Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.6K subscribers
15.4K photos
273 videos
96 files
778 links
Government Organization
Download Telegram
❤8👏5
ከደሳሳ ጎጆ ወደ ዘመናዊ መኖሪያ የተሸጋገረው የአቃቂ ቃሊቲ ነዋሪዎች ሕይወት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በበጎነት መንደር አዲስ ቤት የተረከቡ ነዋሪዎች ከዓመታት እንግልት በኋላ ያገኙትን እፎይታ እና ደስታ ለኤ ኤም ኤን አጋርተዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ አዲስ በተገነባው የበጎነት መንደር ቤት ከተረከቡት መካከል እናት አልማዝ አበራ አንዷ ናቸው፡፡ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የኖሩበት የቀበሌ ቤት በዕድሜ ርዝማኔ እጅግ አርጅታ ዘማለች፡፡

"ቤቷ አረጀች፤ ምስጥ ወጥቶባት እስከ ግድግዳው ድረስ በላው። በምን አቅማችን እንሥራው? የምናገኛት ገቢ ከእጃችን ወደ አፋችን ናት..." ይላሉ እናት አልማዝ ያለፉትን ችግር ሲያስታውሱ። በክረምት ደግሞ የጎርፍ ስጋቱ በእጥፍ ይጨምራል።

ይህ የእናት አልማዝ ብቻ ሳይሆን የጎረቤታቸው የወይዘሮ ሙሉ ታደሰም መከራ ነበር። በጠበቧ ቤት ውስጥ በርካታ ልጆችና የልጅ ልጆች ተሰብስበው ነበር የሚኖሩት፡፡ በዘመመችው ጎጆ የሚበረታው ቅዝቃዜ ለህመም ተጋላጭ ያደረጋቸው ነበር፡፡፣ የሕፃናት የሥነ-ልቦና ጉዳት ፈተና ሆኖባቸው እንደነበር ይናገራሉ።

የሁለት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ካሳሁን አለሙም በወቅቱ የነበረው ችግር መልከ ብዙ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ላሉ 15 ቤቶች አንድ ሽንት ቤት ብቻ ይጠቀሙ እንደነበር ነው የሚጠቅሱት።ይህም ከጤና እና ከንጽህና አንጻር በተለይም ለሕፃናት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበር ነው የሚያስታውሱት።

ለእናት አልማዝ፣ ለወይዘሮ ሙሉ እና ለአቶ ካሳሁን ቤተሰብ ያ ሁሉ ሀሳብ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ዛሬ ታሪክ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ተግባር በበጎነት መንደር ፕሮጀክት አማካኝነት፣ እነዚህ አባወራዎች እና እመወራዎች ዛሬ የዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል።

አዲሱን ቤታቸውን ሲረከቡ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹም በፊት በምኖርበት ቤት በማፈር አዲስ ልብስ ለብሼ ለመውጣት እንኳ እፈራ ነበር የሚሉት እናት አልማዝ ዛሬ ግን በደስታ እወጣለሁ ይላሉ፡፡ ለዚህም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያላቸውን ምስጋና በደስታ ታጅበው አቅርበዋል፡፡

አቶ ካሳሁንም የልጆቻቸውን ፈገግታ በማየታቸው የተሰማቸውን እፎይታ "ትልቅ ለውጥ ነው! በተለይ ከመታጠቢያ እና ከንጽህና መጠበቂያ አንጻር ሙሉ በሙሉ ተለውጠናል። አሁን ልጆቼ የራሳቸው መታጠቢያ እና መጸዳጃ ቤት አላቸው። በነሱ ደስታ እኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ"ሲሉ ያብራራሉ።

ኢትዮጵያውያን ስንተባበር የማንወጣው ተራራ እና የማንሻገረው ችግር እንደሌለ ይህ አጋጣሚ ማሳያ ነው።

አዲስ አበባ ከተማን ደረጃዋን የጠበቀችና ውብ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የነዋሪዎችን ሕይወት መለወጥ እና ሰብዓዊ ክብርን ማስጠበቅ ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራ ለመሆኑ የእነዚህ እናቶችና አባቶች ደስታ ምስክር ነው።
❤7👏5
የስጋ ዋጋ ጭማሪ በሚስተካከልበት ሁኔታ ከስጋ ቤት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የስጋ ቤት ባለቤቶች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ባደረጉት ውይይት በማህበራቸው አማካይነት ተወያይተው የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

