Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.63K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ሲያሳድግ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 5ሺህ ቤቶች ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ናሆም አይናለም የተባለው ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ እንደሚያሳድግ ከህብረተሰቡ ጥቆማ መምጣቱን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ም/ኮማንደር መርዕድ ደበሌ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባደረገው ፍተሻ የጓሮ አትክልት መስሎ በ16 ማዳሪያ ውስጥ የተቀመጠ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በመግለፅ ተጠርጣሪውን በቁጥር ስር በማዋል ወደ ማረፊያ ቤት ለማስገባት በተደረገበት የአካል ፍተሻም በካልሲው ውስጥ ደብቆ ሊገባ መሞከሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ በየአካባቢው መሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ጥቆማና መረጃ የመስጠት ባህሉን ሊያጠናክር እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤10👍1
በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ የሆኑ አራት ግለሰቦች ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፤
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ድርጊቱ የተፈፀመው ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ካዛንቺስ አካባቢ ከጠዋቱ 2:30 አካባቢ ነው፤ የግል ተበዳይ ከሳሮማሪያ ሆቴል ወደ ኢሊሊ ሆቴል ለመጓዝ ለአንድ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ይደውላሉ፡፡

ድርጅቱ ያሠማራውን ተሽከርካሪ ሠሌዳ በመጥቀስ መልዕክት ቢልክም ከቆይታ በኋላ የመጣው ተሽከርካሪና ከድርጅቱ የተላከው የተለያየባቸው ግለሰቧ ጥያቄ ያነሳሉ፤ ሄኖክ ሙሉጌታ የተባለው ተጠርጣሪም አሽከርካሪዎቻችን ሁሉም ስራ ላይ ስለሆኑ ነው እኔ የመጣሁት የሚል ምላሽ ይሰጣቸውና ወደ የተጠቀሰው አካባቢ ጉዞ ይጀምራሉ፡፡

ግለሰቧ የፈለጉበት ቦታ ሲደርሱም ሂሳብ ከፍለው ይወርዳሉ፤ ነገር ግን በሚወርዱበት አጋጣሚ የዋጋ ግምቱ 190ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ULTRA, S 25 ስልክ ተሽከርካሪው ውስጥ ረስተው መውረዳቸውን ስለተረዱት የትራንስፖርት አገልግሎት ለሰጣቸው ሄኖክ ሙሉጌታ ደውለው ስልካቸውን ረስተው ስለ ወረዱ እንዲመልስላቸው ቢጠይቁትም ግለሰቡ በእምቢታው መጽናቱን በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የካዛንቺስ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ሳጅን ሞገስ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡

ግለሰቧም የተፈፀመባቸውን ድርጊት ለፖሊስ ጥቆማ በማድረጋቸው ተጠርጣሪው ላይ ተገቢው ክትትል ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ፖሊስ እንደገለፀውም በተደረገው የክትትል ስራ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ በመግዛትና በመሸጥ ጭምር ተሳታፊ የሆኑትን አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡

ህብረተሰቡ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት ሲጠቀም ከድርጅቱ የሚላክላቸውን የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር በጥንቃቄ ማረጋገጥ እንደሚኖርበትም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ፡- ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤12👍6👏1
የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባደረገው ጥናት በርካታ የተሰረቁ የተሽከርካሪ እቃዎች እና መሳሪያ ከ3 ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ሱማሌ ተራ እንዲሁም ወረዳ 5 ከረዩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ የተሰረቁ የተሽከርካሪ እቃዎችን እየገዙ የሚሸጡ ሲሆን ፖሊስ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ከህብረተተሰቡ በደረሰው መረጃ መሰረት ባደረገው ብርበራ 58 ስፖኪዮ 3 የተሽከርካሪ ቸርኬ እንዲሁም የመኪና ጌጅ ከ2 ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ሲያውል በተመሳሳይ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ከረዩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ 1 ካናኖስ ሽጉጥ ከመሰል 2 ጥይት እንዲሁም ከአንድ ካርታ እና ከአንድ ግለሰብ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ወንጀል ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር መርሻ አዳነ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለው እንደገለፁት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለሽብር እና ለወንጀል መፈፀሚያ የሚውል መሆኑን ህብረተሰቡ በመረዳት መሰል የወንጀል ድርጊት ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ የመስጠት ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበው የተሰረቁ የተሽከርካሪ እቃዎችን የሚገዙ ግለሰቦች ከዋና ወንጀል ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ በመገንዘብ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ሳጅን ፍፁም በቀለ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤20👍11👏7
በተለምዶ ‹‹ትፍታ›› የተባለውን የማታለል ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አንተነህ ጌታቸዉ የተባለዉ ተጠርጣሪ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመዉ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ሻላ መናፈሻ የተባለ አካባቢ ነው፡፡

የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ኤፍሬም ዓለሙ ሲገልፁ ተጠርጣሪ አንተነህ ጌታቸው የግል ተበዳይ አቶ ፋብያን ንጉዲ የተባሉ ጀርመናዊው ግለሰብ ያለው ላይ ምራቅ ከተፋ በኋላ ይቅርታ በማለት ልብሱን በመጥረግ ከኪሱ ውስጥ ግምቱ 140ሺህ ብር የሚያወጣ አይፎን 13 pro max ስልክ ይዞ ተሰውሯዋል፡፡

የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸውን ድርጊት በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ለአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በማመልከታቸው ተገቢው ክትትል ሲደረግ ነበር ያሉት ኮማንደር ኤፍሬም ተጠርጣሪውን ከሚጠቀምበት የሠሌዳ ቁጥር B61211 አ/አ ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር  ስር ማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ የማስፋት ተግባር እንደሚቀጥል ያስታወቁት ኮማንደር ኤፍሬም በግለሰቡና በተሽከርካሪው ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በመምጣት ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል። 

❤2