Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
272 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
❤7🙏1
በመዲናዋ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረበ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ጥራቱን የጠበቀ የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን ለኤ ኤም ኤን አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾች ተናገሩ።

በመዲናዋ የሚገኙ የህብረት ሥራ ማህበራት በሱቆቻቸው ስጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች እያቀረቡ ነው፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያነጋገራቸው ሸማቾች፤ በተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ ስጋ እየሸመቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካነጋገርናቸው ሸማቾች መካከል ግርማ ፍቃዱ፤ የደራሽ ለመርካቶ ህብረት ሥራ ማህበር ደምበኛ መሆናቸውን በመግለጽ 1 ኪሎ ስጋ በ1 ሺህ 200 ብር እየሸመቱ መሆኑን ነግረውናል።

የስጋ አቅርቦቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እናገኛለን፤ ሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የኑሮ ውድነት እንዲረጋጋ የተሻለ አገልግሎት እየሰጡና ሚናቸውንም እየተወጡ ነውም ብለዋል።

ሌላኛው የህብረት ሥራ ማህበራት ደንበኛ ዳንኤል ፋንቱ በበኩላቸው፤ የስጋ አቅርቦቱ በበቂ መጠን፣ በጥራት እና ማህበረሰቡን ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ከደራሽ ለመርካቶ የህብረት ሥራ ማህበር አልማው ኤልያስ፤ ጥራቱን የጠበቀ በቂ የስጋ አቅርቦት እንዳለ በማንሳት ህብረተሰቡም እየገዛ መሆኑን አንስተዋል።

በሸማች ህብረት ሥራ ማህበሩ በቂ ስጋ በማቅረብ ደንበኞች የሚፈልጉትን ሥጋ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ፣ የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራትን አቅም ለማጎልበት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ከቦሌ ንጋት ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበር መንገሻ አቡ፤ በሸማች ማሕበሩ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ያለው ሥጋ ጥራቱ ተረጋግጦ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ያለው የስጋ አቅርቦት የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና አለውም ነው ያሉት፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) በመዲናዋ በሚገኙ በተለያዩ የሸማች ማህበራት ባደረገው ምልከታ ህብተረሰቡ ከሸማቾች ማሕበራት በተመጣጣኝ ዋጋ ስጋ ሲሸምት ተመልክቷል፡፡
AMN
❤8👏6
❤4🙏1
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተናል!

በከተማችን በመሠረታዊ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎችና በቤት ኪራይ ላይ እየታዩ ያሉ ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመቆጣጠርና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተወሰዱ ባሉ የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሔዎች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል።

በውይይቱ የሥጋ፣ የምግብ ዘይት፣ የዳቦ፣ የታሸገ ውኃና የቤት ኪራይ ዋጋዎች ላይ የሚታዩ ያልተገቡ ጭማሪዎች ተገምግመዋል። ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታትና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን ለማረጋገጥም የሚከተሉት ዋና ዋና እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።

1. የምርት አቅርቦትን ማሳደግ

የመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት በመጨመር የዋጋ መረጋጋትን ለማምጣትና ሸማቹ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን።

2. የገበያ ማዕከላትን ማስፋፋትና የደላላ ሰንሰለትን ማሳጠር

አምራቾችንና ሸማቾችን በቀጥታ የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላትን በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ በማቋቋም ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች እንዲቀርቡ እየሠራን ነው። ሕብረተሰቡም ከእነዚህ የገበያ ማዕከላት በመገበያየት የተመጣጣኝ ዋጋ አማራጮችን እንዲጠቀም እናበረታታለን።

3. የሸማቾች ማኅበራትን ማጠናከር

የሸማቾች ማኅበራት የምርት አቅርቦትና ጥራት እንዲያድግ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር የሚያዝ ተዘዋዋሪ ፈንድ (Revolving Fund) መድበናል።

4. የእሑድ ገበያዎችን ማስፋፋት

ሸማቾች መሠረታዊ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የእሑድ ገበያዎችን እናስፋፋለን፤ አቅርቦታቸውንም እናጠናክራለን።

5. ቁጥጥርንና የሕግ ማስከበርን ማጠናከር

የገበያ ሥርዓትን በሚጥሱና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ቁጥጥርና የሕግ ማስከበር ሥራችንን እናጠናክራለን።

6. የቤት ኪራይን በተመለከተ የአከራይና የተከራይ ግንኙነት በሕግ፣ በውል ስምምነትና በጋራ ኃላፊነት መመራት አለበት። ዜጎች መብታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲያስከብሩና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማስረጃ እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። በተመሳሳይም ተደራሽና ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ማሳደግ ዘላቂ መፍትሔ እየተሰራ ነዉ።