መድረኩን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በጋራ መርተውታል።

ከመድረክ የስጋ ቤቶች የዋጋ ጭማሪ አንፃር የተካሄደ ዳሰሳ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከእርድ ከብት ጋር ተያይዞ በግብይት ሂደት የሚታዩ የደላላ ጣልቃ ገብነት ችግርን በማንሳት መንግስት እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

ከእርድ ከብት አቅርቦት አንፃር ችግር ሳይኖር ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር አይገባም ያሉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የስጋ ዋጋ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አያይዘው የከተማ አስተዳደሩ በከተማችን በሚገኙ አምስት የቁም ከብት የገበያ ማዕከላት ላይ አርሶአደሩ ምርቱን በቀጥታ ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ የስጋ ቤቶች የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በስጋ ዙሪያ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት በዘርፉ እሴት የማይጨምሩ ህገ-ወጥ ደላላዎችን ከገበያው የማስወጣትና ሌሎች የቁጥጥር ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አያይዘውም በቀጣይ ከግብር፣ ከንግድ ፍቃድ አንፃር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው የልኳንዳ ማህበራት ተወያይተው አሁን ያለውን ንረት ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ተመን እንዲያወጡ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የስጋ ቤት ባለቤቶች በማህበራቸው አማካይነት ተወያይተው በአጭር ጊዜ የዋጋ ማስተካከያ አድርገው እንዲያሳውቁ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
❤14😁3🙏1
❤8🙏1
በመዲናዋ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረበ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ጥራቱን የጠበቀ የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን ለኤ ኤም ኤን አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾች ተናገሩ።

በመዲናዋ የሚገኙ የህብረት ሥራ ማህበራት በሱቆቻቸው ስጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች እያቀረቡ ነው፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያነጋገራቸው ሸማቾች፤ በተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ ስጋ እየሸመቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካነጋገርናቸው ሸማቾች መካከል ግርማ ፍቃዱ፤ የደራሽ ለመርካቶ ህብረት ሥራ ማህበር ደምበኛ መሆናቸውን በመግለጽ 1 ኪሎ ስጋ በ1 ሺህ 200 ብር እየሸመቱ መሆኑን ነግረውናል።

የስጋ አቅርቦቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እናገኛለን፤ ሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የኑሮ ውድነት እንዲረጋጋ የተሻለ አገልግሎት እየሰጡና ሚናቸውንም እየተወጡ ነውም ብለዋል።

ሌላኛው የህብረት ሥራ ማህበራት ደንበኛ ዳንኤል ፋንቱ በበኩላቸው፤ የስጋ አቅርቦቱ በበቂ መጠን፣ በጥራት እና ማህበረሰቡን ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ከደራሽ ለመርካቶ የህብረት ሥራ ማህበር አልማው ኤልያስ፤ ጥራቱን የጠበቀ በቂ የስጋ አቅርቦት እንዳለ በማንሳት ህብረተሰቡም እየገዛ መሆኑን አንስተዋል።

በሸማች ህብረት ሥራ ማህበሩ በቂ ስጋ በማቅረብ ደንበኞች የሚፈልጉትን ሥጋ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ፣ የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራትን አቅም ለማጎልበት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ከቦሌ ንጋት ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበር መንገሻ አቡ፤ በሸማች ማሕበሩ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ያለው ሥጋ ጥራቱ ተረጋግጦ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ያለው የስጋ አቅርቦት የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና አለውም ነው ያሉት፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) በመዲናዋ በሚገኙ በተለያዩ የሸማች ማህበራት ባደረገው ምልከታ ህብተረሰቡ ከሸማቾች ማሕበራት በተመጣጣኝ ዋጋ ስጋ ሲሸምት ተመልክቷል፡፡
AMN
❤10👏6
❤6🙏1