Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

መስመር ማሳጠር

(በተረት ላሰላስል)
የአስፓልት ላይ መስመሮችን የመቀባት ስራ ያገኘ ሰው በመጀመሪያው ቀን 9 ኪ.ሜ ቀባ፡፡
ፎርማኑም ተደሰተ፡፡
በሁለትና በሶስተኛው ቀን 3 ኪ.ሜ ብቻ ቀባ፡፡
ፎርማኑ በጥቂቱ አዘነ፡፡

በአራተኛው ቀን ግማሽ ኪሎ ሜትር ብቻ ነበር የቀባው፡፡ ይህን ጊዜ በቀቢው ተግባር የተበሳጨው ፎርማን እንዲህ ሊሆን የቻልንበት ምክንያት እንደዲያስረዳው ቀለም ቀቢውን ጠየቀ፡፡

የቀለም ቀቢው መልስ ከዚህ በታች ይነበባል፡-

"ሌሎች ያስጀመሩትንጠማድመቅ ቀላል ነው፡፡ በመጀመሪያው ቀን ሌሎች አስምረው የቀቡትን አደመቅኩ እንጂ አዲስ መስመር ማስመር አይጠበቅብኘም ነበር፡፡ በሁለተኛው ቀንም ያው ነበር፡፡ አንዳንድ የቀድሞ መስመሮች ሙሉ በሙሉ መጥፋታቸው እንቅፋት ሆነውብኘ እያሰመርኩ በመቀባቴ በእርግጥ ዘግይቻለሁ፡፡

አሁን እየቀባሁ ያለሁት ግን ሙሉ በሙሉ አዲስ መስመር እያሰመርኩ ጭምር ነው፡፡ ወደፊት ይህን ተከትለው በፍጥነት ያደምቁ ዘንድ መሰረቱን እየጣልኩ እንደሆነ ግን አምናለሁ፡፡"

መስመር ማስመር ይቀጥላል.....

"ሳይነኩ ማሳጠር"
ውክልና (ሲምቦል) ሃሳብን የማስተላለፊያ አንዱ መንገድ ነው፡፡
"መስመር" የማንነት መለያ ነው፡፡
ስራ ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ሁሉም የራሱ መስመር አለው፡፡
ለምድራችን ጠቃሚ ስራ አበርክተው ያለፉትም ሆነ በእኩይ ምግባራቸውን የሚነሱት ሰዎች የራሳቸውን መስመር አስምረዋል፡፡

አብዛኞች ግን ሌላው የሰመረውን በማጥፋት ተጠምደው ይጠፋሉ፡፡
የራሳቸውን መስመር ይስታሉ፡፡

ነገሩን በምሳሌ እናስደግፈው....

መምህሩ የተማሪዎቻቸውን ግንዛቤ ለመገምገም ጥያቄ ያዘጋጃሉ፡፡
ጥያቄው የመስመር ጥያቄ ነበር፡፡
አንድ ረጅም መስመር አስምረው ሲያበቁ ፡-

ይህንን መስመር ምንም ሳትነኩ አሳጥሩት ሲሉ አዘዙ፡፡

"#ሳይነኩ_ማሳጠር" ታላቅ ብቃት ነው፡፡

ከሌሎች ገዝፈው ለመታየት የተሰመረውን የማጥፋት አማራጭ ለሚመስላቸው ግን ቀላል፡፡
ጥያቄው ኢጎ ወለድ እሳቤን ይነቅፋል፡፡
ምክንያቱም ፣ የተሰመረውን ማጥፋት መስመሩን አያሳጥረውም፡፡
አጥፊውን እንጂ፡፡
መምህሩ ለጠየቁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት አንዱ ጎበዝ ተማሪ ተነሳ፡፡
መምህሩ ካሰመሩት ጎን ሌላ ረዥም መስመር አሰመረ፡፡
በእርግጥም የመጀመሪያው መስመር ከሁለተኛው መስመር ያጠረ ነበር፡፡

በትክክልም መምህሩ ሊያስተምሩተ የፈለጉት ይህን ነበር፡፡
ሌላውን ለማሳጠር ረጅም መስመር ከጎኑ ሊኖር የገሸድ ይላል፡፡ ፉክክር በበዛበት ዓለማችን ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ነው፡፡
ጥቂቶች ሌላውን ሳይነኩ የራሳቸውን መስመር ያሰምራሉ፡፡ ሌሎች ያሰመሩትን ረጅም መስመር አጭር የሚያደርግ ረዥም መስመር፡፡

