በመዲናችን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 08 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አደጋዎቹ የተከሰቱት ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13፣ ወረዳ 1 እና ወረዳ 15 ነው።
የመጀመሪያው አደጋ የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ ቅዱስ ሚካኤል መብራት ከቀኑ 9፡30 አካባቢ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መንግስቱ ታደሰ እንደገለፁት የጉዞ አቅጣጫውን ከአየር ጤና ወደ ጀርመን አደባባይ ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-08136 ኢት ሲኖትራክ ተሽከርካሪ መብራት ይዟቸው ቆመው የነበሩ 10 ተሽከርካሪዎችን እና አንድ የመብራት ፖል ላይ በመግጨት የንብረት ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡
በአደጋውም በትራንስፖርት ተሽከርካሪ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ የ44 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አንዲት እናት ላይ የሞት፣ በአንድ ሌላ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና ርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚያው ዕለት ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ በክ/ከተማው ወረዳ 01 ጀሞ ሦስት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-43228 አ/አ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ይዞ ከጀሞ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ጀሞ ሶስት ሲጓዝ የነበረው አሽከርካሪ ከቀኝ ወደ ግራ ሲሻገር በነበረ ግለሰብ ላይ የሞት አደጋ ያደረሰ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።
በዕለቱ ከምሽቱ 4፡30 አካባቢ ደግሞ በዚያው ክ/ከተማ ወረዳ 15 ሀጫሉ መንገድ አካባቢ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-52305 አ/አ ሀዩንዳይ ተሽከርካሪን በመያዝ ወደ ጋርመንት እያሽከረከረ የነበረ ግለሰብ ከመንገድ ጠርዝ ጋር በመጋጨት የአሽከርካሪው ህይወት ማለፉን አብራርተዋል፡፡
በክ/ከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ቀን ብቻ በደረሱ አደጋዎች የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታወሰው አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያርጉ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
*
ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤29💔7😭7
ህገ ወጥ የይለፍ ወረቀት (Pass) በሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል!
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚከናወኑ ኩነቶች እንደ አስፈላጊነቱ ዕውቅናና የይለፍ ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ይታወቃል ያለው የአዲስ አበባ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የማንኛውም ኩነት ፈቃድ አሰጣጥና የቁስ የይለፍ ፈቃድ ራሱን የቻለ አሰራር ያለው በመሆኑ ፈቃድ ሰጪ ተቋም በራሱ የደብዳቤ ሎጎ በማድረግ እንደሚሰጥም አስታውሷል።
የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የኩነት አመቻችና ፈቃድ ሰጪ ቢሮዎች ኩነት ለማዘጋጀት የጠየቀው አካል አሰራርን በጠበቀ መልኩ ባሳወቀው መሰረት ኩነት ማዘጋጀት የሚችልበት ፈቃድ፣ የመኪና እና መሰል ጉዳዮች የይለፍ ማረጋገጫ በኩነት ፈቃጁ ተቋም ደብዳቤ የተቋሙ ሎጎ ተደርጎበት ይሰጠዋል።
ነገር ግን ቢሮው ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር ያልተፈቀደላቸው አካላት ህገ ወጥ የይለፍ (Pass) ወረቀት በመያዝ እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል።
ህገ ወጦቹ የትራፊክ ቁጥጥርን በመጣስ፣ ከመጠን በላይ በፍጥነት በማሽከርከር፣ ከተፈቀደው መስመር በተቃራኒ በመንዳት፣ የመኪና መለያዎችን ያለ አግባብ በመጠቀም፣ የጥቁር መስታወት ሽፋኖችንና የVIP ፈቃዶችን ያለ ሕጋዊነት መጠቀምና መሰል የህግ ጥሰቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ ይህን ተግባር ለማስቆምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ አስተማሪ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች መሠል ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ አካላትን ሲመለከትም በነፃ የስልክ መስመር 8882 እና ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ቢሮው መልዕክቱን አስተላልፏል።
@ Addis Ababa peace & security administration Bureau

❤52🤔4👎2👏2🤯2
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ5 ዓመታት ፍኖታ ካርታ (road map) ለማዘጋጀት ከተቋማት አመራሮችና ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ዋና መቀመጫ እንዲሁም የዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባን የሚመጥን የፖሊስ ተቋም ለመፍጠር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ5 ዓመት ፍኖተ ካርታ (road map) አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ለመግባት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
የሰለጠነና ቴክኖሎጂን የታጠቀ የሰው ኃይል በመፍጠር በስርዓት የሚመራና የከተማውን ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የሚደረገውን ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ይህ ፍኖተ ካርታ (road map) አስፈላጊነቱ ወሳኝ እንደሆነ የታመነበት ጉዳይ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄነራል አስራት ደኔሮ ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት ገልፀዋል።
ከከተሞች እድገት ጋር ተያይዞ እየተፈጠረ ባለው የዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታ ውስጥ ቴክኖሎጂን ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ወይም Artificial Intelligence ጋር በማጣመር የወንጀል መከላከልና ምርመራ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ የጠቆሙት ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ የፍኖተ ካርታው አስፈላጊነቱም ከዚሁ ጋር የሚሰናሰል መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ በዘመነና ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤት በመታጠቅ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት የከተማውን ሠላምና ፀጥታ ሙሉ በመሉ ለማረጋገጥ እና ተቋሙን ወደ ፊት ለማራመድ የታቀደ በመሆኑ ፍኖታ ካርታው ያለው ፋይዳ የምንፈልገውን ተቋም ገንብተን የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንድንወጣ አጋዥ መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መድድ ለባለድርሻ አካላቱ አስረድተዋል።
ቀጣይ ፍኖተ ካርታው እንደ ተቋም ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተቋሙ የሚያስገኘው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደመሆኑ አፅንኦት ተሰጦት ከሚመለከታቸው አካላት የሚገኙ ግብዓቶችን ተጠቅሞ ወደ ሥራ እንደሚገባ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ ተናግረዋል።
እጅግ እየዘመነች ባለችው አዲስ አበባ ከተማ የሰለጠነ የፖሊስ ኃይልን ለመፍጠር የሚደረገውን ሁለንትናዊ አካሄድ በመደገፍና ትብብር በማድረግ ረገድ ከተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት የተገኙ ባለድሻ አካላት ቁርጠኛ እንደሆኑ በነበራቸው ውይይት ላይም ተነስቷል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ጤናው ፈጠነ

❤12😁2