሉኘ ግን በትክክል አላውቅም፡፡ ዛሬ የሚያገባው ሁለተኛ ልጄ ነው ÷ ሽማግሌው ደግ አይደል ታዲያ?"
በኩራት በአንድ አይኑን እየቃኘን
"ለንጉሴና ለአገሬ ምን ያህል ሰው እንዳበረከትኩ አስቡ፡፡" "ደግሞም ዓይኔ እንዴት ሊጠፋ እንደቻለ ልንገራችሁ?" ከብዙ ዓመታት በፊት ነው ÷ ገና ህፃን የነበርኩ ብሆንም አባቴን መርዳት ጀምሬ ነበር፡፡ መሬቱ ጠንካራና ድንጋያማ ስለነበር ከባድ ስራን ይጠይቃል፡፡ ታዲያ አባቴ ድንጋዩን ሲፈነቃቅል ፍንጣሬ አይኔ ውስጥ ገባች፡፡ ያኔ ህመም የተሰማኘ ስለመሆኑም አላስታውስም፡፡
መድሃኒት አደረጉልኘ ግና አልፈየደልኘም ይኸው እስከዛሬ አይኔ ታውራለች፡፡
የተጨማደዱ ጉንጮቹን እያሻሸ ፈገግታውን ረጨብንና ትረካውን መልሶ ቀጠለ፡፡
"ያኔ እንደዛሬው ዘመን ብዙ ሃኪሞች ስላልነበሩ ሰዎች በየዋህነት ይኖራሉ፡፡ አዎን! በሞኘነት፡፡
ይሁና ከዛሬ ዘመን ሰዎች ይልቅ ደግ ነበሩ፡፡
"የእኔን ያህል እድሜ የኖረ ሰው ስለሰዎች የሚያስበው መናገር ይቻላል፡፡ አይመስላችሁም ጎበዝ እንግዲያውስ ስለሰዎች ላውጋችሁ፡፡
ልጆቼ አባቴ የሞተው የ13 አመት ልጅ ሆኜ ነው፡፡
የስራ ነገር ከተነሳ ግን ሰርቼ የማልደክም ጠንካራ ሰው ነበርኩ፡፡ ከአባቴ የወረስኩት ይህኑኑ ብቻ ነው፡፡ ቤታችንና የእርሻ መሬታችን የተሸጠው እዳ ለመክፈል ሲባል ነበር፡፡ ስለዚህ በአንድ ዓይኔና በሁለት እጆቼ ስራ በተገኘበት እየማሰንኩ ነው የኖርኩት፡፡ ህይወት ፈተና ነበር፡፡ ነገር ግን ወጣትነት ለችግር አይበገርም አይደለም እንዴ?!
"አስራ ዘጠኘ ዓመት ሲሞላኘ አንዲት ጉብል አፈቀርኩ፡፡ ልክ እንደኔው መናጢ ድሃ ነበረች፡፡
ከደከሙ አሮጊት እናትዋ ጋር እየኖረች እንደእኔው የተገኘውን ስራ ሁሉ ትሰራ ነበር ቁንጅናዋ እስከዚህም ቢሆንም ደግና ብሩህ አእምሮ ነበራት የድምፇ ነገርማ አይነሳ! አቤት እንዴት ታንጎራጉር ነበር? መቼም ከዘፋኘ አትተናነስም፡፡
እኔም እኮ ጥሩ ድምፅ ነበረኘ፡፡
እንጋባ! አልኳት በዱብ እዳ፡፡
"ይህ ጅልነት ነው አንድ ዓይናው አለችኘ በንዴት"
አንተም እኔም መናጢ ድሆች ነን ፣ እንዴት ነው የምንኖረው? አባባልዋ ትክክል ነው፡፡ ሁለታችንም ምንመም አልነበረንም፡፡ ይሁና ወጣት ፍቅረኛሞች ምን ይፈልጋሉ? የፍቅር ምሱ ምን እንደሆነ እናንተም ራሳችሁ ታውቃላችሁና በእግር በጥፍሯ ገብቼ አገባኀት፡፡
" መልካም ምንአልባትም አንተ ልክ ነህ" አለችኘ ፍቅረኛዬ ኢዳ በመጨረሻም፡፡
ተለያይተን እንዲህ መኖር ከቻልን አንድ ላይ ደግም እንዴት የተሻለ አንኖርም?! ብዬአት ተያይዘን ወደቤተክርስቲያን ሔድን፡፡
"ይሕስ እብደት ነው አለ ቄሱ፡፡...ምስኪኖች ራስ ሳይጠና ጉተና'
የሰፈሩም ወጣቶች ተሳለቁብን፡፡ በእድሜ የገፉት ደግሞ አስሟጠጡብን፡፡ እኛ ግን ወይፍንክች!
ወጣት ሲባል ግትርና የራሴን መንገድ ቀያሽ ነውና የሰርጉ ቀን ደረሰ፡፡ የሰርጉ እለት የት እንደምናድር እንኳን አናውቅም ነበር፡፡ ሜዳ ላይስ ብናድር ለምን አናድርም፡፡ መሬት አልጋችን ሰማይ ብርድልብሳችን እንዲሆን ወሰንን፡፡
በረዥሙ ዘመኔ ያተረፍኩት ልዩ ታሪክ እነግራችኀለሁ እባካችሁ በትዕግስት ጆሮአችሁን አውሱኘ፡፡
ይቀጥላል🏃♂🏃♂

ከሰርጋችን አንደበት ቀን አስቀድሜ የሰጠኘን ስራ በሚገባ የሰራሁለት ሽማግሌው ጆቫኒ እንዲህ አለኘ ፡- "ዩጉ! የበጎቹን ጎረኖ ማፅዳት ሊኖርብን ነው፡፡ ንፁህ ኬሻ ታነጥፍበታለህ፡፡ በጎቹም እዚህ ማደር ከተዉ ከዓመት በላይ ሆኗል፡፡ አንተ እና አይዳ ልትገቡበት ከፈለጋችሁ በደንብ አፅዱት፡፡ እኛም እዚ ውስጥ ኖረን ነበር" አለኘ፡፡
ሀሳቡን በደስታ ተቀብዬ የበጎቹ ጉረኖ እያንጎራጎርኹ ሳፀዳ ቀና ስል አናጢው ኮስታንዙዩን በር ላይ ቆሞ አየሁት፡፡ "ያንተ እና የአይዳ ቤት ነው? ይሁና አልጋችሁ የት አለ? እኔ ጋር ትርፍ አልጋ አለና ማፅዳቱን ስትጨርስ መጥተህ ውሰድ፡፡" አለኘ
አልጋውን ላመጣ ስሔድ ማሪያ ባለሱቋ ደግሞ ጮኸችብኘ " እናንተ ጅሎች! በኡነት ልትጋቡ ነው? የናንተ የሆነ አንሶላና ትራስ እንኳን ሳይኖራችሁ? አንድ አይናው! ጅል ናችሁ፡፡ ለማንኛውም እስኪ ግን ሙሽራዋ ወደ እኔ ላካት"
ላሜ ኢቶሬ ቪያኖ ከበሩ ላይ እንደቆመ ጮኸባት፡፡ " ምን ያህል ወይን ለእንግዶቹ እንደሚያስቀምጥ ጠይቂው፡፡ ሰዎች እንዴት እንዲህ ያለ አግባብ ግዴለሽ ይሆናሉ?"