ሌላው ያሰመረው ሳይነኩ ያሳጥራሉ፡፡

አያሌዎች ግን የሌሎችን መስመር ለማሳጠር ይተጋሉ፡፡
አለማችን ሌላው አስምሮ ያለፈውን መስመር አጥፍተው የራሳቸውን መስመር ለማርዘም በሚጥሩ አጥፊዎች ተሞልታለች፡፡

የድንክ ግንዛቤ አጭሩን መስመር አርዝሞ ያሳያል፡፡
የመከነ ግንዛቤ ውጤት ፣ የራስን መስመር ከማስመር ይልቅ ሌላው ያሰመረውን አጥፍቶ ማሳጠርን ያስመርጣል፡፡

ይህ ነው ሐቁ፡፡

እኮ ማነው ሌላው ያሰመረውን ሳይነካ የሚያሳጥር!?????

ኄኖክ ስጦታው

ሸገር ታይምስ መፅሔት ግንጣይ ገፅ
ቅፅ 01 ቁ 21 ታህሳስ 2010ዓ.ም

የሌሎችን ሳትነካ የራስህን አርዝመህ አስምር ወዳጄ፡፡
አብሶ ቦለቲከኞቻችን እባካችሁንንንንን የራሳችሁን መልካም ነገር ብቻ እየፃፋችሁ የሌሎችን አሳጥሩ እንጂ በክፋት ከሌሎች አትባሱብን ኧረ መኖር እንፈልጋለን ኧረ የሌሎች መኖርም ነው የኛ መኖር ይቺ ሀገር ያለሰው ምንድነች?? ሁሉን አጥፍተን እንችለዋለን??

ለእኛ እንጂ ለኔ የት ያደርሰናል😔😢

@jahABP ነኘ ቀን ተመኘሁ😔😔🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ሰላም አደራችሁ😍

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
አውታር አፕልኬሽንን ከፕሌይስቶር ዳውንሎድ ታደርጋለህ የታመነ ነው.......ሀይሌ ሩትስን ሙሉ አልበም ስልክህ ላይ ትጭናለህ ከዛ ቀንህን ማሳመር ነው፡፡
ግጥም ዜማ ቅንብር👏👏 .........

የታመነ ነው ይለናል መታሰቢያነቱ ለመዝሙረኛው ለታላቁ ኤልያስ መልካ ነው፡፡

ስጋብዛችሁ በደስታ ነው፡፡
😍😍😘

ሳይነግረው ፊት ለፊት ሸነጋግሎት
እያየው ሲያጠፋ እነዳለየ አልፎት
ከማያተርፍ ወዳጅ መስሎ መልካም
ይበልጣል የገሳጭ ቃል ባይደላም

የታመነ ነው😍

ሰኞን እንዲህ ጀመርናት🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

አውታር የኔ የአንተ የአንቺ የሁላችንም ምርጫ
አውታርን በስልካችን ላይ በመጫን ለሙዚቃ ያለንን ክብር እናሳይ እላለሁ መልካም ጊዜ😍🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" ታላቅ ሁነህ

ታላቅ ሁነህ ኖረህ ታናሽ ሁነህ እንዳትሞት ተጠንቀቅ በመሞቻህ ሰዓት የምትናገሰው የድል ድምፅ እንዲኖርህ ማንንም አትበድል፡፡
ስስታም መንቻካና አፈ ቅቤ ምቀኘነት ደም የሰበረ ዓይን ፣ ሐሜተኛነት ያሞጠሞጠ አፍ ያመጣሉና ተጠንቀቅ፡፡

የሌሎችን ማህደር ስትፈትሽ ያንተም መዝገብ እንዲገለጥ ትምህርት እየሰጠህ መሆኑን እወቅ፡፡
ተሳስተው የበደሉህን አልመው ከበደሉህ ለይ፡፡

በችግርህ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ
★ በዓላማህ የሚዋጉህ
★ የሚወጉህን ሰዎች ፈርተው የሚዋጉህና
★ አንተን ያዳኑ መስሏቸው የሚዋጉህ ናቸው፡፡

እርግጠኛ ጠላት ካልታወቀ ወዳጅ ይሻላል፡፡
ጥንቃቄ ያስተምርሃል፡፡
ስትሞት መቀጠል ከፈለግህ መጽሐፍ ፃፍ፡፡

መፅሐፍ በሦስት አይነት መንጠድ ይፃፋል፡፡
በድንጋይ ፣ በብራና ፣ በወረቀት፡፡
በድንጋይ መስራት አገር መስራት ነው፡፡
በብራና መፅሐፍ ደግነት ነው፡፡
በወረቀት መፃፍ የእውቀት ምፅዋት ማድረግ ነው፡፡


