የኮንስትራክሽን ህግጋትን የተረዳና በዕውቀት የጎለበተ ስራ ተቋራጭና አማካሪ ማፍራት ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና እንዳለው ተመላከተ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያሰናዳውና የስራ ተቋራጮችን እና አማካሪዎችን ዓቅም ለማጎልበት ያለመ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው የዘርፉ ተዋንያን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲውን ተረድተውና የህግ ማዕቀፎቹን ተገንዝበው ስራዎቻቸውን በዕውቀትና በኃላፊነት እንዲሁም በተጠያቂነት ስሜት የመፈፀም ዓቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።
እንደ አሰልጣኙ አቶ መላኩ ይኸይስ ማብራሪያ መሰል ስልጠናዎች ከብልሹ አሰራር አመለካከት የፀዳና ዕውቀትን ያስቀደመ ስራ -ተቋራጭና አማካሪን በማፍራት የኮንስትራክሽን ኢንዱስሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር የማይተካ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል።
ለ2 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከ200 በላይ አዳዲስና ነባር ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን በዘርፉ ብቃት ያላቸው ተዋንያንን ለማፍራትና ኢንዱስትሪውን ዕውቀት ባለው ባለሙያ ለመደገፍ አስቻይ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም

❤11👍8
የአዲስ አበባ ከተማ አንጸባራቂ ዕድገት፡ የመደመር እሳቤ ህያው ተምሳሌት!
ኢትዮጵያ የጀመረችው ጥልቅ የመደመር ስትራቴጂ፤ የከተሞችን ዕድገት ለማፋጠን፣ የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማገዝ፣ ሀገር በቀል ሀብቶችን አሟጦ ለመጠቀምና ለዘመናት የተንከባለሉ የከተማ ልማት ማነቆዎችን በተደራጀ፣ በተቀናጀና ዘላቂነት ባለው ሥርዓት ለመፍታት የሚያስችል ታሪካዊ አቅም ፈጥሯል።
በተለይም የኮሪደር ልማትን በስፋት በመተግበር፣ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ዕድል በማሳደግ፣ አካታች የሆነ የከተማ ልማትን እውን በማድረግና የኢትዮጵያን ከተሞች የኢኮኖሚ ማዕከል በማድረግ ተጨባጭ የሆነ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ትንሳኤ ማምጣት ተችሏል።
በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ማራኪና ለቱሪስቶች ተመራጭ እንድትሆን አድርገዋታል። በአዲስ መልክ የተገነቡት ውብ የኮሪደር ልማቶችና ግዙፍ የኢንዱስትሪ ማምረቻዎች የከተማዋን የኢኮኖሚ የደም ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ በማነቃቃት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የጎላ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በመደመር እሳቤና በቅንጅታዊ አሠራር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር መፋጠን ዋነኛው መነሻና መድረሻ ከተሜነት መሆኑ በግልጽ ተሰምሮበታል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንኑ ሐሳብ በጥልቀት ሲተነትኑ፤ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት የነገ ዕጣ ፈንታቸው ያለው በከተሞቻቸው ውስጥ መሆኑን በማስገንዘብ፤ ከተሞች ለሀገራዊ ጥቅል ምርት (GDP) ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ አጉልተው አሳይተዋል።
የአሁኑም ሆነ የመጪው ዘመን የሀብት ማመንጫ ምንጮች ከተሞች መሆናቸውን አበክረው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተሞችን በፍጥነት ማሳደግ፣ ፈጠራን ማጎልበት፣ ተሰጥዖዎችን መሳብ፣ ምቹ የንግድ ሥነ-ምህዳርን መፍጠርና ለዘላቂ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ማሟላት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር እውን ለማድረግ ሞተር እንደሚሆኑ አብራርተዋል።
በከተሞች ላይ የተጠናና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሙዓለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የብልጽግናን በሮች በሰፊው ከመክፈቱም በላይ፣ አካታችና የማይበገር አቅም በመፍጠር ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ሥርዓት ጋር በጥብቅ እንድትተሳሰር ያደርጋታል።
የተበታተኑ አቅሞችን፣ ሐሳቦችንና ግቦችን በአንድነት በማቀናጀት የላቀ የጋራ ውጤት ለማምጣት የሚያስችለው ይህ እሳቤ፣ በአዲስ አበባ ልማት ላይ በተግባር ታይቷል።
ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በታቀደላቸው ጊዜ የማጠናቀቅ ባህል፣ ከተማዋ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያበረከተች ያለው ጉልህ አስተዋጽዖ፣ እንዲሁም በተጨባጭ እየታየ ያለው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ የዚህ ታላቅ እሳቤ ህያው መገለጫ ነው። በአጠቃላይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት ኢትዮጵያ በመደመር ጎዳና የጀመረችው ጉዞ ሊቀለበስ የማይችልበት የብልጽግና ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያበስር ደማቅ ማሳያ ነው።

❤6👏2😢1
የሶስተኛው ዙር ኮሪደር ልማት በውስጡ ምን አካቷል...!
1. ከጎሮ–ኮዬ ፈጬ እስከ ቱሉ ዲምቱ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት፣ እና
2. ከካራ–ቦሌ አየር ማረፊያ መንገድ በጎሮ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው 22 ኪ.ሜ. የወንዝ ዳርቻ ልማት ፤
👉 የመንገድ ልማት፦
* ከጎሮ–ኮዬ ፈጬ–ቱሉ ዲምቱ 15 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው መንገድ ነው።
* የመንገዱ ስፋት 114 ሜትር ነው።
* በአንድ ጊዜ 8 ተሽከርካሪዎችን ያስተናግዳል።
* ሰፋፊ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች ሥራን ያካትታል።።
👉 የአረንጓዴ ልማት፦
* በ30 ሜትር ስፋት የሚዘረጋ፣ 70 ሄክታር መሬትን የሚሸፍን የመንገድ ዳር የአረንጓዴ ልማት ሥራን ያካትታል።
👉 የውኃና የፍሳሽ ልማት፦
* በ12 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ በቀን 106 ሺህ ሜትር ኪዩብ የመጠጥ ውኃ ለማምረት የሚያስችል ሥራን ያካትታል።
* የፍሳሽ ውኃ ማጣሪያ ጣቢያ ተገንብቷል።
* 206 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ሥራን ያካትታል።።
👉 የወንዝ ዳርቻ ልማት፦
* ከካራ–ቦሌ አየር ማረፊያ መንገድ በጎሮ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው 22 ኪ.ሜ. የወንዝ ዳርቻ ልማት ፣ 11.2 ሄክታር የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ ነው።
* 324 ሄክታር የሚሆን መሬትን የሚሸፍን የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ሥራ ወንዙን ተከትሎ እየተከናወነ ይገኛል።
* 4,100 ሜትር ኪዩብ የጋቢዮን ሥራ እየተሰራ ነው።
* 1,500 ሜትር ኪዩብ የእርከን ሥራን ያካትታል።
በአጠቃላይ ስራው እየተፋጠነ ስለሆነ በአካባቢው ቅድሚያ የማልማት መብት ያገኛችሁ የግል አልሚዎችም እድታፋጥኑ እናሳስባለን።
- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#aa_corridor #aa_riverside #Goro #TuluDimtu #addisababa #Ethiopia

👍1