የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጂክ አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲን ኮሌጅን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የረጅም ዓመታት የማሰልጠን ታሪክ ያለው ሲሆን የኮልፌ ፖሊስ ሠራዊት ትምህርት ማዕከል፣ የፖሊስ ማሰልጠኛ፣ ፖሊስ አካዳሚ፣ ፖሊስ ኮሌጅ ሲባል ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለማደግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡
ዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምዕራፎች ሲሰጣቸው ከነበሩ መደበኛና አጫጭር የፖሊስ ስልጠናዎች ባሻገር በኮሌጅ ደረጃ የማዕረግ ሽግግር ስልጠናዎችን በመስጠት ያስመረቀ ሲሆን አሁን ላይ በዲፕሎማ ለማስተማር ከመንግስት እውቅና ከማግኘቱም ባሻገር በዲግሪ መርሀ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ወደ መጨረሻዎቹ ምዕራፎች ተሸጋግሯል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ ትምህርትና መለዮ ለባሹ ጠንካራ ትስስር ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በሚመለከተው የመንግስት ተቋም ሊያሟላቸው እንደሚገባ የተቀመጡለትን መመዘኛዎች በማሟላት ተማሪዎችን ተቀብሎ ወደ ማስተማር ተግባሩ እንዲገባም የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውሰው የዋና ጠቅላይ መምሪያው ማኔጅመንት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበትም አብራርተዋል፡፡
በዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ የተከናወኑ ተግባራት እና ስትራቴጂካዊ ትንተና የምክረ ሀሳብ ሪፖርት በዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ም/ፕሬዚዳንት አማካሪ ኮማንደር ሰይፈ ሙሉጌታ እንዲሁም በዶ/ር አሮን አብርሃም የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ሊፈፀሙ ስለሚገባቸው ተግባራትም ለስትራቴጂክ አመራሩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤12👏2👎1