መልካሞች እንደተቀባበለ መሳሪያ ፣ በጣት እንደሚተኮሱ ናቸው፡፡
ትንሽ ስታበረታታቸው ብዙ ይሰራሉ፡፡
እባክህ ሞተህ ኑር፡፡"

እርሱ መልካምነት ነው፡፡

@jahABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ
😍🙏😊
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እንኳን አደረሳችሁ መልካም ቀን

"ሰማዕቱ ለክርስትና ወግ አብቃን እንዳንተ ለሰማዕትነት ባንታደል"

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
የፍቅር ትንታኔ



ተብራርቶ ያላለቀ ትንታኔ ፍቅር ብቻ ነው ይለናል ቀጣዩ ፅሁፍ፡፡

🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" የፍቅር ትንታኔ

እንኳን ምድራዊ ሀብትና እውቀት ይቅርና ሰማያዊ ጸጋዎች ያለፍቅር ከባድ ናቸው፡፡
ፍቅርን ስትይዝ ሁሉንም ጸጋ ያዝክ ማለት ነው፡፡
የሃይማኖት ፍቅርና ጉልላት ፍቅር ነው፡፡
ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ባንተ ልብ አለ፡፡
አንተም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አለህ፡፡

ፍቅር ድል አለው፡፡ ስለፀጋ ስጦታዎች ብዙ ጭቅጭቅ አለ ስለሚበልጠው ጸጋ ስለፍቅር ግን ስብከት ጠፍቷል፡፡ ስለፈውስ ብዙዎች ይለምናሉ ነፍስን ስለሚፈውሰው ፍቅር ግን አይፀልዩም፡፡
ማንኛውመ መንፈሳዊ ነገር በእውቀት በእምነት በፍቅር ካልተደረገፈ ሀጢያት ነው፡፡

ትንፋሽ ድንገት የሚቋረጥ ሲመስልህ ፣ የልብህ ምቾት የቀዘቀዙ መስሎ ሲሰማህ ፣ ተስፋህ ጭልጥ ሲልብህ የምትድነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡
እንጨት በምስጥ ፣ እህል በነቀዝ ፣ ልብስ በብል ይበላል ፣ ሰውን ጥላቻ ይገዘግዘዋል፡፡
ሌሎች በኃይል እንዲሰሩ ሞተሩ ፍቅር ነው፡፡

ፍቅር ከሌለ ሰማዕትነት ሊኖር አይችልም፡፡
በየዕለቱ ሰማዕትነት ላይኖር ይችላል፡፡
በየዕለቱ መስዋዕትነት ግን አለ እርሱም ጥላቻን እንቢ ማለት ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ደረጃ ፣ በሁሉም ፀጋ ውስጥ በሁሉም ዘመን ደግሞም ለዘለዓለም የሚፈለግ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
በፍቅር የማይቃጠሉ ልቦች ወንድማቸውን ለመስቀል ይጨክናሉ፡፡

ቤተክርስቲያን የቆመችበቶ ምሶሶ ፍቅር ነው ፣ ያለፍቅር ትወድቃለች፡፡

ፍቅር ራሳችንን በሰው ውስጥ ሰዎችን በራሳችን ውስጥ የምናይበት መስታወት ነው፡፡
ፍቅር ያላቸው ሌሎችን የማስተካከል አቅም አላቸው፡፡
ፍቅር በቀላሎች ሰፈር ያላት ስያሜ ምስኪንነት ፍርሃት ነው፡፡
መንገዶችን ከመስራት ፍቅርን መገንባት ይቀድማል፡፡
የተሰሩት መንገዶች በጥላቻ ይዘጋሉ፡፡
ትልቁ ርዕዮተ አለም ፣ የማይከሽፍ መሳሪያ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ፍቅር ትልቁ ስጦታ ፣ ትልቁ መንገድ ፣ ትልቁ መሪ ነው፡፡

ዓይን ያለ ፍቅር ምን አገባኘ ይላል፡፡ ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ ምላስ ያለፍቅር ከወጣ ይሰብራል፡፡ እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል፡፡
እግር ያለ ፍቅር ከሔደ ድልድይ ያፈርሳል፡፡
ፍቅር የሌለው ሰማዕት ክርስቶስን አላወቀምና በከንቱ ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች እንደጎደለን ብንናገርም በዋናነት የጎደለንፍቅር ነው፡፡