የሽማግሌው ዓይን እንባ አቀረረ፡፡
ከጭንቅላቱ ዘንበል ብሎ ፈገግ አለ፡፡ "ኦ ሲኞሬ!!"
አለ በፈገግታ እጆቹን እያሻሸ፡፡ በሠርጋችኝ ማግስት የፈለግነው ሁሉም ነገር ነበረን፡፡ ሳህኖች ፣ የጠረቤዛ ልብሶችና ሌሎች ቁሳቁሶች ነበሩን፡፡እውነት እላችኀለሁ አይዳ ተፍነከነከች፡፡ አለቀሰችም፡፡ እኔም ሳቅሁ፡፡ የሰፈራችን ሰዎች በሙሉ ሳቁ በሠርግ እለት ማልቀስ ደግ ስላይደለ፡፡
ሲኞሬ! ሰዎችን የራስ አድርጎ የማሰብ መብት መኖሩ እጅግ መልካም ነገር ነው፡፡ የሌላ ሰው ህይወት ቀልድ ፣ ደስታው መሳለቂያው እንዳልሆነ የሚረዱ ሰዎችን መልካም ግንኙነት መፍጠር ጥሩ ነው፡፡
እናም ምን አይነት ሰርግ መሰላችሁ? አቤት እንዴት ያለ እለት ነበር፡፡ የሰፈራችን ሰው በሙሉ ተገኘቷል፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ጎረኖዋ ሲመጣ ወዲያው ወደ ሞቀ፡ጎጆነት ተቀየረች፡፡ ሁሉ በእጃችን ሁሉ በደጃችን፡፡ ወይን ፣ ፍራፍሬ ፣፡ሥጋ ፣ ዳቦ....ሁሉም ሰው ተመግቧል፡፡ ሁሉም ተደስቷል፡፡
ሲኞሬ! ለሰዎች ደግ ከመስራት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም፡፡ እመኑኘ! ከዚህ በላይ መልካም ነገር የለም፡፡
በሠርጋችን ላይ ቄሱ መጥተዋል ማለፊያ ንግግርም አደረጉ፡፡ "እዚህ" አሉ፡፡
"እዚህ ለሁላችንም ሲባክኑ የኖሩ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ እናንተም በተራችሁ ይችህን እለት በልዩ ቀን ለማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኀል ይህ ደግሞ መሆን ያለበት ነው ለእናንተ ብቡ ሰርተዋልና፡፡ እና ሥራ ከመዳብና የብር ሳንቲሞች የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ስለስራው ከምታገኙት ምንዳ በላይ ስራ ጠቃሚ ነው፡፡ ገንዘብ ጤዛ ነው ይጠፋል ÷ ስራ ግን ዘላቂ ነው፡፡ እኚህ ሰዎች ልበቅንና ድሆች ናቸው፡፡ ኑሮአቸው በመከራ የተውተበተበ ቢሆንም ፣ አማረው ግን አያማሩም፡፡ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ ደግሞ ትረዱአቸዋላችሁ ወርቅ እጆችና ቅን ልብ አላቸውና"
ብለው ቄሱ ብዙ አስደሳች ንግግር ለእኔ ፣ ለአይዳ እና ለሰፈሩ ሰው በሙላ አደረጉ፡፡
ሽማግሌው በታደሰ ዓይኖቹ መልሶ ቃኘን እና ሲኞሬ! ስለ ሰዎች ጥቂት ነገርኳችሁ ÷ ጥሩ ነው አይደል?
ፀሃፊ:- ማክሲም ጎርኪይ
ትርጉም:- መኩሪያ መካሻ
ቁም ነገር መፅሔት ቅጽ 15 ቁጥር 301 ሰኔ 2009 ዓ.ም
እኔም እንዲህ አልኩኘ
"ልብ ይበቃል መቆም ለቃል ቤት ይሞቃል በቃል"
እዮባ
መልካም እንሁን መልካምነት መልሶ ይከፍላልና
ለአስተያየታችሁ @jahABP

ሃያሏ አሜሪካ አሁን ላይ ብጥብጥ ላይ ነች፡፡
የሰው ልጅ ላይ የማይሰራ ተግባር በሰራ አንድ ነጫጭባ ድብልቅልቋ ወቷል፡፡
አንድ ወዳጄ ጋር ደወልኩለት እና እህሳ እንዴት ናቹ አልኩ ደና ነን ያው ተቃውሞ በርትቷል ብሎ በጣም ብዙ ነገር አጫወተኘ፡፡
የገረመኘን ያስደነቀኘን አንድ ነገር ነገረኘ፡፡
ይገርምኻል ያልተቃጠለ ነገር የለም ማለት ትችላለህ ይሔ አሁን ደግመህ አሜሪኬ ይሆናል እስክትል ድረስ የተቃጠሉ ቦታዎች አሉ ከባለቤቴም ጋር ትላንት ሔደን አይተነዋል ብዙ ነገሮች ተቃጥለዋል ግን አለኘ......ግን ምን ያህል የተማሩ መሆናቸውን ምታውቀው አለኘ...
እ....አልኩት
ብዙ ህንፃ ሲቃጠል አዳራሾች ሲነዱ አንድ መስታወት በመስታወት ሆኖ የተሰራ ህንፃ ግን አንድም፡ነገር አልሆነም ፍንጥርጣሪ ድንጋይ እንኳን አልነካውም አለኘ፡፡
ገርሞኘ ምን የባለስልጣን ቤት ነው ስለው
ወይ ጉድ እነሱን ቢያገኟቸውማ በምን እድላቸው
እና ምንድነው??
