በክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የተመራ ልዑክ በአዲስ በአበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራትን ጎበኘ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ አበባ)፦ በክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄነራል በላይ ስዩም የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን ጎበኘ።
በጉብኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መድድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እንዲሁም የማዕከልና የክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዦች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በዋና ጠቅላይ መምሪያው በርካታ የመልሶ ማደራጀት (reform) ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የመልካም አስተዳደርና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች፣ የፖሊስ አባላት የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት የሠራዊቱን የስራ ተነሳሽነት መጨመር የተቻለ ከመሆኑም በላይ በወንጀል ምጣኔ ቅነሳ ላይ ለተገኘው ውጤትም የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
በተለይም ከ"ፍልሠት ወደ ምልሠት " በሚል መርህ በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቋሙን የለቀቁ አመራርና አባላትን ተገቢውን ማጣራት በማድረግና የተሀድሶ ስልጠና ሠጥቶ ወደ ተቋሙ እንዲመለሱ መደረጉ በሪፎርሙ ከተከናወኑ በርካታ ተግባራት አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከከተማውን ነዋሪና ከሌሎች የጸጥታ ተቋማትና አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት በተሠሩ የጸጥታ ጥበቃ ስራዎችም 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫና ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸውን ኃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ እንከን ማከናወን መቻሉንም ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ ጠቅሰዋል።
ለክብር እንግዳውና ልዑካቸውም የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችን የተመለከ ዘጋቢ ፊልም እንዲሁም በመጀመሪያው መቶ ቀናት የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ ሌተናል ጄነራል በላይ ስዩም በበኩላቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተሄደበትን ርቀት አድንቀው ሠራዊቱ ያለበትን ማህበራዊ ችግር ተረድቶ ተገቢውን መፍትሔ በመስጠት ለተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ ከአንድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ልትመሠገኑ ይገባል ብለዋል።
በተለይም በመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቋሙን የለቀቁ አመራርና አባላት የስነ ምግባር ችግር የሌለባቸው ተመርጠው ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የጸጥታው አካል መደረጋቸውና ለችግሮች መፍትሔ የተሰጠበት መንገድ ስትራቴጂክ አመራሩን ሊያስመሰግነው የሚገባ ነውም ብለዋል።
በተቋሙ የነበሩ ችግሮችን ተቋቁሞ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገር መቻል ከጠንካራ መሪዎች የሚጠበቅ በመሆኑም ልትመሰገኑ ይገባል ያሉት ሌ/ጄነራል በላይ ስዩም ለቀጣይ ተግባሮቻችን እንደ ምርጥ ተሞክሮ የሚወሰድ ነውም ብለዋል።
አመራሩ በለውጡ በተገኙ ስኬቶች ሳይዘናጋ በቀጣይ ለከተማዋ ሠላምና ጸጥታ መረጋገጥ በቁርጠኝነት በጋራ መስራት እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ጻዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤10👍8