ፍቅርበመጨረሻው ዘመን ይቀዘቅዛል እንጂ አይጠፋም፡፡
ያለፍቅር የተሰበኩ ነፍሰ ገዳይ ይሆናሉ፡፡ ለማፍቀር የልብ ፈቃድና የእግዚአብሔር ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ፍቅር በግልፅነት የምትከብር ናት ፍፁም የምትሆነውም ፍርሃትን ስታሸንፍ ነው፡፡

#ፍቅር_እራሷ_ጌጥ_ናትና_ጌጥ_አትፈልግም፡፡
#ፍቅር_ጽንፍ_የለሽ_ናትና_ዘረኘነት_አይስማማትም፡፡
#ተብራርቶ_ያላለቀ_ትንታኔ_ፍቅር_ብቻ_ነው፡፡
በፍቅር ያጌጡ በወርቅ ከተኝቆጠቆጡ ይበልጣሉ፡፡

ምኞት ዳርቻ ጥማትም እርካታ የሚያገኘው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ያለፍቅር የተዘረጉ ምፅዋቶች ከዱላ አይተናነሱም፡፡
#ኅሊናውን_አጉድለን_ሆዱን_የሞላንለት_ከሰጠነው_የሰረቅነው_ይበዛል፡፡

ፍቅር ሁሉም የሚሰጠው ምፅዋት ነው፡፡
ፍቅርን የማይሰጥ ድሃ የማይቀበል ሀብታምም የለም፡፡ ጎዶሎዎቾ መልካም የሚሆኑት በፍቅር ብቻ ነው፡፡
ሩጫህን የጀመርከው ያለ ጭብጨባ ብቻህን መሮጥ የጀመርህ ቀን ነው፡፡

#የታየህን_እይ_እንጂ_የሚያዩህን_አትይ_ትወድቃለህና፡፡"

የሆነ መፅሐፍ ሳነብ አገኘሁትና ላካፍላቹ ብዬ አሰብኩኘና እንዲህ ለንባብ እንዲመች አድርጌ ቀነጨብኩት፡፡

መፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡

በፍቅር እንኑር እላለሁ😍😍😍

@jahABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ
😍🙏😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

አቤቱ ከመቅደስህ አታርቀን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እውነተኛ ግርዶሽ🤔🤔🤔

🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" እውነተኛ ግርዶሽ

ሐሰተኛ ኑር ያደክማል ፣ እውነተኛ ኑሮ ከራስ ጋር ሰላም ያደርጋል፡፡ እውነተኛ ኑሮ የምትኖረው እግዚአብሔር እንዳለና ስራህን እንደሚመዝን ስታምን ነው፡፡ ነፃነት ጨዋነት ከሌለው ተዘዋዋሪ ባርነት ነው፡፡ ስጋን ከሚገርፉ ገዢዎች ነጻ አውጥተን ነፍስን በሚገዙ አጋንት እጅ የወደቀን ትውልድ ካፈራን የምናሳዝን ነን፡፡
"ከእባብ ጉድጓድ አምልጦ ዘንዶ ጉድጓድ" እንዲሉ አበው፡፡

ዓላማ የሌለው ጉዞ መንከራተት ነው፡፡
በውስጥህ ያለው የሕሊና ሕግ ፣ በመፅሐፍ ያለው የእግዚአብሔር ሕግ በልብህና በተግባርህ *#እንድትገልጠው የተሰጡህ ናቸው፡፡
ስለእግዚአብሔር ለማወቅ በፈለግህ መጠን ወዳጅነትህ እየጨመረ ይመጣል፡፡

#አምላክ_ላይሆኑ_አምላክህን_ያሳጡህን_አትርሳቸው፡፡

ፍልስፍናዎች ፣ ርዕዮተ አለሞች ፣ የበላይ አለቆች ፣ የጦር መሳሪያዎች ፣ የሀብት ጅልቦች ፣ *#ዘረኘነት እነዚህ ሁሉ አምላክ ላይሆኑ ስንቱን አምላክ እንዳሳጡት እወቅ፡፡
#ሰው_ላይሆኑ_ሰው_ያሳጡህንም_አትርሳ፡፡
አለመርሳት ማለት ማለትም ለቀጣዩ ተጠንቀቅ ማለት ነው፡፡

ኅሊናህን ቸል ብለህ ሰዎችን ወዳጅ ለማድረግ አታስብ፡፡ የጠፋ ማህበረሰብ የሚወለደው ከአሉታዊ ነፃነት ውስጥ ነው፡፡
አሉታዊ ነፃነት ልቅነት ነው፡፡ አዎንታዊ ነጻነትን ግን የመናገር ፣ የመኖር ፣ አሳብን የመግለጥ ፣ የወደዱትን ማመን ፣ የእኩልነት እግዚአብሔር የሰጠውን የፆታና የዕድሜ መብብ የሚያከብር ነው፡፡