በውይይታችንም የአቅርቦት ችግሮችን ከመሠረቱ በመፍታት፣ ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን በማረጋገጥና ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን በመቆጣጠር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።

ሕብረተሰቡ አስተዳደሩ ባመቻቻቸው የሸማቾች ማኅበራትና የእሑድ ገበያዎች በመገበያየት የኑሮ ወጪውን እንዲቀንስ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

በተጨማሪም ዜጎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ወይም የገበያ ሕግ ጥሰት ሲያጋጥማቸው በቂ ማስረጃ በማቅረብ ለሚመለከተው የከተማ አስተዳደር አካል ሪፖርት እንዲያደርጉ፣ ከተረጋገጠ መረጃ ውጭ ወሬዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን በጋራ እንዲደግፉ አሳስባለሁ።

የዜጎችን የኑሮ ጫና ማቃለልና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን ማረጋገጥ የጋራ ኃላፊነታችን ነው!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
❤12👍8
❤2🙏1
በመዲናዋ የሸማቾች ማኅበራት የምርት አቅርቦትና ጥራት ለማሳደግ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ (Revolving Fund) ተመድቧል።

የዜጎችን የኑሮ ጫና ማቃለልና ፍትሃዊ የገበያ ሥርዓት ማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ አንዱ የትኩረት መስክ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምርቶችና በቤት ኪራይ ላይ የሚደረግ ምክንያታዊ ያልሆነ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪን ለመግታት፣ የታቀደ የምርት እጥረት እንዳይከሰት ለመከላከል እና ህገወጥ ደላሎችን ከግብይት ሰንሰለቱ ለማስወጣት እየሰራ ያለውን ሥራ ለማጠናከር የሚያግዝ በየደረጃው ካለ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በተደረገው ውይይትና በውይይቱ የተቀመጡት አቅጣጫዎች በከተማዋ የኪራይና የግብይት ህጎች በህብረተሰቡ የነቃ ትብብር እንዲተገበሩ፣ የሸማቾች መብት በተግባር እንዲከበርና በህገወጥ አሰራር ምክንያት የሚደርሰው የኑሮ ጫና እንዲቀንስ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

በሰው ሰራሽ መንገድ የሚፈጠር የዋጋ ንረትና የዕቃ እጥረት የሸማቾችን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከመጎዳቱም በላይ ህጋዊ የንግድ ስርዓቱን ያናጋል።
በመዲናዋም መሰል ሁኔታዎችን የመፍታት አቅም የተፈጠረ ቢሆንም፥ አቅርቦትን ይበልጥ ለማሳደግና የሸማቾች ማኅበራት የምርት አቅርቦትና ጥራት እንዲያድግ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ (Revolving Fund) መድቧል።

ከተማ አስተዳደሩ ህገወጥ ደላሎችን ከሰንሰለቱ በማስወጣት ከአምራች እስከ ሸማች ያለውን ሂደት ግልጽ ለማድረግ የወሰደው ውሳኔ ሸማቾች ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ የማግኘት መብታቸውን የሚያረጋግጥ ነው።

በትግበራ ላይ ያሉ የኪራይና የግብይት ህጎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እና ቁጥጥር ሲታከልበት በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪ መብቱን በማወቅ፣ ህገወጥ አሰራሮችን በመጠቆምና ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

ይህ የተቀናጀ እርምጃ የአዲስ አበባን ሸማቾች ካልተገባ የዋጋ ጫና በመጠበቅ ረገድ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣና ጤናማ የከተማ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው።
❤13👍5
ቢሮው "የሮቦቲክ የግድግዳ ቀለም መቀቢያ ፈጠራን" ገመገመ፡፡

 
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማዘመንና ወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፉ ለማስረፅ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።


ከዚህ አንፃር በዛሬው ዕለትም ለቢሮው የቀረበውን የ "ሮቦቲክ የግድግዳ ቀለም መቀቢያ ፈጠራ" ገምግሟል፡፡

 
በመድረኩ እንደተገለፀው ቴክኖሎጂው ከዚህ ቀደም ለህንፃዎች ቀለም ቅብ አገልግሎት ላይ የሚውለውን የመወጣጫ እንጨት ከማስቀረቱም በተጨማሪ በከፍተኛ ደረጃ ጊዜን የሚቆጥብና ወጥነት ያለው ቅብ ለማድረግ እንዲሁም በዚህ ስራ ላይ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

 
ከዚህ በተጨማሪ ቴክኖሎጂው የቀለም ብክነትን እና በሰው ኃይል የሚፈጠሩ ክፍተቶችን እንደሚቀርፍም ተጠቁሟል፡፡


ይህን ተከትሎ ገምጋሚ ቡድኑም በግምገማው ያስተዋላቸው ነጥቦች ላይ አስተያየት በመስጠት ወደ ቀጣይ ሂደት እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
 

ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
❤9👍8