ትልቅዬ ላይብረሪ ነው አለኘ፡፡ አይገርሙም አለኘ
ማርያምን ቀላል ይገርማለሁ አልኩት ጥሩውንም መጥፎውንም ስትሰማ ከሀገርኸ ሁኔታ ጋር ታገናኘዋለህና እኛ ሃገር ያለውን አሰብኩት ስንት ትውልድ ሚቀረፅባቸው ዩኒቨርስቲ ምናቃጥል ድንቅ ህዝቦች እኮ ነን መፅሐፍቶችን ሰብስበን በአደባባይ ምናቃጥል አስቂኘ ሰዎች እኮ ነን ኧረ ስንቱ ወዳጄ፡፡
ብቻ እራሳችንን ቆም ብለን ብናይ እንዴት ጥሩ ነው፡፡ ፖለቲካን ከትምህርት ጋር ባናገናኘ ምናለ፡፡
ኡነት አስገርመውኛል በአስተሳሰብ በጣም ጥለውን ሔደዋል እኛም ይህን አይተን ልንማርበት ይገባል ባይ ነኘ፡፡
በቀጣይ ከዕረፍት መልስ ሁለተኛውን መፅሐፍ ለመጨረስ አንድ ሁለት እንላለን፡፡ ትንሽ ያዘገየሁት ቶሎ እንዳያልቁ ሰግቼ ነው፡፡
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
እናንብብ እናንብብ አሁንም እናንብብ

ሁለተኛውን መፅሐፍ ነገ እንቀጥላለን አሪፍ እረፍት ያደረግን ይመስለኛል፡፡
ከዚህ መፅሐፍ የቱን ትቼ የቱን እንደምፅፍ ሁላ ነው ግራ የገባኘ የኡነት ብቻ ያስተምራል ያልኩትን እለቃለሁ፡፡
ግን ካለበት ፈልጋቹ አፈላልጋቹ እንድታነቡት ነው ምክሬ እኔ የምፅፈው በጣም ከብዙ ጥቂቱን ነውና፡፡
በመግቢያዬ ላይ እንዳልኩትም ከራሳችሁም አልፎ የሌሎቹንም ሕይወት ትቀይሩበታላችሁ፡፡
ነገ እንቀጥላለን
አዲስ JOIN ያላቹ ቤተሰቦቻችን PIN የተደረገውን ፅሁፍ በማንበብ መረዳት ትችላላችሁ፡፡
በውስጥ መስመር አስተያየታችሁን የምትሰጡኘ ለሁላችሁም አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያክብርልኘ😍🙏😊 አንብባችሁ ሃሳባችሁን ስለምታጋሩኘ በርታ ስለምትሉኘ ደስተኛ ነኘ እኔም የናንተ ድጋፍ ጥንካሬ ይሆነኛልና፡፡
በድጋሚ አመሰግናለሁ 😃😊🙏
@jahABP አስተያየታችሁን አድርሱኘ

ቀጣዩን መፅሐፉ ተፅፎ ያለቀው 1998ዓ.ም ነው ለህትመት የበቃው 2003 ዓ.ም ነው፡፡
መፅሐፉን ስንጀምር ተናግሬ ነበር፡፡
ግን የዛሬውን ሰው ፀባይ ቁጭ አድርጎ ያሳየናል የኔ ያንተ ያንቺ የሁላችንንም የሁላችንንም እኔ ሁሌም ሳነበው እራሴን ደጋግሜ ቆም ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል ከነዚህ ነገሮች መላቀቅ አለብንና፡፡
ታግሳቹ አንብቡትና እናወራበታለን
በቆንጅዬው VOICE RECORD አድርጎ ለሚልክ
የMB እና የስዕል ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡
@JahABP ነኘ

AB POHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
የሚመስል ነገር
የሰው እድሜን በከንቱ የሚጨርስ ፣ ብልጥ ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሳይቀር የሚያታልል ፣ አለሁ አለሁ፦እያለ የማይኖር ፣ መጣሁ መጣሁ እያለ የሚቀር ፣ ዝናብ የሌለው ደመና ፣ የሚያስፈራራ የጉም ጋሬጣ ፣ የማይቆይ የአመዳይ ምንጣፍ ቢኖር የሚመስል ነገር ነው፡፡
ፀሀይን የሚጋርዱ ፣ የነጋዴውን ምንጣፍ የሚያሳጥፉ ፣ ገበያተኛውን የሚበትኑ ፣ የደመቀውን ጭር የሚያደርጉ የረጋውን ግብይት የሚደባልቁ መንገደኛውን በማስቸኮል ልቡን የሚያስደልቁ ፣ ውሃ የተጠማውን የሚያጓጉ ፣ ታይተው የሚጠፉ ፣ ድምፅ አሰምተው የሚሞቱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡
ሳይዘንቡ ፀሐይን የሚከልሉ ፣ ላያርሱ ጨለማ የሚያለብሱ ፣ ላይደርሱ የቀረበውን የሚያርቁ ፣ ላይወርዱ የተዘረጋውን የሚያጥፉ ፣ ቀስ ብሎ የሚያርሰውን የሚያስጋልቡ ፣ መጣሁ እያሉ የሚቀሩ ፣ የተጠማውን መቅጃ የማይሞሉ ፣ የተማመነባቸውን የሚያሳፍሩ ፣ ቀጠሮ አስይዘው የማይገኙ ፣ ብዙ በሽተኞችን አሳምመው ፣ ስሜትን አጨፍግገው በመዝነብ ያረኩናል ሲባሉ በሩቁ ታይተው የሚቀሩ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡ ከጥቁረታቸው ማስፈራራት የተነሳ ሁሉን ትተው ሲጠብቋቸው የሚቀሩ ፣ ፎክረው ሳይዘንቡ የሚመለሱ ፣ ነፋስ የሚበትናቸው ውስጠ ባዶ ደመናዎች አሉ፡፡ የሚመስል ነገር ዝናብ የሌለው ደመና ነው፡፡
በጋውን ክረምት የሚያስመስሉ ፣ በብርሃን መካከል ገብተው የሚያጨልሙ ፣ ሰላማዊ ግብይትን የሚያደፈርሱ ፣ በግርግራቸው ብዙ ንብረት የሚዘርፉ ፣ ዝናብ የሌላቸው ባለራዕዮች አሉ፡፡ ሲያንዣብቡ በረከት ያዘሉ የሚመስሉ ፣ ሲጠቋቁሩ የሚያረኩ የሚመስሉ ፣ ጥቁረታቸውን ታግሶ ዝናብ ለጠበቀባቸው እልም ብለው የሚቀሩ ባለዕራይዎች አሉ፡፡
ፈጣንነታቸውና ፣ ቡድን አሳዳሚነታቸውን ታግሰን መልካም ነገር ይወጣቸዋል ስንል ተስፋችንን አሳፍፈው የሚመልሱ ዛሬም አሉ፡፡ እንደእባብ እየተለሳለሱ አካልን እየዳሰሱ የሚነድፉ ፣ እያሰከሩ የሚሰርቁ ፣ እያደነዘዙ የሚያራግፉ ፣ የመንጋውን ልብ በቅብ ፍቅር የሚያሸፍቱ ዛሬም አሉ፡፡
