Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
270 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
የሰው ተኮር ልማት በተግባር የተረጋገጠበት የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደር!

ዛሬ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደርን ለአካባቢው የልማት ተነሺዎች አስረክበናል።

የከተማ ልማት ዋነኛ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠር ነው።

በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው። ሆኖም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል መሬቱን ለእርሻ፣ ለግጦሽና ለመኖሪያነት ሲጠቀሙ የነበሩ አርሶ አደሮችን ሕይወት የሚነካ በመሆኑ፣ የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል።

በዚህም መሠረት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የልማት ከእርሻና መኖሪያ ቦታቸዉ ተነሺ ለሆኑ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ አርሶ አደሮች የተቀናጀ መኖሪያ መንደር ገንብተን፣ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉ አቅርቦቶችንም አካተናል። ይህም የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር ጠብቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ሁኔታ የሚያሸጋግር ሰው ተኮር የልማት አሠራር ነው።

ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ መንደሩ የሚከተሉትን አቅርቦቶች ይዟል፦

* የወተት ላሞችን የሚይዙ የከብት ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ።
* የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች።
* የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል።
* የስብሰባ አዳራሽ።

እነዚህ አቅርቦቶች ነዋሪዎቹ የተሻለ መኖሪያ እንዲኖራቸው፣ የወተት ልማትና ሌሎች የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ፣ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዲጠብቁ እና ልጆቻቸው ምቹ አካባቢ እንዲያገኙ የተዘጋጁ ናቸው።

ልማት ማለት ሰውን ከነበረበት ቦታ ማንሳት ብቻ ሳይሆን የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታው ለታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንደሚውል ስናስረዳቸው፣ ዩንቨርቲዉ ለልጆቻቸው የመማር ዕድልና ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሚፈጥር በመገንዘብ በፈቃደኝነት ትብብራቸውን አድርገዋል። ለዚህ ከልብ እናመሰግናለን፤ ትልቅ ክብርም ይገባቸዋል።

ይህ ተግባር በመደመርና በትብብር ስንሰራ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ ማድረግና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው።

የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደር ይህንኑ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫችንን በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ ነው። የምንገነባት አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿን ክብር፣ መብትና ጥቅም የምታስጠብቅ፣ ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን።

የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችና በስራዉ ሂደት አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁለ ከለብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
❤10👏4
ሀገራዊ ፋይዳን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በአንድ ያሳካው የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደር ፕሮጀክት!!!!

ከለውጡ አስቀድሞ በነበሩ ልምምዶች በልማት ከቀያቸው የሚነሱ ዜጎች ለቀጣይ እጣ ፈንታቸው ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት ዜጎች ለተለያዩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ሲጋለጡ ቆይተዋል።

ይህን መራር እውነት ከመሰረቱ ለመቀየርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስትራቴጂ ነድፎ ስራዎችን በስፋት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልማት የሚነሱ ዜጎች መፃዒ ዕጣ ፈንታቸውን በሚያቀና መልኩ በለመዱት የሕይወትና የስራ መስመር ተሰማርተው እራሳቸውን ፣ ቤተሰባቸውን ብሎም ሀገራቸውን የሚደግፉባቸው የተቀናጁ ማዕከላትን እየገነባ ሲያቀርብ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለት በክብርት ከንቲባ በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደርም የዚሁ ተግባር ማሳያ ነው።.............
❤5
..........ትልቅ ሀገራዊ ትልም ሰንቆ በመገንባት ላይ ለሚገኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎ (AI) ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት ቦታቸውን የለቀቁ አርሶ አደሮችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክቱ ከመደመር ዕሳቤ የተቀዳው የአካታችነት እና የሁሉን አቀፍነት መርህ የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን ሀገራዊ ፋይዳንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በአንድ ያሳካም ጭምር ነው።

መንደሩ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የወተት ላም ሼዶች ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ ፣ የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን ፣ ወፍጮዎች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል እንዲሁም የስብሰባ አዳራሽ ተሟልተውለታል።

የከተማው የስራ ባህል መገለጫ በሆነው 7/24 መርህ በአጭር ጊዜ በተገነባው በዚህ ፕሮጀክት ላይ የቦሌ ክፍለከተማ ዲዛይንና ግንባታ ፅ/ቤት በባለቤትነት በማስተባበር ፣  መስኤፍ ጠ/ሾ/ተቋራጭ በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኬኦን ኮንሰልቲንግ በአማካሪነት የተሳተፉበት ሲሆን ካለው ፋይዳ ባሻገር የአስተዳደሩ ፕሮጀክቶችን የመፈፀም ዓቅሙ የደረሰበት ከፍታም የታየበት ነው።

ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥቅምት 22/2019
❤9👍8