#የተፈፀሙ_ነገሮች_የተጀመሩ_ነገሮች_ናቸውና
ለመጀመር ተነሳ፡፡ የተጀመሩት ይፈፀማሉና ፍፄሜውን አትፍራ፡፡ ቅዱስ መልዓክ ላንተ ያስፈልግኃል ለደካማውም ሰው አንተ ታስፈልገዋለህ፡፡ ከቆመው መልዓክ የወደቀውን ሰው ሊፈልግ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡
የአምላክ እናትን ባሰብክ ጊዜ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን የላቀ ክብር ትረዳለህ፡፡

የህሊናን ድምፅ ጠንቅቀህ የምትመሰርተው ወዳጅነት ራስን ማጥፋት ነው፡፡ በነፍስህ ዋስትና የሌለበት ሀብት በሬሳ አጠገብ እንደተቀመጠ ጥሩ መዓዛ ያለው ምግብ ነው፡፡ ተገፋን ብለው ወደ አንተ ሚመጡ ሰዎች ምን ሰርተው ወደአንተ እንደ መጡ አጥና፡፡ ጅብ የማያቁት አገር ሂዶ ቁርበት አንጥፋልኘ ይላል" ይባላል፡፡ ከሁሉ ፀያፍ ነገር ሃይማኖትለዋጭነት እንደሆነ እወቅ፡፡

እግዚአብሔር በድንጋይ ጽላት ላይ ቃሉን ቀርጾ የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው መሆኑን ሊያስተምረን ነው፡፡ ስነምግባር ስታጣ የምታሳድበው እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን አሳዳጊዎችንህም ነው፡፡

#የመጨረሻው_ድህነት_እግዚአብሔርን_ማጣት ነው፡፡

#የመጨረሻ_ብልጥግናም_እግዚአብሔርን_ማግኘት_ነው፡፡

እንደገና የቀረ የለምና አትመካ ፣ እንደ መሸ የቀረ ሌሊት የለምና አትሸማቀቅ፡፡
የምትችለውን ማድረግ የማትችለውን ለማድረግ መንደርደሪያ ነው፡፡
እውነተኛ የሀብት ውድድር በማጠራቅ ሳይሆን በመስጠት ከሆነ ደስታ አለው፡፡

#በእግዚአብሔር_መንግስት_ምን_ያህል_አጠቀምክ_ሳይሆን_ምንያህል_ሰጠህ_ትባላለህ፡፡

የማይሰጥ ባለጠጋ ድሃ ነው፡፡
ደሃ ሁለት አይነት ነው፡፡
የገንዘብና የቸርነት ድሃ፡፡
ከቸርነት ድህነት የገንዘብ ድህነት ይሻላል፡፡

ከባድ እስር ቤት በራስ አመለካከት መታጠር ነው፡፡
የሚያቆስለው ሰንሰለትም የመሰስትም እጅ ነው
#የጨለማም_ወህኒም_ማፍቀር አለመቻል ነው፡፡
ዓለም ማለት በጎሬህ መጠን በሰፈርህ ልክ ከመሰለህ ዘረኛ ሆነኃል ማለት ነው፡፡
ዘረኘነት ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት መግጠም ነው፡፡ ምክንያቱም ስለ ዘሩ የምትጠላው ያ ሰው ከዚያ ዘር ለመውለድ ያቀረበው አሳብ የለምና፡፡

#እውነተኛ_እውርነት_ፀሀይን_ሳይሆን_የፀሀይን_ጌታ_ማየት_አለመቻል_ነው፡፡"

መልካም ምሽት
@jahABP ነኘ 😊😍🙏

መልካምነት ደግነት በተግባር እንግለፃቸው

ከትላንትናው መፅሐፍ ላይ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት

*# ምልክት ያለባቸውን እኔ እንደጨመርኩት ልብ ይሏል

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
በጠዋት ደውሎ ከእንቅልፍህ ቀስቅሶ ዛሬ ማርያም አደል አራት ኪሎ ቅድስተማርያም እንሒድ በዛውም መፅሐፍ እንገዛለን ተነስ ብሎህ ሔደህ ተሳልመህ ፀሎትህን አድርሰህ
በረከቱን አፍሰህ...