ጭር ሲል የማይወዱ ፣ ማስመሰል አገልግሎቴ ፣ መበጥበጥ ራዕዬ ያሉ ፣ ያነደዱት እሳት ሌላው ሲያቃጥል እነርሱ ለመሞቅ የሚሹ ፣ ይህንንም አገልግሎት ብለው የያዙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከባል የሚያፋቱ ውሽሞች ፣ ከበግ ጋር የተሰማሩ ተኩላዎች ፣ በበግ እርምጃ እየተራመዱ ራሳቸውን የሚሰውሩ ፣ ሥጋ በል ሳሉ ለዓላማቸው ሣር ለመብላት የጨከኑ ፣ የእረኛው ልብ ከወደቀላቸው በኋላ ምልመላ የሚጀምሩ ፣ ባለራዕዩ እስኪጠላ በሌሊት ሳይቀር መንጋው የሚጎበኙ ፣ መንጋውን ከእረኛው ከለዩ በኋላ ትተው የሚሰወሩ ፣ ነገር ግን ባለ ራዕይ የሆኑ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡
ከራዕይ እንቅፋቶች አንዱ የሚመስል ነገር ነው፡፡
የዘመናችን ሰው እውነተኛ ለመሆን አሳብ እንኳን የሌለው ራሱን በሚመስል ነገር አስሮ የሚኖር ነው፡፡ መልካም ተግባርን በጥሩ ንግግር ተክቶ የሚናገር ከእውነተኛም ጋርም ላለመገናኘት ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው፡፡ እውነት ያልሆኑ ፣ ነገር ግን እውነት እንዲመስሉ የተለፋባቸው ሐሰቶች በዝተዋል፡፡ እውነተኝነትን ደረቅነት ፣ አስመሳይነት ዘመናይነት የሆነበት ዘመን ነው፡፡
"እብድ እውነት ይናገራል" እያልን የጤነኝነት መገለጫው ውሸት ሐሰት መሆኑን ያመንበት ይመስላል፡፡ እኛን የማይገልጡ ቃሎችና አለባበሶች ተግባራችንን ለመሸፈን ብናውላቸውም መሸፈኛዎች ሁሉ የመሸፈን አቅም አጥተዋል፡፡ ጊዜውም ከዋሸህ ከተነቃብህ ጨምርበት ፣ ብዙኃን የተስማማበት ሐሰት ከእውነት ይቆጠራል የሚል ነው፡፡ የዚህ የማስመሰል አብዮት አራማጆች ብዙዎቹ የኃይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡
እነዚህ በገንዘብና በሆዳቸው ፍቅር የሰከሩ ሲሆኑ መንገድ በማሳት የአገር መሪዎችን እንኳን ሲያስቱ የሚታዩ ናቸው፡፡ ዘወትር በውዳሴ ከንቱና በመወዳደስ ሕይወት ስለሚኖሩ ብርሃኑ ጨለማ ፣ ጨለማውን ብርሃን በማለት ምድሪቱን በብሩቱ ስቃይ ሲወጓት እየተመለከትን ነው፡፡
በሚመስል ነገር መያዝ ብርቱ እስር ቤት ነው፡፡ በሲኦል ውስጥ ከሚገኙ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ነፍሶች በሚመስል ነገር ተይዘው ዕድሜያቸውን ያባከኑ ብዙዎቹ በሃይማኖት ካባ ተደብቀው እራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ በሕሊናቸው ፊት ሳይሆን በሰው ፊት እውነተኛ ለመሆን ይጥራሉ፡፡ ውሸታምን ያደናቀፈ ዕድሜ የለውምና እነዚህ ሰዎች ውሸታቸውን የነካባቸውን እንደ እርግጠኛ ጠላታቸው በማየት ለማጥፋት እንኳን ወደኋላ አይሉም፡፡
ሌባ ብርሃን አይወድምና የፈጣሪን ቃል ሲሰሙ ይበሳጫሉ፡፡ሰባኪውን ስም ይሰጡታል፡፡ ቅዱስ የሚሏቸውን የራሳቸውን መምህራን ያከማቻሉ፡፡ በአገር ደረጃም አገር እወዳለሁ እያሉ ህዝብን የሚፈጁ ፣ የወደቀ ዜጋ አልፈው እየሔዱ ሰውዬውን የወከለውን ባንዲራ የሚስሙ ብዙ ግለሰቦች አሉ፡፡
በራዕይ ውስጥ በሚመስል ነገር የተያዙ አያሌ ናቸው፡፡ ራዕይ ማለት ቶሎ ቶሎ መራመድ በተወጠረ ስሜት መስራት ትንፋሽ ለመዋጥ ጊዜ ማጣት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች ራዕይን ለመገምገም ፣ ትርፍና ኪሳራቸውን ለመመልከት ጊዜ የላቸውም፡፡ የሚያባክኑት ኃይል እውነተኞቹ ባለ ራዕዮች የሚያወጡት ሃይል በመሆኑ ያለ ዋጋ እንዳይቀሩ ቆም ቢሉ መልካም ነው፡፡
"ለስሟ ማስጠሪያ ቁና ሰፋች" እንደሚባለው አንዷን ተግባር ለዘለዓለም የሚያወሩ ለመጣ ለሔደው ያችኑ የሚደጋግሙ ከመጠን በላይ አጋነው የሚያወሩ ፣ የሰውን ቀልብ መሳብ ሥራቸው ያደረጉ ሰዎች በሚመስል ነገር የተያዙ ናቸው፡፡ በራዕያችን የምንሰራው የሰራን በማይመስለን ጊዜ ነው፡፡
እንደሰራን ካሰብን ቆመናል ማለት ነው፡፡ የሚሰራ በሰራው ረክቶ አይቀመጥም፡፡ የሚሰራ አይረካም፡፡ ሌሎችም ገድላቸው ተፅፎ እንዲኖር ታሪካቸው በወርቅ ቀለም እንዲሰፍር ይፈልጋሉ፡፡ ለዛሬ ትውልድ ጠቃሚ ሳይሆኑ ለሚቀጥለው ትውልድ ታሪክ ለመሆን ይጨነቃሉ፡፡ ብዙ ነገስታት መሳፍንታት ፣ እንኳን ኖረው ሞተው እንኳን ደምቀው እንዲታዩ ብዙ ለፍተዋል፡፡ ዛሬ ግን ከመደነቅ ይወቀሳሉ፡፡ ሁሉም ነገር እኛ እንዳሰብነው አይሆንም፡፡
ዛሬን ጠቃሚ ሰው ሆነን ለመዋል መጣር ብቻ ህሊናን ነፃ ያደርገዋል፡፡
በራዕይ ውስጥ ትዕግስት ከሚመስል ስንፍና ፣ ትጋት ከሚመስል መክነፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
እናስተውል.....
