በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከል እድሳት ተደርጎ ተመረቀ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአትክልት ተራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በወረዳ 2 ቀጠና 7 ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያስገነባውን ደረጃውን የጠበቀ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስራ አስጀመረ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና መምሪያ የወንጀል መከላከል እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ደገፋ እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከል መገንባት በህብረተሰቡ እና በፖሊስ መካከል ያለውን ግንኝነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በጋራ የምንከላከልበት ነው በማለት በግንባታው ላይ አስተዋፅኦ የነበራቸው አካላትን በዋና መምሪያው ስም አመስግነዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአትክልት ተራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አብርሀም ገብረፃዲቅ በበኩላቸው ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል የተገነባው በህብረተሰቡ በጎ ፈቃደኝነት 3,500,000 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ) ብር ወጪ በማድረግ መሆኑንና ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ገልጸው፤ የፖሊስ ስራ ያለ ህብረተሰቡ ተሳፎ ውጤታማ ስለማይሆን የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ገልፀዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሰራተኛ እና ስራ እድል ፈጠራ ፅ/ቤት ኃላፊ የኋላሸት ተድላ እንደተናገሩት ለማህበረሰቡ ሠላም እና ደህንነት መረጋገጥ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ከገለፁ በኋላ በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ ለማቀራረብ ማዕከሉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
የአካባቢ ነዋሪዎች የቀድሞው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከሉ ለአገልግሎት ምቹ እንዳልነበረ ገልፀው። የማህበረሰቡን ሠላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ ሳይሰለች ለሚሰራው ፖሊስ ከጎኑ በመሆን ማዕከሉ 24 ሰዓት ክፍት ሆኖ እንዲያገለግል የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።
ማዕከሉ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ አስተዋጾኦ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ጻዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤13👍8👎1
በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ሲያሳድግ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 5ሺህ ቤቶች ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ናሆም አይናለም የተባለው ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ እንደሚያሳድግ ከህብረተሰቡ ጥቆማ መምጣቱን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ም/ኮማንደር መርዕድ ደበሌ ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባደረገው ፍተሻ የጓሮ አትክልት መስሎ በ16 ማዳሪያ ውስጥ የተቀመጠ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በመግለፅ ተጠርጣሪውን በቁጥር ስር በማዋል ወደ ማረፊያ ቤት ለማስገባት በተደረገበት የአካል ፍተሻም በካልሲው ውስጥ ደብቆ ሊገባ መሞከሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ በየአካባቢው መሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ጥቆማና መረጃ የመስጠት ባህሉን ሊያጠናክር እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ

❤10
በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ የሆኑ አራት ግለሰቦች ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፤
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ድርጊቱ የተፈፀመው ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ካዛንቺስ አካባቢ ከጠዋቱ 2:30 አካባቢ ነው፤ የግል ተበዳይ ከሳሮማሪያ ሆቴል ወደ ኢሊሊ ሆቴል ለመጓዝ ለአንድ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ይደውላሉ፡፡
ድርጅቱ ያሠማራውን ተሽከርካሪ ሠሌዳ በመጥቀስ መልዕክት ቢልክም ከቆይታ በኋላ የመጣው ተሽከርካሪና ከድርጅቱ የተላከው የተለያየባቸው ግለሰቧ ጥያቄ ያነሳሉ፤ ሄኖክ ሙሉጌታ የተባለው ተጠርጣሪም አሽከርካሪዎቻችን ሁሉም ስራ ላይ ስለሆኑ ነው እኔ የመጣሁት የሚል ምላሽ ይሰጣቸውና ወደ የተጠቀሰው አካባቢ ጉዞ ይጀምራሉ፡፡
ግለሰቧ የፈለጉበት ቦታ ሲደርሱም ሂሳብ ከፍለው ይወርዳሉ፤ ነገር ግን በሚወርዱበት አጋጣሚ የዋጋ ግምቱ 190ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ULTRA, S 25 ስልክ ተሽከርካሪው ውስጥ ረስተው መውረዳቸውን ስለተረዱት የትራንስፖርት አገልግሎት ለሰጣቸው ሄኖክ ሙሉጌታ ደውለው ስልካቸውን ረስተው ስለ ወረዱ እንዲመልስላቸው ቢጠይቁትም ግለሰቡ በእምቢታው መጽናቱን በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የካዛንቺስ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ሳጅን ሞገስ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡
ግለሰቧም የተፈፀመባቸውን ድርጊት ለፖሊስ ጥቆማ በማድረጋቸው ተጠርጣሪው ላይ ተገቢው ክትትል ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ፖሊስ እንደገለፀውም በተደረገው የክትትል ስራ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ በመግዛትና በመሸጥ ጭምር ተሳታፊ የሆኑትን አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡
ህብረተሰቡ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት ሲጠቀም ከድርጅቱ የሚላክላቸውን የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር በጥንቃቄ ማረጋገጥ እንደሚኖርበትም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ፡- ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ

❤11👍4👏1