ወደ መፅሐፍት ቤት🚶‍♂🚶‍♂

ፊት ለፊት ከከበቡን መፅሐፍቶች እየጠቆመ ምረጥ ዛሬ አንድ መፅሐፍ ስጦታ እሰጥሃሐለሁ ብሎ አስመርጦህ እሱን የወደድከውን ስጦታ የሚሰጥ ቁርስ ሳትበላም አትሔድም ብሎ ፅድት ያለች ቁርስ ጨምርበት የሚል ወንድም ካለህ አንተ አለም ላይ በእውነት እልሃለሁ በጣም እድለኛው ሰው ነህ፡፡

የመፅሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ እንዲህ ይላል :-

"መልካም ብትሰራ ሺዝምታ ነው፡፡
አንድ ክፉ ስትሰራ ሺህ ጫጫ ነው፡፡
ተራራ የሚያህለው መለስተኛ መልካምነትህ አይታይም ጉድፍ የምታህል ስተትህ ግን ትጎላለች፡፡
ስትመሰገን አብረው ያላመሰገኑ ስትረገም ሰልፉን ይመራሉ፡፡
በጎ ስትሆንላቸው ምስጋና በልብ ነው ያሉ ስታስቀይማቸው ግን ርግማን በአዋጅ ነው ይላሉ፡፡

ሕግ የሌለ ይመስላል በጎ ስትሰራ ድሞፁን ያጠፋል ትንሽ የበደልህ ቀን ግን ፖሊስ ይልክብሃል ከሳሽ ምስክር ዐቃቤ ህግ ያሰናዳብሃል፡፡

ሕጋውያንም እንደ ሕጉ ናቸው መልካም ስትሰራ አይሸልሙህም ባህሪያቸው አይደለምና ክፉ ስትሰራ ግን ይኮንኑሃል፡፡ ሕጋውያን ናቸውና፡፡"

ወንድሜ በጣም አመሰግናለሁ ይህ ለኔ ትልቅ ነገር ነውና ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥልኘ፡፡
😍🙏😊
እኔ እሷ እና ጥቅምት

ይቺህን ፅሁፍ ተጋበዙልኘማ
AB PHOTOGRAPHY

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
የበዕውቀቱ ስዩም አዳምኤል የግጥም መድብል ከትንሹ ወንድሜ ላነበው ተቀብየው ነበር፡፡

ሳሚሻ ደግሞ ከእጄ ላይ ተቀብሎ እኔ ካላነበብኩት ብሎ ወሰደብኘ ከዛ ዛሬ መለሰልኘ ዝም ብዬ ስገልጠው ይህ ግጥም ላይ ወጣ

ከዛ እርዕሱ ፈገግ ስላስባለኘ ሳሚሻ ይህን ላንብብልህ ብዬው ልክ ማንበብ ስጀምር አብሮኘ ማለት ጀመረ ገርሞኘ ማንበቤን አቆምኩት

አብያ እኔም በጣም የተመቸኘ ግጥም ነው፡፡
ደጋግሜ ስላለበብኩት ለዛ ነው ስትገልጠው እሱ ጋር የወጣልህ አለኘ፡፡

እኔም ጀባ ልላችሁ ወደድኩኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GTAPHIC DESIGN

እኔ ምፈልገው

እውነት መናገር ፣ እኔ ምፈልገው
ካንቺ ጋር መጋባት
ይህ ሐምሌ ፊቴን ፣ ደጋግሞ ማራባት
ከወፎች ጋር መንቃት ፣ በጊዜ ቤት መግባት፡፡

"ምን ድሃ ቢሆን ፣ ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል አባት"
ለሚል መናኛ ጥቅስ ፣ ኑሮዬ የማይመጥን፡፡

ሲሻኘ በየባንኩ ፣ ስፈልግ በሳጥን
የተረፈኘ ገንዘብ
ደጃፍ ላይ ቁጭ ብየ ፣ ድሀ የምታዘብ
ተምሳሌቴነቴን ፣ የሚዳረስ በለም
ሞዴል አባወራ ፣ ተብየ ምሸለም
አገሬን ማስከበር
ህዝቤን ማስተባበር
የልጅ ልጅ አፍርቼ
በመቶ አመት ሙቼ
ሥላሴ መቀበር
ምኞቴ ይህ ነበር፡፡

እውነት ለመናገር ፣ እኔ ምፈልገው
ወንደላጤ ኑሮ
በሴቶች መታጀብ ፣ ልክ እንደ አውራ ዶሮ
ጊዜ እሎኘ ቢሔድ ፣ ቀን ቢገሰግስም
መላው ጭንቅላቴን ፣ ገብስማ ቢለብስም
ላቅማዳም ነው እንጂ ፣ ለትዳር አልደርስም፡፡

ደሞ
ዘር መዝራት እርሜ ነው ፣ ደጋግሜ ባርስም
ባለመኖር ላሉት ፣ ሥቃይ አላወርስም
ቢፈልግ ሌላው ህዝብ
ይፈልፍል እንደዝንብ
ይባዛ እንደጉንዳይ
አገር ስራው ያውጣው! ሰውዬው የራሱ ጉዳይ!!
የራሴ ፈጣሪ ፣ ነኘ የራሴ ገዳይ!!

