Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.66K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ አመት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባከናወነው ተግባር የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበ መሆኑን ገለፀ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በማቅረብ ትውውቅና የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ ስርዓት እንዲሁም የአንደኛ ሩብ አመት የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ የተካሄደው የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክላስተር ዓላማ የህግ የበላይነት የሚያስከብር የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ በመሆኑ ሠላሟ የተረጋገጠ ከተማ ለመፍጠር በርካታ ዓለም አቀፍ እና ከተማ አቀፍ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ማድረግ የህዝብ እና የመንግስት ጥቅም ማስከበር፣ ከአግባብ በላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ላይ የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር፣ የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻዎች አደጋ እንዳይደርስባቸው መጠበቅ፣ ከትራፊክ ፖሊስ እና ከትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትራንስፖርት መስጫ አካባቢ የህብረተሰቡን እንግልት መቀነስ እንዲሁም መከላከል መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመድረኩ ላይም በአንደኛ የሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች አመርቂ መሆኑን ጠቅሰው በመዲናዋ የተከበሩ ኃይማኖታዊና ሕዝባዊ የአደባባይ በዓላት እንዲሁም የተለያዩ ኹነቶች በሠላም እንዲጠናቀቁ የተቻለው በቅንጅት ከባለ ድርሻ አካላት በመሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ የፀጥታ መዋቅሩ ጠንካራ ስራ በመስራቱ መሆኑን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የክላስተር አባላት በሰጡት አስተያየት የነዋሪዎች እንግልት ለመቀነስ በቅንጅት በርካታ ስራዎች መስራት ይጠበቅብናል በማለት የህዝብ እንግልት በተለይ በትንስፖርት አካባቢ ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ፣ በህገ ወጥ እርድ በሚሰማሩ፣ ህገ ወጥ ግብይት፣ በታሸጉ ምግቦች ደህንነት፣ ያለ ደረሰኝ በሚፈፀሙ ግብይቶች፣ በብልሹ አሰራር ውስጥ በሚገቡ አካላት እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የክላስተር አባላት ትኩረት ሰጥተን ልንሰራበት ይገባል ብለዋል።

በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ የሰጡት ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የተለያዩ ግዜያቸው ያለፈባቸው ምግቦች ማስወገድና እርምጃ አወሳሰድ፣ በፀረ ሙስና እና በብልሹ አሰራር ላይ በርብርብ ከፖሊስ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቁርጠኝነት በመስራት የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከሙስና የፀዳች ከተማ መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
*
ዘገባ፡- ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ፃዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤37👍8👏2