Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.67K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
በህገ ወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ ነዳጅ ተያዘ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ቦንብ ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በሁለት ሊትር ፕላስቲክ ጠርሙስ ተቀናንሰው የተዘጋጀ አጠቃላይ 423 ሊትር ቤንዚን በእንቁላል መያዣ ሳጥን በማድረግ ከከተማ ሊወጣ ሲል በህብረተሰቡ ጥቆማ ሊያዝ መቻሉን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመርካቶ አከባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ግዛቸው ወልዴ ገልፀዋል።

ፖሊስ ኤግዚቢቱን በመያዝ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ፍለጋ እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ህጋዊ አግባብነት የጎደለው ተግባርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ተግባር በመደገፍ ረገድ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን እያሳየ ላለው ድጋፍም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
*
ዘገባ፦ ዋ/ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤17👍5👏3
❤7👍2👎1🤔1
በተደጋጋሚ ጊዜ ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ደሳለኝ ጭናሾ የተባለው ተከሳሽ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለያየ ቀናት ነው።

ተከሳሹ ጨለማን ተገን በማድረግና በአካባቢው ላይ ጥበቃዎች አለመኖራቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአንድ ግለሰብ የሞባይል ስልክ መሸጫ ሱቅ የሻተር በር ተንጠልጣይ ቁልፍን በብረት መቁረጫ መጋዝ ቆርጦ በመግባት፣ የተለያዩ ስማርት ስልኮች፣ የሞባይል ባትሪዎች፣ በሶላር የሚሰራ ሬዲዮ፣ የሞባይል ቻርጀር፣ የጆሮ ማዳመጫ ኤርፎን፣ የእጅ ሰዓቶችና የልብስ መተኮሻ ካውያ በአጠቃላይ 1 መቶ ሺህ 450 ብር የሚገመት ንብረት ሰርቆ ለመሰወር ሲሞክር በስራ ላይ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አባላት እጅ ከፍንጂ መያዙን ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በተጨማሪም በተጠቀሰው አካባቢ ከአንድ ምግብ ቤት ውስጥ የበር ቁልፍ ገንጥሎ በመግባት 18,000 ብር የሚገመቱ 3 የወንበር ዥንጥላዎችን እንደሰረቀና ከደበቀበት ቦታም መርቶ በማሳየት ንብረቱን ማስመለስ እንደተቻለ የገለፀው የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን ምርመራ በማጣራት በተከሳሹ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተበትም  አስታውቋል።

የተከሳሽ ደሳለኝ ጭናሾን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 3ኛ የወንጀል ችሎት የክስ መዝገቡን ከመረመረና የሰው ማስረጃዎችን ከአሰማ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ግለሰቡ በፈፀመው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል በሁለት መዝገቦች  በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ህብረተሰቡ መሰል ወንጀል እንዳይፈፀምበት በንግድ ቤቶች አካባቢ አስተማማኝ ጥበቃ መቅጠርና የደህንነት ካሜራ መግጠም እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለፖሊስ በማመልከት ወንጀል ፈፃሚዎች እንዲያዙና በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዘላለም አበበ
ካሜራ፦ ዋ/ሳጅን ሃብታሙ ባዘዘው
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
💔11👍10❤8👎1👏1
በእገታ ወንጀል19 ዓመት ከ6 ወር እስራት ቅጣት ተወስኖበት የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በእገታ ወንጀል ተከሶ በሌለበት 19 ዓመት ከ6 ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበትና  ተሰውሮ የቆየ ግለሰብን በቁጥጥር ሥር በማዋል ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ አስረከበ።

የገንደ ቆሬ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ግዛቸው እንደገለጹት፣ ግለሰቡ ቀደም ሲል በፈጸመው ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ዋስትና ከተለቀቀ በኋላ በቀጠሮ ቀን ባለ መቅረብ ተሰውሮ ቆይቷል።

ኃላፊው እንዳብራሩት መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት በክ/ከተማው ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ጎተራ ማሳለጫ ነዳጅ ማደያ አካባቢ ጅብሪል በቀለ ኃይሌ የተባለው ግለሰብ፣ “የመከላከያ አባል ሳይሆን የመከላከያ አባል ነኝ” በማለት የሰሌዳ ቁጥሩ ከድ 3-32234 ኢ/ት የሆነ ተሽከርካሪን አስቁሞ የመንጃ ፈቃዱን ተቀብሎ አሽከካሪውን “ተከተለኝ” በማለት ይዞት ሊሄድ ሲል በአካባቢው ላይ በነበሩ የወንጀል መከላከል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውልም ችሏል።

ፖሊስ በግለሰቡ ላይ ምርመራ ሲያካሂድ ከቆየ በኋላ የጣት አሻራ በማስወሰድ ባደረገው ማጣራት፣ ግለሰቡ በ2013 ዓ.ም በእገታ ወንጀል በፌዴራል ፖሊስ ታስሮ የነበረና በሌለበት 19 ዓመት ከ6 ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ማረጋገጥ መቻሉን ኢ/ር ተስፋዬ ገልጸዋል።

በመሆኑም የገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ለፌዴራል ፖሊስ ማሳወቁንና ግለሰቡ በሌለበት የእስራት ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ተሰውሮ የቆየ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ አስረክቦታል።

የመምሪያው ኃላፊ ኢ/ር ተስፋዬ ግዛቸው አክለውም፣ ወንጀል ፈጽሞ በመሰወር ከሕግ ተጠያቂነት መራቅ እንደማይቻል ገልጸዋል። ፖሊስ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር በማዋል፣ ጉዳዩ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ፖሊስ ሲጣራ የነበረ በመሆኑ ለሚመለከተው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ማስረከቡንም አስረድተዋል።

በወንጀል ተከሰው በፍርድ ቤት ዋስትና የሚለቀቁ ግለሰቦች በቀጠሮ ቀናቸው ለፍርድ ቤት ቀርበው ሕጋዊ ሂደቱን መከተል እንዳለባቸው ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በቀጠሮ ቀን አለመቅረብ ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድንም በመግለጽ ማንኛውም ግለሰብ ሕጋዊ ሂደቱን እንዲከተል መልዕክቱንም አስተላልፏል።
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤34👍7🙏5🥰3👏2🤷‍♂1