እኔ ምፈልገው.....
እኔ ምፈልገው.....
ምንድር ነው? ምንድነው?
____

ገንዘብ ቢመዘበር ፣ በገንዘብ ይተካል
እድሜ ለጉልበትሽ ፣ በላቡ ለሚያድር
በውርስ በስጦታ ፣ ግፋ ቢል በብድር፡፡

በቆጠብነው ቁጥር
ጊዜ ነው የሚያጥር
እድሜ ነው የሚያልቀው
የምንፈልገውን በቅጡ ሳናውቀው፡፡

አዳምኤል የግጥም መድብል
በእውቀቱ ስዩም

እኔ ደግሞ ምፈልገው......
ጠዋት ደስ ብሎኘ መነሳትን ነው፡፡ ጠዋትህ ካላማረ ቀኑ እንደጨፈገገ ነውና፡፡
ጠዋት ስነሳ የሰው ልጅ በግፍ ተጨፈጨፈ፡የሚባል ዜና መስማት አልፈልግም
እኔ ምፈልገው ህዝቤ ተቻችሎ ሲኖር ማየት ነው፡፡ በዘሩ በሀይማኖቱ እየተመረጠ ምትጨፈጨፍባት ሀገር አልሻም፡፡
ኧረ ነገአችንን አትቀሙን ነገ ብዙ ህልሞች አሉን

ሰው ነንና የሞቱት ሰዎች ህመም ይሰማናል
ያማል ያማል ያማል በጣም ያማል፡፡
ነገ እኛ እንዴት ነው ተምረን እንመረቃለን ምንለው እንዴት ነው ስራስ ለመያዝ ምናስበው፡፡

ነገስ እንዴት ነው ትዳር ስለመመስረት ወጉን ለማየትስ ልጅን መውለድ እንዴት ብለን ነው ምናስበው፡፡

እፈራለሁ ማርያምን ፈሪ ሆኛለሁ ነገስ እኔ አለመሆኔ አንተ አለመሆንህ አንቺ አለመሆንሽ በምን እንርጠኛ ነን??
ተስፋ አስቆራጭ ኑሮ😢😭😭

ነገስ የት ይሆን?? ነገስ ተረኛ ማን ይሆን?
ሁሉም ይህንን ነገር ለምን አያወግዘውም??

እኔ ምፈልገው ነገ ከእንቅልፌ ስነሳ

እኔ ምፈልገው እኔ ምፈልገው......
እኔ ምፈልገው.......
እኔ ምፈልገው.........

@jajABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ

#አቤቱ_ነገ_ተረኛ_አታድርገን፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPHD @ABPGD
"ከዚህ በፊት አይቻት የማላውቃትን ይቺህን ቀን ስለሰጠኸኘ አመሰግንሃለሁ፡፡

የቤቴ በረከት ፣ የጓዳዬ ረድኤት ፣ የአቋሜ ፅናት ፣ የእርጅናዬ ብርታት ሀይለኛው ጌታዬ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሆይ አመሰግንሃለሁ በደመናት ግሩም ነህ በሰማያት ከፍ ያልህ ነህ በመንገድህ ሁሉም ምስጉን ነህ፡፡
የአማልክት አምላክ ፍፁን አሸናፊ ነህ፡፡

አለሙ ሁሉ አንድ ጊዜ አዳንከው፡፡
እኔን ግን ብዙ ጊዜ አዳንከኘ፡፡
የራቅኸኘ ሰዓት ብቻዬን የለቀቅኸኘ ሰዓት የለም፡፡
የዓይንህ ማረፊያ አድርገኸኛል በእኔም መኖር ደስ ይልሀልና፡፡
የቅዱስነት ክብር ላንተ ይሁን አሜን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏"

እንኳን አደረሳችሁ
AB PHOTOGRAPHY

ስራ ላይ ሆነህ ጥበብ ስትፈታተንህ

ለጂን የተቆረጠ ሎሚ😳😳😳

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እሷ እኔ እና ጥቅምት


ልፅፈው ተገደድኩ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂ይሁና
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ጥቅምት_ነው_በጣም_ይበርዳል

ማርያምን ይበርዳል.....


