የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ አደጋን ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በቅርቡ የተጠሪነት ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም በከተማዋ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ በመከላከል ጥራትና ተጠያቂነት ያለው የትራንስፖርት ስምሪት ለማስፈን ከትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መድድ፣ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ እንዲሁም የትራፊክ ቁጥጥር ዋና መምሪያው አመራሮች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማን የትራፊክ ፍሰት ለማሳለጥና የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ተቋሙ በከተማው እያከናወነ ያለውን ሥራ ውጤታማ በማድረግ ረገድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ፖሊስ አመራርና አባላት የሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማስወገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ሲሉም ሌ/ጄነራል አስራት ደኔሮ አሳስበዋል።
የተቀመጠውን አቅጣጫ መሠረት በማድረግ ስራዎችን በቁርጠኝነት በመፈጸም የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት ይገባል ያሉት የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ፤ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የትራፊክ ፍሰቱን ማሳለጥና የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን በመከላከል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ግባችን ነውም ብለዋል።
የትራንስፖርት ማኔጅመንት አሰራር መፈጠሩ የህዝብን ምሬት ፣ የሥራ መደራረብን፣ የመንግስትን ሀብት ከብክነት በመታደግ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ተቋማት ጋር ቅንጅትን በመፍጠር በዘርፉ ያለውን ችግር እንደሚቀርፍ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በጋራ በሚያከናውኑት የትራንስፖርት ማኔጅመንት ትግበራ፤ በስራ ወቅት የነበረውን ችግር ለማስተካከል፣ የህግ ማዕቀፎችን ለመለየት በማሰብና ቀጣይ አብሮ በጋራ በመሥራት የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረ/ኮሚሽነር ሚሊዮን አደፍርስ አብራርተዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዋና መምሪያ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ቁርጠኛ እንደሆነ የዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አበራ ባይሳ ገልፀው ውይይቱ የተቋማቱን የሥራ ድርሻ በግልፅ ያስቀመጠና የሚፈገውን አላማ ለማሳካት በጋራ እንዲሰሩ ያስችላልም ብለዋል።
ከዚህን ቀደም በሁለቱ ተቋማት መካከል አሻሚ ሁኔታዎችን የመፍጠር ተግዳሮት እንደነበር ተወያዮቹ ገልፀው ለችግሩ መፍትሔ ለማበጀት ሁለቱ ተቋማት የትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ማቋቋማቸው የሚያስገኘው ውጤት ከፍተኛ እንደሆነ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን በትራፊክ ፖሊስና በመንገድ ተቆጣጣሪዎች መካከል ያለውን የስራ ድርሻ የሚለይ እንደሚሆንም ተገልጿል።
በውይይቱ መሠረት ስራቸውን በመከወን የከተማውን የትራፊክ ፍሰትና አደጋን የመከላከል ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎቹ ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤25👍2👏2