★ ትዕቢተኛ የራሱን ትልቅነት የሚቀበለው የሌሎችን ትንሽነት በማመን ነው፡፡
★የሚያስፈራውን አምላክ ካልፈራን ፈሪ የሆኑትን የሰው ልጆች መፍራታችን አይቀርም፡፡
★ እግዚአብሔር ከችሎታችን ጋር ሳይሆን ከእሺታችን ጋር ኅብረት አለው፡፡
★ ምንም እንሁን ባለንበት ሁኔታ እግዚአብሔር ጠቃሚ ሊያደርገን ይችላል፡፡
★እኛም ፍፁም አለመሆናችን መረዳት ለፍፁምነት መነሻ ትልቅ መልስ ነው፡፡
★ የምንችለውን ማድረግ የማንችለውን ወደ ማድረግ አቅም ይመራናል፡፡
★ ሥር ያልሰደዱ ሁሉ ቢያምሩም በውበታቸው አይቆዩም፡፡
★ ራዕይ እየገፋ እንጂ እየጠፋ አይመጣም፡፡
★ ራዕይ እኛ ብናልፍም የሚቀጥል እንጂ ከእኛ ጋር የሚያልፍ አይደለም፡፡
ከሁለተኛ መጽሐፍ ስድስተኛ ፅሁፍ
ቤታችን እንሁን እና ንብብ
ለመልካም ነገር የፈጠንን እንሁን
ለአስተያየታችሁ @jahABP ነኝ

😊እንዴት ዋላችሁ😍
"ትውልድን ለመታደግ ሁላችንም ግዴታ አለብን::
ምናልባት ለእኛ መለወጥ የደከመልን ላይኖር ይችል ይሆናል፡፡ ፈጣሪንና እራሳችንን ካወቅን ግን ያልተቀበልነውን ለመስጠት መነሳሳት አለብን፡፡ ሰው ወደመልካም ነገር እንዲመጣ ወደ መጥፎ የሚሔደውን መጀመሪያ ማስቆም አለብን፡፡ ወደ መጥፎ የሚሔደውን ካስቆምን በጥፋት ስፍራ ያለው ይለወጣል፡፡በሸለቆ ውስጥ የወደቀ ሰው አለ፡፡ ወደ ሸለቆው የሚወርደው ሰው ከበዛ ለመውጣት መንገዱ ዝግ ነው፡፡ ስለዚሁም ወደ ጥፋት የሚያወርደው መጀመሪያ መገደብ አለብን፡፡ አሊያ ይህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ዕጣ ያሳስባል፡፡
ወንጀልም በሕግ ከለላ ያገኛል፡፡
ነውሩም ክብር ሆኖ ይፀድቃል፡፡
ትውልዳችን ስናይ የምናስተውላቸው ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮቹን የምንጠቅሰው ያለፈውን መልካም ጊዜ ለማወደስ ዛሬን ለመርገም ሳይሆን የተሻለ ቀን ለማየት ነው፡፡ በዚህ ችግር የሚያልፉ ቆም ብለው እንዲያስቡ ፣ ትውልድን ለመታደግ አሳብ ላላቸው ችግሩን እንዲያዩ ለማድረግ ነው፡፡
ትውልዳችን እነዚህ ችግሮች አሉበት ይላል" ፡-
ምን ምን ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ ይቀጥላል፡፡
እኔ ይሔን ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም እራሴን ከበኩርኩም እንደተመታ ኩም እላለሁ፡፡
የዚህ ትውልድ አካል ነኘና ችግሮቹ በእኔም ህይወት ላይ አሉ ሁሌም እሩጫዬ ከነዚህ ፍላፃዎች እራሴን ማውጣት ነው፡፡ ከዛ ሌሎችንም ለዛም ነው ላካፍላችሁ የወደድኩት፡፡
ሁላችንም ይህንን ፅሁፍ ማንበብ አለብን ከዛ እራሳችንንም ቆም ብለን መመልከት እራሳችንን መለወጥ ከዛ ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት መሆን፡፡
እንቀጥላለን🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
ቆዩልኘ፡፡
@jahABP ነኘ

ትውልዳችን፡-
1) መዳረሻውን ያላየ ነው
ከትውልዳችን አብዛኛውን የመጨረሻ ግቡ ገንዘብ ማግኘት ወይም ዝነኛ መሆን ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች የተጠሉና የማያስፈልጉም ባይሆኑም ራዕይ ግን አይደሉም፡፡ ትውልዳችን የተሻለ ኑሮ እፈልጋለሁ ይላል ፣ ለእርሱ የተሻለው ቤትና መኪና ነው፡፡ ሰውን ለሚያህል ትልቅ ፍጡር ግን እነዚህ ቁሳቁሶች ግብ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ መንገዳችን ላይ ከምናገኛቸው በረከቶች ውስጥ ይመደባሉ። ግባችን ግን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰው ከበሬ ለተሻለ ነገር መኖር አለበት፡፡ በሬ ቀኑን በሙሉ ላቡን ጠብ አድርጎ ይሰራል ፤ እኛም እንሰራለን ፤ በሬ ከስራ መልስ ላም አለችው እኛም ትዳር አለን፡፡ በሬ ጥጆች አሉት እኛም ልጆች አሉን፡፡ ከዚህ ያለፈ ነገር ከሌለን እየኖርን ያለነው እንደ በሬ ነው ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛ ባንሆን ምን ይደንቃል፡፡
ወደላቀው የኑሮ ደረጃ ፣ እግዚአብሔር ወዳየልን ከፍታ መድረስ አለብን፡፡ እርሱም በራዕይ መገለጥ ነው፡፡ ከሕይወት ጥያቄዎች አንዱ "ወዴት ነው የምሄደው?" የሚል ነው፡፡ ሰው መዳረሻውን ካላወቀ በኑሮው ድፍረት አይሰማውም፡፡
ትውልዳችን ላይ በአብዛኛው የምናየው ለዛሬ መሙላት ብቻ መኖር ፣ ለራስ ብቻም ማሰብ ፣ ሁሉንም ሰው የጥቅሙ ገባር አድርጎ መፈለግን ነው፡፡ ለወገኔ የሚል ስሜቱ እየተሟጠጠ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ችግር በእግዚአብሔር የለሽ አስተሳሰብ መበከሉ ነው፡፡ ፈጣሪ የለሽ ሥርዓት ከአደባባይ ቢወድቅም ከሰው ልብ ግን አልወደቀም፡፡
በየትምህርት ቤቱ ይሰጡ የነበሩ የግብረ ገብ ትምህርቶች በአዋጅ መከልከላቸው ከዚያ በኋላ ያተረፍነው ትውልድ ብኩን ትውልድ ነው፡፡ ትዕግስት የጎደለው ፣ ራዕይ አልባ ፣ መረን ትውልድ ለማፍራት ተገደናል፡፡
2) ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል
አይሁዶች:- "ተቀብሎ የማያመሰግን ከቀማኛ ይቆጠራል" ይላሉ አብዛኛው ትውልዳችን ከእግዚአብሔር ፣ ከቤተሰቡ ፣ ከሀገሩ ከመምህራኖቹ ተቀብሎ ፣ እንደ ጩልፊት ነጥቆ የሚሮጥ እንጂ ለምስጋና የሚመለስ አይደለም፡፡ ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል፡፡
ሰዎች እንዲያደርጉለት እንጂ እርሱ ለማንም በጎ ለማድረግ አይሻም፡፡ የሚያስፈልገውን ነገር ያደረጉለትን ሰዎች እንደሞኝ ያያል እንጂ ፍቅራቸውን እንኳን መረዳት አይሆንለትም፡፡ ሁሉንም ሰው ወላጆቹን እንኳን ሳይቀር ለጥቅሙ መሟላት ያፈላልጋል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟላለት ከመሰለው ምንም ከመሆን ፣ ከመጣመር ወደኋላ አይልም፡፡
ፍላጎቱ ጣዖት ሆኖበታል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟሉለት ከሆነ የራሱን ሰዎች እንኳን ይጠላል፡፡ አንዳንዴም ይተናኮላል፡፡ ያስተማረችውን አገሩን ለማገልገል አይፈልግም፡፡
ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት መቀመጥ እንጂ ተግዳሮትን በፍጹም አይፈልግም፡፡ ቀለል ያለውን በመምረጥ ሲጓዝ ቀለል ያለ መስሎ የሚገኝለት ሱስና ሀጢያት ሆኖ ይቀዘፋል፡፡
ትውልዳችን አብዛኛው ወላጆቹን ለመርዳት ፣ ለማመስገን እንኳን ፈቃደኛ አይደለም፡፡ እራሴን መቻሌ የመርዳት ያህል ነው ብሎ በአፉ ይናገራል፡፡ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ስጦታ ሲያጡ "ራሱን መቻሉ ጥሩ ነው" ብለው የሚጽናኑበትን ቃል እርሱ መኩሪያ አድርጎ መጠቀሙ ያሳፍራል፡፡
ገንዘብ ይበትናል እንጂ ጥሩ እርሻ ላይ አይዘራውም፡፡ ለአዝማሪና ለዝሙት ይበትነዋል፡፡ ደስታው ለራሱ ፣ መከራውን ለወላጆቹ መመደቡ በጣም አሳዛኝ አድርጎታል፡፡
ትውልዳችን ያስተማሩትን መምህራኑን የማያከብር ፣ ለራሱ መስፍን ሆኖ ንጉስ አልባ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ የሌሎች ውለታ መመለስ መቻል የሰውነት ክብር ነው፡፡ ውለታን ማሰብ እንኳ አለመፈለግ ግን ከሰውነት ተራ የሚያወጣ ነው፡፡ በፈረንጆች አገር የእናቶች ቀን የመምህራን ቀን እያሉ ፍቅርን በዓል ያደረጉት በትውልዱ ውለታ ቢስነት ነው፡፡
3) ራሱን የማያከብር ነው
ራስን መሆን ለአእምር ጤንነት ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ ራሱን ያልሆነም እራሱንም ያጣል፡፡ ሌሎች ሊያከብሩት የሚችሉት መጀመሪያ እራሳችንን ስናከብር ነው፡፡ ራቁታችንን በራሳችን ሸማ ብንሸፍነውም እንሰወራለን ፤ በሌሎችም ልብስ ግን ሐፍረታችን አይሸፈንም፡፡
ትውልዳችንን ስናየው ገና በአእምሮ ቅኝ ግዛት የተያዘ ፣ እራሱን የማያከብር ፣ ከራሱ መልካም የሌሎችን ክፉ እንደ መልካም የተቀበለ ትውልድ ነው፡፡ ስለዚህ የረጋ ማንነት የለውም፡፡ ሕይወቱን የሚመራው ዘመናዊነት እንጂ ቋሚ እውነት አይደለም ፤ በሳምንቱን ምርጥ ፊልም ሳምንቱን ይመራዋል፡፡ መረጃዎቹን ለመስማት ሳይሆን ለመሆን ስለሚፈልግ በብዙ ጠፍቷል፡፡ ስለ ሌሎች ሲያወራ ስለ ኳስ ተጫዋቾች ደሞዝ ሲጨቃጨቅ ይውላል፡፡ አንድ አባባል አለ፡-
"ትልልቅ ጭንቅላቶች ስለ አሳብ ያወራሉ ፣ መካከለኛ ጭንቅላቶቹ ስለ ሁኔታ ያወራሉ ፣ ትንንሽ ጭንቅላቶች ሁሌም ስለ ሰው ያወራሉ"
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የሰጠው ማንነት አለ፡፡ ያ ማንነት የተለያየ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር ሲመለከት የተለያየ ቀለምን የሚያሳይ ኪነ ጥበብ ነው፡፡ ራሳችንን ስንሆን እግዚአብሔር ሊያይ የፈለገውን ሥዕል እናሟላለን፡፡ ከሌሎች መማር አስፈላጊ ቢሆንም የምንቆምበት መሠረት ግን ያስፈልገናል፡፡ መሠረቱን ለቆ ዕቃ ላውርድ የሚል ዕቃውን ይዞ እንደሚወድቅ እንዲሁ ማንነቱን ጥሎ ከሌሎቹ ልማር የሚል ትምህርቱ ለመቆም አይረዳውም፡፡
ትውልዳችን እንደሌሎቹ መናገር ፣ እንደሌሎቹ መራመድ ፣ እንደሌልቹ መልበስ የሚያረካው የራሱ ነገር በጣም የሚያሳፍረው ነው፡፡
የገንዘብ ባሪያ ሆኖም ገንዘብን ለማግኘት ምንም መሆን የማይቆጨው ፣ ሰውነቱን አርክሶ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስደስተው ነው፡፡ ብዙ ወጣት ሴቶች ስናይ ገንዘብ ካዩ ምንም ዓይነት ክፉ ግብዣን እምቢ የማይሉ ፣ በባዕድ አገር ጭምር አገራቸውን የሚሰድቡ ክብር የለሽ ሆነዋል። ትውልዱን ራሱን አለማክበር ብቻ ሳይሆን ታላላቆቹን በመናቅ ትልቅ የሚሆን ይመስለዋል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

4) ከስህተቱ መማር አይፈልግም
የስህተት ማካካሻው ትምህርት ነው፡፡ ካለፈው መማር ያለ መበደል ያህል ነው፡፡ ስህተትን እንዳልተሰራ ማድረግ አይቻልም፡፡ የሰውነት ክብር ግን ከትላንቱ መማር ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ከትላንቱ የሚማር አይደለም፡፡ ሰው በሁለት ነገር ሊማር ይችላል፡፡
ከስህተት በፊት በመስማት ይማራል ÷ ከስህተት በኋላ ደግሞ ከውድቀት ይማራል፡፡ ትውልዳችን ግን ከስህተት በፊት ለመማር መስማት አይፈልግም፡፡ የቁም ነገር ሃሳብ ሲነሳበት እየሰለቸ ፣ ለፌዝ ተሰጥቶ ይታያል፡፡ ከውድቀት በኋላ ላለመማሩ ምክንያቱ ቶሎ ተስፋ መቁረጡና እግዚአብሔር የእንደገና አምላክ መሆኑን መዘንጋቱ ነው፡፡ ትውልዱ መስማት አይፈልግም፡፡
አክራሪነትን የወለደው ድንቁርና ነው፡፡ ማወቅ የሚመጣው ከመስማት ነው፡፡ አስተማሪዎቻችንን በመጀመሪያ ሰምተናቸዋል፡፡ ከዚያ የዕውቀት ባለቤት ሆነናል፡፡ የማወቅ መሰረቱ መስማት ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ማወቅና መፍትሔ ላይ መድረስ አይፈልግም፡፡ ያለበትን ህይወት እንደመጨረሻ መፍትሔ ተቀብሎታል። ችግሩ በፈጠረው አስተሳሰብ ውስጥ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ አስተሳሰቡ መለወጥ አለበት፡፡
በትውልዳችን ላይ የምናየው ትልቅ ችግር የራሱን አመለካከት አለመኖር የሌሎችን አመለካከት አለማክበር ነው፡፡ ብዙ የተዋቡ ቃላት በቃሉ ያጠናል ፣ የመናገር አምሮት ስላለበት ይናገራል፡፡ በተግባሩ ግን የተበላሸ ነው፡፡ በተግባር የሌለበት የቃላት ኑሮ በመጨረሻም ብቸኛ ያደርጋል ፣ ተስፋ በመቁረጥም ወደ ሞት ያደርሳል፡፡ ስለዚህ ቃል ብቻ ከመሆን መዳን ያስፈልጋል፡፡
አሳባችንን ለመፈፀም በዋናነት የሚያስፈልገን ባለ አደራነት ወይም የቃል ኪዳን ልብ መሆኑን ማሰብ አለብን፡፡ ትውልዳችን ግን ዋናውን ነገር ገንዘብ ነው ብሎ ያስባል፡፡
ከበደ ሚካኤልም እንዲህ ብለዋል:-
"በዓለም አይገኝም ቢፈልጉ ዞሮ፣
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ"
5) ቦታውን ይለቃል
ትውልዳችን ተጓዥ ነው፡፡ አንድ ነገር ያልሆነ ከመሰለው ለዘወትር የማይሆን ነው ብሎ ስለሚያስብ እንደገና የመሞከር ትዕግስት የለውም፡፡ ከጓደኛው ጋር ቢጣላ ሌላ ጓደኛ ይፈልጋል እንጂ ከዚህ ውስጥ የምማረው ትምህርት ፣ ክፉ ከመሰለው ነገር ውስጥ የሚወጣው መልካም ነገር ምንድን ነው?
