Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
270 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
ወንዞቿን አክማ ለነዋሪው እፎይታን የሰጠችው አዲስ አበባ ከተማ

አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ወንዞች ቢኖራትም ወደ ወንዞቿ በሚለቀቁ ቆሻሻዎች እንዲሁም የተለያዩ የኢንደስትሪ ተረፈ ምርቶችና ፍሳሾች ምክንያት በእጅጉ ተበክለው የቆዩና ከቆሻሻ መጣያነት በሻገር ምንም ድርሻ ያልነበራቸው ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፀምባቸው ለዕይታም ለጤናም አደገኛ ነበሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ወንዞች ለመታደግ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ወንዞቿ ታክመው ንጹህ መሆን የቻለቡት ፤ ለከተማዋ ነዋሪ ጤና ያለበሰቡት እና ጠፍተው የነቡሩ ምንጮች እንደገና የፈለቁበት እንዲሁም የውሃ ጤናማነት የተረጋገጠበት ብሎም ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና የቱሪስት መስህብ መሆን የቻሉበት ነው፡፡

በዚህ ለትውልድ ተሸጋሪ እንዲሆን ታስቦ በተሰራው የወንዝ ዳርቻ ልማት የተሸከርካሪ ፣ የሳይክልና የእግረኛ መንገድ ጨምሮ ለማንበቢያ የሚሆኑ ቦታዎች ፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎችና የልጆች መጫዎቻዎች እንዲሁም መንፈስን የሚያድሱ ምቹ የአረንጓዴ ስፍራዎች የተካተቱበት ነው፡፡

በተጨማሪም የወንዝ ብክለትን በማስቀረት የከተማዋን የጎርፍ ተጋለጭነት መቀነስ የተቻለበት አንዲሁም የተበከለ ውሃና አጣርቶ ጥቅም ላይ በማዋል የከተማችንን ውሃ አቅርቦት ማሻሻል የተቻለበትና ምንጮችን ማጎልበት የተቻለበት ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማን ማልማት ሁለንታናዊ ልማት ነው ብሎ በማመን ለነዋሪው ጤና እጅግ አስቸጋሪ የነበሩ ወንዞችን በማከም ወደ ቀደመው ተፈጥሮዊ ማንነታቸው እንዲመለሱ ከማድረግ በተጨማሪ ከተማዋ ውብና ለነዋሪዎች ምቹ ብሎም አለም አቀፍ ተወዳዳሪና ተመራጭ የቱሪስት ከተማ እንድትሆን አድርገዋታል፡፡

አሁን ላይ የአዲስ አበባ ወንዞች ለቱሪስት መዳረሻ ፤የተለያዩ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ኩነቶችን ማስተናገጃ ብሎም ለነዋሪዎች ጤና እፎይታን ሰጥተዋል፡፡ አዲስ አበባ አሁንም ሁሉን አካታች በሆኑ የልማት ስራዎቿ የቆሸሹትን እያፀዳች እና እያስዋበች እንደ ስሟ ውብ እና ማረኪ የሆነ ገጽታን ለነዋሪዎቹ ማስረከብ ትቀጥላላች፡፡
❤8👍6😁3