የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከ ‹‹ ፍልሰት ወደ ምልሰት ›› በሚል መርህ በተለያዩ ምክንያቶች ከሠራዊቱ የለቀቁ የፖሊስ አመራርና አባላት የተሐድሶ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ አስመረቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ የስራ መደቦች ሲያገለግሉ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች ተቋሙን የለቀቁ አመራርና አባላት ባቀረቡት ወደ ተቋሙ የመመለስ ጥያቄ በወንጀል ድርጊት እና በስነ ምግባር ችግር ውስጥ ያልተሳተፉ መሆናቸው የተረጋገጠ ተመላሽ የፖሊስ አመራርና አባላት የተሐድሶ ስልጠና በመስጠት አስመረቀ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊክ መድድ፣ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እንዲሁም የዋና ጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አመራርና አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቢሾፍቱ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ተቋም አስመርቋል፡፡
በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የስራ መመሪያ የሰጡት የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ ህዝብን ለማገልገል ድጋሚ እድል ላገኙት 3ተኛ ዙር ተመላሽ የፖሊስ አመራርና አባላት ስልጠናቸውን በአግባቡ ተከታትለው ለምረቃ በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት፤ ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ በመወጣት ረገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስመዘገበ ያለውን አመርቂ ውጤት በመደገፍ ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ገልፀዋል።
በተቋሙ ውስጥ የነበሩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ተግባራት እየተከወኑ መሆኑን ያነሱት ሌ/ጄነራሉ ከቅርብ ወራት ወዲህ በርካታ የማሻሻያና የመልሶ ማደራጀት ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውንም ተናግረዋል፤ አመራርና አባላቱ የነበረባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የማዕረግና የጥቅማ ጥቅም፣ የመኖሪያ ቤትና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማጥናትና በመመሪያ እንዲደገፍ በማድረግ ችግሮቹ እየተቀረፉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ በተለይም ከ‹‹ ፍልሰት ወደ ምልሰት ›› በሚል መርህ እያከናወናቸው ባሉ የሪፎርም ተግባራት ወደ ተቋሙ ለመመለስ ጥያቄ ያቀረቡ አመራርና አባላትን ተገቢውን ማጣራት አሰልጥኖ ማስመረቁ አንዱ የሪፎርሙ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተመራቂዎች ከተሐድሶው ስልጠና በቂ እውቀትና ክህሎትን በመያዝ በሚሰማሩበት ቦታ ሁሉ ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግልም አሳስበዋል፡፡
በምረቃው ላይ የስራ ሪፖርት ያቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ምክትል ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ሰለሞን ፋንታሁን በበኩላቸው ህብረተሰቡን ሊያገለግሉ የሚችሉ አመራርና አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ተቋሙን የለቀቁ መሆናቸውን አስታውሰው ስትራቴጂክ አመራሮቹ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ወደ ስራ እንመለስ የሚሉ ጥያቄዎች መምጣታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ተቋሙም የቀረቡ ጥያቄዎችን በሚገባ በመመርመር የስነ ምግባር ግድፈት የሌለባቸው አመራርና አባላት ወደ ተቋሙ ተመልሰው የክፍል ትምህርትና የመስክ ስልጠና በመስጠት የተቋሙን የሰው ኃይል ማጠናከር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ ለስልጠናው ስኬት አበርክቶና ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም በስልጠናው የላቀ ውጤት ላመጡ ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል፡፡
ተመራቂዎች በበኩላቸው በአንዳንድ የመልካም አስተዳደር እና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት ተቋሙን ለቀው እንደነበር ገልፀው፤ የለውጥ አመራሮች ተቋሙን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት በሚዲያ በማየታቸው ተመልሰው ህዝብን ለማገልግል መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙም ህዝባቸውን ለማገልገል ለሰጣቸው ሁለተኛ ዕድል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ዋ/ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤29👍12👏4