ለማለት ፍላጎትም ብስለትም የለውም፡፡
ተጓዥ በመሆኑም ሃይማኖቱን ሳይቀር ሲለዋውጥ ይኖራል፡፡ የአዲስ ሃይማኖት አድናቂ ሆኖ ዘመኑን በቅልውጥና ይጨርሳል፡፡ ኑሮው ሁሉ ወጥ ቀማሽነት እየሆነ ፣ በሰማበት ጣዱኝ እያለ የሚንከራተት ይሆናል፡፡ መሠረት ስለ ሌለው ሁሉንም ነገር የሚሰማው ቦታውን ለቅቆ ነው፡፡ ስለዝሙት ሲያነብ ማመንዘር ይፈልጋል ፤ ስለ ክህደት ሲያነብ ክዶ ይሰነብታል ፤ የቤተክርስቲያን ጉባኤ ሲሰማ አማኝ ይሆናል፡፡ አድራሻ አጥቶ የሚንከራተት ትውልድ እያስተዋልን ነው፡፡
ይህን የምጽፈው ትውልዱን በሙሉ ለመኮነን አይደለም፡፡ ችግሩን ማወቅ በራሱ ግማሽ መፍትሔ መሆኑን በማመን ነው፡፡ በጦር ሜዳ ቦታን አለመልቀቅ ለድል ያበቃል፡፡ ማፈግፈግ ግዛትን ለጠላት በፍቃድ ራስን አሳልፎ እንደ መስጠት ነው፡፡
ትውልዳችን በብዙ መከራዎች የታጀበ ፣ የጀመረውን ነገር ለመፈጸም እልህ የሚያንሰው ነው፡፡ እቅዱ ስለሚበዛም ውጤቱ ያንሳል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን መንገድ መሪ አለማግኘቱ የበለጠ ጉዳት ነው፡፡
ሌሎች አምስት ይቀራሉ ይቀጥላል
ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ
እኔ ፣ አንተ ፣ አንቺ ፣ የእኛ ትውልድ በትንሽዬ
መጽሐፍ ያስገርማል፡፡
አስተያየታችሁን አድርሱኝ @jahABP ነኝ
ይቀጥላል🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂

Forwarded from MiKiiĩ {MK} Art Studio
የተለያዩ ዲዛይንና ኳሊቲ ህትመት ያላቸውን የሰርግ ካርዶችን ይዘዙን በፍጥነት እና በጥራት እናደርሳለን
ይደውሉ:- 0920888649 ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉንhttps://t.me/joinchat/AAAAAEhVLV9cI9xT3fq73g
ይደውሉ:- 0920888649 ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉንhttps://t.me/joinchat/AAAAAEhVLV9cI9xT3fq73g
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ሌሎች አምስቱን እንቀጥላለን......
እንዲህ ይላል "ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡
የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡ እያለ ይቀጥላል......ነገ እንቀጥለዋለን
መነበብ አለበት
ነገ ጠብቁኘ🏃♂🏃♂
አሁንም አስተያየታችሁ አይለየኘ @jahABP

6) ሁሉንም ልሞክር ይላል
ትውልዳችን በአብዛኛው ስንመለከተው ክፉ ፣ ክፉ እንደሆነ የሚያውቀው ሲደርስበት ነው፡፡ እሳት ማቃጠሉን ለመረዳት እሳትን መንካት አያስፈልግም፡፡ እሳትን እንደሚያቃጥል ሲነግረን ተቀብለናል፡፡ የተቃጠሉ ሰዎችንም በማየት እሳትን መጠንቀቅ እንደሚገባን ተምረናል፡፡ ሁሉን በሕይወቴ ላረጋግጥ ፣ ሁሉን ቀምሼ ልወቅ ፣ ሁሉን ሞክሬ ልመለስ ማለት መንገዱን መሔጃ እንጂ መመለሻ የለውም፡፡
ሁሉን በዕድሜያችን ለማረጋገጥ ብንፈልግ ዕድሜያችንም አይበቃም፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልና የክፍያ ትምህርት ልዩነት አላቸው፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልያገኘ ሰው ትምህርቱን በደስታ የሚማር ሲሆን በክፍያ የሚማረው ግን የሚከፍለውን ለማግኘት የሚጥር ነው፡፡ እግዚግብሔር በቃሉ አማካኘነት ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥቶናል፡፡ ትዕዛዙን በመፈፀም በነፃ እንማራለን፡፡
እምቢ ካልን ግን በዋጋ እንማራለን፡፡
በዋጋ መማር በስህተት ፣ በውድቀት መማር በመሆኑ ከባድ ነው፡፡
ትውልዳችን ስናይ ከጥፋት መንገዱ በምክር መቆም አይፈልግም፡፡ ፍሬኑ እንደተበጠሰበት መኪና ሲጋጭ ወይም ሲገለበጥ ለመቆም የሚነጉድ ነው፡፡ በወኅኒ ቤት የሚማቅቁ ፣ በበሽታ የተጎሳቆሉ ብዙ ወጣቶችን ስናይ ምክርን በመናቅ በግትርነት የገብበት ነው፡፡
7) ደፋር ነው፡፡
ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡
የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡
ከእኔ የተሻሉ ሰዎች አሉ ብሎ አይቀበልም፡፡ እነ እገሌ ያርሙኘ ለማለት ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በቀዳዳ ያየውን በሰማይ መስክ ላይ እንደታየው አድርጎ ያወራል፡፡ የሞቀ አፍ እንጂ የሞቀ እውነት የለውም፡፡ ትውልዳችን ለመስረቅ ፣ ለመግደል ፣ ራሱን ለማጥፋት ደፋር ነው፡፡ የሰውነቱን ክብር ንቋል፡፡ ሁሉንም አድርጎ ለመደሰት ይፈልጋል፡፡
