በአዲስ አበባ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የመንገድ ትራፊክ አደጋው የተከሰተው ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው ቀጨኔ መቀጠያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን ጭኖ የጉዞ አቅጣጫውን ከኩዩ ወደ አዲስ አበባ ቀጨኔ ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-62732 ኦ/ሮ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ልዩ ቦታው ቀጨኔ መቀጠያ አካባቢ ሲደርስ መሪ ወደ ግራ በመጠቀምና ግራ መንገድ ውስጥ በመግባት ሁለት በጫማ ማስዋብ ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶችና አንድ እግረኛ ገጭቶ ወደ ፊት በመንቀሳቀስ ከቀጨኔ ወደ እንጦጦ የራሱን መንገድ ይዞ ሲንቀሳቀስ ከነበረ ኮድ 4-03305 አ/አ የውሀ ቦቴ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ 07 ግለሰቦች ላይ የሞት አደጋን መድረሱን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር መንግስቱ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
በአደጋው ቀድሞውኑ በአንድ እግረኛ ላይ የሞት አደጋ ከመድረሱም በላይ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ የነበሩ ተጨማሪ ሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ አደጋውን አሰቃቂ ያደርገዋል፡፡
የሚኒባሱ አሽከርካሪ በአደጋው ጉዳት ደርሶበት የህክምና ርዳታ እየተደረገለት ሲሆን በአስራ አንድ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ መድረሱንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
አሽከርካሪዎች ከምንም ነገር በላይ የመንገድ ደህንነት ህጉን አክብረው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤11😭7💔6😢2👍1