የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት ዕውቅና ሰጠ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተከናወነው የእውቅና መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መድድ፣ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በአድማ ብተና፣ መሠረተ ልማትና ቀላል ባቡር ጥበቃ ም/ዋና መምሪያዎች ስር የሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የስራ መመሪያ የሠጡት የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ሌተናል ጄነራል አስራት ደኔሮ ከተማውን የሚመጥን የተሻለና ሞዴል የሆነ የፖሊስ ሰራዊት ለመገንባት ተቋሙ ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤
የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ከፍተኛ ተግባር በመደገፍ የተለያዩ ህዝባዊና ኃይማኖታዊ በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የአድማ ብተና፣ መሠረተ ልማትና ቀላል ባቡር ጥበቃ ም/ዋና መምሪያዎች እያበረከቱት ላለው የላቀ አስታዎጽኦ አመስግነዋል።
ሰራዊቱ ላስመዘገበው ውጤት ክብር ዕውቅና መስጠቱ እንደሚገባ ገልጸው አመራርና አባላቱ ተግባራቸውን የበለጠ በማጠናከር ተቋሙ የተጣለበት ኃላፊነት ከግብ እንዲያደርስ በመጀመረያው ሩብ ዓመት የጀመሩትን አመርቂ ውጤት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የአድማ ብተና ም/ዋና መምሪያ እንደ ተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት ከዳር ለማድረስ፣ የሚጠበቅበትን ውጤት በተግባር በማሳየት በየትኛውም ጊዜ አመራሩና አባላቱ ዝግጁ መሆናቸውን በማንሳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመቱ ለተመዘገቡ ውጤቶች የተቋሙ ስትራቴጅክ አመራሮች ድርሻ የላቀ ነው ያሉት የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊው ኮማንደር ገዛኸኝ ጌታነህ አሁን በተቋሙ እየታየ ያለው ሁለንትናዊ ለውጥና ሲስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መቀረፋቸው በፖሊስ አመራሩና አባላቱ ዘንድ የፈጠረው ተነሳሽነት ለም/ዋና መምሪያዎቹ አመርቂ አፈፃፀም ያለው አበርክቶ ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዋል።
በመጀመሪያው ሩብ ዓመቱ የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ለነበራቸው አድማ ብተና፣ መሠረተ ልማትና ቀላል ባቡር ጥበቃ ም/ዋና መምሪያዎች አመራርና አባላት እንዲሁም ለፕሮግራሙ መሳካት አበረክቶ ላደረጉ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።
ለተገኘው አመርቂ ውጤት የተዘጋጀው የምስጋናና የዕውቅና ፕሮግራም በአመራሩና አባላቱ ዘንደ የሚፈጥረው ስሜት የላቀ መሆኑን የገለጹት ታዳሚዎቹ ህዝብን በታላቅ ሀገራዊ ስሜት ለማገልገል ቁርጠኛ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ማርቺን ባንድና ኦርኬስትራ በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ታዳሚውን በማዝናናት ዕውቅና ተችሮታል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤28👏1
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጂክ አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲን ኮሌጅን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የረጅም ዓመታት የማሰልጠን ታሪክ ያለው ሲሆን የኮልፌ ፖሊስ ሠራዊት ትምህርት ማዕከል፣ የፖሊስ ማሰልጠኛ፣ ፖሊስ አካዳሚ፣ ፖሊስ ኮሌጅ ሲባል ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለማደግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡
ዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምዕራፎች ሲሰጣቸው ከነበሩ መደበኛና አጫጭር የፖሊስ ስልጠናዎች ባሻገር በኮሌጅ ደረጃ የማዕረግ ሽግግር ስልጠናዎችን በመስጠት ያስመረቀ ሲሆን አሁን ላይ በዲፕሎማ ለማስተማር ከመንግስት እውቅና ከማግኘቱም ባሻገር በዲግሪ መርሀ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ወደ መጨረሻዎቹ ምዕራፎች ተሸጋግሯል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ ትምህርትና መለዮ ለባሹ ጠንካራ ትስስር ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በሚመለከተው የመንግስት ተቋም ሊያሟላቸው እንደሚገባ የተቀመጡለትን መመዘኛዎች በማሟላት ተማሪዎችን ተቀብሎ ወደ ማስተማር ተግባሩ እንዲገባም የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውሰው የዋና ጠቅላይ መምሪያው ማኔጅመንት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበትም አብራርተዋል፡፡
በዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ የተከናወኑ ተግባራት እና ስትራቴጂካዊ ትንተና የምክረ ሀሳብ ሪፖርት በዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ም/ፕሬዚዳንት አማካሪ ኮማንደር ሰይፈ ሙሉጌታ እንዲሁም በዶ/ር አሮን አብርሃም የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ሊፈፀሙ ስለሚገባቸው ተግባራትም ለስትራቴጂክ አመራሩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ

❤12👏2👎1