ያልታየውን እንደታየው አድርጎ የሚተርክ ባለ ራዕይ መሳይ ፣ ያልተሰማውን እንደተሰማው አድርጎ የሚያወራ ሩህሩህ መሳይ ፣ እደርስላችኀለሁ እያለ በተቀመጠበት የሚፎክር ታዳጊ መሳይ ነው፡፡ የሚናገረውን ቃል የማይረዳ ጥሬ ቃል ይዞ የሚሮጥ ፈ ተግዳሮት የሚያደናግር ፣ አፍ እንጂ ጆሮ የሌለው እንደ አመንዝራ በቁንጅናው በርን ሁሉ ለማስከፈት የሚሻ ደፋር ነው፡፡
ቋንቋን እውቀት አድርገው የሚኖሩ ብዙዎችን እየወለድን ነው፡፡
ብዙ አስተዋይ ሰዎች በራቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል፡፡ ሰሚ ያጡ ሊቃውንት እንደ አላዋቂ ዱዳ ሆነዋል፡፡ ትልቅ ድንቁርና አለመማር ሳይሆን መማር አለመፈለግ ነው፡፡
አላዋቂነትን እንደ እውቀት በመቁጠር መንጎማለል ነው፡፡ ለማያፍሩ የሚያፍሩ ፣ ለማይፈሩ የሚፈሩ ብዙ አስተዋዮች ይህንን የሚቸኩል ዘመን ጥግ ይዘው እያዩት ነው፡፡
የዚህ ሁሉ ችግር ትውልዱ ለዕድገቴ ሌሎች ያስፈልጉኛል ፣ ለዕውቀቴ ስፋት መጠየቅ ያሻኛል ብሎ አለ ማሰቡ ነው፡፡ የዚህ ትውልድ አባላትም የቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የግዛት አስተዳዳሪዎች እየሆኑ ነውና ችግሩ አሳሳቢ ነው፡፡
8) በምኞት የሰከረ ነው
ትውልዳችን አብዛኛው በምኞት የሰከረ ነው፡፡
ትውልዳችን የምኞት እሳት አንድዶ የሚሞቅ ፣ ትንሽ ፈገግ እያለ ከራሱ ጋር የሚያወጋ ፣ ተግባር የሌለበት ምኞቱ በኩራት የሚናገር ፣ ባልተጨበጠ ነገር ከሰው የሚጣላ ፣ ምኞቱ እየራቀ ሲመጣ ደግሞ ቀቶሎ የሚረበሽ ፣ ተስፋ ለመቁረጥም የሚዳረግ ነው፡፡
ሰው በብዙ ነገሮች ሊያብድ ይችላል፡፡ በቁጣ ያብዳል ፣ በምኞት ያብዳል፡፡ የዕብደት አይነቱ ብዙ ነው፡፡ ሔዋን በምኞት አበደች፡፡ ስለዚህ ያላትን ብዙ ሳይሆን የሌላትን ትንሽ ነገር ነገር መፈለግ ጀመረች፡፡ ውጤቱ ግን የቆጡን አውርድ ብላ እንደሚባለው ተረት ሆነባት፡፡ ትውልዳችን በሰው እጅ ያለው የሚያምረው ፣ የራሱን የማይወድ ፣ በተሰጠው የማይረካ ነው፡፡
ብዙ ትውልዳችን በምኞት አብዷል፡፡ ይህንን ባደርግ ይህ ቢደረግልኘ ፣ ይህ ቢሆንልኘ በሚል መጎምጀዠት ተይዛል፡፡ በሕይወቱ አንድ ትልቅ ነገር ለማድረግ ይመኛል፡፡ በሕይወት ላይ ግን አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ነገር ማድረግ አይቻልም፡፡ በዙሪያችን የከበበን ትንንሽ ነገር ነው፡፡ በዕየለቱ ትንንሽ ጉዳዮችን ስንፈፅም ትልልቅ ተግባር ይሆናሉ፡፡ መመኘት ክፉ አይደለም፡፡ ምኞት ብቻ ግን ክፉ ነው፡፡ ያልሆኑትን ነገሮች እንደሆኑ አድርጎ መጣላት ከትውልዳችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡
የተዘረጋን ድልድይን መፈለግ ሳይሆን ድልድይን መዘርጋት ፣ ድልድይ መሆን ይገባል፡፡ ትውልዳችን ላይ ግን ያንን አናይም፡፡
9) ራስ ወዳድ ነው
ትውልዳችን በአብዛኛው በዓለም ያለው እርሱ ብቻ ሆኖ የሚታየው ፣ ሁሉንም ሰው ለእርሱ እንዲኖርለት የሚፈልግ ፣ መስዋት መክፈል የማይወድ ፣ እኔን ብቻ ይድላኘ የሚል ራስ ወዳድ ነው፡፡ ራስወዳድነት ዘውድ ጭኖ እየገዛን ነው፡፡
"ከራስ በላይ ንፋስ"እንደሚባለው ለራስ ወዳዶች ከበላያቸው ነፋስ እንጂ እግዚአብሔር መኖሩን የማያምኑ ናቸው፡፡
ራስወዳድ ትውልድ ለክህደት ቅርብ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ለራስ ወዳድነት ፣ በር ዘግቶ ለመኖር ምቹ ሆኗል፡፡ ሁሉም ሰው የራሱ የግል ስልክ ፣ የራሱ የኢሜል አድራሻ ፣ የኣሱ መኖሪያ ቤት...እንዲኖረው የሚጥር ነው፡፡ ስለዚህ ትውልዳችን የእኛ ለሚል ነገር ደስታ የለውም ፣ የእኔ ለሚል ነገር የተሰጠ ነው፡፡
ትውልዳችን ምን አገባኘ ማለት የሚወድ ፣ እኔን ካልነካኘ የፈለገው ነገር ይሁን የሚል ፣ ጓደኛውንም እንደ ባላንጣው የሚያይ ትውልድ ነው፡፡ ራስ ወዳድነት ሌላውን ሰው እንዳናይ ያደርገናል ፣ የጊዜያዊ የፍቅርና የጊዜያዊ ልስላሴ ባለቤቶች ያደርገናል፡፡ ጥቅማችን እስኪሟላ አፍቃሪ መሳይ እንድንሆን ፣ የምንሻውን እስክናገኘ በሰው ፊት ለፊት ያለማቋረጥ እንድንቆም ፣ ጥቅማችን ከተሟላ በኀላ ጀርባችንን እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ራስ ወዳድነት ይሉኘታን እንኳን የሚያሳጣ ፣ የጥቅም አምልኮ ነው፡፡
ራስ ወዳድ እግዚአብሔር ማምለክና ባለ ራዕይ መሆን አይችልም፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