Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.6K subscribers
15.4K photos
273 videos
96 files
778 links
Government Organization
Download Telegram
ዛሬ በኤልዶሬት፣ ኬንያ በተከበረው የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘትና ንግግር በማድረግ፤ ለሀገራቸው ነጻነት ለታገሉና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ያለኝን ታላቅ ክብር ገልጫለሁ። ለጀግንነታቸውና ትተውት ላለፉት ዐሻራ የላቀ ክብር አለኝ!

የኬንያ የጀግንነት እና የመስዋዕትነት ታሪክ፤ ከሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመከላከል በአንድነት ከቆሙበት ከኢትዮጵያ የአድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። እነዚህ የጋራ ታሪኮቻችን ነጻነት በስጦታ የተገኘ ሳይሆን በጀግንነት፣ በአንድነት እና በመስዋዕትነት የተረጋገጠ መሆኑን ያስገነዝቡናል።

ታሪካችን የተሳሰረ እንደመሆኑ ሁሉ የወደፊት እጣ ፈንታችንም እንዲሁ የተሳሰረ ሊሆን ይገባል። በመደመር መንፈስ፤ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለህዝቦቻችን ሰፊ እድሎችን እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር በንጹህ ሀይል፣ በመንገድ ትስስር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በንግድ ዘርፎች ያለንን ነባር ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ይኖርብናል።

ዛሬ ክብር ለተቸራቸው ጀግኖች ሁሉ፣ ላቅ ያለ አክብሮቴን አቀርባለሁ። መልካም የማሹጃ (የጀግኖች) ቀን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
❤15👍9
ዓመታዊውን ማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ክብረ በዓል ላይ በክብር እንግድነት የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በኤልዶሬት ቤተመንግስት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል!

Prime Minister Abiy Ahmed, who attended the annual Mashujaa Day celebrations as the guest of honour, has left his Green Legacy by participating in a tree-planting program at the Eldoret State House!
👍9❤4
በጥቂት አመታት በተሰራ ስራ የአየር ንብረትን በመቋቋም ለዓለም አርዓያ የሆነች ከተማ - አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ወደ አረንጓዴ፣ ዘላቂ እና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም ወደምትችል የወደፊት ከተማነት አስደናቂ ለውጦችን እያስመዘገበች ትገኛለች!

በቅርቡ በተደረገ ጥናት አልፋጂኦ (AlphaGeo) የዓለም አቀፍ ግምገማ መሠረት፣ አዲስ አበባ በዓለም ከሚገኙ 72 ዋና ዋና ከተሞች መካከል በአየር ንብረት ተቋቋሚነት በሁለተኛ ደረጃ መቀመጧ ይታወሳል። ይህም የከተማዋ ምቹ የጂኦግራፊ አቀማመጥና በአረንጓዴ ልማት በተሰሩ ስራዎች ከአየር ንብረት ስጋቶች ጋር የመላመድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ያሳያል።

በከተማ ኮሪደር ልማት፣ በወንዞች መልሶ ማልማት፣ በከተማ አረንጓዴ ልማትና በዘመናዊ መሠረተ ልማት ግንባታ አዲስ አበባ የልማት ዕቅዶችን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በማቀናጀት ለነዋሪዎቿ የተሻለ የኑሮ አካባቢን መፍጠር እንደሚቻል እያሳየች ነው።

ይህ ስኬት ለሌሎች ሀገራት እና ከተሞች ትልቅ መልዕክት አለው፤ ራዕይ ያለው አመራር፣ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንትና ለዘላቂ ልማት የፀና ቁርጠኝነት ሲኖር፣ ከተሞች ለአየር ንብረት የበለጠ ተቋቋሚ ሆነው የነዋሪዎቻቸውን ሕይወት ማሻሻል ይችላሉ። በአዲስ አበባ የታየው ለውጥም ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው።

አዲስ አበባ ለአረንጓዴና ዘላቂ የወደፊት ዕድል በጋራ ለመሥራት፣ ልምድ ለመለዋወጥና ፣ እህትማማች ከተሜነትን ለማጠናከር፥ የአየር ንብረት ባለሙያዎችን፣ ባለሀብቶችንና የልማት አጋሮችን በሞቀ ልብ ትቀበላለች።

አዲስ አበባ እየተለወጠች ነው፤ ሌሎች ከተሞችንም እያነሳሳች ነው!
❤12👏4