Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.64K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
በሌተናል ጄነራል አስራት ደኔሮ የተመራ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጂክ አመራሮች ልዑክ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የፖሊስ መምሪያዎች የግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እና ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ጎበኘ፤
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በጉብኝት መርሀ ፣ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ፣ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር እርዚቅ ኢሳ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሀንጋቱ መሃመድ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አህመዲን ጀማል እንዲሁም የአስራ አንዱም ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዦች በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄነራል አስራት ደኔሮ እንደገለፁት ህብረተሰቡ በወንጀል መከላከል ስራው ላይ እያበረከተ ላለው አስተዋፆኦ የምስጋና መረሀ ግብር መደረጉ በቀጣይ ኃላፊነትን የሚፈጥር መሆኑን በመግለፅ በተለይም የአመራሩን እና የአባሉን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር እና ማህበረሰቡ ፖሊስ መምሪያው በሚያደርገው የተለያዩ የተቋማት ግንባታ ስራዎችን በመደገፍ ለፖሊስ አለኝተኝነቱን በመግለፁ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በግንባታ ማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሃንጋቱ መሃመድ በበኩላቸው ህብረተሰቡ በፀጥታው እና በወንጀል መከላከሉ ላይ ለፖሊስ ከሚያደርገው እገዛ ባሻገር የፖሊስ ተቋም የኔ ነው በሚል ስሜት ፖሊስ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ገንዘቡን በማዋጣት እያበረከተ ላለው ድጋፍ በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አህመዲን ጀማል በበኩላቸው የአደባባይ ኩነቶች ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲያልፉ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሉ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በመግለፅ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በተቋማት ግንባታ እና የለውጡ አመራሮች ባስቀመጡት የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ከተልዕኮ ባሻገር የአመራሩን እና የአባሉን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አውስተው በዕለቱም ለ43 የፖሊስ አመራር እና አባላት መኖሪያ ቤት መሰጠቱን ገልፀዋል።

በበጀት አመቱ ትላልቅ የአደባባይ ኩነቶች ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና እና የእውቅና መርሀ ግብር ተካሄዷል።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው አመራርና አባላት በሰጡት አስተያየት የእውቅናው መሰጠት በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አደራንና ኃላፊነትን እንደጣለባቸው በመግለፅ ቤት የተሰጣቸው የፖሊስ አመራር እና አባላት ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

በግንባታ ማስጀመርያ መርሀ ግብሩ ላይ በወረዳ 5 ሰሪቲ ፖሊስ ጣቢያን ለመገንባት እንዲሁም በወረዳ 2 ደረጃቸውን የጠበቁ ፖሊስ መምሪያዎችን ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን ፍጹም በቀለ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤22👏1