እዛች አሁንም ድረስ በፍቅር በምኖዳት ቦታ ላይ ሁሌም ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን፡፡


የዛኔ ግን ብቻዬን ቁጭ ብያለሁ፡፡
ከሱ ጋር ደስ የሚል ወግ ይዣለሁ በተብታባ አፎቹ ቆንጅዬ ጨዋታን ያጫውተኛል፡፡
እኔም ደስ እያለኘ ፈገግም እያልኩኘ አዳምጣለሁ፡፡

ከዛ ድንገት ስሜ ተጠራ
በመታወቂያ ስሜ ሳይሆን በቁልምጫ ስሜ ብዙ ሰው በማይጠራኘ መጠሪያዬ፡፡
እኔም እሱም ዞር ዞር ብለን ሰው ፈለግን ማንም የለም ድጋሚ ተጠራሁ አሁንም ስናይ ማንም የለም፡፡

ከፊት ለፊት መኪኖች ጡሩንባቸውን እያንቧረቁ ሽው ሽው እያሉ ያልፋሉ እሷን አየኀት አላመንኩም ደግሜ እንዳላያት መኪኖች ከለሉኘ እንደምንም አየኀት እራሷ ነች ተገረምኩም ደነገጥኩም ጠፍታ ነበር ስፈልጋት እንዳላገኛት ሆና ጠፍታ ነበር ብዙ ጊዜ ፈልጊያት ነበር ግን ላገኛት አልቻልኩም ነበር፡፡
በእውነት ተገረምኩ..........

የትምህርትቤታቸውው ቲሸርት ለብሳ ረጅም ቀሚስ ዩኒፎርሟን በአንድ እጇ ይዛ ያን ማቀውን ከፍ የሚያደርጋትነ ጥቁር ቡትስ ጫማዋን ተጫምታ ቆማለች ልክ እንደተያየን እጇን ወደላየ አንስታ እያውለበለበች ሰላም አለችኘ ቆምኩኘ ፈገህ አልኩኘ እየተቻኮለች መጣች አቀፈችኘ አቀፍኳት ምን እንደሚሰማኘ አላቅም ንዴት ደስታ ግራ ተጋባሁ ግን ምንም አላልኳትም ንዴቴን ብናገረው ደስ ይለኘ ነበር ግን አልቻልኩም አለመናገርን መረጥኩ ለምን ስልክ አታነሺም ለምን ለምን ቴክስት አትመልሺም ለምን መልሰሽ አትደውይም? ብዙ ብዙ......ግን ዝምታን መረጥኩ ስላገኘኀት ደስ ብሎኘ ይሆን እኔንጃ አላውቅም፡፡

ብዙ ነገር አለች ግን ስለመጥፋቷ ምንም አላለችም ትምህርት ቤት ቀየርሽ አልኳት አው ይሻላል ባክህ....ጠንክሮ መማር ነው አለችኘ የግል ነው የገባችው......ቀጣይ ወደ ዩኒቨርስቲ ስለሆነም ይሆናል🤷‍♂

ከዛ ወደ ትምሮዋ ሸኘኀት ምን እንዳወራን አላቅም እሷ ብዙም አታወራም ሁሌም እንዲህ ነች ግራ ገብቶኘ ነበር ልፅፈው ማልችለው.....የመጀመሪያው ቀን እስከ ትምሮዋ ሸኘኀት በነጋታዎ እንደምነገናኘ ተስማምተን ተለያየን..........የሆነ የማላውቀው ባዶ ቦታ እንደቆመ ሰው ግራ ተገባሁ ከራሴ ጋር እያወራሁ ከሰዎች ጋር እየተጋጨሁ ተመለስኩ፡፡

ከኔ ይልቅ እሱ ተደስቶ ነበር............
" ጠፍታለች የለችም አላልከኘም እንዴ ወይስ አውቀህ ነው አለኘ ፈገግ እያለ😊😊"

በእውነት ወንድሜ ከስንት ጊዜ በኀላ እኔም ሳያት የመጀመሪያዬ ነው፡፡ እንደነከርኩህ ነው ጠፍታ ነበር እኔንም ገርሞኛል እመነኘ እኔም ግራ ገብቶኛል....አልኩት፡፡

"እና ምን አሰብክ ሲለኘ"

እስኪ ነገ እንገናኛለን ተባብለናል ሚሆነውን እናያለን አልኩት፡፡

አይመሽ የለም መሸ አይነጋም የለም ነጋም ነገ ያልኩት ዛሬ ሆነ ................🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂


እቀጥለው ይሆናል..................

@jahABP ነኘ የነገ ሰው ይበለን፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እማሆይ ሰንበትን በዝማሬ🤲🙏🙏

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD